Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

የሀላባና አከባቢዋ ሰለፊዮች ቻነል

Description
قال بعض السلف "عليك بطريق الحق ، ولا تستوحش لقلة السالكين ، وإياك وطريق الباطل ، ولا تغتر بكثرة الهالكين "

እዚህ ቻናል ላይ የሚተላለፉ ማንኛውም ት/ቶች ምንጫቸው አስተማማኝ እንዲሆን እንጥራለን።

↪ቁርኣን↪ሀዲስ↪የሰለፎቻችንና↪የተከታዮቻቸው ንግግሮች ይተላለፋሉ፥

👇የቻናሉ አባል ለመሆን||
↪ @Halaba_Ahles_suna
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 2 days ago
3 weeks, 3 days ago

👉ይህ ግለሰብ እና አቋም የሌላቸው ግብራባሮቹ እንዲህ እንደቀን ፀሐይ ግልፅ በሆነ መልኩ የተናገሩትን ክደው ዛሬ ላይ ትናንት የተናገሩትን በግልፅ በሚጣረስ መልኩ በድፍረት እየተናገሩና ይህንን አሳፋሪ አቋማቸውን ሀቅ እያስመሰሉ የሱና ሰዎችን" ~~የሚናገሩትን የማይኖሩ ጉዶች~~" እያሉ ቢታቹ ሌባ ሆኖ ሳለ ሌሎችን"ሌቦች" እያለ ከሚተቸው ግለሰብ የተለየ ቦታ አይሰጣቸውም።

🔎ለአስተዋይ አጨብጫቢዎች የምንለው: - ዛሬ ላይ ሰለፎች እንኳ የብድዓ ሰዎችን ያወደሰን ሙብተድዕ አላሉም እያሉ የሚቀጥፉ፣ ከብድዓ ሰዎች ጋር በመልካም ነገር ላይ ለመስለሃ መተባበር ችግር የለም የሚሉ፣ ሙመይዓ የሚባል የለም ለማለት የሚቃጣቸው እነ ኸድር ከሚሴም ሆነ ግብራባሮቹ ከመቅለጣቸው እና እያዎቁ ከዐቅላቸው ጋር ከመጣላታቸው በፊት በራሳቸው ድምፅ ምስክርነት ይህ ነበር አቋማቸው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በድሮ አቋማቸው ላይ ናቸው ፥አልተቀየሩም ማለት በምን ሕሳብ ነው ትክክል ልሆን የሚችለው?!

እነ እልያስ አህመድ እንኳን ዛሬ የኢኽዋንን ፊክራ ተቀብለው ኢኽዋን ሆነው ይቅርና ከዛ በፊት ዛሬ ላይ የደረሱበት የጥፋት ማማ ላይ ከመድረሳቸው በፊት እንኳ #ወደ ቁልቁለት እየወረዱ ነው፣#ይህንን አቋም እኛ አንደግፍም፣#ደመረኩሙሏህ #በነሱ መቅራት ተገቢ አይደለም ....ሲሉ ከነበረው ከበፊት አቋም ጋር ፈጽሞ መታረቅ የማይችል የሆነን አቋም ሲያንፀባርቁ ከሁለት ነገሮች በአንዱ ምክንያት መሆኑን ግልፅ ማድረግ ግድ ይላቸዋል።

*1⃣*. በግልፅ ከበፊት አቋማችን ተመልሰናል፣በፊት የያዝነው አቋም ስህተት ነበር ብሎ ማለት። ይህን ካሉ እነሱ ስህተት ነው ሲላሉ ብቻ ሳይሆን እውነትም በፊት የነበሩበት አቋም ስህተት ነበርን? ወይስ እውነታው በፊት የነበሩበት ሆኖ ዛሬ የተመለሱበት ነው ባጥሉ ተብሎ ከመረጃ አንፃር ይታያል።

*2⃣*. መጀመሪያ የተናገርነው ሀቅ ነው። ነገር ግን ለዱንያዊ መጣቀሚያ ፣የተለያዩ ተቋሞችን ለመገንባት እና ባለቤትነትን ለመቆናጠጥ፣ብዙ ሰዎችን ለማግኘት እና በፊት ከምንፃረራቸው ሰዎች ዝናን ለማትረፍ ተስማሚ የሆነ አቋም ባጥልም ቢሆን አስፈላጊ ከመሆኑ አንፃር አድስ አቋም ለመያዝ ወስነናል፣ ይህ ነው የበፊት አቋማችንን እንድንተዋው ያደረገን ቢለው በግልፅ ተናግረው እነደነሱ ጥመትን የፈለገ ጥመት መሆኑን አውቆ እንዲከተላቸው፣ ሀቅ መስሎት የተሸወደ ደግሞ እንዲሪቃቸው ማድረግ ነበር።

እነሱ ግን መቀየራቸው ፍንትው ያለ እውነታ ከመሆኑም ጋር ከላይ ከተጠቀሱ ምክንያቶች አንዱንም ሳይጠቅሱ ሱፊያ ፣ተብሊግ እና ኢኽዋን ጭምር ያዎቀውን በዘዴና ሲስተም የተከረበቱትን መከርበት አይ የለም! አልተቀየርንም እያሉ ቁም ሲሉት የሚቆም ፣ቁጭ በል ሲሉት ቁጭ የሚል አጨብጫቢን ይሸውዳሉ።

📎በጣም ከምገረመው ነገር አንዱ እና በተጨባጭ ያለ ነገር ቢኖር: - ዛሬ ከነ ኢብኑ ሙነዎር የሚከላከሉ ሰዎች ትላንት በሱና ላይ የነበሩና ዛሬ ላይ እያዎቁም ሆነ ባለማዎቅ ከነሱ ጋር አቅላጭነትን ተላምደው ወደ ኢኽዋን እየገሰገሱ ያሉ ብቻ ሳይሆኑ ከመሰረቱ ጀምሮ ኢኽዋን፣ሱፊይ ....የነበሩ ሁላ ናቸው እየተከላከሉላቸው እና ከነሱ ጋር ሆነው የሱና መሻይኮችን እየተቹ ያሉት።

ትላንት እነ ሳዳት ሙስልሙን የለያዩ ጠላት ናቸው ሲሉ የነበሩ፣ከዛም አልፈው የየሁዳ ቅጥረኛ ናቸው ለማለት ይቃጣቸው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ ላይ በአድስ ፊት ከነ ሳዳት መከላከላቸው እነዚህ ሰዎች አቋም ቀይረው ጋብቻ ፈጽመው ነው ወይስ ኢኽዋኖቹ ቶብተው ሰለፊዮች ሆነው?! መልሱን ለአንባቢ ትቼያለሁ።
اللهم يا مقلب القلوب ثبت قلوبنا على دينك وسنة نبيك المطهرة

3 weeks, 3 days ago

ሙመይዓህ የሚባል የለም እያላቹህ
ተልቢስ ለምታደርጉ ሰውች ይሄው በአማረኛ ቋንቋ፣ እናንተ የምትቀበሉት ከሆነው ኡስታዝ ስሙት❗️
ይሄንን መጀመሪያ ላይ ነው የተናገረው
ሌላም እጨምርላቹኋለሁኝ ...

https://t.me/hutemariwochchannel

1 month ago

[ኢብኑ ሙነወር የትናንት አቋሙና የዛሬ አቋሙ፡

በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ ⚠️
----------------------------
🎙🎙በኡስታዝ ባህሩ ተካ (ሀፊዘሁሏህ)](https://t.me/aredualelmumeyia)
ኢብኑ ሙነወር ትላንትና ዛሬ
ትላንት እናስጠጋችኋለን ደመረኩሙላህ ሲላቸው የነበሩትን የመርከዙ ሰዎችን ወክሎ ድንበር ታልፎባቸዋል ብሎ ከኛ ጋር ለመነጋገር ጥሪ እያደረገ ነው !!!!!!።

[#የዶክተር ጀይላንን ሙብተዲዕነት ፍንትው ያለ ስላልሆነ የሸይኽ ኢብኑ ባዝ ንግግር እንደማይመለከተው ይነግረናል !!!! ።

የሀገራችን መሻኢኾችን ጥላሸት እየቀባ ህዝብ ዳኛ ሆኖ ልንወያይ በኦንላይን ኑ ይለናል !!!! ።](https://t.me/aredualelmumeyia)
ለማንኛውም የተጠቀሱትን ፁሑፎች አንብባችሁ ድምፁን ሰምታችሁ ፍረዱ እላለሁ

t.me/aredualelmumeyia
t.me/aredualelmumeyia

1 month ago
السلف كان نهجهم هكذا، إذا جاءهم …

السلف كان نهجهم هكذا، إذا جاءهم خبر يشعر بوقوع عالم من علماء السنة معروف في علمه وعقيدته وسلوكه وتمسكه بالسنة وبعده عن البدع وأهلها بما يخالف السنة يتثبتون ولا يأخذونه ويروجونه مباشرة كما يفعله بعض أصحاب الفتنة الصغار المنتسبين إلى السنة على الشيخ عبد الحميد اللتمي؛ ومن العجائب أنهم يتعاونون في ذلك مع المميعة الذين ليس لهم موقف ثابت في الأشخاص، إذا رأوا أحدا ينشر ما يمكنهم للطعن على من بين ضلالهم من العلماء فرحوا به وروجوه مع أنهم يرونه كذابا أشرا، فلا عجب من ذلك؛ لأنهم تأثروا بآبائهم الإخوان وبدؤوا يثنون عليهم ويدعون الناس إليهم ، ومن ثم اقتضى أن يعملوا بقاعدة هؤلاء:"الغاية تبرر الوسيلة" حتى يأخذوا من كل هب ودب ما أمكن للطعن على العلماء الأكابر ، قاتل الله الباطل وأهله

1 month ago

ሀቅ ፈላጊዎቹ በቀላሉ ይረዳሉ!
💡💡💡💡💡💡

🔦 አንድ እህታችን ነበረች። በተለያየ መልኩ የሱና መሻይኾችን ከሚተቹ ጎን በመሆን የተመዩዕ ባህር የጠለፋቸው ሰወችን ትደግፍ ነበር። በአንድ ወቅት የሚያውቃት ወንድማችን አናገራት። የመልዕክት ልውውጣቸው በከፊል የሚከተለውን ይመስላል፦

እሱ፦ "በመሻይኾችና በነሳዳት መካከል ያለውን ልዩነት በደንብ ታውቂያለሽ!?"
እሷ፦ "ሸይኽ አብዱልሃሚድ የምናገረውን አላውቅም ይላል የሚል ኦዲዮ ሰምቻለሁ"
እሱ፦ "አረጋግጠሻል? ምክንያቱም ለጥላቻ አላማ የሚነገሩ በርካታ ነገሮች አሉ። ለመሆኑ ከነዚህ እንደሰማሽው ሁሉ ከነሸይኽ አብዱልሃሚድና ሸይኽ ሀሰን ገላው በኩል የሚነገረውን አዳምጠሽ ታውቂያለሽ"
እሷ፦ "ምንም አዳምጬ አላውቅም።"
እሱ፦ "ታዲያ እንደት ለማውገዝ ወይም የሚወገዘውን ለመቀበል ቻልሽ?"
እሷ፦ "እሺ ውይይቱን ለምን እንቢ አሉ?"
እሱ፦ "እይውልሽ ውይይቱን እንቢ አላሉም። ነገር ግን ውይይቱ ሀቅ ከተፈለገበት መስተካከል ከተፈለገበት ዳኛው ተራ ሀዝብ ወይም በቴሌግራም የሚከታተል Subscriber ሳይሆን ኡለማ መሆን አለበት። ለዛም ነው ኡስታዝ ባህሩ ተካ በውይይቱ ውጤት ከፈለግን ከውጭ ኡለሞቻችን መጥተው ወይም ሰው ተመርጦ ወደ ኡለሞቻችን በመሄድ ችግሩ መፈታት አለበት ያለው ይሄው የኡስታዙን መልዕክቶች ተመልከች" ብሎ ላከላት በተጨማሪም በጉዳዩ ዙሪያ እነ ሸይኽ ሀሰን የተናገሯቸውን ትንታኔዎች ላከላት።
እሷ፦ "ይሄን ሁሉ አላውቅም ነበር።"
እሱ፦ "በተጨማሪም እነሳዳት እንደሰማሽው የሱና መሻይኾችን እያጠለሹ ❴ሸይኽ አልለውም፤ ከፊሎቹን በንፍቅና እየወነጀሉ❵ የመጅሊስ መሪ የተደረጉትን ግን በሳሎች ናቸው ምናምን እያሉ ይሰቃቅላሉ። ይሄን የሳዳት ድምፅ ስሚው" በማለት ላከላት

➲ ከዛም ❝ከነዚህ ሰዎች የጠራሁ ነኝ❞ በማለት በሰዎቹ ላይ ነቃች። አልሃምዱሊላህ አሁን የነኡስታዝ ባህሩን ትምህርቶች ትለቃለች። የአብዛኛው እህቶቻችን ሁኔታ ከዚህ የተለየ አይደለም።

እህት ወንድሞቼ ሆይ! ከአንድ በኩል የሚነገራችሁን ወይም ተቆራርጦና ተቀናብሮ የሚሰጣችሁን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹስ ምን ይላሉ ብሎ ማሰብ መልካም ነው። ለፍትህ የቀረበው አካሄድ ነገሮችን የለምንም ወገንተኝነት መመርመር ነው።

ሙመይዓዎች በጣም ነጋዴዎች ናቸው። የተለያዩ አጋጣሚዎችን ተጠቅመው የራሳቸውን የማንነት ገፅታ ግንባታ የሚያሸበርቁ ፖለቲከኞች ሆነዋል። አንዳንድ ስህተቶችን እና ክፍተቶችን ተጠቅመው ሌሎችም በማኮሰስ ራሳቸውን በመቀደስ ይታወቃሉ።

➧ አብዛኞቹ «አዎ እነሳዳት እንደዲሮው አይደሉም ረድም ሆነ የዳዕዋ ምርቃናቸው ወርዷል» ይላሉ ከፊሎቹም "በእርግጥ ሳዳትም ሆነ ለሌሎቹ እንኳን ለመርከዙ ሰዎች ይቅርና ለኢኽዋኖችም ያላቸው ጠላትነት ቀንሷል።" እያሉ እውነትን ቁጭ ያደርጋሉ። ነገር ግን ሀቁ አልተገራላቸውም ነበርና ከነሱው አይርቁም።

➽ እንዳጠቃላይ ማንም ሰው የማንም ተከታይ አይደለም። ሳዳትም ይሁን ሌሎቹ ሸይኽ አብዱልሃሚድም ይሁኑ ሸይኽ ሀሰን ገላው ሙሉ ለሙሉ የምንከተላቸው ፍፁማን ሳይሆኑ ሀቅ መያዛቸውን አይተን የምንማርባቸው ናቸው። ምክንያቱም ከነብያችን ﷺ ውጭ ሙሉ ለሙሉ የምንከተለው ሰው የለምና።

በአሁኑ ሰዓት የሀገራችን የሱና መሻይኾች ተናበውና ተመካክረው ወጣቱን ለመምራት ከጥፋት ወደ ልማት ለማቅናት ወደ ዒልም እንዲቅጣጭ ለማድረግ አባታዊ ምክሮችን በማስቀመጥ እያተረፉ ባለበት አብሮ ተሰልፎ በማገዝ ፈንታ ከሙብተዲዖች በላይ መሻይኾችን ማጥላላት እና ዝቅ ለማድረግ መሞከር በጣጥሰው እየቀጣጠሉ የመሻይኾቹን አንድነት ለማፍረክረክ መጣር ርካሽነት ነው።

📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

ሀሳብ  ካለዎ 
⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/AbuImranAselefybot

Telegram

Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ ***💡*** ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ***⤵*** ***↪*** እቀበላለሁ ***↩*** ***⤴*** ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

ሀቅ ፈላጊዎቹ በቀላሉ ይረዳሉ!
1 month ago

🟢የግፈኞች ጉድ

👉 አልከሶ ፣ ሀዋሳ ፣ ሀላባ ፣ ...

👉የተውሂድ ደዕዋ እንቅፋቶች

👉የኢኽዋን እና የሙመይዓ ግፋኞች

👉እንደ እብድ ውሻ በሽታ

👌ሰለፊዮች አብሽሩ የአላህ ነስር ቅርብ ነው።

قال ابنُ كَثيرٍ: قَولُه تعالى:( يَوْمَ تَبْيَضُّ وُجُوهٌ وَتَسْوَدُّ وُجُوهٌ ) يَعني: يَومَ القيامةِ، حينَ تَبيضُّ وُجوهُ أهلِ السُّنَّة والجَماعةِ، وتَسودُّ وُجوهُ أهلِ البِدعةِ والفُرقةِ، قالهُ ابنُ عَبَّاسٍ رَضيَ اللهُ ...

https://t.me/Abuhemewiya

1 month, 2 weeks ago
1 month, 3 weeks ago

👉 አዲሱ ቢድአ - በጎዳና ላይ ኢፍጣር

ቢድአ የሚጀመረው በትንሹና በቀላሉ ነው፡፡ ሲጀምሩት ደግሞ "እምቢ" ብሎ ደስ ደስ ይላል፡፡ ቀስ በቀስም አዳማቂው እየበዛ፣ ሆይ ሆይታው እየደመቀ ይሄዳል፡፡ እናም ቀስ ብሎ የጀመረውን ጉዞውን በሚያካክስ መንገድ፣ ፈጥኖ ከሰው ልብ ውስጥ የመግባት እድሉ እየጨመረ ይመጣል፡፡ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመን ደግሞ፣ እንደ አውሎ ንፋስ አንዴ አገሩን የማጥለቅለቅ እድሉ ሰፊ ነው፡፡
በመቀጠልም ዲን የመጠበቅን ሀላፊነት በጫንቃቸው ላይ የተሸከሙ አሊሞች፣ ሰርጎ ገቡን አዲስ መጤ ኢባዳ ማውገዝ ሲጀምሩ፣ "አይነካብን"፣ "በዲናችን መጣችሁብን"፣ ወዘተ የሚሉ ሰዎች (የአዋቂ አጥፊዎችና ጃሂሎች) ይፈጠራሉ፡፡ "ከምኔው በአዲስ መጤው የኢባዳ ፍቅር ተለከፉ?" ያስብላል፡፡ ከሁሉም በላይ ጥበበኛውና አዋቂው አሏህ እንዲህ ይላል፡-
"የወይፈኑንም ውዴታ በክህደታቸው ምክንያት በልቦቻቸው ውስጥ ተጠጡ..." (አል-በቀራህ፣ 93)
በማህበራዊ ሚዲያ አንቀልባ ታዝሎ፣ እንደ አውሎ ንፋስ አንዴ አገሩን በማጥለቅለቅ ላይ የሚገኘው አዲሱ ቢድአ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ነው፡፡ ይህን አዲስ መጤ ቢድአ፣ አሁን አብዛኛው ሰው በደስታ ተሞልቶ እየከወነው ይገኛል። በእርግጥኝነትም "የጎዳና ላይ ኢፍጣር አይነካብን" የሚሉ ሰዎች ጭምር ካሁኑ ተፈጥረው እያየን ነው።  
በሌላ በኩል ጥቂት ሰዎች የጎዳና ላይ ኢፍጣርን ማውገዝ የጀመሩ ቢሆንም፤ ባብዛኛው እያወገዙ ያሉት፣ "የጎዳና ላይ ኢፍጣር" የሚባል ነገር በሸሪአችን ያልተደነገገና ቢድአ መሆኑን በማሳየት ሳይሆን፣ በአፈፃጸሙ ላይ "አሉ" ያሏቸውን ግድፈቶች በመንቀስ፣ እንዲስተካከሉ በመወትወት ነው፡፡ በጎዳና ላይ ኢፍጣር መሳተፍ ያለበት ወንድ እንደሆነ፣ ሴቶች መሄድ እንደሌለባቸው ወይም ከሄዱ መከተል ስላለባቸው አለባበስ፣ ወዘተ በመምከር ላይ ተጠምደው ይገኛሉ - "አህያውን ፈርቶ ዳውላውን" እንዲሉ፡፡
መጀመሪያውኑ "የጎዳና ላይ ኢፍጣር" ተብዬው፣ በኢስላም ውስጥ የሌለና ውድቅ ተግባር ሆኖ እያለ፣ ህብረተሰቡ ሊነገረው፣ ሊመከርና ሊገሰፅ የሚገባው ስለቴክኒካል አፈፃጸሙ አይደልም፡፡ ኢስላማዊ ተግባር ያልሆነን ነገር፣ "ይሄ ጥቅም አለው። ይሄ ቢቀርና ይሄ ቢካተትበት፣ ይሄ በዚህ ቢስተካከል..." በማለት ቢድአን ለማቆነጃጀት መሞከር ከሞኝነት በላይ ነው፡፡ መሰረቱ ሸሪአዊ ያልሆነ ነገር፣ ኢስላማዊ ተግባር አይደለም፡፡ በሸሪአችን ያልተደነገገን ኢባዳ፣ ለአምልኮም ሆነ ወደ አሏህ ለመቀረብ አስቦ መከወን ቢድአ ላይ መውደቅ ነው፤ ቢድአ ደግሞ ኪሳራን የሚያከናንብ ውድቅ ተግባር ነው - አራት ነጥብ፡፡
በሙስሊም ዘገባ (1718) መሰረት፣ የአሏህ መልእክተኛ (አለይሂ ሰላም) እንዲህ ብለዋል፣
"በዚህ ጉዳያችን (በዲናችን) ውስጥ የሌለን ነገር የሰራ ሰው፣ ስራው ውድቅ ይሆናል፡፡"
ቢድአ ለጀሀነም እሳት የሚዳርግ፣ የተወገዘ የጥመት መንገድ ነው። መልእክተኛው (አለይሂሰላም) እንዲህ ይላሉ፡-
"በሀይማኖት ውስጥ በጣም መጥፎዎቹ ጉዳዮች አዲስ የተፈጠሩ ናቸው፡፡ አዲስ መጤ ነገር ሁሉ ፈጠራ ነው፤ እያንዳንዱ አዲስ ፈጠራ ጥመት ነው፡፡ ጥመትም ሁሉ በገሀነም ውስጥ ነው።"
አንዳንድ የዋሆች ደግሞ "ኢስላምን ለማስተዋወቅ ይጠቅማል" ሲሉ ይሰማል። ቢድአ ላይ በመውደቅ አይደለም ኢስላምን ማስተዋወቅ ያለብን፡፡ ብዛታችንንም ሆነ ድምቀታችንን የምናሳይባቸው በዲናችን የተደነገጉልን ኢዶች አሉን፡፡ ጁምአም ከዚሁ የሚጨመር ነው፡፡ በተጨማሪም ዲናችን የሚያዘንን በትክክል ከተከተልን፣ የእለት ከእለት ውሎና እንቅስቃሴያችን በራሱ ትልቅ ኢስላምን የማስተዋወቂያ መንገድ ነው፡፡ ወንዶች ፂማችንን ባለመቁረጥና ባለመላጨት እንዲሁም ሱሪያችንን በማሳጠር፣ ሴቶች ደግሞ ከቤታቸው ሲወጡ ጅልባብና ኒቃብ በመልበስ የመልእክተኛውን (አለይሂ ሰላም) ትእዛዝ በማክበር ኢስላምን በየእለቱና በየቦታው ሁሉ ማስተዋወቅ ይገባናል፡፡ ፂማችንን እየላጭን፣ ሱሪያችንን እጎተትን፣ ያናታችንን ፀጉር እያንጨባረርን በአንድ ቀን የቢድአ ሆይ ሆይታ ኢስላምን እናስተዋውቃለን ማለት ዘበት ነው፡፡ በነገራች ላይ እለት በእለት መፈፀም ያለባቸው ኢስላማዊ አደቦችን መጠበቅ (ሀቀኝነት፣ አማና መጠበቅ፣ ከመጥፎ ተግባራት መራቅ፣ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል፣ ወዘተ) ኢስላምን ከማስተዋወቅም አልፎ በራሱ ዳእዋ ነው፡፡ ሸሪአችን ሳይመክረን የተወው መልካም ነገር፣ ሳያስጠነቅቀን የተወው መጥፎ ነገር የለም፡፡ ጥበበኛው አሏህ እንዲህ ይለናል፡-
"ዛሬ ሀይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ፀጋዬንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ፡፡" (አል-ማኢዳህ 3)
ባጭሩ ኢስላምን በጎዳና ላይ ኢፍጣር ለማያስተዋወቅ መፍገምገም፣ ቢድአን በቁንጅና ሳሎን የማስዋብ አካል ነው። ዋናው ነጥብ ለአንድ ቢድአ መቶ ቀርቆ አንድ ሺህ ደጋፊ ማስረጃ ቢቀርብ፣ ከቢድአነቱ ላይ የቅንጣት ቅንጣት የማይቀነስ ከመሆኑ ላይ ነው። ኢስላም ያላዘዘውን መስራት ይቅርና ኢስላም በግዴታነት ጭምር ያዘዘውን አምልኮ (ለምሳሌ ሶላት፣ ፆም፣ ሀጅ…) በሸሪአው ከተደነገገው የአፈፃፀም መንገድ ውጭ (ለምሳሌ መጠኑን ወይም ሰአቱን ወይም ቦታውን ወይም ሌላውን የአፈፃፀም ሁኔታ) ብንቀይር፣ ባልታዘዝነው መንገድ የተፈፀመ ነውና ለፍቶ መና እንሆናለን፡፡ ከአሏህ ቅጣትም አናመልጥም፡፡ የዝንጀሮ ቆንጆ እንደሌለ ሁሉ፣ የቢድአም ጥሩ የለውም፡፡
ከፍ ሲል እንደ ተገለፀው፣ የቢድአ ተግባራት በትንሹ ይጀመሩና ከዚያ እየሰፉ፣ አዳዲስ ነገሮችንም እየጨመሩ የመሄድ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በኢስላም ለተወገዙ ተጨማሪ ብልሹና ፀያፍ ለሆኑ ወንጀሎች አመች መድረክ እስከ መሆን ይደርሳሉ፡፡ በጥፋት ላይ ጥፋት፣ በወንጀል ላይ ወንጀል ይደርባሉ፡፡ መጋቢት 30/2015 አዲስ አበባ ላይ የተከናወነው የጎዳና ላይ ኢፍጣር፣ ሴቶችና ወንዶች ልቅ በሆነ መንገድ የተቀላቀሉበት፣ ወደ መጨረሻ ላይ በመንዙማ፣ በነሺዳና በሙዚቃ በመታጀብ የተጨፈረበት ጭምር እንደ ነበር የምስልና የቪዲዮ ማስረጃዎች ወጥተዋል፡፡ አንዱ ቢድአ ለወንድሙ ቢድአ ጥሩ መድረክ ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን የታዘብንበት ነው፡፡ ልክ አቶ መውሊድ ለመንዙማና ለሽርክ ተግባራት፣ ለሴትና ለወንድ ቅልቅል፣ ለጫት ቂምሀው፣ ወዘተ አመች ሜዳ እንደሆነ ሁሉ፡፡
ችግሩ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ከአዲስ አበባው በኋላ በአንዳንድ የክፍለ ሀገር አካባቢዎች የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል፡፡ በነዚህ አካባቢዎች የተካሄደው የጎዳና ላይ ኢፍጣር በየአደባባዩና በየቦታው እንዲቀመጡ በተደረጉ የተለያዩ ስእላ ስእሎችና ቅርፃ ቅርፆች እንዲታጀብ የተደረገ መሆኑ፣ ከአዲስ አበባው ለየት ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ አላባ የሚባለው አካባቢ ግዙፍ የሆነ የካእባን ቅርፅ አቁመው (በአራት ማእዘን ቅርፅ የሰሩትን ነገር የካእባን ስእል ለጥፈው) ነው ኢፍጣር ያካሄዱት፡፡

የደሴ ሙስሊሞች በበኩላቸው የጎዳና ላይ ኢፍጣርን ምክንያት በማድረግ፣ የሚናራ ቅርፅ ያለው ባለአራት ማእዘን በጣም ረጅም ነገር ሰርተው፣ ከፒያሳው አደባባይ ላይ ተክለዋል፡፡  አስገራሚው ነገር አደባባዩ ላይ የተተከለው የሚናራ ቅርፅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ከሚያካሂዱበት የሆጤ ሜዳ በኪሎ ሜትሮች የራቀ መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ የሚናራ ቅርፁን የተከሉበት የፒያሳው አደባባይ፣ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በጥምቀት በአላቸው ወቅት፣ መስቀልና የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ስእላ ስእሎችን ለእይታ የሚተክሉበትና የሚያስቀምጡበት መሆኑ ጭምር ነው፡፡ በስሜት ፈረስ የሚታጀበው የቢድአ አውሎ ንፋስ እንዲህ ነው ጥርግ አድርጎ የሚወስድ፡፡ የተከተሉት አርአያ

3 months, 1 week ago

የመርከዙ ሰዎች የተመዩዕና ኢኽዋንይነት ማረጋገጫ የሚለው ፋይል በወንድማችሁ ባህሩ ተካ ተፅፎ በወንድም ኡቡ ዒምራን ወደ pdf ተቀይሮ ተጠናቅሮ ቀርቧል። አላህ ለሂዳያ ሰበብ ከሚሆኑት ያድርገን።

https://t.me/bahruteka/4532

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago