መዲነቱል ዑሉም

Description
https://t.me/medinetululoom

[email protected]
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 3 months, 2 weeks ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 months, 2 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 5 months, 2 weeks ago

2 months, 1 week ago

#የነፍስ አይነቶች

ሙእሚን ዘወትር ነፍሱን ጀነት ከመግባት ከሚያቅባት ንግግርም ይሁን ተግባር ያፀዳታል።
፤ላሳለፈችው መጥፎ ተግባር ልቦናዋን ተጠያቂ ታደርጋለች። ከአላህ ትእዛዝ ውጭ ላባከነችው ጊዜ ብርቱ ጸጸት ትጸጸታለች። ውዴታውን ባለመታደሏ ታዝናለች። ለሸይጣን ጌጥ እጅ በመስጠቷ ትቆጫለች።
ሁሌ ፍርድ ላይ ሁሌ ዳኝነት ላይ
ምን እና ለምን ታመዛለች።
ምን አጅር አገኝበታለሁ?
ለምን እሰራዋለሁ?

النَّفْسِ اللَّوَّامَةِ ራሷን ወቃሽ ነፍስ

አላህ! ሆይ! የሩቁንም ሆነ የቅርቡን ዓዋቂ የሆንከ፣ የሰማይና የምድር ፈጣሪ፣ የሁሉም ነገር ተንከባካቢ ጌታና ባለቤት፣ ካንተ በስተቀር ሊገዙት የሚገባ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ ከነፍሴ ተንኮል ባንተ እጠበቃለሁ፣ ከሸይጧንና ከአጋሮቹም።”
መልካም አዳር

2 months, 1 week ago

ከአልጋችን ስንወርድ ቀናችንን ለመጀመር
ገፍላ ላይ ስንገባ ለመውጣት አነቃቂ ንግግር አያስፈልገንም።

ብስራትን፣ ምክርን ፣ተግሳፅን፣ ተስፋን ፣ ብርታትን፣ ታሪክን፣መድሀኒትነትን የያዘ ኪታብ አለን።
ባነበቡት ቁጥር በ1 ፊደል 10 ሀሰናትን ሚያስገኝ። በተወዳጁት ቁጥር ጓደኛ ሚሆን። ባጠኑት ባሰሱት ቁጥር አዲስ የሆነ ማይሰለች።
የቀብር ቀን አጫዋች፣
የአሏህን ውዴታ ሚያስገኝ።

የህይወት መርህ የሆነ ኪታብ አለን።
ቁርአን ከሚመሰክርላቸው እንጂ ከሚመሰክርባቸው ሰዎች አሏህ አያርገን..
صباح الخير 🌞

2 months, 2 weeks ago

አላህን ፍሩ እያሉ የሚመክሩ ብዙ ናቸው አላህን የሚፈሩት ግን ጥቂቶች ናቸው። ዑመር ኢብን አብዱልአዚዝ
መልካም አዳር

4 months, 4 weeks ago

إنا لله وإنا إليه راجعون
የኡስታዛችን ኢልያስ አባት ወደ ማይቀረው ሀገር ተሸጋግረዋል አላህ ከፍ ያለውን ጀነተል ፊርደውስ ከሚወዱት ጋር ያርጋቸው እያልን የመዲነቱል ዑሉም አስተማሪዎችና ተማሪዎች የተሰማንን ታላቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰባቸውም መፅናናትን ከፈጣሪያችን አሏህ እንጠይቃለን::

(በያለንበት ፉቲሀ እንቅራላቸዉ)

4 months, 4 weeks ago

ከከዋክብት መንደር ክፍል 2

። በመካው የዳዕዋ ዘመን አብረዋቸው ሆኑ። ወደ መዲና ሲሰደዱ፣ በዋሻው ታሪክና ከዚያ በኋላ እስኪሞቱ ድረስ ከርሳቸው አልተለዩም።

በተቡክ ዘመቻ የሙሰሊሞችን አርማ ተሸካሚ ነበሩ። በዘጠነኛው ዓመተ ሂጅራ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሕይወት እያሉ የሐጅ ሥርዓትን መርተዋል።


ሰይዳችን አቡበክር አስሲዲቅ ለነቢያችን በመከላከል አንደኛ ነበሩ። በነፍሳቸውና በሀብታቸው ይከላከሉም ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ እየሰገዱ ሳለ ዑቅባ የተባለ ሰውዬ ይመጣና አንገታቸውን በለበሱት ሻል አንገታቸውን አጥብቆ ያንቃቸዋል። ያኔ ሰይዱና አቡበክር መጥተው ዑቅባን ገፍትረው “እንዴት ጌታዬ አሏህ ነው ስላለ ብቻ ትጋደሉታላችሁ? ለነቢይነቱም መስካሪ ተአምራት ይዞ እያለ ትጋደሉታላችሁ?” በማለት ተከላከሉላቸው።
:
በእውነትም ሲዲቅ “እውነተኛ ኖዎት” ነቢዩ ንም (ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በጣም ይወዱ የነበሩ ታላቅ ሷሓቢይ ናቸው።

?ከርሳቸው ሞት በኋላም እርሳቸውን ተክተው የሙስሊሞች ኸሊፋ ሆነዋል። የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ምትክ (ኸሊፊቱ ረሱሊላህ) የሚል ማእረግም በሙስሊሞች አግኝተዋል።
አቡበክር (ረ.ዐ) በወገኖቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እና ተግባቢ ሰው ነበሩ።
በቁረይሽ የዘር ሐረግና ታሪክ እውቀትም አቻ አይገኝላቸውም።
ጸባየ መልካም ነጋዴ ነበሩ። ሰዎች የርሳቸውን እውቀት፣ ተሞክሮና መልካም ባህሪ በመሻት በጣም ይቀርቧቸው ነበር። ከርሳቸው ጋር መቀማመጥንም ይወዱ ነበር።በርሳቸው እጅ፣ ዑስማን፣ ጦልሐ፣ ዙበይር፣ ሰዕድ እና ዐብዱረህማን ኢቢን አውፍ ሰለሙ።

የዕቁብ ኢቢን ሱፍያን በታሪክ ዘገባቸው እንዳወሱት፣ አቡበክር ሲሰልሙ አርባ ሺህ (የወርቅ ሳንቲሞች) ነበሯቸው። ወዲያውኑ በአላህ መንገድ መጸወቱት። ለአላህ ሲሉ ስቃይና መከራ ያስተናገዱ ሰባት ባሪያዎችን ገዝተው ነጻ ለቀቁ። እነርሱም ቢላል፣ ዓሚር ኢቢን ፋሀይራህ፣ ዚኒራህ፣ ነህዲያህንና ልጇን፣ የበኒ ሙእመል እንስት አልጋይና ኡምሙ ዓቢስ ናቸው።

የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
*“የትኛውም ሰው ወደ እስልምና ስጋብዘው ይከብደዋል። ለመቀበልም ያመነታል። አቡበክር ሲቀር። እርሱ ግን ወዲያውኑ እንደጠራሁት ሳያመነታ ተቀበለኝ።

ሱላችን እነዲህ ብለዋል
“በባልደረባነትና በገንዘብ ከማንም በላይ የደገፈኝ አቡበክር ነው። ከአምላኬ ውጭ የመጨረሻውን ፍጹማዊ ፍቅር የምለግሰው ሰው ቢኖር ኖሮ ያ ሰው አቡበክር ይሆን ነበር። ቢሆንም የእስልምና ወንድማማችነት እና ፍቅር አስተሳስሮናል።”* (ቡኻሪ፣ ሙስሊምና ቲርሚዚ ዘግበውታል)
ቢከተብ ቢከተብ አያልቅም

5 months ago

ከመተኛታችን በፊት

ውዱእ እናድርግ

ሲዋክ እንጠቀም

የቻልነውን በሰላት እንበርታ

ሱረቱል ሙልክ

አያተል ኩርስይ አንዘንጋ

የለሊቱን ክፍል ለመነሳት ኒያ እናርግ

ሌሉቱን በተውበት አሳምረን እንጀምር።

መልካም መናም ለማየትም አተኛኘታችንን እናድስ
አሏህ የወፍቀን

《በመናም ያየኝ ሰው በትክክል እኔን አይቶኛል ሸይጧን በኔ አይመሠልምና》ብለዋል
《مَنْ رَآنِي فِي الْمَنَامِ فَقَدْ رَآنِي ؛ فَإِنَّ الشَّيْطَانَ لَا يَتَمثّلُ بِي

ነገ ሀሙስ ነው መፆምን አትዘንጉ

5 months ago

የአኺራ ሂሳብ የቀለለው በዱንያ ነፍሳቸውን ለተሳሰቡት ነው!» يا أيها الذين آمنوا اتقوا الله ولتنظر نفس ما قدمت لغد እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፡፡ [ ሱረቱ አል-ሐሽር - 18 ] ራስህን ሂሳብ ምትሰራበት ውሎህን ምትገመግምበት የቀን፣ የሳምንት አልያም ወርሀዊ ፕሮግራም (ሙሀሰባ) አለህ?
anonymous poll

የለኝም – 23
??????? 77%

አዎ አለኝ – 7
?? 23%

? 30 people voted so far.

5 months ago

«وحب رسول الله ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻣﺤﻤﻮﺩ ﻷﻧﻪ ﻋﻴﻦ ﺣﺐ اﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻭﻛﺬﻟﻚ ﺣﺐ اﻟﻌﻠﻤﺎء ﻭاﻷﺗﻘﻴﺎء ﻷﻥ ﻣﺤﺒﻮﺏ اﻟﻤﺤﺒﻮﺏ ﻣﺤﺒﻮﺏ ﻭﺭﺳﻮﻝ اﻟﻤﺤﺒﻮﺏ ﻣﺤﺒﻮﺏ ﻭﻣﺤﺐ اﻟﻤﺤﺒﻮﺏ ﻣﺤﺒﻮﺏ ﻭﻛﻞ ﺫﻟﻚ ﻳﺮﺟﻊ ﺇﻟﻰ ﺣﺐ اﻷﺻﻞ ﻓﻼ ﻳﺘﺠﺎﻭﺯﻩ ﺇﻟﻰ ﻏﻴﺮﻩ ﻓﻼ ﻣﺤﺒﻮﺏ ﺑﺎﻟﺤﻘﻴﻘﺔ ﻋﻨﺪ ﺫﻭﻱ اﻟﺒﺼﺎﺋﺮ ﺇﻻ اﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ ﻭﻻ ﻣﺴﺘﺤﻖ ﻟﻠﻤﺤﺒﺔ ﺳﻮاﻩ»

«ሰይዳችንን ﷺ መውደድ የተመሰገነ ነው እሳቸውን መውደድ ማለት እራሱ አላህን መውደድ ስለሆነ ። እንደዚውም ዑለማዎችን ተቂዮችን መውደድ አላህን መውደድ ነው። ለምን ከተባለ... የተወዳጅ ተወዳጅ ተወዳጅ ነው። የተወዳጅ መልዕክተኛ ተወዳጅ ነው። ተወዳጅንም ወዳጅ ተወዳጅ ነው። ይሄ ሁሉ ውዴታ መሰረት ወደሆነው ውዴታ እንጂ ወደ ሌላ ስለማይመለስ ነው።
ስለዚህ በሀቂቃው የልብ እይታ ያላቸው ጋር ከአላህ ሌላ በእውነታው ተወዳጅ የለም።»
ሰይዲ ኢማም አልገዛሊይ
?ኢሕያኡ ዑሉሚ'ዲን

5 months ago
5 months, 1 week ago
  1. ከእንቅልፍ ሲነቁ የሚሏቸው ዚክሮች

۱ - الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي أَحْيَانَا بَعْدَ مَا أَمَاتَنَا وَإِلَيْهِ النُّشُورُ

  1. «አልሐምዱ ሊላሂልለዚ አሕያና በዕደ ማአማተና ወኢለይሒንኑሹር።»

«ከሞትን (ከእንቅልፍ) በኋላ ህይወትን ለለገሰን አላህ ምስጋናይገባው፡፡»

2

أَصْـبَحْنا وَأَصْـبَحَ المُـلْكُ لله وَالحَمدُ لله ، لا إلهَ إلاّ اللّهُ وَحدَهُ لا شَريكَ لهُ، لهُ المُـلكُ ولهُ الحَمْـد، وهُوَ على كلّ شَيءٍ قدير ، رَبِّ أسْـأَلُـكَ خَـيرَ ما في هـذا اليوم وَخَـيرَ ما بَعْـدَه ، وَأَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما في هـذا اليوم وَشَرِّ ما بَعْـدَه، رَبِّ أَعـوذُبِكَ مِنَ الْكَسَـلِ وَسـوءِ الْكِـبَر ، رَبِّ أَعـوذُ بِكَ مِنْ عَـذابٍ في النّـارِ وَعَـذابٍ في القَـبْر.

አስባሕና ወአስበሐል መልኩ ሊላህ ወልሐምዱ ሊላህ ላኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላሸሪክ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር፤ ረቢ አስአሉከ ኸይረ ማፊ ሃዘል የውመ ወኸይረ ማባዕደሁ ወአዑዙ ቢከ ሚንሸሪ ማፊ ሐዘል የውመ ወሸርሪ ማ ባዕደሁ፤ ረቢ አዑዙ ቢከ ሚነል ከሰሊ ወሱኢል ኪበር፤ ረቢ አዑዙ ቢከ ሚን ዐዛቢን ፈናሪ ወዐዛቢን ፊል ቀብር

እኛ (በሰላም) አንግተናል ። ንግስናም የአላህ ሆኖ አንግቷል ። ምስጋና ለአላህ ነው። ከአላህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አንድ ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግስናም የርሱ ብቻ ነው። ምስጋናም ለርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነዉ። ጌታዬ ሆይ የዚህን ቀንና የቀጠዩን /የሌሊቱን/ መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፡፡ ከዚህ ቀንና ከቀጣዩ /ከሌሊቱ/ ክፉ ነገር በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ጌታዬ ሆይ ከእሳት ቅጣት ከቀብር ውስጥ ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 3 months, 2 weeks ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 2 months, 2 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 5 months, 2 weeks ago