Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
:
:
፡
፡
❤️በጣም የሚዋደዱ ባልና ሚስት ድንገት በማይታወቅ ምክንያት በማሃላቸው ባለመግባባት የተነሳ ግጭት ይፈጠራል... ባል ይናደድና ይደበድባታል፤ ሚስት በጣም ታዝንና ታለቅሳለች ባል ትቷት ወደ መኝታ ቤት ይገባና ይተኛል፤ ሚስት ትንሽ ካሰበች በኋላ ወደ መኝታ ቤት ገብታ ትተኛለች፤ ሲነጋ ባል ከተኛበት ሲነቃ በጣም ደንግጦ ስቅስቅ እያለ ማልቀስ ይጀምራል...ሚስት ጥቅልል ብላበት አቅፋው ተኝታ ነበር፤ ለቅሶውን ሰምታ ትነቃለች እንዲም ትለዋለች እንዳስለቀስከኝ አስለቀስኩ ብድሬን መለስኩ ብላ እየሳቀች ሳመችው.... እሱም በጣም ተደስቶ አቅፎ ሳማት.....እሳትን በውሃ እንጂ በእሳት አታጠፋውምና።.........
GOOD NIGHT?
GOOD NIGHT?
GOOD NIGHT?
https://t.me/yefikir1
@yefikir1
@yefikir1
Telegram
ፍቅሬን በግጥም
https://t.me/joinchat/AAAAAExXHV9q9Kpd\_QG1hA
አልችልም
( ፍቅሬን በግጥም )
፡
የፅጌን ማህሌት የዳዊቱን ደግም፣
ልሰማ ማልጄ ቤተስኪያን ብሄድም፣
አምላኬን ልወድስ እልፍ ብፈልግም፣
፡
እኔ ግን አልችልም፣
፡
ውርጩ ምን ቢወርጭ ነጠላ አጣፍቼ፣
ከመቅደሱ ቆሜ አይኖቼን ዘግቼ፣
ላመሰግን ብዬ ቃል ካፌ አውጥቼ፣
ስምሽን እንዳልጠራ ዝም አልኩኝ ፈርቼ፣
፡
ፀሎቱ እንዲሰምር አሜን ሲል ምዕመን፣
በጉልበቱ ሲወድቅ ሲሰብር አንገቱን፣
በቃሉ ሲቀጣው ደንዳውን ልቡን፣
በምክር ሲጎሽም የምድር ስጋውን፣
፡
እኔ ግን አልችልም፣
ካንቺ ሌላ እንዳስብ ሺ ምክንያት ባገኝም፣
አንቺን አለማሰብ ሀሳብ አይመስለኝም፣
፡
ፈጣሪ ይመስገን ሲሉ መሪ ጌታ፣
ለኛ ይመስለኛል የህዝቡ ዕልልታ፣
በአንድ ልንኖር የተጋባን ለታ፣
፡
አይ እኔ ምስኪኑ፣
ካንቺ ጋር ሆነና ልቤ ቃልኪዳኑ፣
በስምሽ ተሳስሮ ድምፄ ወ ልሳኑ፣
ከቤተስኪያን ቆሟል ስጋዬ በድኑ፣
፡
ከአትሮኖሱ ቆሞ ቀሲሱን ባየውም፣
አይኔን ለአፍታ እንኳ ዳሩ ባልከድነውም፣
እውነት አልሻለሁ ምንም አላየሁም፣
፡
እኔ ግን አልችልም፣
፡
የቃሉን መገኛ ከያዝኩት ደብተሬ ላሰፍረው ፈልጌ፣
ስምሽን እፅፋለሁ ከመስመሩ ግርጌ፣
፡
አሁን ምን ይለኛል የሰማና ያየ፣
የኔ አንቺን ማፍቀር ከፍቅር ተለየ፣
፡
እኔ ግን አልችልም፣
ካንቺ ሌላ እንዳስብ ሺ ምክንያት ባገኝም፣
አንቺን አለማሰብ ሀሳብ አይመስለኝም፣
፡
፡
አልችልም፡፡
እውይ ፍቅር
ፍቅሬን በግጥም pinned «?የድሀ ልጅ ፍቅር ? ?ክፍል ስድስት ? ?በእውነተኛ የህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ? እኔና ሜላት በስልክ ስናወራ ቆይተን ነገ ቤተስብን አስፈቅደሽ እናጠናለን ብያት ስልኩ ተዘጋ። ስልኩን እንደዘጋሁት ሌላ ስልክ ተደወለልኝ የማላውቀው ስልክ ነበር ዝም አልኩት። ደግሞ ተደወለልኝ ግራ ገባኝ ከሜላት ውጪ ይሄንን ስልክ ማንም አያውቀውም... በሶስተኛው አነሳሁት በር ላይ ነኝ ውጣ የሚል…»
poetries Matiyas berza
ፈዋሹ ቁስለኛ
ሐምራዊ ደመና ለበሰ ሰማዩ
ቁልቁል ሲተረተር የግርዶሽ ኪዳኑ፤
ወደ ላይ ሲወጣ የሥቃይ ተማጽኖ
የደሙ እንፋሎት ጠፈር ላይ ደምኖ
ከብርሃን ዕልፍኝ አልፎ እስኪገባ
ጸባኦት እስኪደርስ ከራስ ቅሉ ካባ
እሪታ ጩኸቱ
ቅናቱ ብርታቱ
እስኪቆም ትንፋሹ ወጣ ገሠገሠ
አካሉ ካለበት ሰማየ ሰማያት አልፎ እየጣሰ፤
ማን ካህን ይቆማል በጌቴሴማኒ
ምን ትርጉም ሊያመጣ የኃያላን ወኔ
ማን ቀምሶ ይኖራል ከጽዋው ጠብታ
ትንፋሽ ትነሣለች ከሰውነት ገብታ።
እሱማ እሱ ግን ይሄን ሁሉ ችሎ
ዕርጉም እስከሚባል ዕርግማን ላይ ሆኖ
ያሰማል ሰቆቃ ከሰው ዝቅ ብሎ።
___
ማርከን ዜማ @Markengeta
▷ @markenzema_bot ◁
▷ @markenzema_bot ◁
✟መልካም ፋሲካ✟
△Join Us△
የደም ሙሽራ
ገጣሚ ማቲያስ በርዛ
ዓለም ነበር የተሳለችው ከክርስቶስ ጀርባ በጅራፍ ብዕር
አብም ቢሆን ዓለምን ያየው
በልጁ ነው በእጆቹ ቀዳዳ በጣር ጩኸቱ ጭንቅ በደሙ ፍልቅልቅ፤
የመስቀል ዘንግ ተገልድሞ በትከሻው
ጻዕር አልተለየው እስከ ነብሱ ትግል እስከ መጨረሻው
አንተን የወለደች ማሕጸን ብለው እንዳልመረቁ
ሸላቾች ዶትለው የስላቅ ሳቅ ሳቁ
ለራሱ የሾህ አክሊል ተጎነጎነ
ሰው በዘይት ሲወዛ እሱ በደም ሸገነ
ዙፋን ክብሩ የሆነ የመላዕክት ዜማ ጌጡ
አካሉ ለግቦ ቁስሎቹ በዘገር ሲፈርጡ
የሕይወት ቃል የወጣበት አንደበቱ ለጣር ሲከፈቱ
ደዌያንን የፈወሱ እጆች ዓይንን የፈጠሩ
በደረቀ እንጨት ለሥቃይ ሲወጠሩ
የለበቁ ሽራብ ሥጋውን ይዞ ሢነሳ
ዐጥንቱ እስኪገለጥ ቁርበቱ ሲሳሳ
አንቺ ዓለም አንቺ ዓለም
ያኔ ባንቺ ሲዞር ያልሰጠሽው ቦታ
ዛሬ ፈቀድሽለት ያን ዲብ ጎልጎታ።
በገፍ የተከተለው ሆሳዕና ብሎ
በጀማ የመጣው አገር አጠቃሎ
ይሰቀል ይሰቀል ምንም ባላረገ
ሕሙማንን በታደገ።
ፀሐይ ምን ይዋጣት በቀትር ጨለመች
ፊቱ አልቆመችም ከዕርቃኑ ሸሸች
የጨለማ በርኖስ ሥጋውን ሸፈነ
ጻዕር ሲፈራረቅ ድምጹ ታፈነ
ማቀቀ ደቀቀ ላመ
እስከ ነብሱ ስቅታ ታመመ
ዓይኑ ፍቅርን አለቀሱ ጣሩ ተማጸነ
ለጉዳቱ ትቶ ላመፃችን ለመነ
የሱ መስቀል ይለያል
በደም ተጨማልቋል።
አንተ የክርስቶስ አባት በኤሎሄ የተጠራህ
በዕንባው ሰዓት የቀረህ
ወዴት ነው ወዴት ሄደህ?
ምድርን በውኃ ሰዶምን በእሳት
ቁጣህ አይደለም ወይ ያኔ የገረሰሳት?
ታዲያ አንድያህ ታናሽ የሌለው
የሰው ልጆች ክፋት ለሞት ሲያቀዋልለው.
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
ማርከን ዜማ @Markengeta
▷ @markenzema_bot ◁
▷ @markenzema_bot ◁
✟መልካም ፋሲካ✟
△Join Us△
ፍቅሬን በግጥም pinned «?የድሀ ልጅ ፍቅር ❤️ ? ክፍል አምስት? ?በእውነተኛ ህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ? ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ እየጠበቅን ነው ሜላት ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ አኮረፈች ሁሌም ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና ጉንጫን በእጆቼ ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ,.…»
?የድሀ ልጅ ፍቅር ❤️
? ክፍል አምስት?
?በእውነተኛ ህይወት ታሪክ ላይ የተመሰረተ?
ሜላትን ልሽኛት ታክሲ ተራ ቆመን ታክሲ እየጠበቅን ነው ሜላት
ፊቷን ጥለዋለች ሳመኝ
አለችኝ ግንባሯን በስሱ ሳምኳት ይበልጥ አኮረፈች ሁሌም
ስሽኛት ግንባሯን ስሜ ነው
የምለያት .ግን ማኩረፏ ስላስደነገጠኝ ጉንጭና ጉንጫን በእጆቼ
ይዜ ከንፈሯን ሳምኳት ደስ
አላት ለመጀመርያ ጊዜ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው ,.
ድንገት አጠገባችን መኪና ሲጥጥ ብሎ ቆመ ደንግጠን ዞር
ስንል የሜላት አባት መኪና ነበር
ነይ ግቢ የሚል አጭር ቃል ,ሜላትም እሽ ብላ ቻው ብላኝ ወደ
መኪናው ገባች አባቷ እኔን
ገላምጦኝ መኪናውን አስነስቶ ሄደ.,
ወይኔ አምላኬ ምናለ ባልሳምኳት ብታኮርፍ ይሻል ነበር ብዬ
አሰብኩ ቀኑ አርብ ስለነበር
ቅዳሜና እሁድ እንዴት ሊያልፍ ነው ስልክ እንኳን የለኝ ብቻ
ጨነቀኝ እቤት ገብቼ ለእናቴ
የተፈጠረውን ነገርኳት አዘነች ግን በቃ አይዞህ አምላክ ያለው
ይሆናል አለችኝ ,እሽ አልኳት
በማግስቱ እነ ሜላት ሰፈር ቤተክርስቲያን ሄድኩ ሜላት የለችም
ጨነቀኝ ምን ተፈጥሮ
ይሆን አላውቅም ሜላት ግን የለችም.,እሁድም አላገኝኃትም
ይበልጥ ጨነቀኝ.,
ሰኞ ጠዋት በጠዋት ተነስቼ ትምህርት ቤት ሄድኩ ሜላት ግን
የለችም ተደውሎ ወደ
ውስጥ እየገባሁ እያለ አንድ መኪና መጥቶ በር
እኛ ክፍል በር ላይ ስደርስ ሜላት ከየት እንደመጣች ሳላውቅ
መጥታ ተጠመጠመችብኝ
ከንፈሬን አንገቴን አይኔን
ሁሉ ነገሬን ሳመችኝ ደህና ነህ ይቅርታ ይቅርታ እሽ አለችኝ ምን
ተፈጠረ ምን ሆነሽ ነው
አልኳት ለረፍት ሰአት እነግርሀለው አሁን እንግባ መምህር
ሳይገባ አለችኝ እሽ አልኳትና
እሷም ወደ ክፍሏ እኔም ወደ ክፍሌ ገባን.,
የእረፍት ሰአት ደርሶ ሜላትን አግንቻት የተፈጠረውን
እስክትነግረኝ ቸኩያለው በጣም
ጨንቆኝም ነበር ,መማር ሳይሆን መፍዘዝ ሆነ ሰአቱን መግፋት
ብችል ገፍቼ አሳልፈው ነበር
ግን አልቻልኩም ,የእረፍት ሰአት ደረሰ መድረስ አይቀር ወጥቼ
ልክ ሳገኛት ተጠምጥሜ
ሳምኳት ምንድነው የተፈጠረው ንገሪኝ አልኳት እሽ አለችኝና
ቁጭ አልን,.
ሜላት ከቤተሰቧ ጋር ትልቅ ብጥብጥ እንደተፈጠረና ሁለተኛ ከኔ
ጋር ከታየች ችግር
እንደሚፈጠር ነግረዋት ሰለነበር አንተንም እንዲጎዱህ
ስለማልፈልግ ነው የጠፋሁት
ጠዋትም ወንድሜ እንዳያይህ ብዬ ነው ዝም ብዬህ የገባሁት
ከዚህ በኃላ ከ ትምህርት ቤት
ውጭ መገናኝት የምንችል አይመስለኝም ምናልባት ማታ ማታ
ቤተክርስቲያን እንገናኛለን
አለችኝ እሽ ብቻ አንቺ ምንም አትሁኚብኝ አልኳት .,
ሜላትም ከቦርሳዋ ውስጥ አንድ ትንሽዬ ስልክ አውጥታ በዚህ
ስልክ እንደዋወል አለችኝ
እሽ አልኳት በቃ ከልቤ እንደምወዳትና ብትለየኝ እንደምጎዳ
በደንብ ገባኝ ከዝይች ቀን
ጀምሮ በስልክ ወይም ትምህርት ቤት ካልሆነ በስተቀር ሌላ ቦታ
መገናኝት አቆምን ሜላት
ማጥናት ትታለች በቃ ከኔጋር ለምዳ ብቻዋን ማጥናት
አልቻለችም.,
የማትሪክ 12ኛ ፈተና እየደረሰ ነው እኔ በጥናት ተወጥሪያለው
ሜላት ግን ማጥናት ትታ
እቤት ነው የምትውለው እኔም በምን መልኩ ላስጠናት
እንደምችል ግራ ገብቶኛል ,ማታ
ነው ስልክ ደወልችልኝ አወራን ምንም እንዳላጠናች ነገረችኝ
አጥኚ ነገ ከትምህርት መልስ
እንደምትቆይ ተናገሪና እናጠናለን አልኳት እሽ ብላኝ ቻው
ተባብለን ስልኩ ተዘጋ..በድጋሚ
ስልኬ ጮኸ የማላውቀው ስልክ ነበር,........
ይቀጥላል.......
▬▬▬????▬▬▬
@yefikir1
@yefikir1
ለማንኛውም አስተያየት
@Temee_bot
:¨·.·¨: ❀
·. ┈┈••◉❖◉●••┈ይ ?️ላ?️ሉ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago