Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
If you want Emmaus press in the form of application, here it is.
የጥቂት ደቂቃዎች ቆይታ በቤተክህነት ቤተመጻሕፍት።
የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያን አስመልክቶ የምንጠቀምባቸው አብያተ መጻሕፍት በብዛት ተዘግተዋል። ከአንድ ወዳጄ ጋር አጋጣሚውን በመጠቀም ለምን የቤተ ክህነቱን ቤተ መጻሕፍት አናየውም የሚል ዐሳብ መጣልንና ተያይዘን ወደዚያው አመራን።
ግቢ ውስጥ ከገባን በኋላ ወደ ላይብረሪው የሚያደርሰው መንገድ ላይ ብዙ ከቆሙበት ሳይንቀሳቀሱ ዓመታት ያለፋቸው ላንድ ክሩዘር መኪኖች ተመለከትን ። ይዞታቸው ደህና ይመስላል ። ግን ሰውነታቸው በፀሐይና በዝናብ መፈራረቅ መጎዳቱ ይታያል ። ጎማዎቻቸውም ተኝተዋል ።
መኪኖቹን አልፈን ወደ ላይብረሪው ስንደርስ መግቢያው ላይ ጥበቆቹ አብጠርጥረው ፈተሹን። ከዚያ እኛ እንደ ማንኛውም ቤተ መጻሕፍት መስሎን ልንገባ ስንል በቦርሳችን ውስጥ የነበሩትን መጻሕፍት ይዘን እንዳንገባ ከለከሉን ። 'ለምን?' ብለን ስንጠይቅ ውስጥ ካሉት መጻሕፍት መለየት አንችልም' ። 'ውስጥ ያሉት መጻሕፍት ሌላ ቦታ እንደሚደረገው በቁጥር እና በማኅተም አይለዩም ወይ' ብንላቸው 'አይለዩም' አሉን ። ግን 'የያዝናቸውን መጻሕፍት አሳይተናችሁ ብንገባስ' ብለን አማራጭ ለማበጀት ሞከርን። 'አይቻልም' ። ይሁን ብለን መጽሐፎቻችንን አውጥተን ሰጠናቸውና ልንገባ ስንል ። 'አይ ቦርሳም ይዞ መግባት አይቻልም' አሉን ። ግራ ተጋብተን ተያየንና ከቦርሳዎቻችን ውስጥ ማስታወሻዎቻችንን አውጥተን ቦርሳዎቹን ስንሰጣቸው - 'ማስታወሻም አይገባም' አሉን ። 'ንጹሕ ወረቀት እንሰጣችኋለን እንጂ የተጻፈበት ማስታወሻ ተይዞ አይገባም' ።
ግርምታችን ያለ ጥርጥር ፊታችን ላይ እየተነበበ ቦርሳዎቻችንን ከነማስታወሻዎቻችን አስረከብን - እኔ ኮምፒዩተሬን ያዝሁ - ወዳጄ ደግሞ አንዲት እምብዛም ያልተጻፈባት ትንሽዬ ማስታወሻ ይዞ እንዲገባ ፈቀዱለትና እሷን ይዞ ገባን ።
አሁንም ግን ከመግባታችን በፊት ሌላ ማስታወሻ ተሰጠን '6 ሰዓት ይዘጋል እኮ ለነገሩ' ። ሰዐታችንን አየን - ወደ ስድስት ተቃርቧል ። ለማንኛውም ይዞታውን እንየው እስከዚያ ብለን ገባን ።
ውስጥ ስንገባ ማንም አልነበረም ። ባለን ሰዓት ሼልፎቹን ለመቃኘት ሞከርን። ቤተመጻሕፍቱ እጅግ ሰፊ ፣ የሚያምር ውቅር እና ይዞታ ያለው ነው። ጥሩ ጥሩ መጻሕፍት አሉት ፣ ግን በአግባቡ ካታሎግ አልተደረጉም። ዝብርቅርቃቸው ወጥቷል። አዳዲስ መጻሕፍት ከገቡም እንደሰነባበቱ ለመረዳት ጥቂት ደቂቃዎች በቂ ነበሩ። ገና ሼልፎቹን ቃኝተን ሳንጨርስ አንድ መነኩሴ ብቅ አሉና "ሰዓት ደርሷል ፤ ሊዘጋ ነው" አሉን። "እስከ ስድስት ነው የሚሠራው ቤተመጻሕፍቱ" ሲሉም አከሉ። ከሰዓት ስንት ሰአት ነው የሚከፈተው?" ብለን ጠየቅናቸው። "ስምንት ሰአት" ብለው መለሱ። "ከዚያስ እስከ ስንት ይቆያል?" ፤ "እስከ 10" ። "ጠዋትስ ስንት ሰዓት ይከፈታል ?" አልናቸው ። "ሦስት ሰዓት" ተያየን እና እቃዎቻችንን ይዘን ወጣን ። በፊታችን ላይ ግርምት ፡ በውስጣችን ደግሞ ብስጭት እንደሰፈኑ - ከብዙ ዓመታት በፊት የተገተሩትን መኪኖች አልፈናቸው ከግቢው ወጣን ።
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago