ቤተ-ግጥም እና ፍቅር

Description
ግጥም '''ስሜቶች ከተደበቁበት ወረቀት ላይ ሰፍረዉ እልፍ ትዝታዎች ከተበተኑበት ተሰብስበዉ የሚቀመጡበት የጸሃፊያን ሀሳብ ማረፊያ የአንባቢያን መጽናኛ ነች''።
በዚ ቻናል @betagitim
ግጥሞች??
ደብዳቤዎች✍️? ያገኛሉ።
ሃሳብ እና አስተያየቶን በዚ ???
ያናግሩን @dawit_wegayew
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

2 months, 1 week ago

እበጂልኝ(ቁ.2)

በፍቅርሽ ላብድ ነው
ብዬ ስጠይቅሽ
እስቲ አብደህ አሳየኝ
ያለው አንደበትሽ
ህሊናሽ ሲደማ
ሲቀጣሽ ምላስሽ
እኔ ተመለስኩኝ
አንቺ የእዉነት አበድሽ

መቼም ማንነቴ
ላንቺ መሥዋዕት ነው
ደግሜ ለፍቅርሽ
ነፃነቴን ልጣው
ልውጣልሽ ከእብደቴ
ከዛ ነፃ ዐለም
አንቺን ሚመልስሽ
ከኔ ሌላ የለም

ማበድሽ እንደኔ
አይደል ለነፃነት
ሠበብሽ እኔው ነኝ
መሆኔ መሥዋዕት

መዳኑን የሚሠጥ
ፈጣሪ ነውና
ልምበርከክ በፊቱ
ልበል ደፋ ቀና
ምህረቱን ሠጥቶን
ካየሁሽ በጤና
አንድ ላይ እንሁን
እሺ በይኝና

ቻፒ

❤️?

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @betagitim         

2 months, 1 week ago

እበጂልኝ
ፍቅርሽ ክፉኛ ቢቀጣኝ
አንደበቴ ታስሮ
መናገር ቢያቅተኝ
መፍትሔ ፈልጌ
ደፍሬሽ መጣሁኝ።

ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ
አፌ ኩልትፍ ኩልትፍ
ላብድ ነዉ በፍቅርሽ
ብዬ ብጠይቅሽ
እስቲ አብደህ አሳየኝ
ነበረ ምላሽሽ

ፍቅርሽ አጃጅሎኝ
እብደትን ሞከርኩት
ፀጉሬን አሳድጌ
ልብሴን ቀዳደድኩት
ወጣሁኝ ጎዳና
ብርዱን ተላመድኩት

ለካስ እብደት ውስጥ
ጥልቅ የሆነ ሚስጥር
የራስ ነፃ ዓለም
ጭንቀት የሌለበት
ፍቅርሽን ረስቼ
እብደት ተመችቶኝ
በዛው ቀጠልኩበት

ምን ይሆን ምላሽሽ
እንዲ ስሆን አይተሽ
መሥዋት መሆኔን
እንደፍላጐትሽ

ፀፀቱን ካልቻልሽው
እየነሳሽ ጤና
አንድ ላይ እንሁን
አንቺም እበጂና።

ቻፒ

❤️?

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @betagitim         


?

2 months, 1 week ago

#ተሽጦ_ያተረፈ
።።።።
አንቺማ
ሰራሁለት እያልሽ÷ ለፍፈሽ ላገሩ
ከድሮ ዝነጣው
ከድሮ ማማሩ
አፋታሁት ብለሽ÷ ቸረቸርሽ ጉራሽን
ምን እንደተሰራሽ÷ አታውቂም ጉድሽን!
።።።።።።
በእሷእጅ መዳሰስ÷ ሸይጣን ጋር መደነስ!
ከ'ሷጋር ማስቀደስ÷ ጠንቋይ ደጃፍ መድረስ
እሷ ላይ መጠምጠም÷ በአላህ መረገም
ተብሎ እንኳ ባገር
እንደ ቀላል ነገር
ይሁዳ መሆንሽ÷ አንድም ሰው ሳይጠፋው
በዚያ ውብ ከንፈርሽ
ተስሞ ለመሸጥ÷ የበዛው ወረፋው
ለምን ይመስልሻል?
አንዳንዱባርነት÷ ከነፃነት ሲሻል
የታሰረ ባርያ፥ መሲሁን ይሸሻል
።።።።።።
ባንቺ የተሳመ
እየተቋደሰ÷ ከእንቡጥሽ ውብ ለዛ
እየተካፈለ ከልዩ መኣዛ
በነገድሽው ማግስት÷ ይህችን አለም ገዛ!
በይጉድሽን ስሚ!
«አለምእንደሆነ
ከንፈር አምላኪ ነው÷ ለአሻራሽ ይጋፋል
ባንቺ የተሸጠ÷ አንቺ ላይ ያተርፋል»

---- // ----
ገጣሚ፦ ናትናኤል ጌቱ
?

❤️?

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
jᵒⁱⁿ⇝ @betagitim   
@betagitim      


?

2 months, 2 weeks ago

ተነጋግረን እንግባባ!

ንጉስ የሆንክ እስኪመስለኝ
ከበታችህ ተቀምጬ፤
አንዳች ነገር እስክትለኝ
በዝምታህ ቃል ተውጬ።

ይሁን መታገስ ነው ጥበብ
ብዬ ምንም ብችልህ፤
አስታውስ እኔ ሚስትህ እንጂ
ሴት አሽከርህ አይደለሁም!

ለቃላትህ መደንገጤን መታዘዜን
እንዲሁ አይተህ፤
ፍቅርን ሰቶ እንደመቀበል በዝምታ
እኔን ቀጥተህ!

አትቀጥልም አልቀጥልም
ይሄን ነገር እንድታውቀው፤
አዋቂ ነን አትዘንጋ
ችግር ካለም ተናገረው!

ግና እንደ ልጅ አታኩርፈኝ
አትገላምጠኝ ዝም ብለህ፤
ያልፋል ብዬ ታገስኩ እንጂ
ትዕግስት አለኝ ከተረሳህ!

ጥሎ መሄድ ላያቅተኝ እባክህን
አትፈትነኝ፤
ተነጋግረን እንግባባ በዝምታህ
አታርቀኝ!

Kiya
@zemenenbegetem
@zemenenbegetem

2 months, 2 weeks ago

የተቀነጨበ

ጨዋታ ከሳቅሽ
ከለዛ አንደበትሽ ተደማምሮ ሳለ
ከተፈጥሮሽ እንጂ ከልብሽ ምን አለ?
.
.
.
እንጃልን እኛማ
ላወጋልን ሁሉ
ለሳቀልን ሁሉ ሞትን ካልንማ።

ዮኒ
     ኣታን

@betagitim
@betagitim

2 months, 2 weeks ago

ከእለታት ባንቺ ቀን
°°°°°°°°°°°°°°°°°
ውል ለሌለው ጀንበር ለአሰመሳይ ጨረቃ
የኔ እውነት እንዲ ነው አልወድሽም በቃ
ጠብቄሽ ንቀሽኝ መጣው ስትይ ጠፋሽ
ጠፋች ብዬ ሳምን በየት በኩል መጣሽ
ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ
የለሽም ነበረ አለሁ ባልሽበት ቤት ጠርተሽኝ ስነቃ
የኔ እውነት እንዲ ነው አላምንሽም በቃ
መገን አፈጣጠር እረ ጉድ ልቦና
እያነሱ መጣል ላንቺ እውቀት ነውና
አልከስሽም እንጂ ላበጀሽ ከኔ ጎን
ገብቶሽማ ይሆናል ህመሜ አንድ ሰሞን
በሚል ቁንጽል ሲቃ ናፍቆት እየሸመንኩ
ከልብሽ ተጥዬ ስንት አመታትን ኖርኩ
ዘመም ወለም ያለው የትዝታችን ቀን
መምጣት መሄድ 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን
መራቅ መቅረብ 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን
መውደድ መጥላት 'ሚሉት ትርጉም እየሰጠን
እንደ ማምሻ ጸሐይ እንደ ጠዋት ኮኮብ
ለየቅል ለመብላት ምን ያደርጋል መሶብ
አብሮነት ያለበት ጀንበር ብናነጋ
መጣመር ያለበት ለሊት ብንዘረጋ
ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ
ትዝታሽ ነው ቀሪው ከእንቅልፌ ስነቃ
የኔ እውነት እንዲ ነው አልረሳሽም በቃ
በመናፈቅ ጸሎት ጠዋቴን ጀምሬ
በትዝታ መዝሙር እለቴን ቀምሬ
ከመራራቅ መሶብ እንድኖር ስበላ
አንቺ እንደው ምንድነሽ የምትይኝ ችላ
ርሀብ ያለበት መጥገብን ጠግቤ
ተመስገን እንድለው እግዜር ይጠብቃል እኔ አንቺን ተርቤ
አይ እግዜር ምስኪኑ
ፍቅር መሳይ አንቺን ከልቤ ላይ ተክሎ
መኖር ይከጅላል አንዱ ፍቅር ተብሎ
አዬ እግዚያብሔር ደጉ
ስለሷ ለመሞት እያጓጓ ልቤ
እንድኖር ያዘኛል መሞቱን አስቤ
አይ እግዜአብሔር ቸሩ
እሷን በሚባርክ የዋህ ነብሴ መሀል
መንግስትህን መውረስ ለኔ ምን ያደርጋል
እያልኩኝ ስሞግት
እያልኩኝ ስሟገት
የተራራቅን እለት
ሴጣን እስኪቀና በለበስኩት ድፍረት
ይኸው እድሜ ለአንቺ እግዜርም 'ረገመኝ
እሱን እየከዳው ለአመልክሽ አማረኝ
ውል ለሌለው ጀንበር ለአስመሳይ ጨረቃ
የኔ እውነት እንዲ ነው አላምንሽም በቃ
ዱልዱም ስንኩል ብዕር ላይጽፍሽ እያወኩ
ግጥም አይሉት ርሐብ ልጽፍልሽ ጀመርኩ
ከዚ በላይ ያለው እያንዳንዱ መስመር
ነበር ነበር ያለው ነበርነት ነበር
በነበርነት ውስጥ ያለው ቀጭን ሲቃ
አንድ አይነት እውነት ነው አልረሳሽም በቃ!

✍? @betagitim
? @betagitim

5 months, 1 week ago

?
እየሰማኋት ነው....
ከመስኮቴ ማዶ ወፍ ትዘምራለች ፣
(ደግሞም አያታለሁ...)
ባፏ ስንጥር ይዛ ትመላለሳለች ።
(የሞተ ቅጠል ላይ....)
የወደቀ ዛፍ ላይ ጎጆ ትሰራለች ፣
(በመዝሙሯ መሀል...)
ለደካማ ጎኔ....
(ለተስፋ ቢስ እኔ)
ምስጢር ትነግራለች።
እንዲህ ትለኛለች....
(እንዲህ ትለኛለች...)
?
<< በምድረ በዳ ማቆጥቆጥ.....
በደረቅ መሬት መለምለም ፣
(በድንጋይ አልጋ መተኛት)
በሾህ ፍራሽ ላይ ማለም !!

(''ከበደኝ'' ብለህ....)
''ስፍራ አጣሁ '' ብለህ...
ምኞትህ ባዶ ከሚሆን ፣
(''በድን ነው '' ባሉት ስር መኖር...)
''አይሆንም '' 'ካሉት ላይ መሆን...!
ተማር ከኔ....
(ውሰድ ከኔ...)
ሁን እንደኔ።>>

?
<<(ግርምም አይልህም ወይ?!...)
ነፍስ የለሽ እበት ስር ትል ተፈለፈለ ፣
መቃብር አፈር ላይ አበባ በቀለ ፣
(በሞት ቀጭን ክሮች መኖር ተቀጠለ ።)

[
ሞት ህይወትን ሰራ ፣
ጨለማው አበራ ።
]
አትማርም ከዚህ?!
አታየኝም እኔን......?!
ሙት ላይ ምለመልም ተስፈኛ መሆኔን!
በገረጀፈው ላይ እራሴን ማደሴ ፣
(የወደቀ ዛፍ ላይ ጎጆ መቀለሴ...)
ትርጉም አይሰጥህም?
(ምንም አይመስልህም?)
እባክህ ስማኝ!
(ስማኝ እባክህ...)
ምን የሚሉት ነው ልብህ መድከሙ?!
ምን አስጨነቀህ ሌሎች ባይቆሙ?!
''አልበራም'' አትበል ስለ ጨለሙ...!
ውድቀት አትፍራ ስለ ወደቁ ፣
''አልነቃም'' አትበል ሌሎች ባይነቁ ።
የከሳሰሩትን....
(ባዶ የቀሩትን)
ምሳሌ አታርጋቸው ፣
ስላንተ አይነግርህም....
መውደቅ መክሰራቸው!
(አንተም ሌላ ሰው ነህ....)
ሌሎች ሌላ ናቸው ።
''አትችልም'' አይበልህ-- አለመቻላቸው ፣
''አታልፍም'' አይበልህ -- አለማለፋቸው ፣
[
''ስላላለፉ አላልፍም'' ብለህ....
''አልቻሉምና አልችልም'' ብለህ...
(ተስፋህን ገድለህ!)
]
ውብ ህልሞችህን....
ባጭር ከመንገድ አታስቀራቸው ፣
ልብና እግርህን አታስንፋቸው ፣
የወደቁትን ድልድይ አርጋቸው!
(ያላለፉትን እለፍባቸው ።)
ተማር ከኔ....
(ውሰድ ከኔ...)
ሁን እንደ`ኔ።>>..........

..............Telegram................
? @betagitim
? @betagitim
? @betagitim

5 months, 2 weeks ago

የምርቃና ግፉ !

( በረከት በላይነህ )

..

የሙዚቃ ሊቁ..
ሙዚቃ ቀማሚው ዜማ እየቀመረ፤
ጠባቧ እስቱዲዮ ጫት ሞልቷት ነበረ ።

..

ሳተናው ነጋዴ ትርፉን እያሰላ ፥
ሊቅም ቁርሱን በላ።

..

ሹማምንቶቻችን ፥..
ገንቢ አፍራሾቻችን ዕቅዱን ሲፅፉ ፤
በትዕዛዝ ያደገ አወዳይ ቀጠፉ።

..

ጎረምሳው አፍቃሪሽ ጫት በዱቤ ቅሞ ፤
ደብዳቤ ፃፈልሽ...
ከገራባ መሐል ምርቅን ቃላት ለቅሞ !!

..

እናስ!

መሪ ከተከታይ ፤
ፍትሕ ከተበዳይ፤
ጥበብ ከአድናቂው ፤
ምላሽ ከጠያቂው ፤
የነቃ ከእውኑ ፤
የተኛ ከሕልሙ ፤
ውበት ከቀለሙ ፤
እኮ በምን ስሌት ፣ እንደምን ይስማማ ?
ሰጪና ተቀባይ እኩል አልቃሙማ !!!

?
@betagitim
@betagitim

5 months, 2 weeks ago

?
ትላንት ላይ ቁሜ ራሴን እያየዉት
ልቤ ድፍን ሁኖ ትላንት ላይ የቆምኩት
በእርግጥ በህይወት ኑሬ ሁሉን እንኳን አየዉ
ራሴን ያጣዉት ነበር እንዳልሺኝ ያኔ ወድሃለዉ።
?

✍️ዳዊት

@betagitim
@betagitim

5 months, 2 weeks ago

ሲፈቀር የሚባል...
,
.
.
"ፈገግ ስትዪ...
ጥርስሽ ምስራቅ ሆነኝ ፣ የፀሐይ መውጫ በር
ከሳቅሽ ሰማይ ላይ ...
ንጋቴን አያለሁ ፣ ተሰቅላ እንደጀንበር።
አንቺ ስትስቂ...
የጨረቃ ገላ ፣ እስኪያልቅ ይሸረፋል
"ሙሉ"
"ግማሽ"
"ሩብ"
እያለ ይጠፋል
ኮከብ እንደ ቅጠል ፣ እግሬ ስር ይረግፋል።"
ብዬሽም አልነበር?
..................................
"ስታኮርፊ ደሞ
ነፍስሽ ምእራብ ነች ፣ መውጫ ለጨለማ
ከኩርፊያሽ ሰማይ ላይ...
ምሽቴን አያለሁ ፣ ንጋቴን ስቀማ።
አንቺ ስታኮርፊ...
ሳቅሽ ሚያደርቃቸው ፣
"ኮከብ ነን" ባይ ሁላ ፣ ይድናል ከመርገፍ
ጨረቃም ሙሉ ነች...
ዳግም ስትስቂ አይታ ፣ ገላዋ እስኪሸረፍ
እስከዚያው ድረስ ግን....
ምን ጨለማ ቢገዝፍ፣
ትንሽ ብርሀንን ፣ አይችልም ማሸነፍ!!"
ብዬሽም አልነበር?
...................................
"ስትስሚኝ ደግሞ...
መለኮት ከንፈርሽ ፣ ከንፈሬን ሲያጠምቀው
ምኔ እንደተነካ ፣ሳይገባኝ ሳላውቀው
ከገነት ደጃፍ ነው ፣ ደርሼ ምወድቀው።
ሲኦል ከቆመ ነፍስ ፣ ገነት የወደቀ አይደል የሚፀድቀው!!?"
ብዬሽም አልነበር?
ግን በቃ አትመኚኝ!!
ይሄን ሁሉ ያልሁሽ...
ስለጠፋብኝ ነው ፣ ልልሽ ያልሁት ነገር!!!
.....................................
አሁን ግን የምልሽ...
"ልቤና አንደበቴ ፣ አይተዋወቅም
አፍቃሪና እውነት....
ሩቅ ለ ሩቅ ናቸው!
ሰማይ ከምድር ላይ ፣ ያን ያህል አይርቅም
ሳፈቅርሽ እንዲህ ነኝ...
የምልሽ ሲጠፋኝ ፣ ያልሁትን አላውቅም!!!
ግን አፈቅርሻለሁ።"
እያልሁሽ አልነበር?
የማይባል የለም! ፣ ይባላል ሲፈቀር!!!!

@betagitim
@betagitim

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago