ውብ ወግ

Description
ለሀሳብ አስተያይት @Niyu21
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

6 days, 12 hours ago
ሀገሬ ናፍቆኛል!

ሀገሬ ናፍቆኛል!

ድፎ ዳቦ ተጋግሮ እንደወረደ በጥርሴ የምታስገምጠኝ ናፍቃኛለች።

አዲስ ዓመት የሚቀየረው እኔ ሀገር ነው።እዛ ሀገር አለኝ የምለውን ሁሉ አስቀምጫለሁ።እዛ ሄጄ ‛ምድር ግን  እንዴት እንዴት ያደርጋታል?’ እስከምል ስትኳኳል፤ እንደ ሀገሬው ሰው ቃል የማይዛባው የቆላ ዝናብ አዳሩን ጥሎ ጠዋት ብራ ሲሆን አይቼ፣ ቦታውን የከበበው ተራራ ፍፁም አረንጓዴ ፍፁም ቢጫ ሲሆን አይቼ፣ የከሴ ችቦ ተለኩሶ በመሃል የምትጠለፍ የአንስላል ቅጠል (ኡዞ ጠረን ያላት) ጭስ ሲሸተኝ ዓመቱ ተቋጭቶ ሌላ መጀመሩን አምናለሁ።ከደጇ አልቀርም

ዞማ ድፍርስ ጎርፉን በቀጭን የምንጭ ዘለላ እስኪተካ ካላየሁ መስቀል መምጣቱን አላምንም።እኔ ሀገር ፀሀይ መውጫዋ እኛ ቤት እስኪመስለኝ ሰርክ  ስትዘረጋ አይቻታለሁ።ሚካኤሉ ጋር ስትገባ ጠብቄ ሸኝቻታለሁ።እዛ ካልሄድኩ  አምናውም ዘንድሮው ለኔ ያው ነው።

እዛ ሀገር አሉኝ ያልኳቸውን ሁሉ አስቀምጫለሁ። ከሩቅ ቦታ ያመጣሁትን ፍቅር ‛የሀገሬ ልጅ'ዬ!’ እስከምል እንዳይርቅብኝ አድርጎ ሰጥቶኛል። ተያይዘን አዲስ ዓመትን አይተናል። አዲስ ዓመት በአካል የሚታየው እኔ ሀገር ነው።

‛ዝምታ ነው ወሬያቸው’ እላለሁ። አማራ እንደሆኑ አያወሩም። አያሳስባቸውም።ከድንጋይ ቦታቸው ላይ ቅባት ያለው ጤፍ ያጭዳሉ። በቀያይ ጉንጮቻቸው ማድያት ልጆቻቸውን ያስተምራሉ። ወንድ ልጅ በቀን የማይተኛበት ገጠር ሀገሬ ውስጥ የሚኖሩ ቀያይ ሰዎች፤ ሥራ ነው ወሬያቸው።እጠይቃታለሁ።ልቤ እየተሰነጠቀ

“ሰላም ነው?”

“ሰላም ነው፤ ምንም የለ ሥራችንን እየሠራን ነው”

“ኑሮ ተወደደ?”

“አዋ ይወደዳል”

መልሷ አጭር፤ በጣም አጭር ነው። መንገዱ ከተዘጋ ወራት አለፉ።ድምጿ አይበገርም። ማንም ያስተዋለው አይመስልም።መፅናት፣ዝምታ፣ ሁኔታን መናቅ ብቻ ነው ሳወራት የማገኘው።

© ጺዮን

@wegochi

1 week ago

ከስድስት ኪሎ ወደ መገናኛ ታክሲ ተሳፍሬ ስሄድ ከአንድ አባት ጎን ነበር የተቀመጥኩት።

ፈገግተኛ ናቸው። ፂማቸው ሙሉ ለሙሉ ሸብቷል፣ ረዳቱ ጠጋ በሉ ሲሊቸው፥ ሰዓት ሲጠይቁ፥ እንቅስቃሴያቸው ሁሉ በትህትና እና በፈገግታ ነው።

'ሂሳብ' አለ ረዳቱ።

አራቱንም ኪሴን በረበርኩ የለኝም...ረዳቱ የሰጡትን አስልቶ መልስ ሲልክላቸው ለሁለት ሰው አሉት።

'ከማን ጋ' አላቸው።

በትህትና ከሱ ጋ አሉት ... እኔን እየጠቆሙ።

ፈገግ አባባላቸው እንደሰጡኝ አይደለም። ሱሪያቸው አርጅቷል፤ ሹራባቸው ብዙ ግዜ ተደርጌያለሁ ይላል፤ ግን...ማጣት አላሳሳቸውም...።

ደግነታቸውን አልተነተኑም መውረጃቸው ደረሰ።

'ደህና እደር ልጄ' ብለው ወረዱ።
. . .
ደግ እንድሆን መልእክተኛ ናቸው ? አሳዝናለሁ እንዴ ስታይ ? ዓለም እንዳትደብረኝ ነው እንደዚህ ዓይነት ሰዎች በመንገዴ የሚመጡት ?መታደሌ!

©አድኃኖም ምትኩ

@wegochi

1 week, 1 day ago
በስራ የቆሸሹ እጆች እና ንፁሕ ልብ …

በስራ የቆሸሹ እጆች እና ንፁሕ ልብ ካለው ሰው ጋር ለዘላለም ኑሪ። ይህ ሁሉ መስዋትነት የሚከፍለው ለአንች ነውና!

ውድ ልብስ ሳይሆን ውድ ነፍስ ያለውን አጥብቀሽ ያዥ አንዴ ልቡ ከሸፈተ መመለሻ የለውምና!

ሐብት ባይኖረው ሁሌም ብሩህ ፈገግታ ከሚለግስሽ ሰው ጋር ቆይ ደስታ አንዱ የህይወት ግብ ነውና!

እጆቹን እያቆሸሸ አንችን ከሚንከባከብሽ ጋር ኑሪ።ምንም ሳይኖረው ሁሉን ከሚሰጥሽ ጋር ቆይ።

ውብ ቀን!

@wegochi

1 week, 4 days ago

"ንጉሥ ከመሆኔ በፊት ሰው ነበርኹ!"

ይህንን አባባል የዱባይ 'አባት' የአረብ ኤምሬት መስራች የሚባሉት ሸህ Zayed ነው የተናገሩት ይባላል ... መኪናቸውን እያቆሙ ተራ ነገር ከተራው ሰው ጋር ሲያደርጉ ታይተው እንዴት ሲሏቸው ነው አሉ: ንጉሥ ከመሆኔ በፊት ሰው ነበርኹ ያሉት

በምን ትዝ አለኝ ....

ጋሽ ጥላሁን ገሠሠ በነበረው የጤና ችግር እግሩን ሊቆረ'ጥ ደቡብ አፍሪካ በሄደ ጊዜ እና ህክምናውን ከአገኘ በኋላ እዛው ሆስፒታል ውስጥ እያለ ከአለም ዙሪያ ያለማቋረጥ ብዙ ሰዎች ስለጤንነቱም፤ እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርህም ለማለት ስልክ ይደውሉለት ነበረ

ከህክምናውም እስኪያገግም ድረስ እዛው ደቡብ አፍሪካ በአንድ ሆቴል መቆየት ነበረባቸው [ከባለቤቱ ከሮማን ጋር]

<< አንድ ቀን ምሳ ሰአት ደርሶ ምሳ ለመብላት ሮማን በዊልቸር እየገፋችኝ ወደ ሬስቶራንት ሄድንና ልንበላ እየተዘጋጀን ሳለ አንድ ነገር ትዝ አላት። ለካስ የምወስደውን መድሃኒት ክፍላችን ውስጥ ረስተነው ኑሯል"

ባለቤቱ ወደ ክፍላቸው መድሃኒቱን ልታመጣ ሄደች

"ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመልሳ ስትመጣ ተአምር ያየች ይመስል ተደናግጣ ነበረ።

ምን ሆነሻል?

"ስልክ"

ታዲያ ስልክ ቢደወል እንዲህ ያስደነግጣል? አልኳት። ሰልችቶን ነበረ። ስልካችን ያለማቋረጥ ይጠራል። እናነሳዋለን። ስለደህንነቴ መረጃ እጠየቃለሁ፤ እመልሳለሁ። ከማውቃቸው ሰዎች ይልቅ እኛ ነን የምናውቅህ የሚሉ አድናቂዎች ይደውላሉ። የእግሬ መቆረጥ ትልቅ ዜና መሆኑ የገባኝ ከአለማት ሲደወልልኝ ነበር። ... ምን የተለየ ነገር አጋጥሟት ነው ታዲያ?...

የሆነው ግን ሌላ ነበረ። ወ/ሮ ሮማን የረሳነውን መድሃኒት ለማምጣት ወደክፍሉ ስትገባ ስልኩ ጠራ። አነሳችው። 'ጤና ይስጥልኝ' ስትለው የማታውቀው ሰው ነበረ።

"ማን ልበል?"

"ከሊቀመንበር ነው የተደወለው፤ ጥላሁን ገሠሠን ማግኘት ፈልጌ ነው"

"ሊቀመንበር?"

"አዎ! ከሊቀመንበር መንግሥቱ ኃ/ማርያም፤ እኔ ረዳታቸው ነኝ፤ ጥላሁንን ማግኘት ፈልገው ነበረ"

"አሁኑኑ በአምስት ደቂቃ አመጣዋለሁ... " ብላ እየበረረች ወደ ሬስቶራንቱ ሄዳ በዊልቸር የተቀመጠውን ባለቤቷን ይዛ ወደ ክፍላቸው ሲገቡ እና ስልኩ ሲጠራ እኩል ሆነ

" ሃሎ" አለች፤ ረዳታቸው መሆኑን ነገራት፤ ስልኩን አቀበለችኝ

" ሊቀመንበር ነኝ" አለኝ አንድ ድምጽ

" ሊቀመንበር ማን?" አልኹኝ ኮስተር ብዬ

"ስንት ሊቀመንበር አለ?" አለኝ ሰውየው እየሳቀ "ያው ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ናቸዋ፤ ከሃራሬ ዝምባዋብዌ "

"እሺ ጌታዬ" አልኩ፤ እሳቸው ቀረቡ

"ጓድ ጥላሁን! እግዚአብሔር ይማርህ። የእግርህን መቆረጥ ሰማን እና በጣም አዘንን፤ ምን ይደረግ? መጥተን እንዳንጠይቅህ ያለንበትን ሁኔታ ታውቃለህ"

"አውቃለሁ ጌታዬ፤ ይህም ይበቃኛል" አልኳቸው

"አይዞህ! ምን ከእንግዲህ ወዲህ እንደነኃይሌ ገ/ሥላሴ እና ቀነኒሳ በቀለ ማራቶን አትሮጥበት፤ አይዞህ። ለእናት አገርህ ብዙ ሰርተሃል። ከእንግዲህ ወዲህ የሚቀርህ ነገር ስለሌለ እግሬን አጣሁ ብለህ ብዙ አትጨነቅ። አይዞህ፤ በርታ" አሉና ተሰናበቱኝ >>

የዱባዩ ንጉሥ "ንጉሥ ከመሆኔ በፊት ሰው ነበርኹ" ያሉት እንዲህ ሰዋዊ ስራ ሲሰሩ ተገኝተው ነበረ፤ ጓድ መንግስቱም ሊቀመንበር ከመሆናቸው በፊት እንደእኛው ሰው ነበሩ።

©ማስተዋል አሰፋ

@wegochi

2 weeks ago

ልጁ በድግሪ ይመረቅና እንደ ብዙሀኑ አፍሪካውያን በስራ አጥነት ይሰማራል፡፡ ማስታወቂያዎችን በተቻለው አቅም ተከታተለ ፤ ብዙ ቦታዎች ላይም አመለከተ ፤ ግን ምንም ለውጥ የለም፡፡

ስራ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ በዚህ መሀል አንድ የእንስሳት ፓርክ የስራ ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ልጁ ከሁሉም ቀድሞ ይገኝና ያመለክታል፡፡ የፓርኩ ሰዎች የልጁን የትምህርት መረጃ ማየት ሳያስፈልጋቸው የአካሉን ግዝፈት ብቻ አይተው ለስራው እንደሚሆናቸው አውቀዋል፡፡

ሰዎቹ ቀስ ብለው ወደ ቢሮ አስገቡትና ማስታወቂያው ላይ በግልፅ ስላላሰፈሩት የስራው ሁኔታ ያስረዱት ጀመር፡፡

"ይኸውልህ ወንድም! ብዙ ቱሪስቶችን ሲስብልን የነበረው ጎሬላ በእርጅና ምክንያት ሰሞኑን ሞተብን፡፡ ሌላ ጎሬላ ደግሞ የለንም፡፡ ጎሬላ ካላሳየን ደግሞ ገቢያችን ይቀንሳል፡፡ስለዚህ ያንተ ስራ የሚሆነው ጎሬላ የሚያስመስልህን ልብስ አስለብሰንህ እንደ ጎሬላ በሰዎች ፊት ማስመሰል ነው የሚሆነው!" በማለት ስራውን አስረዱት፡፡

ልጁ ስራውን ሲሰማ ቢከብደውም አማራጭ ስላጣ ተስማማና ስራውን ጀመረ የመጀመሪያውን ቀን እንደ ጎሬላ ለብሶ እንደ ጎሬላ እየፎከረና እየተንጎማለለ በፓርኩ ውስጥ ሲያስመስል ዋለ፡፡

ችግር የተከሰተው በሁለተኛው ቀን ነበር፡፡ እንደ ጎሬላ ለብሶ ፓርኩ ውስጥ ሲያጓራና እንደ ጎሬላ ሲፎክር ሳለ አንድ አንበሳ ወደርሱ እየሮጠ ሲመጣ ተመለከተ፡፡

በዚህ ጊዜ ሮጦ እንዳያመልጥ መውጫም ስላልነበረው ጎሬላነቱን ረስቶ "ኡ ኡ ኡ! ድረሱልኝ!" እያለ ይጮኽ ጀመር!

በዚህ ጊዜ አንበሳው አጠገቡ ደርሶ ነበር፡፡ አንበሳውም ዝቅ ብሎ በጆሮው እንዲህ አለው "ኧረረረረረ አቡሌ አትፍራ! እኔኮ ከቤ ነኝ ፣ የክላስህ ልጅ!" .... ለካ አብሮት የተመረቀው ከቤም የአንበሳ ልብስ ለብሶ እንደ አንበሳ ለማስመሰል በፓርኩ ተቀጥሮ ኖሯል😁

© unknown

@wegochi

2 weeks ago

ሮበርት ዲ ቪንቸንዞ የተባለ ታዋቂ አርጀንቲናዊ የጎልፍ ተጫዋች በአንድ ትልቅ ውድድር አሸንፎ ተሸለመ፡፡ የሽልማቱን ብር ቼክ ሲቀበል ደስታው በቴሌቪዥን መስኮት ታየ፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ መኪናውን ወደሚያቆምበት የፓርኪንግ ሥፍራ ሲሄድ አንዲት ወጣት ሴት አነጋገረችው፡-

‹‹ያገኘኸውን ድል አስመልክቶ እንኳን ደስ አለህ ልልህ እወዳለሁ›› ካለች በኋላ ልጇ በጠና ታሞ በሞት አፋፍ ላይ እንደሆነ ለሐኪሞችም ሆነ ለሆስፒታል የምትከፍለው እንደ ሌላት፣ መላም እንዳጣች ነገረችው፡፡

ዲ ቪንቸንዞ በወጣቷ ታሪክ በጣም ተነካ፡- ብዕሩን መዝዞ ሽልማት የተሰጠውን ክፍያ ቼክ አውጥቶ እርሷ እንድትወስድ ፈረመላት፡፡
ለልጅሽ ጥቂት የተሻሉ ቀናት እንዲኖረው የተቻለሽን ሁሉ አድርጊ ብሎ ሸኛት፡፡ በሚቀጥለውም ሳምንት የአገሪቱ የጎልፍ ተጫዋቾች ክለብ መኮንን ዲ ቪንቸንዞ ምሳ በሚበላበት ስፍራ መጣ፡፡ ወደ ጠረጴዛውም ቀርቦ ባለፈው በፓርኪንግ ሥፍራ አንዲት ሴት እንዳገኘህና የሽልማትህን ገንዘብ እንደሰጠሃት ሰማሁ አለሁ፡፡

ዲ ቪንቸንዞ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ልክ ነህ  በሚል መለሰለት አንድ አሳዛኝ ዜና ልነገርህ ነው ልጅቱ አጭበርባሪ ነች ምንም ዓይነት የታመመ ልጅ የላትም፡፡ ከነጭራሹም አላገባችም፡፡ አታላሃለች ጓደኛዬ›› አለው፡፡

ዲ ቪንቸንዞ መለሰ፡- "እና ምንም ዓይነት የታመመና በሞት አፋፍ ላይ ያለ ልጅ የለም ነው የምትለው?"

" በትክክል" መኮንኑ መለሰ፡፡

ታዲያ ይህ ነው አሳዛኝ ዜና ያልኸው? ይህ ለኔ በሳምንቱ ውስጥ ከሰማሁት ሁሉ የበለጠ አስደሳች ዜና ነው ከሽልማቱም በላይ!

አንድ በስቃይ ያለ ሕጻን አለመኖሩን ከመስማት የበለጠ ምን የምሥራች አለ?!" በማለት መለሰ፡፡

ገንዘብ ሳይሆን መገንዘብ በልባቸው የሞላ ባለጸጋዎችን ያብዛልን!

2 weeks, 1 day ago

አዲስ የተሾመው አስተዳዳሪ ሙላን አስጠራና "ሙላ እኔ ዋጋዬ ስንት ነው?" ብሎ ሲጠይቀው ሙላ ፈጠን ብሎ

"500 ብር ከ15 ሳንቲም" አለው።

የተናደደው አስተዳዳሪ"ያምሀል?የለበስኩት ልብስ እንኳን 500 ብር ነው እኮ" ብሎ ሲጮህበት

ሙላ ፈገግ ብሎ "እሱንም ሒሳቡ ውስጥ አካትቸዋለው" አለው🤣

@wegochi

2 weeks, 2 days ago

ውጪ ሐገር መኖር የማልፈልገው

እሺ መንገድ ላይ በሩቁ ቤተክርስቲያን ሲያይ ቆም ብሎ የሚሳለም ሰው አለ? ቃሪያ ስንግ ያለበት በያይነቱ አለ? እሺ አትክልት በዳቦ ከበላችሁ ስፕሪስ ጁስ ከጠጣችሁ በኋላ ስትወጡ በር ላይ የተጠቀማችሁትን በታማኝነት ተናግራችሁ የምትከፍሉበት አትክልት ቤት አለ?

እሺ ጉልት አለ? ምርቃት አለ? በአጠገቡ ስታልፉ ሽታው ውልብ
የሚል የበርበሬ ወፍጮ ቤት አለ ወይ? ቂቤ ሲነጠር መንደሩን
የማያውደው መዓዛስ?

እሺ በየመንገዱ ሳጥን ያለው ሊስትሮ አለ? መንገድ ላይ ኪሎው 25 ብር የሚሸጥ የጋሪ ላይ ሙዝ አለ?

ሸንኮራ አገዳስ? ነጠላ ያዘቀዘቁ እናት በአጠገቤ ያልፋሉ? ጥቁር
በጥቁር የለበሱስ? ሳያቸው ምን ሞቶባቸው ይሆን ብዬ መገመት
እችላለሁ ? ጽዋ ይዘው የሚያልፉ እናቶችስ?

ጠዋት የሰማዕታትና የመላእክት ስእል ዘርግተው በግራማፎ
አየሩን የሚባርኩት አባትስ?

ድፍን 5 ብር ሰጥታ መስቀል
የምትሳለመው ባለ ረዥም ፓሪ ቀሚስ ፣ ባለ ረዥም ማንገቻ
ትንሽዬ ቦርሳ ያነገተች ባለ ነጠላ ጫማ ወጣትስ አለች?

መልስ በጭቅጭቅ የሚሰጡ ረዳት ያላቸው ታክሲዎችስ አሉ? "የቤትሽን አመል እዛው " የሚል ጥቅስ አላቸው? እሺ "ሙቅ ሻወር አለ" የሚል ማስታወቂያስ?

የልኳንዳ መብራት አለ ወይ? ቅንጥብጣቢ ፈልገው በሩ ላይ
የሚኮለኮሉት ውሾችስ? ባቅላቫ አለ? ሎተሪ አዟሪስ እሺ?

ዘመናዊ ሚዛንስ? ሊነጋጋ ሲል የቤተክርስቲያን የቅዳሴ ዜማስ ይሰማል? የጥምቀት ማግሥት የመንገድ ላይ ጉዝጓዝስ ?

እንዳውም ያስታወስኳቸው የአዲስአበባን ብቻ ነው የየከተሞቹ
የራሳቸው መልክ አላቸው
ይሄ ሁሉ አለመኖሩ አልበቃ ብሎ ደሞ ሰአት ይቀይራሉ ፤ አንዳንዴ
ቀንና ለሊቱ እኩል አይደለም
እንዴት እዛዛዛዛ ይኖራሉ?

©ጠይም ጽጌሬዳ

@wegochi

3 weeks, 3 days ago

‹‹ትንንሽ ደስታዎች››
(በገብረክርስቶስ ደስታ ‹‹የሚያፅናኑ›› ላይ ተመስርቶ የተጻፈ)
-------

ሆድ ሲብስ 'ሚያባብሉ፣
ከዓለም ጣጣ- ለአፍታም ቢሆን 'ሚከልሉ

በፈተና 'ሚያጸኑ፣
በግርግር 'ሚያረጋጉ፣
ከኑሮ ውክቢያ- ለአንዲት ቅፅበት 'ሚታደጉ…

ነገር ሲመር 'ሚያጣፍጡ…

እነሆ ትንንሽ ደስታዎች…
ሽርፍራፊ እርካታዎች…
ብጥስጣሽ እፎይታዎች

የፍቅር ውጥን
የሚያጓጓ፣  ልብ 'ሚያግል

ቀጭን ደሞዝ…
ለአምስት ቀናት- እንደንጉስ 'ሚያንቀባርር

ሚጢጢ ቤት
እንደልብህ 'ምትሆንባት
ኡፎይ ብለህ 'ምታርፍባት

አዲስ ልብስ
ፕ-ስ-ስ-ስ!

አዲስ ጫማ
ላረማመድ የሚስማማ…

ቆንጆ ጭልፋ፣ ማንቆርቆሪያ
ብርጭቆ፣ ድስት፣ አዲስ ቂጣ መጋገሪያ

የተቆላ ቡና፣ ፈልቶ ሲወርድ፣ ሲጨስ እጣን
ትኩስ ቄጠማ ተጎዝጉዞ ያለው ጠረን

ሻይ በስኳር ከአምባሻ ጋር
ምሳ ሽሮ- እራት ምስር

ኮልታፋ ህጻን ነፍስ የማያውቅ
ያለ ሰበብ ስቆ 'ሚያስቅ

ሳያስቡት በድንገት
የሚደውል ወዳጅ ዘመድ
እንዴት ነህ ብቻ ለማለት…

ውብ የራስጌ መብራት

መጽሐፍት!  መጽሐፍት! መጽሐፍት!

ዘፈን! ዘፈን! ዘፈን!
የጂጂ፣ የቴዎድሮስ፣ የአስቴር፣ የመሐሙድ፣
የፍቅርአዲስ እና የጥላሁንዘፈን!

መታቀፍ መታቀፍ…!
በሚያፈቅሩት እቅፍ እንደሞቁ እንቅልፍ

እንቅልፍ! እንቅልፍ! እንቅልፍ!

ሆድ ሲብስ 'ሚያባብሉ፣
ከዓለም ጣጣ ለአፍታም ቢሆን  'ሚከልሉ

በፈተና የሚያጸኑ፣
በግርግር 'ሚያረጋጉ
ከኑሮ ውክቢያ ለአንዲት ቅፅበት 'ሚታደጉ…

ነገር ሲመር ሚያጣፍጡ…

እነሆ ትንንሽ ደስታዎች…
ሽርፍራፊ እርካታዎች…
ብጥስጣሽ እፎይታዎች

7 months, 1 week ago

“ዘመናዊነት” (Modernism) የሚለው ቃል ራሱ የስልጣኔ ሳይሆን የኢኮኖሚ ቃል ነው፡፡ ሰዎች በስሜት እንዲመሳሰሉ ካደረግህ ተመሳሳይ ምርት ብታመርትም ተመሳሳይ ገዥ ታገኛለህ፡፡

ውበት የሚባለው በተፈጥሮ ወይም በእውነት ሳይሆን በፋሽኑ ኢንዱስትሪ እንዲዳኝ ተደረገ፡፡ነጮቹ “ቅጥነት ነው ቁንጅና” ካሉ ቀጭኗ የተሻለ ዋጋ
ታወጣለች፡፡እሷ የምትለብሰው ፋሽን ዋጋው ከፍ ያለ ይሆናል፡፡

ውበት ማለት ቅጥነት ነው? “ድንቡሽቡሽነት” ከውበት መለኪያነት
ተሰረዘ? የኢትዮጵያዊቷ ሴት ውበት ለኪ ማን ነው? እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱ የሆነ የቁንጅና መለኪያ አለው፡፡የአንዱም ለሌላው አይሰራም፡፡ በባህል፣ በሐሳብ፣ በአኗኗር ከማይገናኝ ዓለም ላይ ሰብስበህ አንድ የዓለም ቆንጆ እንዴት ይመረጣል?

የሞዴሊንግ ትልቁ ሥራው ሸቀጥ ማሻሻጥ ነው፡፡ እውቀት አይደለም፡፡ ሐሳብ አይደለም፡፡ የሞዴሊንግ ዓለም እየሰፋ ከሄደ
ራሳቸው ሴቶቹ ቆንጆ ለመሆን የውበት መጠበቂያ ምርቶችን በብዛት ይጠቀማሉ፡፡
ቆንጆ የምትላት ሴት መጀመሪያ በተፈጥሮ ማንነቷ እንዳልተወዳደረች፤ በሂደት ግን የቁንጅና መጠበቂያ ምርቶችና የሜክአፕ ግዞተኛ ትሆናለች፡፡ ያለ ሜክአፕ በፍፁም ከቤት የማትወጣ ትሆናለች፡፡ ሴቶቹ ላይ የማይሠራ ሙከራ (Experiment) የለም፡፡
“የፆታ እኩልነት” የሚለውን ትርክት በጣም በአፅንኦት ረጋ ብለው ቢታይ በጐ ነው፡፡

“ወንድነት ምንድነው?”፣ “ሴትነት ምንድነው?”የሚለውንም መመርመር በጣም ያስፈልጋል፡፡ዛሬ ሴትን የምትለካት በእውቀቷ አይደለም፤ በጥበቧ አይደለም፤
በምርምሯ አይደለም፡፡ ማሰብና መመራመር ሳትችል ቀርታ ሳይሆን፤ ሸቀጥ እንደሆነች ተደጋግሞ ፕሮፓጋንዳ መሠራቱ ያመጣው ውጤት ነው፡፡ባል ከሚስቱ ሐሳብ ሳይሆን ሚስቱ ተውባና ተቀባብታ የወሲብ
ማሽን ሆናለት እንድትኖር ነው የሚፈልገው፡፡ ይህም አስተሳሰብ የGlobal consumer Culture Society ነው፡፡

© Burhan Addis

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад