ነሲሓ መስጅድ Nesiha Mosque Official Channel مسجد النصيحة

Description
ከነሲሓ መስጂድ (18) ትምህርቶች፣ ኹጥባዎችና የተራዊሕና ቂያም ሰላቶች የሚተላለፉበት፣ ለጀመዓው ማስታወቂያና መረጃ የሚተላለፍበት Official ቻነል ነው።

الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
Advertising
We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 6 months, 4 weeks ago

💫"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
🕌በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 3 months, 3 weeks ago

1 year, 8 months ago

*? ዘካተል ፊጥር በገንዘብ ተተምኖ ማወጣት ያወገዙ ፉቀሃዎች ረሂመሁሙላህ*

  • `ኢማሙ ማሊክ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ብለዋል፡-

{ለአንድ ሰውም የዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ቢያወጣ ተቀባይነት የለውም፣ ደግሞም የነብዩ ﷺ ትእዛዝ አይደለም።}

?አልሙደወነቱል ኩብራ ( 2/385)

══════❁✿❁═════

ኢማሙ አሽሻፊዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦

“ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ማውጣት አያብቃቃም።”

❒ አል ኡም (2/72)

══════❁✿❁═════

  • ኢማሙ አል ነዋዊ - አላህ ይዘንላቸውና - (ከታዋቂዎቹ ሻፊዒዮች አንዱ):
    (አብዛኞቹ የፊቅህ ሊቃውንቶች ዘካተል ፊጥርን በዋጋ ተምኖ ገንዘብ እንዲወጣ አልፈቀዱም)*ብለዋል።

❒ ሸርሑ ሙስሊም (7/60)

══════❁✿❁═════

  • ኢማም አሕመድ - አላህ ይዘንላቸውና -
    *(ዘካተል ፊጥር ዋጋውን ተምኖ በገንዘብ ለችገረኛ አይሰጠውም።”አሉ። በዚህን ግዜ እንዲህ ተባሉ፡- “ሰዎች፦ ዑመር ኢብኑ ዐብዱል ዐዚዝ  ዘካተል ፊጥርን በገንዘብ የሚሰጡ ሰዎችን ይቀበሉ ነበር። ይላሉ።” እሳቸውም፦
    “የአላህ መልእክተኛ ﷺ የተናገሩትን ትተው እገሌ እንዲህ አለ ይላሉን?!” በማስከተልም፦
  • ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ብለዋል፡- * (የአላህ መልእክተኛ ﷺ  ዘካተል ፊጥር በምግብ፣በእህል ሙስሊሞች ላይ ግዴታ አደረጉባቸው።) ብለዋል። አላህም እንዲህ አለ፡- (አላህን ታዘዙ መልእክተኛውንም ታዘዙ)*
  • ሰዎች ግን እገሌ፣ እነእገሌ፣ አሉ፣ ተባለ እያሉ ሱናን ሲነገራቸው የነቢዩን ﷺ ንግግር ይመልሳሉ!!(ይተዋሉ)!!)* *

❒ አልሙግኒ (2/352)

══════❁✿❁═════`

ኢማሙ ሻፊዒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

⛔️ከአላህ መልእክተኛ ﷺ የተረጋገጠ ሱና እርሱ ዘንድ የደረሰው ሰው በሙሉ፣ ለየትኛውም የሰው ንግግር  ብሎ (ሱናን) መተው እንደሌለበት ዑለማዎች በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።”

?(አርሪሣላህ ገፅ 425)

http://t.me/sultan_54

Telegram

የኡስታዝ ሱልጣን ኸድር የትምህርት መድረክ (official)

ይህ በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር እውቅና የተከፈተ ብቸኛው (official) ቻነል ሲሆን የእርሱ ትምህርቶችና አጫጭር መልእክቶች በየጊዜው የሚተላለፉበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ አላህ መልካም ምንዳውን ይክፈለው፤ ከዕውቀቱም ተጠቃሚ ያድርገን! ትምህርታዊ ቁም ነገሮች ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ እንዲሁም ሐሳብና አስተያየት ካልዎት በዋትስ ኣፕ ይላኩልን! ***♻***: https://api.whatsapp.com/send?phone=

*****?*** ዘካተል ፊጥር በገንዘብ ተተምኖ ማወጣት ያወገዙ ፉቀሃዎች ረሂመሁሙላህ**
2 years, 2 months ago
ልዩ ዕድል ለኢልም ፈላጊዎች

ልዩ ዕድል ለኢልም ፈላጊዎች

በታላቁ መስጂደነበዊ የሙቱኖች ሂፍዝ ፕሮግራም ባሉበት ሆነው በርቀት በመሳተፍ ቋሚ የሀረም ተማሪዎች የሚያገኙትን የብቃት ኢጃዛና የምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላሉ።

ፕሮግራሙ በእውቁ ኢማም ሸይኽ አብዱልሙህሲን አልቃሲም አስተባባሪነት የሚካሄድ ሲሆን፤ ለተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ኢጃዛውንም የሚሰጡት እራሳቸው ናቸው።

ማሳሰቢያ፦ ይህ ፕሮግራም የሚመለከተው ወንዶችን ብቻ ነው!

በጉግል Meet የቀጥታ ስብሰባ በኩል ለመሳተፍ
http://meet.google.com/yxs-smgf-dwn

ለበለጠ መረጃ የኢትዮጵያ ተማሪዎች አስተማሪ ሸይኽ ሙሀመድ ሰዒድን በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ +966558142209

ለጀማሪዎች በተሰናዳው የተምሂዲ ፕሮግራም እና በቀጣይ እርከኖች የሚተሀፈዙትን ኪታቦች በተከታዩ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://a-alqasim.com/books-cats/mutoon/

رابط الاجتماع
http://meet.google.com/yxs-smgf-dwn

تحميل برنامج Google Meet
http://onelink.to/dac8a4

عن برنامج حفظ المتون
https://www.mottoon.com/Login.aspx

مواقيت الصلاة بالمدينة المنورة
http://bit.ly/Mawaqit

2 years, 2 months ago

የመውሊድ በዓል በሚዛን ላይ
""""""""""""""""""""""""
ነሲሓ መጽሔት ቅጽ Vol2 ቁጥር 1

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው ፡፡ ሰላት እና ሰላም ለዐለማት እዝነት በተላኩት በነቢያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በሰሃባዎቻቸው እና እነርሱን በመልካም በተከተሉት ሁሉ ላይ እስከ እለተ ቂያማ (ትንሳኤ) ድረስ ይውረድ፡፡
ቁርዓን እና ሐዲስን እንዲሁም ዝርዝር የሸሪዓ ህግጋትን በትክክል መረዳት ለሁሉም ሙስሊም በእጅጉ አስፈላጊ ቢሆንም ቀላል ግን አይደለም።
አላህ ለዚህ ኡማ ታላቅ ውለታ በመዋል ኡለማዎችን ሰጥቶን ያላቸውን ታላቅ ክብር ገልፆልናል፡፡ የሙስሊሞችን እምነት፣ የአምልኮ ‘ዒባዳ’ አተገባበር እና የስነምግባር እሴቶችን ማረም የዑለሞች ተቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ከሰሀቦችና እነሱን ከተከተሉ ታቢዒዮች መካከል ታላለቅ ዑለማዎች እና የፊቅህ ጠበብቶች ቁርዓንን በተገቢው መልኩ በመረዳት እና ዕድሜያቸውን ሙሉ በማስተማር ሀላፊነታቸውን ተወጥተዋል። ሰሃባዎች ከማንም በበለጠ በዕውቀት የበለፀጉ ከመሆናቸው ባሻገር የመልእክተኛውን ﷺ ንግግር እና ሱና በመተግበር ፋና ወጊዎች እንደነበሩ አያጠያይቅም።
አብደላህ ኢብን መስዑድ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና በአንድ ወቅት ስለሰሃባዎች እንዲህ ብለው ነበር፤ "ከዚህ ከነቢዩ ዑመት ከማንም በበለጠ፤ ቅን ልቦና፣ የጠለቀ እውቀት፣ የተቃና ፈለግ እና ያማረ ስብዕና ባለቤት ነበሩ። እነሱ ማለት አላህ ለነብዩ ጓደኝነት የመረጣቸው ህዝቦች ናቸው፡፡ ክብራቸውን እወቁላቸው። ፋናቸውንም ተከተሉ። እነሱ ቀጥተኛው መንገድ ላይ ነበሩ።" ኢብኑ ዐብደል በር / ጃሚዑል በያኒል ዒልም በሚባለው ኪታባቸው ቅጽ 2/946-947 ሰሃባዎች በሐቅ ላይ አንድነታቸውን ለመጠበቅ የተለያዩ ሸሪዓዊ አጀንዳዎች ላይ ይመካከሩና ይተራረሙ ነበር፡፡ ያልደረሳቸውን መረጃ ሲያገኙም ወደ ሐቅ ከመመለስ የሚያግዳቸው ነገር አልነበረም። ለሐቅ ተገዢ ስለነበሩ እርምት ለሰጣቸው አካል ምስጋና እና ክብራቸው ከመጨመሩ ባሻገር በመካከላቸው የነበረው ወዳጅነት አልጎዳም። ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ብለዋል "ሰሃባዎች፣ ታቢዒዮች እና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ዑለማዎች በመካከላቸው አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ የአላህን ትዕዛዝ ይከተሉ ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል «በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትሆኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡» ሱረቱ ኒሳዕ : 59 በተለያዩ የዲን አጀንዳዎች ላይ በምክክር መልክ ይወያያሉ፡፡ አልፎ አልፎ የዒልምና እና የተግባር ጉዳዮች ላይ የአቋም ልዩነት ሲኖር መዋደድን፣ መተሳሰርን እና ኢስላማዊ ወንድማማችነትን በጠበቀ ሁኔታ ይተራረማሉ።" መጅሙዑል ፈታዋ 24/172

በየዓመቱ የረቢዐል አወል ወር በገባ ቁጥር የነቢያችንን የልደት በዓል መውሊድን የማክበር ጉዳይ ሰዎችን ሲያወዛግብና መነጋገሪያ ሲሆን ይታያል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሙእሚኖችን በመሰረታዊም ይሁን በቅርንጫፋዊ የዲን ጉዳዮች ላይ አለመግባባት ቢፈጠሩ ጉዳያቸውን ወደ ቁርዓንና ሐዲስ በመመለስ መፍትሄ እንዲፈልጉ በሚከተለው የቁርዓን አንቀጽ አዟል፡፡

فَإِن تَنَازَعْتُمْ فِي شَيْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى اللَّهِ وَالرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا ٤:٥٩

«በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ የተከራከራችሁበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው» ሱረቱ ኒሳዕ : 59

ከዚህ ቁርአናዊ መመሪያ በመነሳት ለአንባቢዎቻችን ነሲሓ ይሆን ዘንድ ትክክለኛውን አቋም እናመላክታለን። አላህ ሀቁን አይተው ከሚከተሉት ሰዎች ያድርገን። ይህ በዓል በሸሪዓ መሰረት የሌለውና ሰዎች በዲን ውስጥ የጨመሩት አዲስ ነገር ከመሆኑ ባሻገር አላህና መልእክተኛው ያልደነገጉትን ተግባር በቀን የተገደበ ወደ አላህ መቃረቢያ አምልኮ ማድረግ መሆኑ ዋነኞቹ የመውሊድ ችግሮች ሲሆኑ፤ በተጨማሪም ክርስቲያኖችን በመፎካከር የመጣ መሆኑ ከእነሱ ጋር መመሳሰል ነው። በተጨማሪ በዚህ በዓል ውስጥ በሸሪዓ የተወገዙ በርካታ ተግባራት ይፈፀማሉ። መውሊድ አንድን ስራ ቢድዓ የሚያሰኙ ምክንያቶች ሁሉ እንዳሉበት አያጠራጥርም። ይህም በሚከተሉት ሶስት ነጥቦች ይብራራል፤
1) አዲስ ነገር መፍጠር (ኢሕዳስ)
ካለ ሸሪዓዊ ማስረጃ፤ ማንኛውንም ቀን ወይም ወር ልዩ ሀይማኖታዊ ክንውን የሚፈፀምበት እንደሆነ በማሰብ በዋጂብነት ወይም ሱናነት ሰዎችን የምናበረታታበት ከሆነ በዲን ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር ነውና ሀራም ነው።

አሏህ እንዲህ ብሏል:-
أَمْ لَهُمْ شُرَكَاءُ شَرَعُوا لَهُمْ مِنَ الدِّينِ مَا لَمْ يَأْذَنْ بِهِ اللَّهُ
«ከሀይማኖት አላህ በእርሱ ያልፈቀደውን ለእነሱ የደነገጉ ተጋሪዎች ለእነርሱ አሏቸውን?» ሱረቱ ሹራ ቁጥር 21

ቡኻሪ እና ሙስሊም በዘገቡት የተረጋገጠ ሰሂህ ሐዲስ ነቢያችን ﷺ ብለዋል፤

مَنْ أحْدَثَ في أمْرِنَا هَذَا مَا لَيْسَ مِنْهُ فَهُوَ رَدٌّ

«በዲናችን ውስጥ ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ ስራው ተመላሽ ይደረግበታል» ብለዋል።

ይህ ማለት በሸሪዓ ያልተደነገገን ነገር ፈጥሮ ቢፈፅም ተቀባይነት አያገኝም ማለት ነው።

እንደሚታወቀው፤ መውሊድን ረሱል ﷺ የተከበሩት ኸሊፋዎች እና ሌሎችም ሰሀባዎች አላከበሩትም። እንደዚሁ በተከበረው ዘመን ውስጥ የኖሩት ሰሀባዎችን በመልካም ሲከተሉ የነበሩ ታቢዒዮች አልሰሩትም። እነሱ ደግሞ ከማንም በላይ የሱና አዋቂዎችና ለነቢያችን የነበራቸው ውዴታም ከማንም በላይ እንደነበር እሙን ነው። የነብዩን ፈለግ በሚገባ በመከተልም የማይታሙ እንደ ነበሩ ለማንም ግልፅ ነው። ለኛ አርአያ መሆናቸውም ተነግሮናል። ምንም ሳንጨምር መንገዳቸውን አጥብቀን እንድንይዝ የአላህ መልዕክተኛ አደራ ብለውናል፤

عَلَيْكُمْ بِسُنَّتِي وَسُنَّةِ الْخُلَفَاءِ الرَّاشِدِينَ الْمَهْدِيِّينَ، وَعَضُّوا عَلَيْهَا بِالنَّوَاجِذِ، وَإِيَّاكُمْ وَمُحْدَثَاتِ الْأُمُورِ، فَإِنَّ كُلَّ مُحْدَثَةٍ بِدْعَةٌ، وَكُلَّ بِدْعَةٍ ضَلَالَةٌ
«የእኔን እና የቅን ምትኮቼን ሱና አደራ! በጥርሶችችሁ አጥብቃችሁ ያዙ! አዳዲስ ፈጠራዎችን ተጠንቀቁ (ተከልከሉ)፣ በዲን ውስጥ የተጨመረ ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው» ኢማሙ አህመድ ዘግበውታል

መውሊድ በቀደምቶቹ ዘመን እንዳልነበረ እና ኃላ የተፈጠረ (ሙህደስ) ለመሆኑ መውሊድ አክባሪዎች ሁሉ የማይክዱት እውነታ ነው። መውሊድ ማክበርን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት ከአራተኛው
ክ/ዘመን በኋላ እራሳቸውን ፋጢሚዮች ብለው ይጠሩ የነበሩት ኡበይዲዩች ግብፅን በ362 ዓመተ ሂጅራ የወራሩ ጊዜ ነበር።

ቀጣዩን ያንብቡ? https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1336321059824881&id=1003047829818874

Facebook

Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

2 years, 2 months ago

بوابة القبول لطلاب المنح بجامعة الإمام محمد بن سعود الإسلامية
من 1-3-1444
إلى 15-3-1444

القبول في جامعة الإمام الرياض

https://apply.imamu.edu.sa/pages/user.aspx?fid=6b8f5a90-39a1-4268-bdc3-3a0c16e37049

2 years, 3 months ago

https://youtu.be/74uE0tbC_xY

YouTube

የነብያችንን መውሊድ ለምን አናከብርም!

2 years, 4 months ago

? እጅግ ወሳኝ ትምህርት!
? ስለ መላኢካ ዓለም ምን ያህል ያውቃሉ?

(عالم الملائكة)

ዘውትር ማክሰኞ እና እሮብ ከመግሪብ እስከ ዒሻእ

? ዓለም ባንክ ሰላም መስጂድ የተሰጠ ትምህርት

https://t.me/sultan_54

2 years, 4 months ago

الأشاعرة ليسوا من أهل السنة والجماعة

الشيخ فلاح بن إسماعيل مندكار رحمه الله

2 years, 4 months ago

ወንድምህ ማለት …
ካለህ ላይ ትሰጠዋለህ እሱም ይሰጥሀል ለችግርህ ጊዜ ከጎንህ ይቆማል፣ አንተ ከሱ ኪስ ትወስዳለህ እሱም ካንተ ኪስ ይወስዳል ፣ ሁሌ መስማማት ላይኖር ይችላል፣ አዎ በአንዳንድ ጉዳዮች ላትስማማ ትችላለህ በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ትስማማለህ አንተ ትወቅሰዋለህ እሱም ይወቅስሀል መጨረሻ ላይ ግን እርስ በርሳችሁ ትታረቃላችሁ ልባችሁ ላይ ቂምን አትቋጥሩም የቀኑ መጨረሻም ሌሊት ላይ አብራችሁ በሳቅ በጨዋታ ታሳልፋላችሁ።ይህ ነው ትክክለኛ ወንድማማችነት።አንተ ስትደሰት ይደሰታል፣ አንተ ተከፍተህ ማየት አይወድም አንተ ስትከፋ እሱም ይከፋዋል ፣ አንተ በሌለህበት ስትታማ ካንተ ይከላከልልሀል ፣ ነውርህን ይሸፍንልሃል ፣ ወደ መልካም ነገር እጅህን ስትዘረጋ እሱም ይዘረጋል፣ ክፍተትም ካለብህ ይሸፍንልሃል፣ እንጂ እንደሌላው ዳር ይዞ አንተን አያማም ፣ የሆነ ችግር ወይም አደጋ ቢደርስብህ ቀድሞ የሚደርስልህ ወንድምህ ነው!
የሆነን ነገር ከጠየቅከው ይሰጥሀል ፣ አኩርፈኸው ዝም ብትለው እሱ በሰላምታ ይጀምርሃል ያናግርሃል ፣ መልካም በሆኑ ነገራቶች ከራሱ አንተን ያስቀድማል ፣ ለችግርህ ቀድሞ ይደርሳል ፣ ከአይኑ ስትሰወር ይናፍቅሀል ይፈልግሀል፣ ስትዘነጋም ያነቃሃል።ጌታውን ሲለምን ዱዓዕ ሲያረግ አይረሳህም ፣ በዱዓው ያስታውስሃል።
ወንድም ማለት ራስ ላይ የሚደፋ አክሊል ፣ አንገት ላይ የሚደረግ ጌጥ ነው ፣ እርሱ ማለት ላንተ ውበት ነው። ወንድም በሆነ ችግር ወድቆ ብታገኘው ልታነሳው ይገባል ፣ ችግር ላይ ቢወድቅ እርዳው ደግፈው ፣ ቢደክም ቢልፈሰፈስ አንሳው አበርታው ።
ወንድም ማለት በችግር ጊዜ ደራሽ ነው ፣ አጋዥ ነው ፣ በችግር ጊዜ እንደ ጥላ ያገለግልሀል ፣ ልትወድቅ ስትል እንደ ምርኩዝ ያገለግልሃል።
? ስለ ወንድምነት ካደረገው የጁምዓ ኹጥባ የተወሰደ
https://t.me/sultan_54

2 years, 5 months ago

الرد السلفي الدامغ على شبهة أن
(الأمة عالة على علوم الأشاعرة)

#አህባሽ #ሱፍያ #አሽዓሪያ

We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 6 months, 4 weeks ago

💫"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
🕌በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 3 months, 3 weeks ago