የአማራ ፋኖ በጎጃም መረጃ

Description
የአማራ ፋኖ በጎጃም 💪💪💪

ይህ የአማራ ፋኖ በጎጃም የቴሌግራም ገጽ ነው።
👉 አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago

1 month, 1 week ago

**ዘመቻ ዮሃንስ በተሰዋበት የቅኔዋ ምድር ዋሸራ እና ጎንጅ ቆለላ የአብይን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በሁለተኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር በእጥፍ ድርብ ደሙን መልሰናል ጀግና ጠላቱን ተበቅሎ የወገኑን ደም ሳይደርቅ ሲመልስ እንዴት ደስ ይላል መሰላችሁ!! ውጊያችን ይቀጥላል።ጆንየ ቁመን እየሔድን የሞትህለት አላማ አይደናቀፍም ።

©ዝናቡ ልንገረው#ትግላችን_አይሸጥም_አይለወጥም‼️#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

16/05/2017 ዓ.ም**

2 months ago

ስለ ዘመድኩን በቀለ እንቅጯን ልንገራችሁ😉

ዘመድኩን በቀለ ለዘመናት የአማራን ህዝብ እንባ ለማበስ የደከመ ነው። በዚህ ትግል ወጣቶች ትግሉን እንዲቀላቀሉ እና እንዲደራጁ እንደ እሱ የለፋ የለም። በተለይም "መክት፣ አንክት ይሄን አራጅ መንጋ" በሚለው ንግግር እናውቀዋለን። የማይደራጅ የመሰለውን ህዝብ ፅኑ እምነት ኖሮት እንዲደራጅ አድርጓል፣ እንዲታግል ምክንያት ሆኗል። ሚድያ ላይ ግንባር ቀደም ነው። አንደኛ ነበር፣ነውም። ታድያ እስክንድር ነጋ አይነካብን፣ ደመቀ ዘውዱም አይነካብም ይሉ የነበሩ ሚድያዎች ዛሬም አስረስ ማረን አትንካብን ይላሉ። እነዚህ የፖለቲካ ጨቅላዎች።

ዐማራ ሆኖ ራሱ ስለዐማራ እንደዘመድኩን የጮኸ የለም [እንዲህ ስል 1000... % ደረቴን ነፍቼ ነው።

ማይነካ ሚመስለውን ባለግርማ ሞገሱን፣ ጀግናውን ብላ ብላ ተብሎ በዐማራው ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ዘመዴ ሲቃወም አንዳንድ ሚድያዎች በዘመዴ ላይ ድንጋይ ወርውረውበታል። ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ስሙን ሊያጠፋው ነው እያሉ ብዙዎች አሙት፣ ሰደበት። ዘመድኩንም እንዲህ አለ " የምወድህ የማከብርህ ደመቀ ዘውዱ ሆይ ጥያቄ አለኝ....የምሰማቸው እና የሚደርሱኝ መረጃዎች ለዐማራ ሰላም የማይሰጡ ነገሮች አሉ። በጊዜ አጥራልን። ህዝብን ማሾፍ አይችልም።" ነበር ያለው። በኋላ ግን የአፄ ቴዎድሮስ እስትንፋስ ተብሎ ይሞካሽ የነበረው፣ የዘመናችን ጀግና፣ ትንታግ እየተባለ ይዘመርለት የነበረው ደመቀ፣ ጭንብሉን አወለቀ። ኮሎኔሉም "ፋኖ ሌባ! ፋኖ የዐማራን ህዝብ አይወክልም! አብይ አህመድ እግዚአብሔር የላከለን የዘመናችን ጎበዝ ንጉሥ ነው።" አለ። ከዚ በኋላ ነበር ደመቀን ሰው የጠላው። ዘመዴ የዚህን ኮ/ል ሴራ በጠዋት ሲጀምር ትንሽ ትልቁም ሰደቡት። ግን ዘመድኩን በመረጃ፣ በማስረጃ እና በምክንያት በዝረራ አሸነፈ።

The Iron man የሚባለውን እስክንድር ነጋን ብቻውን በመረጃ ሞግቷል። እስክንድር ነጋ ሆይ ችግሮች አሉ ይባላሉ በጊዜ ውጣ እና አጥራ ሲለው እስኬው ዙሪያ ጥምጥም ሄደ። ይሄም አላዋጣው። ሆኖም ግን የእስክንድር ነጋን ሴራ ዘመዴ ብቻውን አሸንፏል።

ኮ/ል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ እስክንድር ነጋን ችግሮች ሳይባባሱ እንፍታቸው ነው ያለ መምህር ዘመድኩን በቀለ። ሁለቱም ሰዎች ግን የልባቸውን ስለሚያውቁ መቅረብ አልፈለጉም። አስረስ ማረም እንደ እስክንድር ነጋ እና ደመቀ ዘውዱ እጣፋንታው እንዳይሆን የአማራ ሪቮሊሽን ስጋት ነው።

የሰሞኑ የአስረስ አቋም እና ንግግር ስሜታዊነት ይበዛዋል። መሪ ስትሆን እኮ አቤት ወዴት ማለት አለብህ። የምትመራው ደግሞ የአማራን ህዝብ ሲሆን አስበው😎

ስለአስረስ ደግሞ የአማራ ፋኖ በጎጃም 22 ስራ አስፈፃሚ አካላት አሉ እነሱ ይዳኙት። ፋኖ ማርሸት አጠፋ ተባለ አርመው መክረው ወደ ስልጣኑ እንደመለሱት ሁሉ ጀግናውን አስረስ ማረንም የጎጃም ፋኖ ይመረምረዋል።

ዘመድኩንም ከድርጅት እኔ እበልጣለሁ የሚለውን ቅብጠት ወዲያ ጣል።

"ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ" አክሳሪ ጨዋታ ነው።

መርጋት አለነ

2 months, 2 weeks ago

*🔥#ሰበር_ዜና‼️*

ዋርካው ምሬ ወዳጆ ጥብቅ መመሪያ አስተላለፈ!
ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ መግለጫ!

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የአማራ እናት አምጣ የወለደችው ፋኖ በዱር በገደል "አይደለም መሳሪያቸውን፤ ቀበቶቷቸውን እናስፈታዋለን" ብለው የገቡትን የእነ አብይ አህመድ ቡድንና ጋሻጃግሪዎችን ድባቅ እየመታ ባለፈው አንድ ዓመት ከመንፈቅ አማራዊ አኩሪ ተጋድሎዎችን እያደረገ ወደፊት እየገሰገሰ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ በወሎም አደረጃጀቶቹን እያጠናከራና እያዘመነ በጀግኖች መስዋዕትነት  ተጋድሎዎችን እያደረገ ትግሉ የደረሰበትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ በርካታ ስራዎችንም እየሰራ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ በወሎ አካል የሆነው የላስታ ጀነራል አሳምነው ኮር በሚንቀሳቀስበት ላስታ ላሊበላ አካባቢ  የገና በዓል በድምቀት እንደሚከበር ይታወቃል።  በመሆኑም አገዛዙ ይህንን ደማቅ ሐይማኖታዊ ክብረ በአል የራሱንና የፖለቲካና ወታደራዊ ትርፍ መጠቀሚያ ለማደረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል፤ ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዝ ተከታዮችን ጥብቅ ትዕዛዞችንና መምሪያዎችን አውርጃለሁ።

፩. እንግዶቻችን የላሊበላ ኤርፖርትን ጨምሮ በሹምሽሃ ቀበሌ፣ ከሲመኖ ወንዝ ምላሽ ወደ ላሊበላ ከተማ እና ከናዕኩተላብ ከተማ ውጭ መንቀሳቀስ እንደማይቻል።

፪. የኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ ሲቭል አቬሽን ባለስልጣን ከሲቪል መንገደኞች ውጭ አገልግሎት እንዳይሰጥ።

በቀጠናው የሚንቀሳቀሰው የላስታ ጀነራል አሳምነው ኮር በተራ ቁጥር ፩ እና ፪ ያሉትን የመቆጣጠርና የማስከበር ሥራ እንዲሰራ በተጨማሪም አሁን ባለን መረጃ መሰረት ወደ ላስታ የሚያስገቡት በኩልመስክ፣ በጋሸና እና ከሰቆጣ ወደ ላሊበላ ከተማ የሚያስገቡት መስመሮች በድርጅታችን ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የተረዳው አገዛዝ በቅዱስ ላሊበላ ኤርፖርት ሰራዊት ለማራገፍ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አውቃችሁ፤ የአገዛዙ ሰራዊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ይዞ ለመንቀሳቀስ ከተረጋገጠ አየር መንገዱን ጨምሮ አውሮፕላኑ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የመካናይዝድ ኃይሉ ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ።

ድል ለአማራ ሕዝብ!
ዋርካው ምሬ ወዳጆ
©የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️#ምረር_አማራ💪#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

15/04/2017 ዓ.ም**

4 months ago

የይርጋ ሲሳይ ( ስኳድ ) እና የሰማ ጥሩነህ ( አገው ሸንጎ ) አዲስ እቅድ በባሕርዳር !!

በባሕርዳር ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የስርዓቱ ሰራዊት መኖሩ ይታወቃል። በብርሃኑ ጁላ የሚመራው ወራሪ ሰራዊት ፣ በኮሚሸነር ደስየ ደጀን የሚመራው የክልሉ የፀጥታ ኃይል ተብዮ አድማ ብተና ፣ ሚኒሻ እና ፖሊስ እንዲሁም በደሳለኝ ጣሰው የሚመራው ሰላምና ደህንነት ቢሮ  በአሁኑ ወቅት ከሞትና ኩብለላ የቀራቸውን ጥቂት ኃይል አሟጠው የፋኖን ትግል ለመግታትና ለመቋቋም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።

ጎን ለጎን ያወጡት እቅድ ግን በሁሉም አደረጃጀት ውስጥ ካላቸው ገዳይ ቡድኖች በተጨማሪ ከዚህ በፊት በኮሚሽነር ደስየ ደጀን ቡድን የተዘጋጁ የጥበቃ ኤጀንሲዎችን ባሕርዳር ከተማ ውስጥ ባሉ ትልልቅ የግድ ድርጅቶች ፣ ፋብሪካዎች ፣ የንግድ ተቋማት ፣ ሪልስቴቶች እና ትልልቅ የመኖሪያ መንደሮች ላይ በማሰማራት የ Community Intelligence በማጠናከር የፋኖን ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ሚስጥራዊ ግንኙነት መረጃ በመሰብሰብ የሥርዓቱ ድጋፍ ሲጨ ሃይል ለማድረግ ታቅዷል።

በዚህ እቅድ ውስጥ ሚኒሻውን እና አድማ ብተናው ወስጥ ልዩ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ጥቂት ወታደሮች ወደ  የጥበቃ ኤጀንሲዎች ሄደው የተቀላቀሉ ሲሆን ፤ወደ ሚመደቡበት ማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ተመሳስለው የፋኖን የከተማ እንቅስቃሴ መረጃ እየሰበሰቡ ፋኖ በከተማ ያለውን ሴል ሲያውቁ እና ሲያገኙ ከአድማ ብተናው እና ከብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ጋር በመሆን እርምጃ ለማስወሰድ የተዘጋጀ ነው።

በባሕርዳር ከተማ ማህበረሰብ ውስጥ የጥበቃ ኤጀኒሲዎች ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ ሆነ ተብሎ በሰላምና ደህንነት ቢሮ በአድማ ብተና ፈጻሚነት የተዘጋጀ የሰው ፣ የህጻናት ፣የሴቶች ፣ የንብረት እገታ አፈናዎች የተሰላቸው የነጋዴው እና መካከለኛ ኑሮ ነዋሪው የማህበረሰብ ክፍል እንዲማረር ከአደረጉ በኋላ የጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲመደቡላቸው ያደርጋሉ በመቀጠልም የራሳቸውን ገዳይ ቡድኖች እና መረጃዎችን ለማሰማራት መሆኑ ታውቋል።

በዚህ እንቅስቃሴ እና እቅድ ውስጥ ስርዓቱ ባህርዳር ከተማ ላይ ብቻ ለግዜው ያቅደው እንጂ በሌሎች ትልልቅ የአማራ ከተሞች ተሞክሮውን ለመተግበር የወደፊት እቅድ ተደርጓል ። አገዛዙ አካሄዱን የመረጡበት ምክንያትም ፋኖ የከተማ ሴሉን በማሳደጉ እና በከተሞች ሰርጎ ገብቶ የሚፈፅማቸው ኦፕሬሾኖችን ለመግታት በየቦታው የራሱን የመንግሥት ሴል ለማስቀመጥ እንደሆነ ታውቋል።

በባህርዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኙት የባሕርዳር ብርጌድ ሻለቆች እንደ ደጉ በላይ ሻለቃ ፣ግዬን ሻለቃ ፣ አራራት ሻለቃ ፣አሳምነው ሻለቃ እና አራራት ሻለቃ ወደ ከተማው ሰርገው በመግባት የስርዓቱ ሎሌና ባንዳዎችን አንጠልጥለው በመውሰዳቸው አሁን በጥበቃ ኤጀንሲ ስም የመንግሥት ሃይል በማስቀመጥ ፋኖ ጥበቃ ናቸው ብሎ ተዘናግቶ ኦፕሬሽን በሚከውንበት ወቅት መረጃ በመስጠትና  ከጀርባ ጭምር በመውጋት ከተማ ውስጥ የሚደረገው ኦፕሬሽን ስኬታማ እንዳይሆን የታቀደ አዲስ እቅድ ነው።

ለባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕት የፋኖኦፕሬሽኖች ባንዳ እና የስርዓቱ አዳሪዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድና ታንቀው ሲወሰዱ ጥቂቶች ተመልክታችኋል። ይሁን እንጅ ከዚኽ በተቃራኒ እገታ ፣አፍኖ ገንዘብ ድርድር በከተማው የሚፈጽመው ሆነ ተብሎ የሥርዓቱ አፋኝና ዘራፊ ቡድን መሆኑን በጥቂቱም ቢሆን የምትረዱት ሃቅ ነው።

ስለሆነም አገዛዙ አሁን ተቋማትን በስውር ለማስጠበቅ የጥበቃ ሽፋን ኤጀንሲን አመጣለሁ እያለ በየአካባቢው የሚወተውተው ሁሉ ከጀርባው የተሸከመው የስርዓቱ ተልዕኮ መሆኑን ቀድማችሁ እንድታውቁና በአጠቃላይ የጥበቃ ኤጀንሲዎች በማን እንደሚዘወሩ ሴራቸውን  ልትገነዘቡ ይገባል እንላለን ።

ይህንን የአገዛዙ ተንኮልና ሴራ እያዎቀ የአገዛዙን ሴራ በጥበቃ ኤጄንሲ ሥምና ሽፋን የተቋማት የጥበቃ ኤጀንሲ ይመደብልን ብሎ የሚያስተባብርና የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በየአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል ለማስጠቃት ከአገዛዙ ጋር ተናቦና ተባብሮ እየሰራ እንደሆነ በውስጥ አርበኞች መረጃ ደርሶናል ።

በዚህ መሰረት የአገዛዙ ተባባሪ በመሆንም ሆነ፤ ሴራውን ባለማወቅ የትኛውንም የጥበቃ ኤጀንሲ አዲስ ቅጥር የምትፈጽሙ ድርጅቶች ፣ ንግድ ተቋማት ፣ ፋብሪካዎች ፣ ሪልስቴቶች በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልዕክት በአዲስ የቅጥር ውል የቀጠራችሁት የጥበቃ ኤጀንሲ አባል ከአገዛዙ ጋር በማበር ለሚፈጽመው ማንኛውም ፀረ-ፋኖ እንቅስቃሴ እና አገዛዙ ላቀደው አዲስ የፋኖ ጥቃት ሙሉ ሃላፊነት ትወስዳላችሁ። ይህንንም ተከትሎ የፋኖ ለሚወስደው ሴራውን የማክሸፍና የበቀል እርምጃ በጥበቃ ኤጀንሲ ድርጅቱ  ብቻ ሳይሆን በቀጣሪ ድርጅቱ ጭምር ይሆናል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም በባሕርዳር ከተማ የውስጥ ሸማቂ ኃይል የተላከ መልዕክት!!

#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም*?#ምረር_አማራ?#ድል_ለአማራ_ፋኖ?#ድል_ለአማራ_ህዝብ?*

25/2/17 ዓ.ም**

4 months, 1 week ago

አሳዛኝ ዜና!

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።

ጥቃቱ የደረሰው በዞኑ የሶዶ ወረዳ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ጋር በሚዋሰንበት አካባቢ ቢርቢርሳና ጋሌ ቀበሌ  ልዩ ስሙ ''ኩሬ'' እንዲሁም ''ቢጢሲ'' ተብለው እስከሚጠሩ ስፍራዎች ነው።

በሸኔ ታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት እስከ 40 ሰዎች መገደላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ዛሬ ከስፍራው የደረሱን ተደጋጋሚ መረጃዎች አመላክተዋል።

ጥቃቱ ትላንት ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2:00 ገደማ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት መራዘሙን የጠቆሙት የአካባቢው ነዋሪዎችና የሟቾች ቤተሰቦች በጥቃቱ ሕጻናትን ጨምሮ እናቶችና አረጋውያን መገደላቸውንም ተናግረዋል።

የተከፈተባቸውን ጥቃት መመከት ያልቻሉ አርሶ-አደሮች ቤታቸው ውስጥ እያሉ በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ከነከብቶቻቸው እንዲሞቱ መደረጉንም ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ድል ለተገፋው ለአምሓራ ሕዝብ
?*?*?⚔️⚔️⚔️???**

ለበለጠ መረጃ ቻናላችን ተቀላቀሉ ሸርም አርጉት ለጓደኞቻችሁ ጋብዙት?*?*?**https://t.me/AddisNewszena

4 months, 1 week ago

ቡሬ

4 months, 1 week ago

አሁን

በደቡብ ጎንደር ዞን አዲስ ዘመን ከተማ በአሁኑ ሰዓት በአራቱም አቅጣጫ በፋኖ ተከባለች ውጊያው ትንቅንቅ ላይ ናቸው።

4 months, 1 week ago
4 months, 1 week ago

#አዲስ-ቅዳም

አዲስ-ቅዳም አነጋግ ላይ የጀረመው ውጊያ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ከባባድ መሳሪያዎች ጭምር ጥቅም ላይ የዋሉበት ውጊያ እየተካሄደ ነው። የ3ተኛ ክፍለ ጦር /ጎጃም አገው ምድር /የኤፍሪም አጥናፎ ብርጌድ እና በአከባቢ የሚገኙ ፋኖዎች በውጊያው እየተሳተፉ ነው።

#Amhara #Ethiopia

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago