Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
**"ሰው እያለ አጠገባችን
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከ'ኛ አብሮ በሕይወት ቆሞ
መልካሙን ስሙን - መጥራት ሲያንቀን፤
ሰው ካልሞተ ወይ ካልሔደ አይነሣም እንላለን...
እንዲኽ እያልን . . .
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን :
አበባውን ቀጥፈን ጥለን
አበባ እናስቀምጣለን "
(ጋሽ ነብይ መኮነን)
?????
''የቃለ-እሳት ነበልባሉ
የድምፀ ብርሃን ፀዳሉ
የኅብረ ቀለማት ኃይሉ
አልባከነምና ውሉ
የዘር-ንድፉ የፊደሉ
ቢሞት እንኳን ሞተ አትበሉ።''?
ጸ.ገ.መ
REST IN PEACE ?**@Love_Of_Sophia@Love_Of_Sophia
**ምሽት በረንዳ ላይ
(በዕውቀቱ ስዩም)
አገር ምድሩ መሽቶ
ሌቱ ምጣድ ሆኖ ፥ በኮከብ ተሟሽቶ
የጎዳናው መብራት ፥ጨለማው ላይ ሲገን
ከመስኮት አምልጦ ፥የወጣ ወጋንን
ሳር ቅጠሉን ሲያሳይ
አጥብቄ ስፈልግ ፥የእለት ያይኔን ሲሳይ
የሌት አይኔን ሲሳይ
በኩርማን ገላዋ፤ እራፊ ደርባ
የራሷ ሻጭ ሆና ፤ለሸመታ ቀርባ
በሌት ይፋ ሆና፥ በቀን ልትደበቅ
ያልቀጠረችውን ፥የምትጠባበቅ
አንዲት ሴት እያየሁ
አሰላስላለሁ ፤
“ አብረዋት ያደጉ፤ ብጤዎቿ ሁሉ
በድሜና በውበት እሷን የሚያክሉ
ተድረው እንደ ሴት፥ ተከብረው እንደ ሰው
የባሎቻቸውን ደረት ተንተርሰው
ፍቅር ሲያጣጥሙ
ወይ በንቅልፍ ሲሰጥሙ
ይች ወገን አልባ
የሌሊት አበባ
በቀትር ተኝታ ለውድቅት የነቃች
የቱን ፍሬ በልታ ለዚህ ፍዳ በቃች ?”
እያልሁ አስባለሁ፥
ደሞ ከደጃፌ ትንሽ ማዶ ርቆ
የመሸበት ለማኝ ፤ መንገዱ ዳር ወድቆ
በግልጥ ይታየኛል
“ ረፍትን ላክልኝ ፥ወይ እንጎቻህን ጣል
በራብ እና በንቅልፍ ሰው እንዴት ይቀጣል"
የሚል ይመስለኛል ፤
በረንዳ ላይ ቆሜ፥ በሌሊት ስምሪት
ከመስኮት በወጣ፥ የብርሀን ቅሪት
አይቼ ማልዘልቀው
ያገሬ ጎዳና የት ላይ ነው የሚያልቀው
መከራና ውበት የሚያፈራርቀው::**
ሰላም!
'Facebook' የምትጠቀሙ ቤተሰቦቼ!
አንድ ትልቅ ውድድር ላይ ለመሳተፍ እየሞከርን ነው።
ኑና ተመልከቱን እስኪ።
ሉንኩ ?*?*?**https://www.facebook.com/100027198434296/posts/1490263351890265/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
Yeabsira Bekele
እዛ የሐሳብ ውድድር ያለበት ቤት መጥታችኹ አበረታቱን እስኪ። ቢያንስ ተስፋ ካለኝ በዚያው እንድነሣሣ አሳዩኝ። ሌሎችም ሥራዎች እንዳጋራችኹ... በታችኛው ግጥም ተወዳድሬያለኹ። 'ሊንኩ'ን ከሥር አያይዝላችኋለኹ። ***🤱*** እናት ***🤱*** አንድ ንጣይ ቅጠል ብቻ ከሰው ግንጥል እንደው መኾን ሲቻል ..... ብዙ የብዙ ወዳጅ...
እንኳን አደረሰን!
እንኳን አደረሳችኹ!
ክብር ለዓለም ደራሲዎች!
የንባብና የመጻሕፍት አክፍሎታችኹን ለማድረስ እነዚኽን ገጾች ጠቆምናችኹ።
? መጽሐፍ ስትፈልጉ ??
@Light_Book_Delivery
@Light_Book_Delivery
#Group
@Light_Book_Delivery_1
@Light_Book_Delivery_1
#FACEBOOK
https://facebook.com/groups/982081539119593/
https://facebook.com/groups/982081539119593/
#ለመጽሐፍ_ዕቁብ
@Light_Equb
@Light_Equb
#ለጽሑፎች
@Love_Of_Sophia
@Love_Of_Sophia
#Group
@SOFIA_Discussion
@SOFIA_Discussion
ለመጻሕፍት ወዳጅ ጓደኞቻችኹ በማጋራት እንኳን አደረሳችኹ ይበሏቸው።❤
#ከሞተች_ቆይቷል **ከሞተች ቀይቷል
ብዙ ዘመን ኾኗል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፏ አለ
ደብዳቤዋም አለ
በጠጕሯ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀን ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ
አበባ ሔድኩ ይዤ
እዛ አበባ አልጠፋም
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም
የዚኽ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ
የዚኽ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይኹን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት
ሕይወት ነዶ ጠፍቶ
ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጓዳ ሔጄ ልተኛበት።
ይመስላል ዘላለም
ሰው ሰውን ሲወዱት
ዐይኑን ዐይኑን ሲያዩት
ይመስላል ዘላለም
አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም
ሰው ባ'ካል የሚኖር
ድሮ ዐውቀዋለው
ተረድቼዋለኹ
ፀሐይ ጥቁር ስትኾን
ቀን ቀንን ሲያጠላው
ሌት ሌትን ሲሸፍን
እረስቸው እንደኹ፡፡
እንዴት አንቺን ልርሳ
ነፍሴ አብሯት የሚኖር የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡
˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው
አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝
ማን ነበር ማ ነበር
ማ ነበር እንደዚኽ ብሎ የገጠመው?
ይመስላል ዘላለም
አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ
አንተ የኔ ጌታ
አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ
አንቺ የኔ እመቤት
ይመስላል ዘላለም፡፡
እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው
ልቤ ተነደለ
የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው
ደሜ ገነፈለ
የደም ጥቁር እንባ
ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ
አለቀሰቅሳትም
ቡዳ እሷን አይበላም
ቢስ እሷን አያይም
አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለኹ
ዐውቃለው ዐውቃለኹ
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ እጣን
መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሔም ቅኔ ማኅሌቷ
እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ
ፍቅሬ ሙሽራዬ
እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ
አቴቴዋ ይታጠናል
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ
እንባዬ ወረደ…………………..
እንግዲኽ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ
በድካም መድከም ባ'ሳብ ሐሳብ አለ
ባ'ዘን…………..ሐዘን……….ሐዘን።
ለተናፈቅሽው ❤
© ገብረ ክርስቶስ ደስታ!**@Love_Of_Sophia@Love_Of_Sophia
**የሴትነት ከፍታ እናት ናት።
ብልኽ ናት። አይመስልኽም እንጂ ከእሷ በላይ የሚረዳኽ የለም፤ ሳትናገር ነው የምታውቅኽ። እንጠባይኽ ብላ ያየችውን እንዳላየች ስለምታልፍና ነጻነትኽን ከማንም በላይ ስለምትጠብቅ እንጂ ስለአንተ ከራስኽ በላይ ታውቃለች።
እስከመጨረሻው አብራኽ የምትጓዘው እናትኽ ናት። ካላመንኸኝ በዕለተ ዐርብ እስከመስቀል አብሮት ማን እንደነበር እስከሞት የደረሰውን ጌታ ጠይቀው።
ሴት ልጅ የምትከብረው በመውለድ እንደኾነ ቅዱሱ መጽሐፍም ይነግርኻል። ስትወልድ የሰውነት ኹሉ ልክ ትኾናለች። ከፈጣሪኽ በታች አምላክኽ ትኾናለች።
እናትኽ...
ስትጨልም አብራኽ ትጨልማለች፣ ስትሰንፍ ፍጹም ልታበረታኽ አብራኽ ትሰንፋለች፣ ብርታቷን ልታጋባብኽ በወረት ሳይኾን በፍጹም ፍቅር የምትጥር ናት።
እሷ ጋር የአንተ በሽታ በሽታዋ ነው። ስለአንተ ደኅንነት እንጂ ለበሽታኽ ግድ አይሰጣትም።
እሷ ጋር የአንተ ዝቅተኛነት ሳይኾን መኖርኽ ብቻ ዋጋ አለው።
እሷ ጋር ከአንተ ሐዘን በላይ የሚያሳዝናት የለም።
እሷ ጋር ደሀ ብትኾንም ሀብትዋ እንደኾንኽ ትቆጥራለች።
እሷ ጋር መለዋወጥ፣ በአንተ ተስፋ መቁረጥ የለም።
ሰዎች መልክኽን፣ ዕውቀትኽን፣ ሞራልኽን፣ ሕመምኽን፣ ችግርኽን፣ ስንፍናኽን ተመልክተው ሊሸሹኽ፤ አይረባም ብለው ከሕይወታቸው ሊያስወጡኽና ተስፋ ሊቆርጡብኽ ይችላሉ።
እናትኽ ግን ስትወልድኽ እንደተደሰተችው ኹሉ እስከሕቅታዋ ድረስ ያው በአንተ ደስተኛ ናት።
ስለምታደርግላት አይደለም...በቃ ስላለኻት ስለተወለድኽላት ብቻ ደስተኛ ናት።
ከእሷ ውጪ የአምላክኽ ምድራዊ አምሳል ማን ሊኾን ይችላል?
ማንም የማይተካት የፈጣሪኽ ጸጋ ናት።**@Love_Of_Sophia@Love_Of_Sophia
የሩቅ - ቅርብ
ድንገት ይመጣሉ፤ ብድግ ብለው ይሔዳሉ።
ሳታስበው ያገኙኻል፤ ማሰብ ስትጀምር የሉም።
ስትተኛ ሥርኽ ነበሩ፤ ስትነቃ ታጣቸዋለኽ።
ድክመትኽን ዕያዩ ቀርበውኽ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ትሰለቻቸዋለኽ፤ በአንተ ላይ ተስፋቸው ይሟጠጥና ከአንተ መሸሽ ይመርጣሉ።
ደካማነትኽ ከፍቅራቸው በልጦ ብተውኽ ምን አጣለኹ ይሉኻል።
ያገኙኽ ትናንት ነው፤ የተዉኽ ደግሞ ዛሬ። በአንድ ቀን ውስጥ (በጥቂት ጊዜያት ግፋ ቢል በትንሽ ዓመታት) ከአንተ ለመራቅ ኹለቴ አያስቡም።
ፍጹምነትኽን ስለሚሹ ጥቁር ነጥብ ካዩብኽ እስከዛሬ በምድር ከታዩት አስከፊው ሰው አንተ ትኾናለኽ።
ስሕተት ከተገኘብኽ በቃ አታስፈልግም።
በሩቁ - ይቀርቡኻል።
የሩቅ - ቅርብኽ ናቸው። ርቀውኽ ይመለከቱኻል። ከአንተ ጋር ያላቸው ቅርበት ገደብ በተበጀለት አጥር የተቀጠረ ነው።
እነኚኽ ብዙኃኑ ናቸው።.
.
.
.
.
(ክፍል ፩)
አንዲት እድሜ ለስንት ትኾናለች???
በጨዋታችን መኻል "ባል ፈልግልኝ" አለችኝ ምን ዓይነት? አልኋት።
"ጥሩ ጠባይ ካለው ይበቃኛል"። የምሯን እንደኾነ ኹሉ ነገሯ ይናገራል። ጉጉቷ አንጀቴን በላው።
ፍቅረኛ ኖሮሽ ያውቃል? አልኋት።
ጥያቄውን ለማሰላሰል ስታገል በደረቁ ወጣብኝ።
"ነበረኝ"
"ዛሬ ነገ እያለ ሕልሙ ላይ ተመስጦ ድክመቴን እያጎላ እያሳጣ ከዛሬ ነገ እንጋባለን እያለ ቀኔን ዕድሜዬን በልቶ ተልካሻ ምክንያቶችን ጠቃቅሶ ተለየኝ። አኹን ሌላ ከእኔ በአሥር ዓመት የምታንስ ጉብል አግብቶ ወልዶ ይኖራል"
ምናለ....
ካልወደድኻት፣ ካላገባኻት ብትተዋት፤ ቀኗን ባታኝከው! ውበቷ ሳይደበዝዝ፣ የከጀለችውን አማርጣ በጊዜዋ ታግባ።
* ጊዜ ለሴት ልጅ ከወንድ ልጅ የበለጠ ትርጉም አለው።
✍ አድኃኖም ምትኩ
? አዎ!...እሱ ጋር ያመኛል!
(የተቀነጨበ)
**ምን ኾኜ ነው?
ተስፋ ነበረኝ የምፈልገው ልደርስበት የምመኘው ሥፍራም ነበረኝ ።
ምን ኾኜ ነው?
ትንሽ ነገር ያስደስተኝ ነበር። እናቴ ከወትሮ ለየት ያለ ወጥ ከሠራች ዓለም ሙሉ ይመስለኝ ነበር። ደስተኛ ነበርኹ። አኹን ዳስ ተጥሎ ቢደገስልኝ ግድ አይሰጠኝም። ጥቂት ይበቃኝ ነበር እኮ። በሹክሹክታ የነገሩኝ ጎልቶ ይሰማኝ ነበር። አኹን እየጮኹብኝም አልሰማ። ትንሽ እኮ ይበቃኝ ነበር...
ምን ኾኜ ነው?
በፊት ስሔድበት የሚያስደስተኝ ስፍራ ነበር። አኹን ቦታ ለመቀየር ብቻ ነው የምንቀሳቀሰው። በፊት አንድ ማንኪያ ቡና እርካታን ያጎናጽፈኝ ነበር...አኹን የጀበናውን ያኽል ቡና ብይዝም የጠጣው አይመስለኝም። በቡና አልነቃ። በአነቃቂዎች አልነቃ። ዐውቄ ነው መሠል ተኝቻለኹ።
ምን ኾኜ ነው?
ማን ነው ተስፋ የነፈገኝ ?
በማን ነው የደከምኹት ?
መቼ ኑሬ ነው ያረጀኹት?
ድሮ መቼ ነው?
ድሮ የዛሬ ዓመት? ድሮ ትላንትና?**
የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ
©ሶፊ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад