የቀደምቶች መንገድ

Description
ይሄን ቻናል ለመክፈት ያነሳሳኝ፦
① የዲን መሰረታዊ እውቀቶችና ሰዎች ከእሳት ድነው ጀነትን የሚወርሱበት በሆነው ጥቅል የአህሉስ-ሱንና ወል-ጀማዐህ እምነት ላይ ትኩረት ይሰጣል።

② በሺርክና በቢድዐህ የተበከለውን የሙስሊሞች ዐቂዳ በማስተካከሉ ዘርፍ ላይ የጎላ ሚና ይኖረዋል።

③ ሙስሊሞችን ወደ ቁርኣንና ወደ ነብዩﷺ ሱንና እንዲመለስ

ፊ ዓቂደቲ አሰለፊ አስሷሊሕ(አህሊ'ስ ሱንነቲ ወ'ል- ጀማዕህ)
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

2 months ago

ከንቱ ጩኸት ከንቱ እሪታ
ሌላ ማምልክ ትቶ ጌታ
በገዛ እጁ ክብሩን ንቆ
ከመሬት ላይ አፈር ዝቆ
ብጥብጥ አርጎ እየጋተ
ያ ሚስኪን ሰው ውስጡ የሞተ
ዛፍ ላይ ጨሌ እያሰረ እየፈታ
በፍርሀት ያለ ያጣ ደስታ
ለጠንቋዩ ለዛ ከንቱ
የሚገብር አለ ስንቱ?
ከቀብር ደጅ ከሙታኑ
የሚጠና ከካፊሩ
ስጠኝ ብሎ የሚለምን
በህይወቱ ላይ የሚጨክን
ከፈጣሪ የተጣላ
ኢባዳውን በጠቅላላ
ያደረገ ለጥንቆላ
ስንት ቂል አለ ከኛ መንደር
ሱጁድ ሚወርድ ለሙት ቀብር
ሚጠውፈው ሚለምነው
ድረስ ብሎ ሚጠይቀው
በየአመቱ ሚዘይረው
ክብር እያለው ክብሩን ያጣው
በሌላ አይደል በዚህ እኮ ነው
ተውሂድ ትቶ ሽርክ መጠጣቱ
ከንቱ ጩከት ባዶ ከንቱ
ጌታ እያለ ለመቃብር መደፋቱ

የቀደምቶች መንገድ የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቅለው ሼር ያድርጉ👇👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

2 months, 2 weeks ago

የተውሒድ ትምህርት ክፍል አንድ
👇
ክፍል አንድ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/34
ክፍል ሁለት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/35
ክልፍ ሶስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/37
ክፍል አራት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/38
ክፍል አምስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/40
ክፍል ስድስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/41
ክፍል ሰባት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/42
ክፍል ስምንት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/44
ክፍል ዘጠኝ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/46
ክፍል አስር 👇
https://t.me/ahlul_jenah/47
ክፍል አስራ አንድ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/48
ክፍል አስራ ሁለት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/49
ክፍል አስራ ሶስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/50
ክፍል አስራ አራት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/52
ክፍል አስራ አምስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/53
ክፍል አስራ ስድስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/54
ክፍል አስራ ሰባት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/55
ክፍል አስራ ስምንት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/56
ክፍል አስራ ዘጠኝ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/58
ክፍል ሃያ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/59
ክፍል ሃያ አንድ 👇
https://t.me/ahlul_jenah/60
ክፍል ሃያ ሁለት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/61
ክፍል ሃያ ሶስት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/62
ክፍል ሃያ አራት 👇
https://t.me/ahlul_jenah/66

🚨Share ሼር
ወንድማችሁ ሙ @jezakellah

የቀደምቶች መንገድ የቴሌግራም ቻናል
ጆይን & ሼር👇👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

2 months, 2 weeks ago

⚠️ እንንቃ ከዝሙት የባሰ ነው።❗️

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

እንትናን አወቃችሁት? እናቱጋ ዝሙት ሰራ!
.
.
ብላችሁ አፋችሁን ይዛችሁ ትደነግጣላችሁ አይደል።? ነገር ግን እገሌ በአላህ ላይ አሻረከ(ከፈረ ካደ)ብላችሁ ምንም አይመስለንም። ይሄ ወላሂ የሽርክን ከባድነት አለማወቃችን ነው።❗️

እናትን ከመድፈር በላይ ሽርክ ከባድ ወንጀል ነው።! እያሻረክን ከሞትን ተስፋ የለንም። ዘላለም ጀሃነም ላይ እንበሰብሳለን። አላህን በማስረጃ እንወቀው። በተለይ ከታች ያሉትን ርእሶች በደምብ ተረድተን ልናምንባቸው ልንሰራባቸው ይገባል። ካልሆነ ከከሳሪዎች ከእድለ ቢሶች እንሆናለን። ስማችን ሙስሊም ስልሆነ ብቻ ጀነት አይገባም።

የትኞቹን እና የት እናግኛቸው ካላችሁኝ ከታች ቻናሉ ላይ ሁሉንም ማግኘት ትችላላችሁ ተረግግተን ሁሉንም እናንባቸው ከቁርአንና ከትክክለኛ ሃዲሶች የተውጣጡ ናቸው።
አጥብቀን እንያዛቸው የጀነት ዋስትናችን ናቸው። ርእሶችም፦
.አላህ ለምን ፈጠረን?
.ኢባዳ ወይም አምልኮ ምንድን ነው?
.አላህን እንዴት ነው የምናመልከው?
.አላህን የምናመልከው በፍርሃት እና በተስፋ(በመከጀል)ላይ ሁነን ነዉን?
.በኢባደህ/አምልኮ ላይ?
.ኢህሳን(ማሳመር)ማለት ምን ማለት ነው ?
.አላህ መልዕክተኞችን(ሩሱሎችን) ለምድነው የላከው ?
.ተውሂድ አርረብ ምንድነው?”(አላህን በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ ማላት ምን ማለት ነው)?
.ተውሂድ አል-ኡሉህያ(በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ) ምንድነው?
.ተውሂድ ሲፋቲ-አልላሂ ወአስማኢሂ(አላህን በስሞቹና በባህሪው ብቸኛ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው)?
. አላህ የት ነው ያለው ?
. አላህ ከኛ-ጋር ነውን ?
. የተውሂድ ጥቅሙ ምንድነው ?
. ስራ(ኢባዳ)ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስገልጉ መስፈርቶች እነማን ናቸው ?
.ትልቁ ሽርክ
?
.የትልቁ ሽርክ አይነቶች?
.ትልቁ ሽርክና አይነቶቹ?
.መቃረብና ሸፈዓን/ምልጃን መፈለግ?
.ጅሀድ መወዳጀትና ሁክሙ?
.በቁርኣንና በሃዲስ መስራት?
.ሱናና ቢድዓ በዲን ላይ ?
.ተቀበይነት ያለው ዱአ?
.አቂዳ(የእስልምና እምነት)

👉 ይቀጥላሉ

🔥ተውሂድን ላላረጋገጠና ሽርክ ላይ ለተዘፈቀ ስሙ ይሄን የአላህ ዛቻ👇

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም(ኀጢአት)ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡

🎁 እነዚያ ተውሂዳቸውን አረጋግጠው ከሽርክ ለጠሩትና መልካምን እየሰሩ ለፅኑ ደሞ በዚህ መልኩ አብስሯቸዋል።
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የጀነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።

🔋 ከላይ የላኩላችሁን ርእሶች ከታች ባለው አዲሱ ቻናላችን ገብታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። ቻናሉንም ልናሳድገው ይገባል ለጓደኞቻችን ሁሉ ሼር እናድርግላቸው።
🚨🚨🚨🚨ሼር Share

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

የቀደምቶች መንገድ👇👇👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah
👆👆 ጆይን & ሼር 👆👆

4 months, 2 weeks ago

? የተውሒድ ትምህርት? ?         ? ክፍል ሃያ አንድ(21)        ?በቁርኣንና በሀዲስ መሰራት ጥያቄ.1 አላህ ቁርኣንን ለምንድነው ያወረደው ? ?መልስ.1 አላህ ቁርኣንን ያወረደው ልንመራበትና ልንሰራበት ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦ “ከጌታቹ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ ”(ሱራህ አንኒሳእ 4:59) የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦“ቁርኣን…

5 months, 1 week ago

? የተውሒድ ትምህርት? ?
? ክፍል ሃያ አንድ(21)

?በቁርኣንና በሀዲስ መሰራት

ጥያቄ.1 አላህ ቁርኣንን ለምንድነው ያወረደው ?

?መልስ.1 አላህ ቁርኣንን ያወረደው ልንመራበትና ልንሰራበት ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦ “ከጌታቹ ወደ እናንተ የተወረደውን ተከተሉ (ሱራህ አንኒሳእ 4:59)

የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦“ቁርኣን አንብቡት በሱም ስሩበት ቁርኣንንም የገቢ ምንጫቹ አታድርጉት”(ሰሂህ.አህመድ ዘግበውታል)

ጥያቄ.2 ትክክለኛ በሆኑ ሀዲሶች መስራት እንዴት ይታያል?

?መልስ.2 ትክክለኛ በሆኑ ሀዲሶች መስራት ዋጂብ/ግዴታ ነው። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦“መልዕክተኛው ያመጣላቹህን ነገር ያዙት(ስሩበት)ከሱም የከለከላቹ ከሆነ ነገር ራቁ (ሱራህ አልሃሺር 59:7)

የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)እንዲህ ብለዋል፦ “ የኔን ፈለግ/ሱና እና ቅንና የተምሩ የሆኑ ምትኮቼንም ፍለግ በመከተል ላይ አደራ እሷንም አጥብቃቹ ያዙ”(ሰሂህ. አህመድ ዘግበውታል)

ጥያቄ.3 ያለሀዲስ በቁርኣን ብቻ እንብቃቃለንን ?

? መልስ.3 ሀዲስን ትተን በቁርኣንና ብቻ አንብቃቃም። ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦“ ወደ እነሱ የተወረደውን ቁርኣንንም እንድታብራራላቸው ወደ አንተ ዚክርን(ሀዲስን)አወረድን "(ሱራህ አንነህል 16:44)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦“ አዋጅ,እኔ ከቁርኣን ጋር አምሳያውን(ሀዲስን) ተሰጥቻለሁ።(ሰሂህ.አቡዳውድ እና ሌሎችም ዘግበውታል

ጥያቄ.4 በአላህ እና በመልዕክተኛው ንግግር ላይ ሌላን ንግግር እናስቀድማለንን?

? መልስ.4 በአላህ እና በመልዕክተኛው ንግግር ላይ ሌላን ንግግር አናስቀድምም ምክንያቱም ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ ያመናቹ ሆይ,ከአላህና ከመልዕክተኛው ፊት አታስቀድሙ።”(ሱራህ አል-ሁጁራት 49:1)

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
ፈጣሪን በማመጽ ለፍጡር መታዘዝ የለም።”(ሰሂህ.ጠበራኒ ዘግበውታል)

ከኢብኑ አባስ ንግግሮችም መካከል፦“ ከሰማይ የሆነ ድንጋይ እንዳዮርድባቹህ እፈራለሁ እኔ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ስላቹ እናንተ ደሞ ’አቡበከር እና ዑመር እንዲህ ብለዋል! ትሉኛላቹ?”
(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)
? ? ይ ቀ ጥ ላ  ?  ሼር ሼር ሼር

ሚዲያን ለዲናችን ብቻ❗️?
         ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

አዲሱን የቀደምቶች መንገድ የሚለውን
  የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቅሉን
? ጆይን & ሼር??
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah
? የ ጀ ነ ት ሰ ዎ ች ?

7 months, 1 week ago

? የተውሒድ ትምህርት? ?   ? ክፍል አስራ ዘጠኝ(①⑨) ጥያቄ.(⑥)በህይወት ካሉ ሰዎች ምልጃን መጠየቅ ይቻላልን? መልስ.6⃣ በዱንያ ጉዳይ በህይወት ያሉ ሰዎችን አማላጅነት(እርዳታ)መጠየቅ ይቻላል። ከፍ ያለው አላሁ(ሱብሃነሁ ወተዓላ)እንዲህ ይላል፦  “መልካም የሆነን ማስታረቅ ያስታረቀ የሆነ ሰው ለሱም መልካም የሆነ ድርሻ ይኖረዋል እንዲሁም መጥፎ የሆነን ማስታረቅ ያስታረቀ የሆነ ሰው ለሱም…

8 months, 1 week ago

? ? የተውሒድ ትምህርት? ? ? ክፍል አስራ ሰምንት(①⑧)      ?መቃረብ እና ምልጃን መፈለግ ? ጥያቄ.2⃣ ዱዓእ በመሀል ወደ አላህ የሚያደርሰው ሰው ያስፈልገዋልን? መልስ.2⃣ ዱዓእ በመሀል ወደ አላህ የሚያደርሰው ሰው አያስፈልገውም። ምክንያቱም ከፍ ያለው አላሁ(ሱብሃነሁ ወተዓላ) እንዲህ ይላል፦ ?"ባሪያዎቼ ሰለ እኔ በጠየቁህ ግዜ እኔ ለነሱ ቅርብ መሆኔን ንገራቸው”(ሱራህ አል…

8 months, 1 week ago

?ለተውሂድ ትኩረት እንስጥ የምንለውኮ በምክንያት ነው ወዳጆቸ!

ተከተሉኝ ትንሽ
  ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

የአዳጋዎች ሁሉ አደጋ የወንጀሎች ሁሉ ከባድ በአላህ ላይ ማሻረክ፣ ፈጥሮህ አሳድጎህ ተንከባክቦህ እያለ በሱ ላይ ማጋራት ነው። በአላህ ላይ ማጋራት በየትኛውም ሁኔታ ሊያጠቃን ይችላል ማንም ከሽርክ ንፁህ ነኝ ብሎ ሊተማመን አይገባውም።
እኔ ስለ ሽርክ ሊነገረኝ አይገባም ከሽርክ ርቄ አይደል መስጅድ የመጣሁት ልንል አይገባም ምክንያቱም መስጅድ ውስጥ ሁነንም ሽርክ ላይ ልንወድቅ እንችላለን።
ሽርክ ማለት ላይህ ላይ መጦ ሲወድቅ የሚታወቅ ነገር አይደለም ከጉንዳን ኮቴ የበለጠ ስውርና ድብቅ ነው

በለሊት ጨለማ ላይ በጥቁር ድንጋይ ትንሽየ ጉንዳን ሲሄድ እንዳይታወቀው ድምፁም የማይሰማውን ያክል ሽርክ ስውር እንደሆነ ተነግሮናል ለዛም ነው ነብያቶች ሳይቀር ይሄን ወንጀል የፈሩት ታዲያ እኛስ ልንፈራውና ልንርቀው ሁሌም ልንተዋወስ አይገባም!?

እንደ ካንሰር አያሉ የተለያዩ በሽታዎችን ፈርተን እንደምንጠነቀቀው ከዛ በላይ ከሽርክ ልንጠነቀቅ ይገባናል ምክንያቱም የከባዶች ሁሉ ከባድ በሽታ ስለሆነ። ሶላት አለመስገድ፣ የሰው ነፍስ ማጥፋት ፣ዚና ፣ወለድ፣ወላጅን መበደል ሌሎችም ነብያችን ይሄን የሰራ ከኛ አይደለም እያሉ የገለፇቸው ከባድ ወንጀሎች አሉ ከነሱ በላይ ነው ይሄ ሽርክ የሚባል በሽታ። ስለዚህ እኛም ልንርቀው ቤተሰቦቻችንንም ልናስጠነቅቅ ይገባናል። ይሄን የአላህ ቃል ሰምቶ የማይፈራ አለ?

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ
አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡

እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ የሆነ ጌታ ነው በመሆኑም ግን በሽርክ ላይ ድርድር የለኝም እያለ ነው። ታዲያ ምንን ተማምነን ነው ስለ ሽርክና ተውሂድ የማንተዋወሰው ለምን ነው ስለ ተውሂድና ሽርክ ሲነሳ የሚያመን። ስለ አላህ በብቸኝነት መመለክ እንዳለበት ሲሰሙ ልባቸው የሚጨነቀውኮ ከእስልምና የወጡ ሰዎች ነበሩ ነገሩ ተገልብጦ ግን ስለ ሽርክ ሲነሳ ስለ ተውሂድ ኪታብ ሲቀራ ሰላም የሚያጡ አሉ። አላህ ይመልሰን

ተውሂድን እናሰራጭ ተውሂድ ውስጥ ብዙ ተዘርዝረው ማያውቁ ትምህርቶች አሉ።
አንዳንዱ ደግሞ እኔ ተውሂድ ይዣለሁ ወንጀልን ባተራምስም አላህ አይቀጣኝም ብሎ የሚያስብ አለ ይሄ ሞኝነት ነው አላህን በሁሉም ነገር ላይ ልንፍራ ይገባል። አላህ መፍራትም ማለት የከለከለውን መከልከል ያዘዘውን መስራት ማለት ነው። የምንችለው ነገርም ስለመሆነ ነው አንድን ነገር ራቁት ወይም ስሩት የሚለን። 

ስለ ተውሂድ በማስረጃ ልናውቅ ይገባል።

የተውሂድ ትምህርት በሚል ስለቅላችሁ የነበረው አስተማሪ ተከታታይ ፁሁፍ ክፍል 19 ደርሷል ኢንሻ አላህ ይቀጥላል። ከዚህ ትምህርትም በኋላ በሰፊው እንመካከርበታለን።

ለሃቅ ሁሌም እጅ እንስጥ ሚዛናችን ቁርአን ሃዲስ እንጂ ሰዎች አይሁኑ!

ወንድማችሁ @jezakellah

የቀደምቶች መንገድ
አዲሱን ስለተውሂድና ሽርክ ምንተዋወስበትን ቻናል ተቀላቀሉ ለጓደኞቻችሁም አጋሩ! ባረከላሁ ፊኩም
????
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

የተውሂድ ትምህት ይቀጥላል ክፍል 19

9 months, 4 weeks ago

??? የተውሒድ ትምህርት ??? ? አስራ ስድስት(①⑥)           ? ትንሹ ሽርክ እና አይነቶቹ ? ? ጥያቄ.1⃣ ትንሹ ሽርክ(ማጋራት) ምንድነው? መልስ.1⃣ ትንሹ ሽርክ ማለት ይዩልኝ/ይስሙልኝ ማለት ነው። ይህም ማለት ማንኛዉንም የአምልኮ ስራ በሚሰራበት ግዜ ለአላህ ብሎ ሳይሆን ሰው እንዲያይልኝ ሰው እንዲሰማልኝ ብሎ መስራት ነው። አላሁ(ሱብሃነሁ ወተዓለ)እንዲህ ይላል፦ ? "ጌታዉን መገናኘትን…

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад