Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Sheger Press️️

Description
Official channel of sheger press

If you want to give a suggestion or comment, contact us 👉 @birukepromo
Advertising
We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 3 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 4 days, 13 hours ago

2 days, 19 hours ago
**የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት …

**የአዉሮፓ ህብረት ፤ "የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር" ሲል ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ አጠበቀ

የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ መክፈል አለባቸውም ተብሏል**

የአዉሮፓ ህብረት ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለአመታት በህብረቱ አባል ሀገራት ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የኖሩ ዜጎቹን ለመመለስ ቸልተኛ ነበር ሲል ወቅሷል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያዊያን ቪዛ የሚያገኙበትን መንገድ ማጥበቁን አስታዉቋል።

ዳጉ ጆርናል ከአሶሴትድ ፕረስ ዘገባ እንደተመለከተው ፤ የአውሮፓ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ ለመስራት የሚፈጅባቸዉን ጊዜ በሶስት እጥፍ መጨመሩን ነዉ።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊያን በ15 ቀናት ዉስጥ ቪዛ ያገኙ ነበር የተባለ ሲሆን በዚሁ ዉሳኔ መሰረት ወደ 45 ቀናት ከፍ እንዲል ተደርጓል። ይህም የኢትዮጵያ መንግስትን በህገወጥ መንገድ በአዉሮፓ ይኖራሉ የተባሉ ዜጎችን እንዲመልስ ጫና ለመፍጠር ነዉ ብሏል ዘገባው።

ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከታዘዙ ሶስት ሰዎች መካከልም አንዱ ብቻ መመለሱ በህብረቱ የመንግስትን ተባባሪነት ጎድሎታል የሚለዉን ክስ ለማሳያነት ቀርቧል። ይህም በፈቃዳቸዉም ይሆን ካለፍላጎታቸዉ ህገወጦችን ለመመለስ የሚደረገዉን ሂደት አጓቶታል ብሏል።

በዚህ ዉሳኔ መሰረትም የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና ባለስልጣናት አሁን ለጉዞ ቪዛ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የቪዛ ቀናቸዉም ቢያልፍ የአዉሮፓ ምድርን ለቅቀዉ እንደማይወጡ ህብረቱ ገልጿል።

@sheger_press
@sheger_press

2 days, 23 hours ago
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን …

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ።

የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል።

በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። 

መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።

@sheger_press

4 days, 4 hours ago

መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር አለበት።

በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም።ውጤቱ መተግበር ይኖርበታል።

እንደ ሀገር የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም ላይ ነው።ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል።ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው  እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም>>

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት የተወሰደ

@sheger_press
@sheger_press

1 week, 3 days ago
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ …

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን እንደማይፈታ የገለጹት የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ÷ ታሪካዊ አጋጣሚ በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም ትጥቅ አንግበው እየታገሉ ያሉ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው÷ አሁንም ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያመቻቻቸው መድረኮችም ማንኛውም ሰው በነጻነት የሚሳተፍባቸው መሆናቸውን አስረድተው÷ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

@sheger_press
@sheger_press

1 week, 4 days ago
1 week, 4 days ago

**ቀሲስ በላይ መኮንን ከሰሞኑ "ተሳትፈዉበታል" በተባለው የማጭበርበር ድርጊት የተነሳ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተሰማ

👉🏼 ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በሀሰተኛ ሰነድ ልጭበረበር ነበር ያለ ሲሆን "ታማኝ" በተባሉ ሰዎች የተፈጸመው ሙከራ ወደፊት "በባለስልጣናት ላለመሞከሩ ማረጋገጫ ስለሌለኝ ነዉም" ብሏል**
ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል መባላቸውን ዳጉ ጆርናል ተከታታይ መረጃዎችን አድርሷል። ይህንኑ ተከትሎ ቀሲስ በላይ የተጠረጠሩበት ድርጊት መነጋገሪያ ሆኖ የቆየ ሲሆን ዘ ሪፖርተር ደግሞ አዲስ መረጃ አጋርቷል።

ቀሲስ በላይ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመገኘት ሀሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከህብረቱ የሂሳብ ቁጥር ለግንባታ እና ሌሎች ስራዎች ክፍያ በሚል 6 ሚሊዮን 50 ሺህ ዶላር ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

ስማቸዉ ያልተጠቀሰ የዘ ሪፖርተር ምንጭ ታድያ ይህንን ድርጊት ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት የዉጪ ምንዛሬ የሚያስቀምጥበትን የባንክ ሂሳብ ከኢትዮጵያ ዉጪ ለማድረግ እንዳሰበ ተናግረዋል። ህብረቱ ለሶስተኛ ጊዜ በተጭበረበረ ሰነድ ከባንክ ሂሳቡ ሊወጣ የነበረ ገንዘብን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ያስታወቀ ቢሆንም "እምነትና እዉቅና" ባላቸዉ ሰዎች የተፈጸመዉ ተግባር ወደፊት በባለስልጣናት ለላመሞከሩ መተማመኛ የለኝም በማለቱ መሆኑን ዘገባው አመላክቷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በአፍሪካ ህብረት ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ያለዉ ቅርንጫፉ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተከፈተ ሲሆን በዋነኛነት የአፍሪካ ሒሳቦችን በተለይ ለማስተዳደር ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከልን ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የዉጭ ምንዛሪ ክምችት ያላቸዉ አካውንቶችን በማካተት ቁጥጥር ያደርጋል።

ቀሲስ በላይ በወቅቱ ሀሰተኛ የህብረቱ ማህተም ያረፈባቸዉን ወረቀቶች በመያዝ ለግባታ እና የማሽነሪዎች አቅርቦት በሚል ክፍያዉን መጠየቃቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። ክፍያዉ ከመፈጸሙ በፊት ወደ ህብረቱ የስልክ ጥሪ ያደረጉት የባንኩ ሰራኞች የክፍያዉን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ሲሞክሩ የህብረቱ የፋይናንስ ክፍል የማያዉቀዉ መሆኑን እና ክፍያዉ እንዲታገድ ህብረቱ መጠየቁ መረጃዉ ይደርሳቸዋል።

ህብረቱ ይህንን ተከትሎም ግለሰቡ እንዲያዙለት ጠይቆ ቀሲስ በላይ በህብረቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ዉለዉ በፌዴራል ፖሊስ ተላልፈዉ መሰጠታቸዉን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ ይታወሳል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የፋይናንሺያል አስተዳደር ዲቪዥን ኃላፊ ማዳሊስቶ ሙኡሶ ሎሌም ወዲያውኑ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ክፍል ደብዳቤ ጽፈዋል ብሏል ዘገባዉ። ኃላፊዉ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከአፍሪካ ህብረት ሒሳብ ወደ አራት ግለሰቦች ሒሳብ እንዲዘዋወር የጠየቁ ሰነዶች ሁሉም ፎርጂድ ናቸው ብለዋል በጻፉት ደብዳቤ።

ከዚህ ክስተት በኋላ የህብረቱ እና የባንኩ  ሰራተኞች ለፖሊስ ቃላቸዉን መስጠታቸው በዘገባዉ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ለዜና ምንጩ ከሰጡት ቃል ዳጉ ጆርናል እንደተመለከተው "በመሠረቱ ጥሬ ገንዘብ በውጭ ምንዛሪ ብቻ ሊሰጥ አይችልም ። ለማጭበርበር የሞከረዉም ግለሰብ መጥቶ መጠኑን በጥሬ ገንዘብ ሲጠይቅ ይህን እንኳን አያውቅም ነበር ማለታቸዉን ነዉ።

አክለዉም " ግለሰቡ እዚህ አገር የዶላር አካውንት ከሌለው ገንዘቡ ቢተላለፍም እንኳ የትም ሊደርስ አይችልም።  አጭበርባሪዎች በየቀኑ ወደ ባንካችን ይመጣሉ።  ባንክ ስለምንሰራ የተለመደ ነው።  እኛ ግን ሁልጊዜ ከመሳካታቸው በፊት እናጣራለን።  ለፍርድም እየወሰድናቸው ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞቹን ሒሳቦች የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት።  ያንንን እያደረግን ነው።  የአፍሪካ ህብረትም እስካሁን ድረስ ቀጥተኛ ቅሬታ አላቀረበብንም" ሲሉ አቶ አቤ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

"ማጭበርበር ሲያጋጥም ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው" ያሉት ስማቸው ያልተጠቀሱት የዜና ወኪሉ የአፍሪካ ህብረት ምንጭ" አሁን ማጭበርበሩ በተከበሩ ሰዎች እየተሞከረ ስለሆነ ተጨንቀናል" ብለዋል። ይህ ድርጊት  "ባለስልጣናት አንድ ቀን ተመሳሳይ ነገር ላለማድረጋቸዉ ምንም አይነት ዋስትና የለንም" ያሉም ሲሆን  "እምነት እያጣን ነው" ብለዋል።

ባለስልጣኑ አክለዉም በዚህ የተነሳ "ኢትዮጵያ ውስጥ ለደሞዝ አነስተኛ መጠን ያለው ፎሬክስ(የዉጪ ምንዛሪ ) ለመያዝ ወስነናል ፤ የድርጅቱን ገንዘብ ከኢትዮጵያ ውጭ ማቆየት እንድናስብ ያስገድደናል" ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣን መናገራቸውን ዳጉ ጆርና ከዘገባው ተመልክቷል።

Via The Reporter

@sheger_press
@sheger_press

2 months, 1 week ago

መረጃ‼️

በአማራ ክልል በምሥራቅ፣ ምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች በመንግሥት ኃይሎችና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭቶች እንደቀጠሉ ናቸው።

በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር እንዲኹም በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በኹለቱ ወገኖች መካከል ግጭቶች መካሄዳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

በተለይ በደቡብ ወሎ ዞን፣ በአምባሰልና ውጫሌ ከተሞች አካባቢ በሚካሄደው ግጭት ሳቢያ፣ በደሴ እና ወልድያ ከተሞች መካከል የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መስተጓጎሉን ምንጮች ገልጸዋል።(wazema)

@sheger_press
@sheger_press

2 months, 1 week ago

ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኙ መጠለያዎች ከተጠለሉ ተፈናቃዮች መካከል የተወሰኑት ዕሁድ'ለት ወደቀድሞ ቀያቸው ምሥራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች መመለስ እንደጀመሩ መስማቱን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

@sheger_press
@sheger_press

2 months, 1 week ago

መረጃ‼️

ትናንት ከመኮይ ወደ ደብረብርሀን ሲመጡ የነበሩ ወጣቶች መታገታቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።

አሁን ላይ መለቀቃቸው ምንጮች አድርሰውናል።

በሌላ በኩልደግሞ ‼️
ከአዲስ አበባ ወደ ወልድያ  ሲጓዙ የነበሩ ተሳፋሪዎችም መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን 

አንዳንዶቹ ታጋቾቹ ማምለጣቸው የተሰማ ሲሆን ቀሪዎቹ እስካሁን ያሉበት አልታወቀም።

@sheger_press
@sheger_press

2 months, 2 weeks ago

አዲስ አበባ‼️
‹‹በትምህርት ቤቶች ውስጥ የኩፍኝ ምልክት ታይቷል የሚለዉ መረጃ የተሳሳተ ነው››-   የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ‼️

አሀዱ በደረሰዉ ጥቆማ ትምህርት ቤቶች ላይ ኩፍኝ መሰል ምልክቶች እየታዩ በመሆኑ ስር የሰደደ ችግር ሳይከሰት ኩፍኝ መሆኑን አረጋግጦ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ እንዲሰጠዉ ይጠየቅልን የሚል ሀሳብ ቀርቦለት ነበር፡፡

አሃዱም በትምህርት ቤቶች ያሉ ህፃናት ንክኪ በበዛበት ሁኔታ ውስጥ የሚውሉ ከመሆኑ እና ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ጉዳዩ ተጣርቶ መፍትሄ እንዲሰጠዉ ጥቆማዉን ይዞ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮን አነጋግሯል፡፡

በተገኘው ምላሽም ጥቆማዉ በደረሰበት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ላይ ማጣራት ተደርጎ ክስተቱ እንደሌለ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ነገር ግን መሰል ችግሮች ከታዩ ህብረተሰቡ ጥቆማዎችን እንዲሰጥም ቢሮው አሳስቧል፡፡

@sheger_press
@sheger_press

We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 3 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 4 days, 13 hours ago