ቤተ መጻሕፍት

Description
"መጻሕፍት፡ ለሰው ልጅ መድኀኒት የታዘዘባቸው የማዘዣ ወረቀት መኾናቸዉን ተገንዝባችኊ አንቡቧቸው።"
('ርጢን' ገጽ ፲፫)፧፧፧፧

የ'ቤተ መጻሕፍቱ' ሊንክ
https://t.me/betemetsihaf

ለማንኛውም አስተያየት https://t.me/getnetfekadu
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

4 days, 21 hours ago
[#**ኅዳር**](?q=%23%E1%8A%85%E1%8B%B3%E1%88%AD)[**#ጽዮን**](?q=%23%E1%8C%BD%E1%8B%AE%E1%8A%95)

#ኅዳር#ጽዮን

"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው

ጽዮን የሚለው ስም
. በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራ እና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል
. በትንቢታዊ ምስጢሩ ግን
ድንግል ማርያም
ቤተ ክርስቲያን እና
ዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል

ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፡-

  1. በብሉይ ኪዳን ታቦተ ጽዮን የፈጸመችውን ልዩ ልዩ ገቢረ ተኣምራትን በማሰብ

  2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስን እና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት በመሆኑ

  3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት "ክርስትና" የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት #ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበት

  4. ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ምሳሌ ራእይ ያየበት

  5. ነቢዩ ሕዝቅኤል በተቆለፈች ቤተ መቅደስ

  6. ዕዝራ በቅድስት ሀገር ምሳሌ ራእይ ያየበት

  7. አብርሃና አጽብሃ በወርቅ እና በዕንቁ ያሠሩት ባለ ዐሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት

  8. በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል
    ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ
    ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ

በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል ይከበራል፡፡

ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው
በአክሱም ጽዮን ማርያም ብቻ ነው ማለት ሳይሆን፣
ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን #ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

ምልጃዋ አይለየን🙏

5 days, 19 hours ago

#ፈሪሃ#እግዚአብሔርን(እግዚአብሔርን መፍራትን) ገንዘብ ስታደርግ

ገንዘብ ካላቸው በላይ ባለጠጋው አንተ ነኽ፤

'እንዴት' ትለኝ ይኾናል፤

እኔም 'እንዲኽ ብዬ' እመልስልኻለው፤

የባለጠጎቹ ገንዘብ ያልቃል፤
ያንተ ግን ብል እና ዝገት አይበላውም፤

ጊዜ አይለውጠውም፤

አያልቅም፤

ወደ ሰማያት፣
ወደ ሰማየ ሰማያት፣
ወደ ምድር፣
ወደ አየራት፣
ወደ እንስሳቱ ዓይነት፣
ብዙ የብዙ ብዙ ወደሚኾኑት ዕፅዋት፣
ወደ ደቂቀ አዳም በጠቅላላው፣
ወደ መላእክት፣
ወደ መላእክት አለቆች፣
ወደ ኃይላት #ተመልከት

እነዚህ ኹሉ የአምላክኽ ፍጥረት ናቸው፤

የእነዚኽ #አምላክ እና #መጋቢ
ባርያ መኾን
"ድሃ መኾን" አይደለምና፥
'ድሃ አይደለኽም' ብዬ እነግርኻለው።

[{ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ}]

1 week, 5 days ago

#የነቢያት#ጾም

. ከልደት በዓል አስቀድሞ የሚጾም ሲሆን፣ #ከኅዳር ፲፭/15/ ቀን ጀምሮ ለ፵፫/43 ቀናት ተጹሞ፣ የሚፈሰከው በልደት በዓል ነው፤

. ይኽ ጾም በዘመነ ብሉይ እና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤

. ዛሬም እኛ ምእመናን፣
እንደ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣
የአባቶችን ፈለግ ተከትለን፣
ከፈጣሪ ጋር ለማግኘት እንጾመዋለን
መጾምም ይገባናልም፡፡

በመሆኑም በጌታችን ልደት፣
ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት፣
ይህ ጾም የነቢያት ጾም ይባላል፤

. የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መኾን ያስተማሩበት ስለሆነም ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

. ምንም እንኳን ትንቢቱ የተፈጸመ ቢሆንም፦
በረከት ለማግኘት
የነቢያትን ፈለግ ተከትለን
በየዓመቱ እንደ ዐዲስ ደስ ብሎን

ክብር ይግባውና ጌታችን ለፍርድ መጥቶ፣ መንግሥቱን ከሚያወርሳቸው ቅዱሳኑ ጋር እንዲደምረን

"የነቢያትና የሐዋርያት፣ የጻድቃን እና የሰማዕታት አምላክ ተለመነን" እያልን #እንማጸንበታልን#እንጾመዋለን፡፡

3 months, 1 week ago

አንድ ወንድም አንድን አረጋዊ
"ልቤ ደንድኖብኛል፤ እግዚአብሔርንም አልፈራውምና ምን ላድርግ" ብሎ ጠየቀው።

አረጋዊውም
"እግዚአብሔርን ከሚፈራ ደግ ሰው ጋር ኑር[ዋል]"
አለው።

[ከበረሐውያን ሕይወት እና አንደበት ፤ በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ፤ ገጽ ፻፰/108፤ ፳፻፫/2003 ዓ.ም.]

3 months, 1 week ago

ፍቅር ከሌበት ልቡና ፥ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሊመነጭ አይችልም፤

ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላው ልቡናም፥ የንስሓ መሰናክል ነው።

3 months, 1 week ago

በብዙ ወንዶች መፈለግ ጽድቅ አይደልም፤

ጥያቄው የተፈላጊነትሽ መደብ የቱ ነው የሚለው ነው፤

ለዝሙት ከኾነ የፈለጉሽ፦
ላቷን ገልጣ ከምትሄድው ፍየል ለይተው አላዩሽም ማለት ነው፤

መታየት እኮ አያመጻድቅም

ምስጢር መስማት የምትወጂውን ያኽል ነው ምስጢር መኾን ያለብሽ አራት ነጥብ

...

© ...

6 months ago
6 months ago

ቅዱስ ኒፎን አጋንንት የተለያየ ሰይጣናዊ ሃሳብን፣
በሰዎች ጆሮ እያንሾካሾከ፣
እንዴት እንደሚፈትኗቸው ይመለከት ነበር።

ሰዎች ግን፦
በተለያየ ዓለማዊ ጉዳዮች ተጠምደው፣
ይኽነን ፈጽሞ አያስተውሉትም።

በዚህም፦
የዲያብሎስ ሃሳብ፥
የራሳቸው እስኪመስላቸው ድረስ

ተቀብለው በመፈጸም እና በማስተዋወቅ ተጠምደዋል።

በአብዛኛዎቹ ላይ
ቁጣ፣
ሐሜት፣
ዘለፋ፣
ጠብ፣
ክርክር፣
ቅያሜ
እና የመሳሰሉት ተንሰራፍቶባቸዋል።

[ራእየ ኒፎን ፤ ትርጒም በቀሲስ ታምራት ውቤ፤ ገጽ ፹/80 ፤ ፳፻፲፫/2013 ዓ.ም.]

6 months, 1 week ago

??? ጸሎት ???

፩. ጸሎት ከክፉ ነገር ይጠብቅሃል፤

፪. ጸሎት በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፫. ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ይበልጥ ያቀርብኻል፤

፬. ጸሎት ደስተኛ ያደርግኻል፤

፭. ጸሎት ተስፋን ይሰጥኻል፤

፮. ጸሎት የራስ ወዳድነት ስሜትኽን ይቀንስልኻል፤

፯. ጸሎት ከኹሉም ስቃዮች ይፈውስኻል፤

፰. ጸሎት ፈተናን ለማሸነፍ ይረዳኻል፤

፱. ጸሎት በመንፈሳዊ ሕይወትኽ ጠንካራ እንድትኾን ያደርግኻል፤

፲. ጸሎት ነገሮችን ይለውጣል።

7 months, 4 weeks ago

ወንድምኽን ለመቃወም፣
ክፉ አሳብ በተነሣብኽ ጊዜ ጸልይ

በአንተ ላይ የሠራዉን ክፋት፣
[ከውስጥኽ] ልታስወግደው የሚቻልኽም
በጸሎት ነው፤

? ለሰው ልጆች ኹሉ
ወንድማዊ የኾነ ፍቅር፥
በአንተ ውስጥ እንዲያድግ መንገዱ ይኼው ነው።

ለሰው ልጆች መጸለይ ስትጀምር፣
ወንድማዊ ፍቅር በአንተ ውስጥ
ተፀንሶ ይወለዳል
ያድጋልም

አንድ ሰው ክፉ ነገር ሲፈጽምብህ፥
ለርሱ ትሑት እና በጎ ሰው ኹንለት፤

በትሕትና ቅረበው

ከሥጋ ፈተናም ታድነዋለኽ

[{ከአበው አንዱ}]

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago