The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.
Last updated 1 week, 4 days ago
🌐 https://ipapkorn.github.io
Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️
Bots: https://t.me/iPapkornBots/2
Last updated 1 day, 18 hours ago
Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.
Last updated 1 week, 6 days ago
በሶማሊያ የአፍሪካ ሽግግር ተልዕኮ (ኤቲኤምኤስ) ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ሰላም እና ደህንነት ላደረጉት የላቀ አስተዋፅኦ ተሸላሚ ሆነዋል።
በቅርቡ የስራ ጉብኝታቸውን ያጠናቀቁት ወታደሮቹ አልሸባብን በመዋጋት እና በደቡብ ምእራብ ግዛት የሚገኙ የአካባቢውን ማህበረሰቦችን በመጠበቅ ለሰሩት ስራ ምስጋና ተችሯቸዋል ።
ማክሰኞ ዕለት በባይዶዋ የተካሄደውን የሜዳሊያ ሽልማት ሥነ ሥርዓት የመሩት የሽግግር ተልእኮው ወታደራዊ ዋና አዛዥሜጀር ጀነራል ክንዱ ገዙ ወታደሮቹ ላሳዩት ድፍረት፣ ሙያዊ ብቃት እና ከራስ ወዳድነት ነፃ ለሆነ አገልግሎት አመስግነዋል።
"እነዚህን የሚገባቹን የክብር ሜዳሊያዎች በምትቀበሉበት ወቅት ያደረጋችሁትን አስደናቂ ስኬት እና የማይናወጥ ቁርጠኝነት ለማክበር ተሰብስበናል። ይህ ሥነ ሥርዓት በሶማሊያ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ያላችሁን ድፍረት፣ ስነ ምግባር እና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው" ብለዋል።
#ግማሽ ክፍለ ዘመን እንቅልፍ ያላዩ ዓይኖች
ስምንት መቶ ሰባት ዓመታትን ወደኋላ ስንመለስ “ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን” “የአእላፍ ቅዱሳን አባት” በመባል የሚታወቁት ታላቁ ጻድቅ የተወለዱበት ዓመት 1210 ዓ.ም ላይ እንገኛለን፡፡ ጎንደር ስማዳ ዳሕና ሚካኤል የተወለዱት አባት ገና በጉብዝናቸው ወራት በ30 ዓመታቸው ዓለምና አምሮቷን ንቀው ወደ ትግራይ “ደብረ ዳህምሞ” የአባታችን አቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ በመግባት ከጻድቁ አምስተኛ የቆብ ልጅ አባ ዮሐኒ ካልዕ ደቀ መዝሙር ሆኑ፡፡ በደብረ ዳሞም ቀኑን ለመነኮሳት በመታዘዝ፣ በመፍጨትና ውሃ በመቅዳት ሌሊቱን ደግሞ እኩሉን በጸሎት እኩሉን ቅዱሳት መጻሕፍትን በመገልበጥ ያሳልፉት ነበር፡፡ ከሰባት ዓመታት ተጋድሎ በኋላም በ37 ዓመታቸው ምንኩስና ተሰጣቸው፡፡
በዚው ዓመትም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብዙ ተአምራትና አገልግሎት የምትሰራበት ስፍራ እግዚአብሔር አዘጋጅቶልሀልና ወደ ወሎ ሐይቅ ሒድ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ደብረ ዳሞና ሐይቅ እስጢፋኖስ እጅግ የተራራቁ ቢሆኑም መልአኩ ነጥቆ የተፈቀደላቸው ስፍራ ላይ አደረሳቸው፡፡ በዚም ለሰባት ዓመታት ከሐይቁ በስተሰሜን በሚገኘው የጴጥሮስ ወጳውሎስ ገዳም በማስተማርና በማገልገል ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በእነዚህ ዓመታት ሌሊቱን በሐይቁ ውስጥ ገብተው በመጸለይ ያሰዳልፉ ነበር፡፡ በኋላም ቅድስናቸውን የተመለከቱ አበው በብዙ ትግል አበምኔት አደርገው ሾሟቸው፡፡ ይህም የታላቁ ስራቸው መጀመሪያ ሆነ፡፡
አባታችን አቡነ ኢየሱስ ሞአ ከደሴ ከተማ በ30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም 800 ደቀ መዛሙርትን በመሰብሰብና በማስተማር ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት ያፈረሰቻትን ቤተ ክርስቲያን ይገነቡ ጀመር፡፡ ታላላቅ መጻሕፍትን በማሰባሰብ የመገልበጥና የማባዛት ስራ ያሰሩ ሲሆን ደቀ መዛሙርቶቻቸውንም በማስተማር በመላው ሀገሪቱ ለሐዋርያዊ አገልግሎት አሰማርተው ቃለ እግዚአብሔር እንዲስፋፋ፣ ትምህርት ወንጌል እንዲሰርጽ አድርገዋል፡፡ ለ45 ዓመታት በዘለቀው የገዳሙ አበምኔትነት አገልግሎታቸው አይናቸው ከእንቅልፍ ጋር ተገናኝቶ እንደማያውቅ ገድላቸው ያስረዳል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ይህን ተጋድሏቸውን ለፍሬ አድርጎላቸው ታላላቅ ጻድቃን አባቶችን አፍርተዋል፡፡
ከእነዚህም መካከል የደብረ ሊባኖስ ኢትዮጵያዊው ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ አባ ኂሩተ አምላክ ዘጣና ሐይቅ፣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ አባ ዘኢየሱስ፣ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ አባ አሮን ዘደብረ ዳሬት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንጉሱ አፄ ይኩኖ አምላክንም በትምህርተ ሃይማኖት አንጸው ለክብር ያበቋቸው እርሳቸው ናቸው፡፡ የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስም ጌታችን ወርዶ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ በተወለዱ በ82 ዓመታቸው በ1292 ዓ.ም ሕዳር 26 ቀን ወደ ማያልፈው ክብር ጌታችን ጠርቷቸዋል፡፡ አስገራሚው ነገር አበምኔት ከመሆናቸው በፊት ለሰባት ዓመታት በገዳሙ አስተዳዳሪነት ደግሞ ለ45 ዓመታት በጠቅላላው ለ52 ዓመታት በቆየው ተጋድሏቸው እንቅልፍ የሚባል በአይናቸው አልዞረም፡፡
ገዳማውያን ዓለምንና አምሮቷን ትተው ሲመንኑ የበለጠውን ክብር ሽተው፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ሰፊ ጊዜ ለማሳለፍ ፈልገው እንጂ ተሞኝተው አይደለም፡፡ መስቀሉን ተሸክመው ሲከተሉት ዓለም እንደ ሞኝነት ይቆጥርባቸዋል፡፡ በረከታቸው ግን ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ድንቅ ይሰራል፡፡ አሁን በዘመናችን ያሉትን ገዳማትና መናንያን ስንደግፍም ይ ቃል ኪዳንና በረከት ከኛ ጋር ይሆናል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
አሸነፈ‼️
መካኒኩ ሁለት ሚሊዮን ብር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ እድለኛ ሆነ
በመካኒክ ባለሙያነት የተሰማራው ወጣት ያብስራ ወርቅነህ በ29ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በ2ኛው ዕጣ የ2ሚሊየን ብር ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡
ወጣት ያብስራ የሸኖ ከተማ ነዋሪ ነው።
በአማራ ክልል በፋኖ ሀይሎች ተረሸኑ ስለተባሉት ከ30 በላይ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የፀጥታ አባላት ጉዳይ!!
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 በላይ የአካባቢው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፀጥታ አባላት በፋኖ ሀይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎችን እና የአካባቢው አስተዳደርን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።
በዞኑ ደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ከተማ ኅዳር 26/2017 ዓ.ም. ለሁለት ወራት ለመንግሥት "መረጃ እና ድጋፍ ሰጪ" በሚል ተጠርጥረው በፋኖ ሀይሎች ተይዘው የነበሩ በርካታ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት "መረሸናቸው" ታውቋል። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዋለ አለማየሁ 20 ከሚሆኑ የወረዳው ካቢኔዎቻቸው ጋር የግድያው ሰለባ መሆናቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።
መስከረም መጨረሻ በአካባቢው "ከባድ ውጊያ" መደረጉን ተከትሎ መስከረም 29/2017 ዓ.ም. ወረዳው በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር መግባቱን እና የመንግሥት ኃይሎች ወረዳውን ለቀው መውጣታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህንንም ተከትሎ "[መከላከያ] የሚሊሻ፣ የፖሊስ አባላትን እንዲሁም ካቢኔዎችን በሙሉ መስመር ላይ ነው ጥሏቸው የሄደው" ሲሉ አንድ ነዋሪ፤ 'ባልተለመደ ሁኔታ' የወረዳው አስተዳደር ከተማዋ ውስጥ መቅረቱን ገልጸዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ዓለም 20 የሚሆኑ የወረዳው የሥራ ኃላፊዎች መከላከያ ሠራዊት "ለስምሪት" አካባቢውን ለቆ ሲወጣ "ተቆርጠው" መቅረታቸውን ተናግረዋል። በፋኖ ሀይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት የአካባቢ አመራሮች "ፈረስ ቤት ሚካኤል" በተባለ የከተማው መውጫ ላይ ተወስደው መረሸናቸውን ሦስት ነዋሪዎች እና የዓይን እማኝ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ከቤተክርስቲያን ወደ ቤት በመመለስ ላይ የነበረች የ15 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ የመድፈር ጥቃት የፈፀመባት ተከሳሽና ተባባሪዉ በእስራት ተቀጡ
በሰሜን ሸዋ ዞን ጂዳ ወረዳ አይዳዳ ቀበሌ ዉስጥ ከፀሎት መልስ ወደ ቤታ በመመለስ ላይ የነበረችውን ልጅ ተከታትሎ የመድፈር ጥቃት የፈፀመዉ ግለሰብና ተባባሪዉ በእስራት መቀጣታቸዉን የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ገለፀ።
የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት የሴቶች፣የህፃናትና የህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል መርማሪ አቃቤ ህግ እንዳሻሽ ደምሰዉ እንደተናገሩት ተከሳሽ ሰቦቃ መኮንን የተባለዉ ግለሰብ ከግብረ አበሩ ደጀኔ ተፈራ ጋር በመሆን የ15 አመቷንታዳጊ በመጠልፍ አንደኛ ተከሳሽ ሰቦቃ ባዘጋጀዉ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በማስገባት አንደኛ ተከሳሽ ሰቦቃ ታዳጊዋ ላይ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት በማስረጃ መረጋገጡን ተናግረዋል ።
ሁለቱም ግለሰቦች በአንድ ቤት ዉስጥ በር ዘግተዉ መጠጥ እየጠጡ ቆይተዉ ምሽት ላይ የመድፈር ጥቃት የተፈፀመባት ታዳጊ ወደ ቤቱ ሲገባ በመጠጥ ተዳክሞ መምጣቱን የተገነዘበችዉ ተጎጂ እንቅልፍ እስኪወስደዉ ጠብቃ ከቤት አምላጣ ወደ ወላጆቻ ቤት ተጉዛ የደረሰባትን ጥቃት ለቤተሰቦቻ ማሳወቃ ተገልጿል ።ቤተሰቦቻም በነጋታዉ ልጃቸዉ ላይ የደረሰዉን ጥቃት ለፖሊስ በማሳወቃቸዉ ፖሊስ ሁለቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ካዋለ በኃላ ጥቃት የደረሰባትን ታዳጊ ለህክምና ምርመራ ወደ ጤና ጣቢያ የላካት መሆኑን ገልጸዋል።
ከጤና ጣቢያ የተገኘዉ መረጃ የመደፈር ጥቃት የደረሰባት ልጅ ክብረ ንፅህናዋን ያጣች መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን ፖሊስም የምርመራ መዝገቡን በተገኘዉ የህክምና ማስረጃ እና ሌሎች መረጃዎች በማጠናቀር ለአቃቤ ህግ ልኳል፡፡ክሱን ሲከታተል የነበረዉ የሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ሶቦቃ መኮንን በፈፀመዉ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ህዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ11 አመት እስራት ሲቀጣ ሁለተኛ ተከሳሽ ደጀኔ ተፈራ የጠለፋ ተግባር ላይ በመተባበር ወንጀል በ4 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን አቃቤ ህግ እንዳሻሽ ደምሰዉ ገልፀዋል።
ትላልቅ የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠሩ መሆናቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገለጹ፡፡
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡
በስብሰባው የምክር ቤት አባላት ለመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡
በዚህም የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይ ውስብስብ ችግሮች እንዳሉ በመጥቀስ የዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ እና እየተገነቡ ባሉ የመስኖ ፕሮጀክት ላይ ለሚስተዋሉ ችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሚኒስቴሩ ምን እየሰራ ነው ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
እንዲሁም የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች በህብረተሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየፈጠሩ መሆናቸውን አንስተው÷ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉና አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ እንዲገለጽም ጠቁመዋል፡፡
ፋና ቴሌቪዥን ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ የሰላም ስምምነት በኋላ ለመጀሪያ ጊዜ በሚባል መልኩ የኤርትራዉን ፕሬዚዳንት የሚያጣጥል ዘገባ ሰራ
ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገራቸው ብሔራዊ ቴሌቪዥን ላይ ቀርበዉ ረዘም ያለ ቃለምልልስን ሰጥተዉ ነበር።
በወቅቱ በጎረቤት ሀገራት በተለይም በኢትዮጵያ ዉስጣዊ ጉዳይ ላይ ፕሬዚደንቱ አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ስለ ህገመንግስት ፣ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሀገራቸዉ ከሶማሊያ እና ግብጽ ጋር የገባችዉ ስምምነት ኢትዮጵያን የማያሰጋ ነዉ ብለዉ አስተያየት ሰጥተዉባቸዉ ነበር።
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ሰላም ለመፍጠር የተደረጉ ሂደቶች ተቀዛቅዘዋል ተብሎ መረጃ መናፈስ ከጀመረበት አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚመስል መልኩ ታድያ በትናንትናው እለት በመንግስታዊ ሚዲያ ፋና ሚዲያ በኩል "የአስመራው መንግስት ነገር-የራሷ አሮባት" በሚል ርዕስ ፕሬዚዳንቱን የሚያጣጥል ዘገባ ተሰርቷል።
#ለድንቅ ስራ የተመረጠ እጅ፣ የተቀባ ራስ
በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ገድለ ላሊበላን የጻፉት የውቅር አቢያተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ቅርጽና አሰራር ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡፡ “በላሊበላ እጅ እኒህ አብያተ ክርስቲያናት ከምድር ልብ ወጥተው የሚሠሩበት ጊዜ ደረሰ… ምድርን ከፈጠረ ጀምሮ ተሠውሮ የነበረውን ሕንጻ እንዲገልጥ እግዚአብሔር ወዷልና።” የልዩ ጥበባዊ መገለጥ፣ የድንቅ አእምሯዊ ሀሳብ፣ የመጠቀ የስነ ሕንጻ ጥበብን የመረዳት አቅም ውጤት የሆኑት እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት እውን ለመሆናቸው የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዳለበት ይህ አገላለጽ ማሳያ ነው፡፡
ይህን መነሻ አድርገው ቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስቲያናቱን ሲወቅር የመላዕክት እገዛ እንዳለበት የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ያብራራሉ፣ አንድም እነዚህ የጥበብ ውጤቶች ልዩና የማይደገሙ ተደርገው ቢሰሩም በሰው እጅ መሰራታቸውን መቀበል ያስፈልጋል፡፡ ያም ሰው እግዚአብሔር ስራውን ሊገልጽበት ፈልጎ ይህን እውቀት በአእምሮው ያኖረለት እጁንም የባረከለት ንጉሱ ቅዱስ ላሊበላ ነው ይላሉ፡፡
ቅዱስ ላሊበላ ገድሉ በንግስና ስሙ ጠቅሶ ስራውን ሲያብራራ “ገብረ መስቀልም ልዩ ልዩ የሆኑ የብረት መሣሪያዎችን አሠራ። ለመጥረብም የተሠራ አለ። ለመፈንቀልም የተበጀ ብረት አለ። ለመፈልፈልም የተሠራ አለ። እነዚህን ቋጥኝ ድንጊያ የመቅደስ ሕንጻ የሚፈጸምባቸውን አሠራ። ገብረ መስቀልም ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምድራዊ ሐሳብን፣ ሚስቱንም ደስ ለማሰኘት ፈቃድ ቢሆንም አላሰበም። ሁሉንም በሙሉ መንፈስ ስለ እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት አሰበ እንጂ።” ይላል፡፡ መጽሐፉ ከዚህ ጋር አያይዞ በንጉሥ ላሊበላ አዛዥነት በሀገሬው ሰዎችና በመላእክት እገዛ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቱ እንደተሰሩ ይነግረናል፡፡
“ንጉሱ ሕዝቡን ሁሉ ወደ እርሱ ሰብስቦ በአብያተ ክርስቲያናቱ ሕንጻ ሥራ የምትረዱኝ ሁላችሁም የምትቀበሉትን ደሞዛችሁን ተናገሩ አላቸው፣ እግዚአብሔር እንድሠራ አዞኛልና። እናንተም በአንደበታችሁ ደመወዛችሁን እንዴት እንደምትቀበሉ ተናገሩ። በጠራቢነትም ሥራ የሚረዳ፣ ጥራቢውንም በማውጣት የሚረዳ ሁላችሁም በአንደበታችሁ ተናገሩ። እንደ አላችሁኝ እሰጣችኋለሁ” ሲልም አወጀ፡፡
ያለ ፈቃዳችን አስገደደን እንዳትሉኝ። በአጉረመረማችሁ ጊዜ ድካማችሁ ብላሽ እንዳይሆን። “ሁላቸውም ልባቸው እንዳሳሰባቸው ነገሩት። እርሱም ስጦታቸውን ሳያጓድል እንዳሉት ሰጣቸው። የአብያተ ክርስቲያናቱን ሕንጻ ሥራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ፈጸመ ድረስ ለሚፈለፍልም ሆነ ለሚጠርብ የቤተ ክርስቲያኑን ጥራቢ ለሚያወጣም ሆነ ደሞዛቸውን በጊዜው ይሠጣቸው ነበር።” ይላል ገድለ ቅዱስ ላልይበላ፡፡
ይህን ድንቅ ስፍራ መጎብኘት በተለይ በልደቱ ቀን ታሕሣስ 29 በስፍራው መገኘት ልዩ እድል ታላቅ በረከትም ነው፡፡ ይህን ልዩ ቀን ላስታ ላይ ለማሳለፍ ለምትፈልጉም ልዩ የጉዞ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
ለአረጋውያን፣ ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ምቹ ማረፊያም አዘጋጅተናል፤ ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።
የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17 ዓ.ም
የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17 ዓ.ም
የጉዞ ዋጋ ምግብን ፣ ማረፊያንና መስተንግዶን ጨምሮ :-6,500
ለበለጠ መረጃ:-0938944444
አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
የ28 ሰዎች ህይዎት የቀጠፈ የሱዳን ቦምብ ጥቃት
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 28 ሰዎች ሲሞቱ 37 ሰዎች ቆስለዋል፡፡
የደቡብ ካርቱም የድንገተኛ አደጋ ክፍል በሰጠው መግለጫ፤ በነዳጅ ማደያው ላይ በተወረወረ ቦምብ ነው አደጋው የደረሰው፡፡
ይህም የ28 ሰዎችን ህይዎት በመቅጠፍ ከ37 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ባለፈ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማስከተሉ ተነግሯል፡፡
ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የዥንዋ ዘገባ አመልክቷል።
The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.
Last updated 1 week, 4 days ago
🌐 https://ipapkorn.github.io
Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️
Bots: https://t.me/iPapkornBots/2
Last updated 1 day, 18 hours ago
Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.
Last updated 1 week, 6 days ago