ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 month, 2 weeks ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 1 month, 2 weeks ago
BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot
Last updated 3 weeks, 5 days ago
ማሰብ ጉዞ ነው፡፡ እምነት ግን በእኛ ሐገር ማረፊያህን ካገኘህ በኋላ የምታደርገው ጉዞ ነው፡፡ አምነህ ስለምትጀምር ብዙ ጊዜ አምላክን አታገኘውም፡፡ በሕይወትህ ውስጥ የሆነ ጥያቄ ሲመጣብህ ሮጠህ የሀይማኖት አባትህን ትጠይቃለህ እንጂ ለራስህ አታስበውም፡፡ ስትወለድ ተወልደሀል፡፡ አድገህበታል፡፡ ስሙን (ክርስቲያን ወይም ሙስሊም የሚለውን) ሰጥተውሃል፡፡ አምነሃል፡፡ የትም አትሄድም፡፡ ፍለጋ አታደርግም፡፡ “አንብበው እስቲ” ተብሎ የእምነት መጽሐፍ ቢሰጥህ እንኳን የምታነበው መልስ ለመስጠት እንጂ ለማመንና አለማመን አይደለም፡፡ ያመንከውን አምነሃል፡፡ እምነት ውስጥ ለምሳሌ “አምላክ አለ-የለም” የሚለው አይነት ሐሳብ አለ፡፡ ሐሳብ ውስጥ ግን እምነት የለም፡፡
ሐሳብ ጉዞ ነው፡፡ ሁሌ ታስባለህ፡፡ ፍፁም አይደለሁም” ነው የሚለው የሚያስብ ሰው፡፡ የሚያስብ ሰው ከሚያምነው በጣም የሚለይበት ጥሩ ጐኑ አሳቢው “ጐዶሎ ነኝ” ሲል አማኙ “ፍፁም ነኝ” ይላል፡፡ ትልቁ ልዩነታቸው ይህ ነው፡፡ አንድን አማኝ ስለ ኳንተምን ፊዚክስ አንሳና ጠይቀው እስኪ፡፡ “ሁሉም ነገር እኮ መጽሐፉ ላይ ተጽፏል፡፡ ምንም ያልተጻፈ ነገር የለም” ነው የሚልህ፡፡ ግን ምናልባትም መጽሐፉን አላነበበው ሁሉ ይሆናል፡፡ ቢያነብም አልመረመረውም ይሆናል፡፡ አምኖ መጀመር ማለት ይኼ ነው፡፡ የሃይማኖት መጽሐፉን በጥልቀት አንብቦ መፈተሽን እንደ ሐጢአት ነው የሚወስደው፡፡ አምኖ መጀመር ችግሩ ይሄ ነው፡፡ ካመንክ አምነሃል በቃ፡፡ ፍተሻ አያስፈልግህም፡፡ ስለዚህ ባታነብም፣ አንብበህ ባይገባህም “ልክ ነው” ብለህ ትወስዳለህ፡፡ አሳቢ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሁሌም አዲስ ሐሳብ እንዳለ ያስባል፡፡ አስር ገፅ እንዳነበበ ይጠይቃል፡፡ በሐሳብ በየቀኑ እያደግህ ትሔዳለህ፡፡ በኛ ሀገር በእምነት ውስጥ ግን በየቀኑ እያነስክ ነው የምትሄደው።
ቡርሃን አዲስ ነው ይህንን የነገረን
በህይወት ስትኖር የምታርፍበት ብዙ ፌርማታ አለ፡፡ በየፌርማታህ ያለህን ለውጥ መመዘን እንጂ በመጨረሻ ልትደርስ ያሰብከውን ተቻኩለህ መድረስን አትመን፡፡
በየማረፊያዎችህ ጥቂት ጥቂት እድገቶች ካሉህ እያጣጣምካቸው እለፍ፡፡
እየኖርክ ብትሳሳት እያደክም ነው። ካላስረገጥከው ግምትህ የምታገኘው ስሜትህን መረበሽና ስህተት እንዳይሆን አስተውል። በእጅህ ካለ እውነት በመነሳት መልካምን ትሆናለህ።
https://youtu.be/dB05iXi8Knw?si=5vsGzb1dP8sf4ZuB
YouTube
ጦርነት በፍልስፍና እይታ...'አድዋን እንዴት ነው ምንረዳው?' | ነፀብራቅ ከቡርሀን ጋር | Netsebrak @NBCETHIOPIA
National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be free from extremism and racism; for peace to prevail; for building a market-led economy; it is a corporation…
የጨበጥነውን አንፈራም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።
የያዝነው መዳፋችን ላይ ያለ ሁሉ የኛ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የምንጋፈጠው የፊት ለፊት ጦር አያስፈራንም፡፡ እስክንጀምረው ብንብረከረክ እንኳ አንዴ ላንመለስ ከእሳቱ ከጠለቅን የሞት ሽረት ይሆናል ጉዳዩ… ፡፡
የምንፈራው ያልያዝነው ወይም ከኛ ቁጥጥር ውጪ የሆነውን ነው፡፡ ወደ ኋላ ያለ ታሪካችንን እንፈራለን፤ እኛ ከምንቆጣጠረው ልክ ውጪ የመሆን አቅም ስላለው ነው፡፡ ወደ ነገም ስለሚመጣው ቀን እንፈራለን፤ እንደርስ ይሆን እንዳሰብነው እንሆንበት ይሆን ብለን ስንጠይቅ እርግጠኛ መሆን ሲሳነን ነው፡፡
ፍርሀት የእምነት ትጋትን ይነፍጋል፡፡ አቋምን ያከሳል፤ የዛሬን መኖር ይወስዳል፡፡ ፍርሃት በለውጥ አቅም ጥረታችን ሁሉ ጣልቃ እየገባብን ብርታታችንን ያጎላል፡፡
ከሚወዱት ሰው ጥቂት ደስታ ማየት ብዙ እፎይታ ነው።
ቡርሐን አዲስ
በማስተዋል መታገስንና በህይወት ግብግብ ልምድን መካበትን አስረግጠህ ተላመድ። በተፈተንክበት ጉዞህ በላቀ ትማራለህ። ከሀሳባዊ ግንዛቤህ በበለጠ የኖርከው ውሎ አዳር እርግጥ የሆነ ምሳሌህ ነው። ኑሮህን ከንባብህ አቻ ስፈርና በምትኖረው ተገንባ፣ የኖርከውን መማሪያ ስለ ማድረግ ፈንጥቅ።
ውሃን ውሃ ስለተባልክ ብቻ አትረዳውም በውሃ በዝናቡ ርሰህ ወይም ጠጥተህ ወይም ዋኝተህበት ማለፍ አለብህ፡፡ ነገሮች ስለተነገሩህ ብቻ አይሞሉህም፤ ስታልፍባቸው የልምድህ አካል ሲሆኑ ነው ይበልጥ የሚገለጡህ።
https://youtu.be/3F-uwO75cxA?si=kXibQuSK8xCwJivJ
YouTube
ነፀብራቅ! - አሉባልታ እና ትክክለኛ መረጃ ልዩነታቸው ምንድን ነው? @NBCETHIOPIA
National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be free from extremism and racism; for peace to prevail; for building a market-led economy; it is a corporation…
https://youtu.be/COG4qUWXPD4?si=HZADFlvPoOSqOBGl
YouTube
ሰው እንደ ሃይማኖትና ባህል ... ! - ነፀብራቅ @NBCETHIOPIA
National Media SC is here to support, the success of our country's transformational journey; to develop a civic-democratic political culture; which will be free from extremism and racism; for peace to prevail; for building a market-led economy; it is a corporation…
https://youtu.be/7_EilgkGCjg?si=hW0Y_8lIct5Z4kuj
YouTube
"ከልክ ወርደናል" በቡርሃን አዲስ
"ከልክ ወርደናል" ሆኖ መገኘት የሚል ሃሳብ ላይ የተሰጠ ድንቅ ማብራሪያ በቡርሃን አዲስ LIKE , SHARE , SUBSCRIBE