Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
³⁰ ....አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ በወንበዴዎችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ደግሞ ገፈፉት ደበደቡትም በሕይወትና በሞት መካከልም ትተውት ሄዱ።
³¹ ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ አይቶትም ገለል ብሎ አለፈ።
³² እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ስፍራ መጣና አይቶት ገለል ብሎ አለፈ።
³³ አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥
³⁴ ቀርቦም ዘይትና የወይን ጠጅ በቍስሎቹ ላይ አፍስሶ አሰራቸው፥ በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ ወሰደው ጠበቀውም። ይላል
ሉቃስ 10፦30-34
➠እኛም በበደላችን እና በኃጢአታችን ምክንያት በሰይጣን እጅ ተጥለን ሙታን በነበረበት ሕግም ነቢያትም ባራሩልን ፣ ያዩን ዓይኖች ባላዘኑልን ጊዜ አንድ ከደጉ ሳምራዊ ይልቅ የተሻለ የሚራራ ወዳጅ አገኘን ።
➠ ይህም ወዳጅ ቁስላችንን በዘይት የሚያክምልን ሳይሆን ቁስላችንን የሚቀበል ፣ ህመማችንን የሚሸከም በቁስሎቹም የሚፈውሰን ስሆን
➠ይህም ወዳጅ ስያገኘንም በሰይጣን እጅ ወድቀን እና ቆስለን ብቻ ሳይሆን ሞተን ጭምር ነበርና 👉 ሞታችንን ወሰደ ። ✞
➠በሉቃስ 10 ፤ 30 ላይም ታሪኩ በምሳሌነት የተጠቀሰው ደጉ ሳምራዊም በመጨረሻም ባልንጀራውን በራሱ አህያም ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማደርያ እንደወሰደው...
➠ ከሳምራዊው የሚበልጥ ደጉ ወዳጃችንም እርሱ በሰራው በእርሱ ስራ ላይ አስቀምጦን ወደ ዘላለም ማረፍያችን ይወስደናል ።
አሜን 🙏
👉ይህም ወዳጅ ኢየሱስ ይባላል ።❤🙏
➠አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት share ማድረግ ይቻላል ።
➠ ያለ እግዚአብሔር እንዳትሆኑ ። ?
መጽሐፈ አስቴር ምዕራፍ 1
በ ንጉሥ በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ ሆነ፤ ንጉሥም ለባለምዋሎቹና ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ የግርማዊነቱን ክብር 180 ቀን ያህል አሳያቸው።
➠ይህም ቀን በተፈጸመ ጊዜ በሱሳ ግንብ ውስጥ ለተገኙት ሕዝብ ሁሉ ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ንጉሡ በንጉሡ ቤት አታክልት ውስጥ ባለው አደባባይ ሰባት ቀን ግብዣ አደረገ።ግብዣውም እንደ ንጉሡ ለጋስነት መጠን እጅግ ብዙ ነበረ።
➠ በ7ተኛ ቀን ንጉሡ አርጤክስስ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ደስ ባለው ጊዜ፥ ንግሥቲቱ አስጢን መልከ መልካም ነበረችና ውበትዋ ለአሕዛብና ለአለቆች እንዲታይ ወደ ንጉሡ ፊት ያመጡአት ዘንድ አዘዛቸው።
➠ ነገር ግን ንግሥቲቱ አስጢን ? በንጉሡ ትእዛዝ ትመጣ ዘንድ እንቢ አለች፤
➠በባህል ሆነ በሃይማኖት በኩል ብናየው አስጢን እንቢ ማለትዋ ትክክል ነበር ። ምክንያቱም ሴት ልጅ ክብራን በሚገባ አለባባስ ሰውነቷን መሸፈን ይጠበቅባታል እንጂ... ንጉሥ ግን በስካር መንፈስ ሚስቱ በአደባባይ ውበትዋን እንድትገልጥ አስጠራት።
➠ነገር ግን እንደ ፋርስ አገር ልማድ ሴቶች ፊታቸውን እንኳ በሚሸፋፋኑበት ነውርን ከማድረግ እንቢ ብትልም
➠ያለ እግዚአብሔር መሆን መጨረሻን አያሳምርምና....ምን ማለት መሰላችሁ እግዚአብሔር ሳናውቅ መልካም ብንሆን መልካም ብናስብ ፣ ጎበዝ ብንሆን ፣ ጥበበኛ ብንሆን ፣ ሀብታም ብንሆን ፣ሰማይ credit አይሰጠንም ።
➠ከዚህም በኃላ የሆነው ነገር ግን በጣም ያሳዝናል ንግሥቲቱ አስጢን ወደ ንጉሡ ፊት ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትገባ ትእዛዝ ወጣ።
➠ ንግሥትነትዋን ከእርስዋ ለተሻለችው ለሌላይቱ እንዲሰጥ ተደረገ ።
➠አስቴር ምዕራፍ 2
መርዶክዮስ የሚባል ብንያማዊ
ያሳደጋት አስቴር ወደ ንጉሡ ቤት ተወሰደች። በአስጢንም ፋንታ ነገሠች።
➠ያለ እግዚአብሔር መሆን ማለት ከኢየሱስ ውጪ መሆን ማለት ነው ። ከኢየሱስ ውጪ ስንሆን ደግሞ ሰማይ አያውቀንም ።
➠እግዚአብሔር በእኛ መልካም ሥራ ፣ በእኛ መልካም አሰብ ፣በእኛ መተንፈስ ፣ በእኛ መብላት ፣ በእኛ መጠጣት አያውቀንም ምክንያቱም እሱንማ እንስሳትም ፣ እፅዋትም ይኖሩታል ። ሰማይ የሚያውቀን በኢየሱስ ስንሆን ብቻ ነው ።
1ኛ ዮሐንስ 5
¹² ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
➠ያለ እግዚአብሔር መሆን ካልፈለግን ያለ ኢየሱስ መኖረን መቆምና በኢየሱስ መኖርን መጀመር ነው ።
➠ በጣም ሀብታም ሰዎችን ልናውቅ እንችላለን ሀብትን መሰብሰባቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ ያለ እግዚአብሔር ከሆነ ግን የሚጠፋው አላቸው የማይጠፋው ግን የላቸውም ?
1ኛ ዮሐንስ 5
¹³ የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
➠አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት share ማድረግ ይቻላል ።
ዘፍጥረት 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
➠ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅተህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ አለው..ርብቃም ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ሲነግር ትሰማ ነበር።
➠ ርብቃም በዚህም ጊዜ ለተናሽ ልጅዋ ለያዕቆብ አዘነችለት መልካምና ጣፋጭ መብል አባቱ ይስሐቅ እንደምወደው አድርጋ በማዘጋጀት ለታናሹ ልጇም ለያዕቆብ ሰጣችሁ ። ለምን እንዲህ አደረገች ካልን ? በአባቱ ለማስባረክ ነው።
➠ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ሲያነብ የተረዳሁትን አንድ ነገር ላካፍላችሁ
➠ኢየሱስ ለእኛ ለተናናሾቹ እንዴት እንዳዘነልን ፣ እንዴትስ እንደራራልን ፣ በእግዚአብሔር አብ ሊያስባርከን እግዚአብሔር አብ የሚወደውን ፣ ከእኛ የጠየቀውን ሁሉ እርሱ በመፈጸም ለእኛ ሰጠን
➠በዚህ ክፍል ያለው ቃል ስናጠና ያዕቆብ በጣም እንደ ፈራ ና እናቱንም ወንድሜ ጠጕራም ሰው ነው፥ እኔ ግን ለስላሳ ነኝ ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ መርገምንም በላዬ አመጣለሁ፥ በረከትን አይደለም። አላት
¹³ እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፤ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ...
“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤”
— ገላትያ 3፥13
ቁጥር ¹⁵ ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረችውን የታላቁን ልጅዋን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፥ ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አለበሰችው፤
“ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።”
— ገላትያ 3፥27
“የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፤”
— ቆላስይስ 3፥10
➠ያዕቆብም ወደ አባቱም ገብቶ አባቴ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ፥ አንተ ማን ነህ? አለ።
¹⁹ ያዕቆብም አባቱን አለው፦ የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ አለው
➠ ይህም ኢየሱስ በኩር ሆኖ እግዚአብሔር የዘዘውን በማድረግ እኛን ለመስባረክ ወደ አብ መግባቱን ያሳየናል።
➠ “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤”
— ሮሜ 8፥29
“በዚያም ኢየሱስ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት የሆነው፥ ስለ እኛ ቀዳሚ ሆኖ ገባ።”
— ዕብራውያን 6፥20
ቁጥር ²⁰ ይስሐቅም ልጁን፦ ልጄ ሆይ፥ እንዴት ፈጥነህ አገኘኸው? አለው። እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላክህ ወደ እኔ ስለ አቀረበው ነው አለ።
➠wow በረከታችንን የተቀበልንበትን ኢየሱስን ወደ እኛ ያቀረበው እግዚአብሔር ይባረክ ። አሜን
➠ ክብር ለአባትና ልጅ ።?
➠አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት share ማድረግ ይቻላል ።
ዘፍጥረት 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ኖኅም ስለ ጥፋት ውኃ ልጆቹንና ሚስቱን የልጆቹንም ሚስቶች ይዞ ወደ መርከብ ገባ።
➠ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔር እየፈራ 8 ነፈስ የዳኑበትን መረከብ በእምነት እንዳዘጋጀ እንደዝያው እግዚአብሔር አምላክ በእኛ አልፎ ሌሎችን የምያድንበትን divine program ያዘጋጅብን ። አሜን
??????????
➠እንድሁም እግዚአብሔር ኖኅን ከትውልዱ መሀል ጻድቅ ፍጹምም ሰው ፣አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሞገስም ይለው ሆኖ እንዳገኘው እንድሁ ያግኙን ። ?
ጸጋ እና ሰላም ይብዛላችሁ ።
Telegram
መንፈሳዊ ቤት
“.. ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።” 1ጴጥ 5፥2
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад