የአባቶች ምክር

Description
አስተማሪ የሆኑ የአባቶች ምክሮችን ÷መንፈሳዊ ፅሁፎችን፣ መፅሐፍቶችንና ትምህርቶችን የምናጋራበት ቻናል ነው። ሊንኩን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ! የክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ!@Father_advice
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

2 weeks, 1 day ago

“ ተፈጸመ ”
ዮሐንስ 19፥30

2 weeks, 1 day ago
2 weeks, 1 day ago

◦ በሚፈርደው ፈረዱበት
🌿 @father_advice🌿
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
✞ በሚፈርደው ፈረዱበት

በሚፈርደው ፈረዱበት
በሚምረው ጨከኑበት
በቁጣ ጎተቱት ቀይ ግምጃ አለበሱት

አዳምን የፈጠረ እጅ በመስቀል ቀኖት ተቸነከረ
ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከወንበዴ ጋር ተቆጠረ
ህይወት እፍ ያለውን አፍ ጨክነው ሀሞት አጠጡት
በሞቱ ሞትን ይሽር ዘንድ ጌታን በመስቀል ሰቀሉት

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት

በመፍራትና በመራድ መላዕክት ፊቱ ለሚሰግዱለት
የአለሙን ሁሉ ጌታ በአደባባይ ላይ አቆሙት
ለሱራፌል የክብር ዘውድ ያቀዳጃቸውን ጌታ
ፍቅር ያነበብንበት ፊቱ በክፉ ባርያ ተመታ

ይህን ያህል..........

ፅድቅና የፀና ሰላም የሀጥያት ስርየት በሰጠን
እንደ ክፉ ሰው ተቆጥሮ በእሾህ አክሊል አጌጠ
ለኪሩቤል የግርማን ልብስ የሚያለብሳቸውን እርሱን
እርቃኑን ይሰቀል ብለው እጣ ተጣጣሉበት ልብሱን

ይህን ያህል......

በኢየሱስ መንገላታት አለም እንዲድን ከፍዳ
ቅዱሱ ደምና ውሀ ከአምላካችን ጎን ተቀዳ
ሰላም ለእናንተ ሲለን እጅና እግሩን አየን
ሙስና መቃብር ጠፋ ይኸው በአዲሱ ኪዳን

ይህን ያህል......

ዘማሪ
🔊    ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ 

🌿 @father_advice🌿
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

2 weeks, 5 days ago

#እግዚአብሔር_መልካም_ነው!

"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"
(ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ)

╔═F══════════A══╗
💚🌿 @Father_advice🌿  💚
╚═F══════════A══╝
                                      ♡ ㅤ⌲       
                                     ˡᶦᵏᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

2 weeks, 5 days ago

✝️እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :-✝️

መዝሙር ፥50

14: ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥
ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤

15: በመከራ ቀን ጥራኝ፥
አድንህማለሁ፡ አንተም ታከብረኛለህ።

16: ኃጢአተኛውን ግን እግዚአብሔር አለው፦
ለምን አንተ ሕጌን ትናገራለህ?
ኪዳኔንም በአፍህ ለምን ትወስዳለህ?

17: አንተስ ተግሣጼን ጠላህ፥
ቃሎቼንም ወደ ኋላህ ጣልህ።

18: ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር፡
እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።

19: አፍህ ክፋትን አበዛ፥
አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።
20: ተቀምጠህ ወንድምህን አማኸው፥
ለእናትህም ልጅ ዕንቅፋት አኖርህ።

21: ይህን አድርገህ ዝም አልሁህ፤
እኔ እንደ አንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ፤
እዘልፍሃለሁ በፊትህም እቆማለሁ።

22: እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፤ አለዚያ ግን ይነጥቃል የሚያድንም የለም።

23: ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤
የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።

@father_advice

2 weeks, 6 days ago

#እግዚአብሔርን_ፈልጉት
✍️
ልጆቼ፦ እግዚአብሔርን በእምነት በፀሎት እንሻው ከእኛ የጠፋ ገንዘባችንን ነቅተን ተግተን በብዙ ድካም እንድንሻው እንዲሁ ሃሳባችንን ወደ እግዚአብሔር ልናቀርብ ይገባናል፤ ልጃችን ቢጠፋብን ፈልገን በቅርብ ያላገኘነው እንደሆነ ሃይላችንን በድካም ድካማችንን በሃይል የምንለውጥ አይደለንምን?

የጠፋውን ልጃችንን ስለመፈለግስ እናገኘው ዘንድ የብሱን በእግር ባህሩን በመርከብ የምንዞር አይደለንምን? ፈልገንም ያገኘነው እንደሆነ ዳግመኛ እንዳይጠፋብን ለመጠበቅ እንተጋ የለምን?

እንዲህ ከሆነ መሓሪ እግዚአብሔርን በእምነትና በፀሎት እንሻው ዘንድ ምን ያህል ይገባን ይሆን? እግዚአብሔርን ፈልጉት!

ነጋዴ ወርቅ ቢጠፋበት ወርቁን ያገኘው እንደሆነ ሁሉን ቦታ እንደሚፈልግ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት!

እናት ልጇ ቢጠፋባት እስክታገኘው ድረስ አርፋ እንደማትቀመጥ እንዲሁ እግዚአብሔርን ፈልጉት!

እግዚአብሔርን እሹት ፈልጉት እስክታገኙት ድረስ በእምነት በፀሎት እሹት፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@father_advice

2 months, 4 weeks ago

+++ እግዚአብሔር ለአንተ ፍትሐዊ ነው? +++

ጋሽ ስብሐት ለአብ ገብረ እግዚአብሔር በአንድ የሬዲዮ ጣቢያ ላይ ቃለ መጠይቅ ሲደረግለት ለጋዜጠኛው "እግዚአብሔር በአንዳንድ ነገሮች ጥሩ አላደረገም" አለው። ጋዜጠኛውም "እንዴት? እስኪ ለምሳሌ?" ቢለል፣ "ለምሳሌ ለእኔ ያደላል" ሲል መለሰለት።

እኛስ እንዲህ የምንልባቸው አጋጣሚዎች የሉም? በእርግጥ  "እግዚአብሔር ለእኔ ያደላል" ስንል "ከሌላው ያስበልጠኛል" እያልን አይደለም። በዚህስ "እግዚአብሔር የሰውን ፊት አይቶ አያደላም"።(ገላ 2፥6) ነገር ግን እርሱ እያንዳዳችንን ልክ እንደ አንድና ብቸኛ ልጅ ያህል የሚወድ አምላክ ስለሆነ ከዚህ ተአምራዊ የአባትነት ፍቅሩ የተነሣ ሁላችንም ለእኛ  "የሚያደላ" መስሎ ይሰማናል።

ለመሆኑ "አምላክ ለእኔ ያደላል" ስንል ምን ማለታችን ይሆን? እግዚአብሔር ያደላልኛል ስንል እኔ ምንም ሊደረግለት የማይገባ አመጸኛ ሰው ሆኜ ሳለሁ ክፋቴን ሳይሆን ደግነቱን እያሳየ ያኖረኛል ማለታችን ነው። አንዲት እናት መልካም ከሆኑ ልጆቿ መካከል አንድ አስቸጋሪ ልጅ ቢኖራት ይጎዳብኛል ብላ ለእርሱ እንደምትሳሳ፣ ፈጣሪዬ እኔ አመጸኛ ልጁን ከስንፍናዬ የተነሣ እንዳልጠፋበት በስስት ያየኛል ይጠብቀኛል እያልን ነው።

ሶርያዊው ማር ይስሐቅ እግዚአብሔር እኛ ኃጢአተኞቹ ላይ በሚያደረገው ሁሉ ፍትሑ አልታየምና እንዴት "ፍትሐዊ ነው" ብለን ልንናገር እንችላለን ይለናል። እውነት ነው፤ እስኪ አስቡት:- በአመሻሹ ገብተን በሠራናት ጥቂት ሥራ ከጠዋት ጀምረው ከደከሙት ጋር እኩል ዲናር የሚከፍለንን፣ ገንዘቡን ወስደን በማይገባ ኑሮ ስላባከንን ፈንታ ጸጸታችንን ብቻ ተመልክቶ ወደ እኛ ሲሮጥ በመምጣት አንገታችንን አቅፎ የሚስመንን እና መልሶ በገንዘቡ ሁሉ ላይ የሚያሰለጥነንን ጌታ እንዴት "ለእኔስ ፍትሐዊ ነው" ልንለው እንችላለን?

እግዚአብሔር ከሕይወት ይልቅ ሞት፣ ከበረከት ይልቅ እርግማን ለሚገባን ለእኛ በደለኞቹ አንድም የሚገባንን አላደረገብንም። ታዲያ እግዚአብሔር እኛ ላይ ባሳየው ነገር "ፍትሐዊ" ነው ትላላችሁ?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

@Father_advice

2 months, 4 weeks ago

“ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን ለአምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ ወደ ሥራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሰመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

3 months ago

"Some people are careful and scrutinize what they say when they are before a recording device because the device records everything they say on it. However, when they are not in front of a recording device, they speak without caution and without reserve, and…

4 months, 4 weeks ago

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ  አፈወርቅ

📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
ወዳጄ ይህንንም ምክኒያት አድርገህ ከማንበብ አትቦዝን መፅሐፍ ቅዱስ ከእንስሳት ለአንዱ አልተፃፈም ! ለእኔና ለአንተ ለአንቺ ነው እንጂ
ጥያቄ ካለህ
1.ጥያቄህን ብቻ ሊመልሱ እንጂ አንተን ሊወቅሱ ከማይችሉ ሰዎች ጠይቅ.ይመልሱልሃል

2.የጥያቄህን መልስ መፅሐፍትን ስታነብ ልታገኜው ትችላለህ
3.ራሱ ቸሩ አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በልቦናህ በመፃፍ እንድታስተውል ያደርግሃል

መፅሐፍ ቅዱስን እናንብብ
📓✝️

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago