ሞዐ ተዋሕዶ ቻነል MOA TEWAHIDO / MO'AA TAWAAHIDO / MOA Orthodox

Description
https://t.me/defend_orthodoxy_EOTC_Followers
We recommend to visit

https://t.me/defend_orthodoxy_EOTC_Followers

Last updated 1 month, 4 weeks ago

Kazu's
@in2Gaza

Last updated 6 months, 1 week ago

1 month, 4 weeks ago

👉   ጾም ማለት ምን ማለት ነው ?

ኅዳር 15 ጾመ ነቢያት የሚገባበት ቀን ነው
ይህ ጾም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ እንደሆነ የታወቀ የተረዳ ነው የመጣው የጾም ወራት ነውና ስለ ጾም የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ መማር እና በተግባር መኖር የነጻ ፈቃድ ግዴታ ነው
ጾም ማለት ምን ማለት ነው ?
ጾም ማለት
"ተከልኦተ ብእሲ በጊዜ መብልእ
ዕውቅ" እንዲል
ከታወቀ መብል መከልከል ነው
ይህ ማለት ከሥጋ ከወተት ከእንቁላል  ወዘተርፈ በአጠቃላይ ሥጋን ከሚያለመልሙ ምግቦች መከልከል ማለት ነው
ሁለተኛ ጾም ማለት
"ጾምስ ጸባሕተ ሥጋ ይእቲ "
ጾምስ በለኝ የሥጋ ፈቃድን ለነፍስ ፈቃድ
መገበር ነው
ፈቃደ ስጋ ምንድን ነው ? ከተባለ
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይዘረዝርልናል
" የሥጋም ስራው ይታወቃል ፥
እርሱም
ዝሙት ፥
ርኵሰት ፥
መዳራት ፥
ጣዖትን ማምለክ ፥
ሥራይ ማድረግ ፥
መጣላት ፥
ኩራት  ፥
የምንዝር ጌጥ
ቅናት ፥
ቍ ጣ ፥
ዐድመኛነት ፥
መለያየት ፥
መናፍቅነት ፥
ምቀኝነት ፥
መግደል ፥
ስካር ፥
ዘፋኝነት ፥
ይህን የመሰለ ሁሉ ነው ። አስቀድሜም እንደነገርኋችሁ፥ ይህንየሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም።
ገላ5:19-21
መጾም ከእነዚህ ከተዘረዘሩት ነው
በሌላም አንቀጽ ገና በሕገ ኦሪት ሳለ ፈቃደ ሥጋ
እና ፈቃደ ነፍስ ልቡናውን እንደጦር ሜዳ አድርገው እንደተፋለሙበት ይገልጻል
" ነገር ግን በሰውነቴ ውስጥ ያለውን ሌላ የኀጢአት ሕግ እመለከታለሁ በልቡናዬም ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር ተሰልፈው ተዋጉ እንዲል ሮሜ 7፥23
አንድ ሰው የፈቃደ ሥጋ እና የፈቃደ ነፍስ መፋለሚያ ሰፊ ሜዳ ነው
የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ፈቃድ አስገዝቶ በፈቃደ ነፍስ መገለጽ ደግሞ በጠባብ በር ማለፍ ነው  አምላካች ክርስቶስ እንደተናገረ
"በጠባቢቱ በር ግቡ ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ   ሰፊ በር ፥ ሰፊ መንገድም አለችና፥ ወደ እርሷም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ፤ ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ  ፥ መንገዷም ቀጭን ናትና፥ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው ።
ማቴ 7፥13-14
ጠባቢቱ በር የነፍስ ፈቃድ ስትሆን
ሰፊ በር የተባለ  የሥጋ ፈቃድ ነው
የአንድ ክርስቲያን የመጀመሪያ ተጋድሎው
ፈቃደ ስጋን ማሸነፍ ነው አሸናፊነትም በሹመት በሽልማት ይገለጻል ይታወቃል
እኛም ብዙ ጊዜ ጾም ሲመጣ
ጹመናል ብለን የምናስበው
ከመብል ከመጠጥ
ከጥሉላት (ከሚያለመልሙ)
ነገሮች ነው
ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም
የስሜት ህዋሳትንም እንዲጾሙ
በማድረግ በራስ ላይ ንጉሠ ነገሥት ሆኖ መሾም ነው
እኔ ለእኔ አንባ ገነን ንጉሥ ነኝ
በስሜት ህዋሳት ከመንገሥ
በላይም ሌላ ተአምር የለም
እንደሌለም ተገልጿል።

ሊቁ ዮሐንስ አፈ ወርቅን
እንስማው

"ተአምራትን ማድረግ ትፈልጋለህን ?"

"እንኪያስ በዘፈን የደነቆረ ጆሮህን መዝሙር እንዲሰማ አድርገው
ሴትን በመመኘት የታወረ ዓይንህን
ፈጣሪውን እንዲያይ አድርገው
በስርቆት የሰለለ እጅህን በምጽዋት እንዲዘረጋ አድርገው
ወደኅጢአት ቤት በመኼድ ሽባ
የሆነ እግርህን ወደ እግዚአብሔር
ቤት እንዲሮጥ አድርገው
ሐሜትን በማውራት ዲዳ
የኾነ ከንፈርህን መልካም
እንዲናገር አድርገው
ከተአምራት ሁሉ የበለጠ
ተአምር ይኼ ነውና ። " ይለናል
ስለዚህ ጾም ማለት
ተአምር ማለት በህዋሳት መንገሥ
ከፈቃዳተ ሥጋ መፍለስ
በቅዱሱ እግዚአብሔር መቀደስ
ከብልየተ ስጋ (በኀጢአት ካረጀ ሥጋ) መታደስ
ማለት ነው።

አብርሃም ፈቃዴ

ክፍል ሁለት ይቀጥላል ..........

2 months ago
ነገረ ባንዳ ን — በቅጡ መረዳት …

ነገረ ባንዳ ን — በቅጡ መረዳት ይቀረናል። ይህን ተምህርት እናስተውል

https://youtu.be/bmVmjaOvz4k?si=2D1VcOrrdRbIeTC2

ክፍል 2 https://www.youtube.com/watch?v=fyxGy0JjnsI

5 months ago

?????? ፓትሪያርኩ ተጠያቂ ናቸው!!

We recommend to visit

https://t.me/defend_orthodoxy_EOTC_Followers

Last updated 1 month, 4 weeks ago

Kazu's
@in2Gaza

Last updated 6 months, 1 week ago