Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
1ኛ፦ ዑለማኦቹ ዝም እንዳሉ ምን አሳወቃችሁ? እናንተ ካላወቃችሁ ደጋፊ ናቸው ነው የሚባለው? ዘመኑ የኢንተርኔት ነው ቢቃወሙ እናገኘው ነበር የሚል አይቻለሁ። በዚህ መልኩ ከደነ -ቆረ አካል ጋር መግባቢያው ሩቅ ነው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
مَنْ أَرَادَ أَنْ يَنْصَحَ لِذِي سُلْطَانٍ فَلَا يُبْدِهِ عَلَانِيَةً، وَلَكِنْ يَأْخُذُ بِيَدِهِ فَيَخْلُو بِهِ، فَإِنْ قَبِلَ مِنْهُ فَذَاكَ وَإِلَّا كَانَ قَدْ أَدَّى الَّذِي عَلَيْهِ
"ለባለስልጣን መምከር የፈለገ ሰው ባደባባይ አያውጣው። ነገር ግን እጁን ይዞ ገለል አድርጎ ይምከረው። ከተቀበለ እሰየው። ካልሆነ ግን ያለበትን አደራ ተወጥቷል።" ሸይኹል አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። (አንዱ ሐይሠሚ ዶዒፍ ብለውታል እያለ ገፅ ጠቅሶ ሲዋሽ አይቻለሁ። ቦታው ላይ የሌለ ቅጥፈት።)
እናንተ ስላላያችሁ ብቻ ዑለማኦች ዝም እንዳሉ ነው የምታስቡት? እንዲህ አይነቱ ጥያቄ ሶሐቢዩ ኡሳመቱ ብኑ ዘይድ ላይ ተነስቶ ነበር። "ለምን ዑሥማንን ገብተህ አታናግርም?" ሲሏቸው እንዲህ ነበር ያሉት፦
إِنَّكُمْ لَتُرَوْنَ أَنِّي لاَ أُكَلِّمُهُ إِلَّا أُسْمِعُكُمْ، إِنِّي أُكَلِّمُهُ فِي السِّرِّ دُونَ أَنْ أَفْتَحَ بَابًا لاَ أَكُونُ أَوَّلَ مَنْ فَتَحَهُ
"እናንተ ካላሰማኋችሁ በስተቀር እንደማላናግረው ነው የምታስቡት። እኔ የሸር በር ከፋች ሳልሆን በሚስጥር አናግረዋለሁ፤ የመጀመሪያው ከፋች አልሆንም።" [አልቡኻሪይ፡ 3267] [ሙስሊም፡ 2989]
ኢብኑ ዐባስም የሃገር መሪን በመልካም ስለ ማዘዝና ከመጥፎ ስለ መከልከል ሲጠየቁ "የግድ የምታደርገው ከሆነ ባንተና በሱ መሀል ይሁን።" [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይበህ፡ 7/470] [ሹዐቡል ኢማን፣ በይሀቂይ]
ይሄ ነብያዊ መንገድ፣ ይሄ የሶሐቦች አካሄድ የኢኽዋንና የኸዋ - ሪጅ በቀቀኖች ዘንድ የመድኸሊያ እምነት ነው። ሐዲሦቹንና ኣሣሮቹን አትፍቋቸው እንግዲህ። ዑለማኦቹ የናንተን ክስ ፈርተው ነብያዊውን አስተምህሮት ጥለው የሰካ.ራም ህግ ይከተሉ ወይ? እነዚህ የኢኽዋን መንጋዎች ድንቁ -ርናቸውን ንቃት ያደረጉ የመሀይማን መንጋ ናቸው። ፕሮፌሰሩ ከተራው ሰው አይለይም። ጭንቅላት ከሆድ የከበረ አካል ነው። ይሁን እንጂ ጭንቅላት አንድ ከሆድ የሚያንስበት ነገር አለው። ባዶ ሲሆን አይናገርም። ሳይነቃ እንደነቃ ያስባል። በዚህ ጉዳይ ላይ ንቃት ያለው በነሱ ጩኸት ውስጥ ይመስላቸዋል። ግና ንቃት ያለው በዑለማእ አካሄድ ውስጥ ነው። ኢብኑል ቀዪም እንዲህ ይላሉ፦
"ረቂቅ ከሆኑ ማስተዋሎች ውስጥ የሆነው የአዛዥን ስህተት ባደባባይ አለመመለስህ ነው። ስልጣኑ ስህተቱን ለመርዳት እንዲያነሳሳው ያደርገዋልና። ይሄ ሁለተኛ ስህተት ነው። ነገር ግን ሌሎች በማያስተውሉበት ሁኔታ ተለሳልሰህ አሳውቀው።" [አጡሩቁል ሑክሚያህ፡ 1/103]
"መድኸሊይ" በሏቸው እሳቸውንም።
2ኛ፦ "የሳዑዲ መንግስት ሐቅ የሚናገሩ ዓሊሞችን ይገድላል፣ ያስራል" ትላላችሁ አይደል? ያ ከሆነ ዓሊሞቹ ዝም ለማለት በቂ ምክንያት አላቸው ማለት ነው። ሸሪዐው የሚለው "መናገር ያልቻለ ሰው በልቡ ይጥላ" ነው።
3ኛ፦ በቱርክ፣ በኢራን፣ በሙርሲ አስተዳደር ወቅት ስለተከሰቱ ጥፋቶች ዝም ያሉ አልፎም አድናቂ የሆኑ ምሁራኖች ላይ ለምን ተመሳሳይ ክስ አላነሳችሁም? ጩኸታችሁ በተለየ የሱና ዑለማኦችና ሰለፊያ ላይ የሚሆነው ለምንድነው?
4ኛ፦ ቡድናዊ ጥላቻ አስክሯችሁ እንጂ እውነት እናንተ ኢስላምን የሚያጠለሹ ጥፋቶች ላይ በመናገር ምን የረባ ታሪክ አላችሁ? "የበደዊ ቀብር ላይ በያመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ሺርክ ሲፈፅም አልአዝሀር ዩኒቨርሲቲ የታለ? የኢኽዋን መሪዎች ለምን ዝም ይላሉ? ነው ወይስ የቀብር አምልኮ ሺርክ ከጭፈራ ያነሰ ጥፋት ነው? በነ ገኑሺ የኢኽዋን አስተዳደር ላይ የቀይረዋን ዩኒቨርሲቲ፣ የቱኒዚያ ምሁራን፣ እናንተን ጨምሮ ምን አደረጋችሁ?ሱኒዮችን በመጨፍጨፍ፣ በኣሉል በይት ላይ ድንበር በማለፍ ሺርኪያት ከሚፈፅሙ፣ ሶሐቦችን ከሚያወግዙ ሺዐዎች ጋር ህብረት የመሰረተው የነ ቀርዷዊ ማህበር ተመሳሳይ ዘመቻ ተከፍቶበታል ወይ? ዐሊይን ጨምሮ ብዙ ታላላቆችን የሚያከ - ፍሩት ኢባዲያ ኸዋ -ሪጆች ከነ ቀርዷዊ ማህበር ውስጥ የታቀፉ ናቸው። የኢባ .ዲያው ሙፍቲ አሕመድ አልኸሊሊ የማህበሩ ምክትል ነው። በሱና ዑለማእ ላይ እየጮኸ ያለው የሺ0፣ የሱፊያ፣ የኢኽዋን፣ የኸዋ .ሪጅ ጭፍራ እዚህ ሰፈር ድምፁን አያሰማም። "ሙፍቲ" ዑመር ጠቅላዩን "መለይካ ይመስላል" ሲል ይሄ አሁን የሚጮኸው መንጋ ትንፍሽ አላለም። አደም ካሚል ጠቅላዩን ከታላላቅ ነቢያት በላይ አድርጎ ሲያወድስ የኢኽዋን መንጋ ያሰማው ተቃውሞ የለም። የት ነበራችሁ? ከዑለማኦቻችን ላይ እጃችሁን አንሱ። ምላሳችሁን ሰብስቡ። ኢንሻአላህ እናንተን እርቃናችሁን ለማስቀረት የሚሆን አቅም አናጣም።
5ኛ፦ ደግሞስ ሃሜት ተፈቀደ እንዴ? የተረጋገጡ ጥፋቶችን ስናስጠነቅቅ የዑለማእ ነውር እየተከታተሉ የምትሉ አይደላችሁምን? ታዲያ ምነው መርሃችሁን ለቃችሁ ያውም በሌሉበት ዑለማኦችን ታጠለሻላችሁ? ቀርዷዊ ዘፈን ሲፈቅድ፣ አጅነቢያ ሴት ሲጨብጥና መጨበጥን ሲፈቅድ፣ ዲሞክራሲ ከኢስላም ነው ሲል፣ ሰይድ ቁጥብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ሲያስተባብል፣ ሶሐባ ሲሳደብ፣ ህዝብ ሲያከ - ፍር፣ "ሙፍቲ" ዑመር በሙስሊሞች ላይ ጠላት ሲቀሰቅስ፣ ... እስኪ የተቃወማችሁበትን አሳዩን? ጭራሽ ለምን ተነኩ ብላችሁ አይደለም ወይ የምትጮሁት? የቢድዐ ቁንጮዎች ላይ ስንናገር ሃሜተኛ፣ ዑለማእ ተሳዳቢ ስትሉ አልነበረም ወይ?
ፅሁፌን ሳጠቃልል ሰዑዲያ ውስጥ በሚፈፀም ጥፋት ሁሉ ሰለፊያን ተጠያቂ የሚያደርጉ ደናቁ - ራን ናቸው። ቱርክ ከሰዑዲያ የበለጠ ከኢስላም የራቀች ናት። ነገር ግን ቱርክ ውስጥ የሚፈፀሙ ጥፋቶችን ወደ ሱፊያም፣ ወደ ኢኽዋንም አያስጠጉም። የሰለፊያ መንገድ ዘፈንና ጭፈራ አይደለም ከዚህ ያነሱ ነገሮችን ያወግዛል። የሱና ዑለማኦች አቋም ለወዳጅ ቀርቶ ለጠላት የሚታወቅ ነው። ዘፈን የሚፈቅዱት እነ ቀርዷዊ ናቸው። ሲኒማ ለማየት ሶላት ጀምዕ ያደረጉት፣ የፈረንጅ ዳንስ እየከፈሉ የተማሩት እነ ዑመር ቲልሚሳኒ ናቸው፣ የኢኽዋን ሶስተኛ ሙርሺድ። ሺርክን ዲን አድርገው የሚዋጉለት ኢኽዋንና ሱፊያ ናቸው።
ለማንኛውም ኢብኑ ሰልማን ወይም ቱርኪ አሉሸይኽ የሰለፊያ ዓሊሞች አይደሉም። የተከሰተውን ጥፋትም የሰለፊያ አቋም ነው ብለው አላቀረቡም። እነሱ ላይ የሚታይን ሁሉ ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጋ አካል በነ ኤርዶጋን፣ በነ ዑመር አልበሺር፣ በነ ቱራቢ፣ በነ ገኑሺ፣ በነ መሃቲር ፖለቲካ ሁሉ ኢኽዋንና ሱፊያ ሲከሰስ ሊቀበል ይገባል። እንዲያውም ከፖለቲከኞቹ አልፎ የነ ሐላጅ፣ ቢስጧሚ፣ ኢብኑ ዐረቢ፣ ኢብኑል ፋሪድ፣ ኢብኑ ሰብዒን፣ ቲልሚሳኒ፣ የነ ቀርዷዊ፣ ኩፍ - ሪያት ሲነገሩ የምትጮሁ እንደሆናችሁ እናውቃለን። ገዛሊና የምታስተዋውቁት ኪታቡ ኢሕያእ ዑሉሙዲን ብዙ ሙንከራት የያዘ እንደሆነ የራሱ ተማሪዎች ጭምር የተናገሩት ነው። የሱና ዑለማእ ላይ የምትሰነዝሩትን ሩብ ያህል እንኳ እዚህ ላይ አትናገሩም። ይልቁንም እንዲህ አይነቱ እውነት መነገሩ ነው የሚያበሳጫችሁ። ስለዚህ የፖለቲከኛን ጥፋት ሰለፊያ ላይ ሊደፈድፍ የሚነሳን አካል የራሱ ቡድን ቁንጮዎችን ጠማማ አካሄድ ምን እንደሚመስል አፍንጫውን ይዘን ልንግተው እንገደዳዋለን።
ኩን ሰለፍየን አለል ጃዳ
ክፍል 03 **በሱና መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን(ዘወትር እሁድ ከጧት ) እየተሰጠ ያለ
የኪታቡ ርዕሶች ዝርዝር
√ የሱና ትርጉም በሰፊው ተብራርቶበታል
① የቋንቋ ሙሁራኖች ዘንድ
② የሙሀዲስ ሙሁራኖች ዘንድ
③ የፊቂህ ሙሁራኖች ዘንድ
④ የኡሱሉዮች ሙሁራኖች ዘንድ
⑤ ትክክለኛው የሱና ትርጓሜ ቀደምቶች ዘንድ
በሸይኽ ሙሀመድ ሰዒድ ሀፊዘሁሏህ**
**የጁማዓ ኹጥባ
በሸይኽ ኢሳ አደም
በመጨረሻው ቀን ማመን በሚል አርዕስት እጥር ምጥን ያለች ቆንጆ ምክር ነች
አድምጧት
በደሴ ከተማ
በደወይ ሜዳ መስጅድ የተደረገ**
ስለ ኸውፍና ረጃዕ ሰፋ ያለ ማብራሪያ
ደሴ ከተማ ካሉ መሻይኾች አንዱ በሆኑት ሸይኽ አብዱለዓዚዝ
ከኢርሻድ ቂርዓት የተቆረጠ
በደሴ ከተማ በደወይ ሜዳ መስጅድ
ኡርጁዘቱል ሚዒያህ ክፍል 02 **በሱና መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን(ዘወትር እሁድ ከጧት ) እየተሰጠ ያለ
የተዳሰሱ ነጥቦች
√ የነብያችን صلى عليه وسلم የህይወት ታሪክ የተዳሰሰበት
√ ነብያችንصلى عليه وسلم ታሪ ክ
ሸይኽ ሙሀመድ አሚን**
https://t.me/sunnamesjdatdessie
**አቂደቱ ጡሀውያ
ክፍል ሶስት
በሱና መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን(ዘወትር እሁድ ከጧት) እየተሰጠ ያለ
በአሏህ ስሞች ና ባህሪያት ዙሪያ የተለያዩ ማብራሪያዎችና ቃኢዳወችን በሰፊው አብራርተዋል
እና ሌሎችም ወሳኝ የሆኑ ቃዒዳዎች ተብራርተውበታል።
በሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ሀፊዘሁሏህ**
**ኩን ሰለፍየን አለል ጃዳ
ክፍል 02
በሱና መስጂድ በሳምንት አንድ ቀን(ዘወትር እሁድ ከጧት ) እየተሰጠ ያለ
√ የሱና ባልተቤቶች ሊኖራቸው የሚገባ አቋም
√ በመካከላቸው አለመግባባት ሲከሰት ምን ማድረግ እንዳለበቸው
√ የአህለ ሱና መስራች መሀመድ ኢብኑ አብዲል ወሀብ ነው ለሚለው እንዳልሆኑ አጥጋቢ ምላሽ ተካቶበታል።
በሸይኽ ሙሀመድ ሰዒድ ሀፊዘሁሏህ**
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад