Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Freshman and Preparatory Students Channel

Description
We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 3 weeks, 5 days ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 1 day, 12 hours ago

1 month, 3 weeks ago
***👇******👇******👇******👇******👇******👇******👇***

👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/atc_news/23609

2 months ago

3rd year የዋቻሞ ዩንቨርሲቲ IT ተማሪ በዚህ ቻናል ላይ ካለ #inbox ...🙏

2 months, 2 weeks ago

ወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ

2⃣016 e.c Remedial students dorm placement for males

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

3 months, 3 weeks ago
[#JigJigaUniversity](?q=%23JigJigaUniversity)

#JigJigaUniversity

ለጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የትምህርት ዘመን (Remedial) አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፡

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም (Remedial) አዲስ ገቢ ተማሪዎች መግቢያ ቀን 👉 ከጥር 13 እስከ 15/2016 ዓ.ም ድረስ መሆኑን አሳውቋል፡፡ ስለሆነም ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀን በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉ ዩንቨርሲቲው አሳስቧል።

ማሳሰቢያ፡-
- ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በሚመጡበት ወቅት ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎችን ኦሪጂናልና ፎቶ ኮፒ፣

- ስምንት ጉርድ ፎቶ-ግራፎች፣ ብርድ ልብስ፣
አንሶላ እና የስፖርት ትጥቅ ይዘዉ መምጣት ይኖርባቸዋል፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ፅ/ቤት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

3 months, 3 weeks ago
Freshman and Preparatory Students Channel
3 months, 3 weeks ago
[#AksumUniversity](?q=%23AksumUniversity)

#AksumUniversity

በ2016 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ጥር 6 እና 7/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ የ8ኛ፣ 10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➭ ከ9ኛ አስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የቅርብ ጊዜ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

5 months, 2 weeks ago
***💥***New Curriculum Text Book Mathematics Tutorial

💥New Curriculum Text Book Mathematics Tutorial

Class 12 Mathematics 👇
https://www.youtube.com/playlist?list=PL195s8cg0viqXDe42am3JRfOLNPN7085s

5 months, 3 weeks ago

“ተማሪዎችን ለመቀበል ከዝግጅት የሚጎድለን የለም” የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር)

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራ አጠናቀው ተማሪዎችን እየተቀበሉ ነው፡፡ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ዝግጅታቸውን አጠናቀው የተማሪዎችን መምጫ ጊዜ የሚጠባበቁ ዩኒቨርሲቲዎችም አሉ፡፡ ዝግጅታቸውን አጠናቀው ተማሪዎችን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ ከሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንደኛው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፍሬው ተገኘ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው የዝግጅት ምዕራፉን በክረምት ወቅት ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ እንደማንኛውም ጊዜ በ2016 ዓ.ም የሚያስፈልገውን ሁሉ አዘጋጅቶ በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ተማሪዎች የሚጠሩበትን ጊዜ ወስኖ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡ በክልሉ በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃ እና የድሕረ ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አቅዶት ከነበረው ጊዜ መዘግየቱንም ገልጸዋል፡፡

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ከጀመረ ጀምሮ ለድሕረ ምረቃ ተማሪዎች ትምህርት እየሰጠ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ የዝግጅት መዕራፋቸውን ቀደም ብለው መጨረሳቸውንም አስታውቀዋል፡፡ ለተማሪዎች የተሻለ ጊዜ እየጠበቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በላቀ መልኩ በተማሪዎች ተመራጭ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ በተማሪዎች ፍላጎት መመረጡ ደስተኛ እንዳደረጋቸውም ተናግረዋል፡፡ እውቀትን እና በቅቶ መውጣትን የሚሹ ተማሪዎች ዘንድሮም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን ሊመርጡ እንደሚችሉ ነው የገለጹት፡፡ በክልሉ ያለው የሰላም ሁኔታ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው ትምህርት የሚሰጥ ታላቅ ዩኒቨርሲቲ መኾኑን ተማሪዎች ማወቅ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል፡፡ የግብዓት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥም የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ የግብዓት አቅርቦት ቀጣይነት ያለው በመኾኑ የሰላም እጦት ካለ ችግር ሊፈጥር እንደሚችልም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ "ተማሪዎችን ለመቀበል ከዝግጅት የሚጎድለን የለም፤ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን ጨርሶ ተማሪዎችን ለመቀበል እየጠበቀ ነው" ብለዋል፡፡ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጡ ተማሪዎች መምጣት እንዲችሉ ሁኔታዎችን መፍቀድ አለብን ያሉት ፕሬዚዳንቱ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ኾነው እየጠበቁ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡ የድሕረ ምረቃ ትምህርቱ እየቀጠለ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡

የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማርም በሁሉም በኩል ዝግጅት ተደርጎ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል፡፡ ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጀምሮ የትምህርት መጓተት ተፈጥሮ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ እንደ ሀገር የኮሮና ቫይረስን ጊዜ ያለፍንበት መንገድ እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባው ነው ብለዋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን የትምህርት መጓተት ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም ማካካስ መቻላቸውንም አስታውቀዋል፡፡

በሰሜኑ በነበረው ጦርነትም ጫናው ቢለያይም በዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራ መስተጓጎል ተፍጥሮ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረውን መጓተት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ማካካሱንም አስታውቀዋል፡፡ የመማር ማስተማሩ መስተጓጎሉ በትምህርት ጥራቱ ላይ የከፋ ተጽዕኖ ሳያደርስ ማካካሳቸውንም ነው የተናገሩት፡፡ በ2016 ዓ.ም ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ ለመግባት በተዘጋጁበት ወቅት በክልሉ የሰላም ችግር መፈጠሩንም ገልጸዋል፡፡

ከአሁን በፊት በነበሩ ችግሮች እንዴት መውጣት እንዳለብን ትምህርት ወስደናል ያሉት ፕሬዚዳንቱ አሁንም ተማሪዎችን በምንቀበልበት ጊዜ የትምህርት ጥራቱን በማይጎዳ መልኩ ለማስኬድ ልምድ እና ዝግጅት አለን ነው ያሉት፡፡

መረጃው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

5 months, 3 weeks ago

የወሎ እና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጋቸውን አስታወቁ

በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክንያት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስቀድመው መጥራት አልቻሉም፡፡ በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን መጥራት ከጀመሩ ቆይተዋል፡፡ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ግን ለተማሪዎቻቸው የደኅንነት ዋስትና እስኪሰጥ ድረስ ከመጥራት ተቆጥበዋል፡፡

በክልሉ የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እያስተማሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችም አሉ፡፡

የዩኒቨርሲቲውን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር)፤ ወሎ ዩኒቨርሲቲ በጦርነቱ ምክንያት የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓቱ ተዛብቶበት እንደቆየ አስታውሰዋል፡፡

በዚህ ዓመት ሦስት ወሰነ ትምህርቶችን ለማስተማር አቅደው እንደነበር የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ የተጓተተውን ትምህርት ለማካካስ አስቀድመው በመጥራት ትምህርት ለመጀመር አቅደው እንደነበርም አንስተዋል፡፡

በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በእቅዳቸው መሠረት ተማሪዎችን መቀበል አለመቻላቸውንም ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎችን ከመስከረም 11/2016 ጀምረው ጠርተው እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፤ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የተማሪዎችን የመቀበያ ጊዜ ማራዘማቸውንም ተናግረዋል፡፡ በቅርብ የተደረገ ጥሪ አለመኖሩንም አስታውቀዋል፡፡

ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ለመምጣት የሚያስችል መንገድ እንደማያገኙ በመረዳት እና ተማሪዎቹም ለመምጣት እንደሚቸገሩ ባስታወቁት መሠረት ጥሪውን ማራዘማቸውን ነው የገለጹት፡፡

በጸጥታው ምክንያት በተፈጠረው የመንገድ መዘጋጋት ተማሪዎችን ለመጥራትም ሆነ የግብዓት አቅርቦት ለማግኘት ፈተና ሆኖባቸው እንደቆየም አስታውሰዋል፡፡ የግብዓት አቅራቢ ነጋዴዎች ግብዓት ለማግኘት ሲቸገሩ መቆየታቸውንም ገልጸዋል፡፡ በተለይም የጤፍ ግብዓት ፈትኗቸው እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡ ለገጠማቸው ችግር መፍትሔዎችን በመውሰድ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን እያስተማረ መሆኑንም የገለጹ ሲሆን፤ ሌሎች ችግሮች ተፈጥረው መደናቀፍ ካልተፈጠረ በስተቀር ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ነንም ብለዋል፡፡

የጸጥታ ኹኔታው አስተማማኝ ከሆነ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዩኒቨርሲቲው ኹሉንም አይነት ዝግጅት አድርጓል ነው ያሉት፡፡

“ተማሪዎች በጉዞም ላይ ሆነ ከገቡ በኋላ የጸጥታ ችግር እንዳይገጥም የሚመለከተው አካል እውቅና እስከሚሰጥ ድረስ እየጠበቅን ነውም” ብለዋል፡፡  የጸጥታ ሁኔታውን የሚመራው አካል እውቅና የሚሰጥ ከሆነ ተማሪዎችን እንቀበላለን ነው ያሉት፡፡

የሰላም ኹኔታው አስተማማኝ ባለመሆኑ የዓመቱን የምግብ ግብዓት በአንድ ጊዜ ማስገባት እንደማያስችልም አንስተዋል፡፡ የገበያ መስመሩ እስካልተደነቃቀፈ ድረስ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉትን ኹሉንም ዝግጅት አድርገናል ብለዋል፡፡ ተማሪዎች በትዕግሥት እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከሰሞኑ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አይቀበሉም በሚል የተሰራጨው መረጃ ተማሪዎችን ማስደንገጡን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን የማስተማር ፍላጎት እና በቂ ዝግጅት ያደረገ መሆኑን ሊያውቁት ይገባልም ብለዋል፡፡

የመቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ካሳ ሻውል (ዶ.ር) መቅደላ አምባ ዪኒቨርሲቲ ከበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመስከረም 2016 ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ማዘጋጀት ያለበትን ኹሉ ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ችግር ካልሆነ በስተቀር እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስቸግር ነገር የለምም ብለዋል፡፡ የሰላም ኹኔታው ከተስተካከለ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን ይቀበላል ነው ያሉት፡፡

ከግብዓት አቅርቦት ጋር በተያያዘ ችግር እንዳይፈጠር አስቀድመው ሰርተው እንደነበር ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ “የጸጥታ ኹኔታውን አስተማማኝነት ማረጋገጫ ካገኘን ተማሪዎችን ለመጥራት የሚያስቸግረን ነገር የለምም” ብለዋል፡፡

ተማሪዎች  በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አይቀበሉም የሚለውን ሀሰተኛ መረጃ በመተው ራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡ 

የሰላሙ ኹኔታ መስተካከል ካሳየ ተቀብለው እንደሚያስተምሯቸው በመረዳት ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

5 months, 3 weeks ago

ማስታወቂያ

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ካምፓሶቹ በሚሰጡ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ በማታና በረዕፍት ቀናት ተማሪዎችን ተቀብሉ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡

⚡️የማመልከቻ መስፈርቶች፡-

፨12ኛ ክፍል አጠናቀው የብሔራዊ ፈተና ተፈትነው የዘመኑን መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ እና ፈተናውን ከወሰዱ አምስት አመት ያልበለጣቸው፤

፨በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርቱን/ቷን የተከታተለና/ችና የማለፍያ ነጥብ ያገኘ/ች (የተፈጥሮ ሳይንስ 200 እና ከዚያም በላይ ሶሻል ሳይንስ 150 እና ከዚያም በላይ እንዲሁም ለአይነስውራን 100 እና ከዚያም በላይ)፤

፨በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 ያጠናቀቁና COC ያለፉ በሙያው ቢየንስ ሁለት ዓመት ያገለገሉ እና ዩኒቨርሲቲው የሚያዘጋጀውን የመግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችሉ፤

፨በቀድሞ የትምህርት ስርዓት 12+ 2 ዲፕሎማ ያላቸው ወይንም በማንኛውም የት/ት ዓይነት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው፤

፨የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከኢፌድሪ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

💥ማሳሰቢያ፡-
➡️ምዝገባው የሚከናወነው በኦንላይን ወይም በአካል በመቅረብ ማመልከት ይቻላል፡፡
➡️አመልካቾች ጥቅምት 27-ሕዳር 19 /2016 ዓ.ም ማመልከት ይችላሁ፡፡
 አመልካቾች የንግድ ባንክ ቁጥር 1000013481788 በመጠቀም የማመልከቻ ክፍያ 50 ብር መክፈል ይጠበቅባቸል።
 በአካል ቀርበው የሚያመለክቱ ዘወትር በስራ ሰዓት ዋናው ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 41 በመቅረብ ማመልከት ይቻላሉ፡፡
 በኦላይን የሚያመለክቱ የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲው ድረገጽ (https://portal.hu.edu.et) አካውንት በመፍጠር አስፈላጊዎችን መረጃዎችን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
 ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመልከቻ ፎርሙ በመመለስ ፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን፣ ባንክ የከፈሉበትን ደረሰኝ በማማያዝ ምዝገባዎትን ማጠናቀቅ ይኖርብዎታል፡፡
 የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማታና በእረፍት ቀናት በ2016 ዓ.ም የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር
1. Business and Economics College

1.1 Main Campus (Weekend and Evening)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management
1.2 Awada Campus (Weekend)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management
1.3 Aleta Wondo Campus (Weekend)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management

  1. Social Science and Humanities College (Weekend and Evening)
     Journalism and Communication (Weekend only)
     English Language and Literature
     Sidaamu Afoo and Literature
     Geography and Environmental Studies
  2. Natural and Computational Science College (Weekend and Evening)
     Biology
     Sport Science

  3. College of Education (Weekend and Evening)
     Lifelong Learning and Community Development
     PGDT-Weekend (Mathematics, Physics, Biology, Chemistry, Sport Science, English, Geography, Civic, ICT, Sidaamu Afoo, Econoics, History, Amharic)

  4. Institute of Technology (Weekend and Evening)
     Computer Science
     Civil Engineering
  5. Daye Campus (Weekend)
     Mathematics
     Biology
     Physics
     English Language and Literature
     Plant Science
     Agribusiness and Value Chain Management
     Computer Science
     Agricultural Economics
  6. College of Agriculture (Weekend and Evening)
     Agricultural Economics
  7. College of Law and Governance (Weekend and Evening)
     Law

  8. Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources-Shashemene Campus (Weekend)
     Land Administration and Surveying
     Geographic Information Science
     Natural resource management
     Environmental science

ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 3 weeks, 5 days ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 1 day, 12 hours ago