Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
🔴🔗 livestream 🔗🎤
👉አድስ ኪታብ
ኑ እንማር, ኪታብ ይዛችሁ ቀጣይነት ያለው ነው በዚ ሰዓት
➛ ረቡዕ
➛ ሀሙስ
➛ ጁመዓህ በተከታታይ..
➛ልቅራ ወይስ ብለህ እንዳታመነታ ጀምር ትጠቀማለህ አደራ
➛ተማሪዎች አደራ ተከታተሉ
ከ 2:40 ጀምሮ
የኪታቡ ስም= ቡሉግ አልመራም
ሸር አድርጉ ሙስሊም መእሚናት
መልእክተኛው እየሱስ
~
በጊዜው የነበሩ ሰዎች ነብይ እንደሆነ ነበር የሚያውቁት። “ከዚህ የተነሣ ሰዎቹ ኢየሱስ ያደረገውን ምልክት ባዩ ጊዜ፦ ይህ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው አሉ።” (ዮሐንስ 6፡ 14)
ባሪያ እንደሆነ ነው ያስተማረው። “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።” (ዩሐንስ 13፡16)
እሱን የሚያመልኩት መለኮታዊ ሳይሆን ሰውሰራሽ ስርአት የሚከተሉ ናቸው። "ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።" (ማቴዎስ 15፡8-10)
እየሱስ አምላክ ሳይሆን አምላኩን የሚማፀን ባሪያ ነው። “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ ኤሎሄ፥ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጓሜውም አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? ማለት ነው።” (ማርቆስ ወንጌል 15:34)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
ሁላችን ጉዞ ላይ ነን፣ ወደ ኣኺራ!
ሟቾች እንደሆንን ሁላችንም በርግጠኝነት እናውቃለን። የማናውቀው የቀጠሮውን ቀን ነው።
ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦
"ሁሉም ይጓዛታል - ያቺን የሩቅ ጉዞ
የሌለው ባዶውን - ያለው ስንቁን ይዞ።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
5 ወሳኝ ምክሮች በስደት ላሉ ለእህቶች
1--የዋህነት አታብዙ
~እህቶች የዋህነታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከልኩ በላይ ሲሆን ግን ይጎዳል። ሁሉም ነገር ላይ የዋህ አትሁኑ ።ለምን? እንዴት? ማለት ያለባችሁ ነገር ላይም ለምን በሉ። ብልሆች፣ብልጦች፣አስተዋዮች ሁኑ።
2--ሁሉንም አትመኑ
~ሁሉንም በማመናችሁ ያጣችሁት ነገር የለም? የተጎዳችሁት ነገር የለም? በእርግጠኝነት ይኖራል ።ጥርጣሬም አታብዙ ግን ሁሉንም አትመኑ።
ልቅ በሆነ እምነት ስንት ነገሮቻቸውን ያጡ አሉ መሰላችሁ። በተለያዩ ሽፋን በተለያዩ ካፓ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም እወቁ። ተጠንቀቁ።ንቁ። እራሳችሁን፣ገንዘባችሁን ጠብቁ።
3---ስትሰጡ በልክ ስጡ።
መስጠት ያሰጣል።አላህም ይተካል። ጀነትን ያስገኛል።ደስታን ይሰጣል።መካራን ያስወግዳል። ግን በልክ ይሁን ።
4- ለችግር ግዜ የሚሆናችሁን ገንዘብ አስቀምጡ።
~ሰው ነን መታመም ሊመጣ ይችላል።ስራ መፍታት ሊኖር ይችላል። የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዛ ችግር እዳም እንዳትገቡና እንዳትቸገሩ ለዚህ ቀን የሚሆን ከደሞዛችሁ፣ከጉዳዮቻችሁ ሸረፍ እያደረጋችሁ አስቀምጡ።
5--ደርስ ላይ ፣ቂረአት ላይ በርቱ
~በቻላችሁት አቅም ግዜያችሁን ለመጠቀም ሞክሩ ።በስደት ቆይታችሁ ባለቻችሁ ሽራፊ ግዜ ለመጠቀም ሞክሩ። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ በሗላ ሁሉ ነገሩ እንደጠበቃችሁት ላይሆን ይችላል። የመቅራቱም ሞራል እንደዛ ላይሆን ይችላልና በርቱ።ሸምቱ።
በሶሻል ሚድያው ተጠቀሙ።
✍አቡ ሀፍሷ
~››@AbuHafsaYimam
~››@AbuHafsaYimam
የልብ ድርቀትን ለመከላከል
~
በዚህ ዘመን በልብ ድርቀት ያልተጠቃ ይኖር ይሆን? ሃሳብ ጭንቀታችን ዱንያ ብቻ ሆነ። ዒባዳችን ለዛ አጣ። መተዛዘን ጠፋ። ስግብግብነት ነገሰ። ስስት ከደም ከስጋችን ጋር ተዋሀደ። የዱንያ ምኞታችን ከመርዘም አልፎ ተንዘላዘለ።
ወንድሞች እህቶች ወላሂ! የልብ ድርቀት በጣም ሊያስጨንቀን የሚገባ ህመም ነው። የልብ ድርቀት አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የአላህ ቅጣት ነው። ከዚህ ህመም ልባችንን እንዴት እናክም? ከዚህ የአላህ ቅጣት እንዴት እንውጣ? ጥቂት ሰበቦችን ልጠቁም። ራሴም ጤነኛ ሆኜ አይደለም። ከማጨስ እንደሚያጠነቅቅ አጫሽ፣ ከህመም እንደሚያስጠነቅቅ ህመምተኛ ቁጠሩኝ።
1- አላህን በማሰብ ራስን አጠቃላይ ከወንጀል መጠበቅ፣ የቅርብም ይሁን የሩቅን ሰው ከመበደል መጠንቀቅ፣ ግብይታችንን፣ ገቢያችንን ሐላል ማድረግ፣ የሰው ሐቅ እንዳይመጣብን መጠንቀቅ
2- ምላስን ከውሸት፣ ከመጥፎ ንግግር፣ ከሃሜትና መሰል ክፍቶች መቆጣጠር፣ ጆሮዎቻችንን ሐራም ነገሮችን ከማዳመጥ፣ አይኖቻችንን ሐራም ነገሮችን ከመመልከት፣ እጆቻችንን ለሐራም ነገሮች ከመጠቀም፣ ልባችን በክፋት፣ ምቀኝነት፣ ጥላቻ፣ ... ላይ ከመጥመድ መቆጣጠር
3- ዚክር ማዘውተር፣ በቋሚነት የቁርኣን ዊርድ መያዝ፣ ደጋግሞ ከልብ ዱዓእ ማድረግ፣ ተደቡር፣ ተፈኩር ማድረግ፣ በዱዓእ፣ በቁርኣን ማልቀስ
4- ከሰላት፣ ከፆም፣ ከሶደቃው፣ ... ከግዴታው ባለፈ ነፍል ዒባዳዎችን ማዘውተር
5- ሞትን፣ ቀብርን፣ ሂሳብን፣ ሲራጥን፣ ... ኣኺራን ማሰብ
6- ደግሞ ደጋግሞ ኢስቲግፋርና ተውበት ማድረግ
7- ቁርኣን በእርጋታ መቅራት፣ ኹሹዕ የሚያጋባ አቀራር ያላቸውን ቃሪኦች ማዳመጥ፣
8- ቀብር መዘየር፣ የታመመን መጠየቅ፣ ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤትን አቅም በፈቀደ መጠየቅ
9- ችግረኛን በገንዘብም፣ በሃሳብም፣ በጉልበትም፣ በእውቀትም መርዳት፣ ሶደቃ ማድረግ
10- የዙህድና የረቃኢቅ ኪታቦችን ማንበብ፣ ውስጥን ሰርስረው የሚገቡ ሙሓደራዎችን እየፈለጉ ማዳመጥ፣ የነብዩን ﷺ ስራዎች፣ ራስን ለመታዘብ የሚያግዙ የሰለፎችን አስገራሚ ታሪኮች፣ የዑለማኦችን ጣፋጭ ወጎች በትኩረት መከታተል
11- በየትኛውም የዒባዳ መስክ ላይ ኢኽላስን አጥብቆ መፈተሽና ማቃናት።
12- ከራስ ጋር መተሳሰብ። ጊዜ አልፎ ጊዜ በተተካ ቁጥር ወደ ሞት እየቀረብን ነው። ከአምና ዘንድሮ፣ ከባለፈው በዚህኛው፣ ሳምንታችን፣ እለታዊ ውሏችን መሻሻል አለው? ወይስ ያው ነው? ወይስ ጭራሽ እየባሰበት ነው? ከዱንያችን በላይ ኣኺራችን ያሳስበናል? ድንገት ብንሞት ያለንበት ሁኔታ በፀፀት ጣት የሚያስነክስ አይደለም? ራሳችንን ለመለወጥ የምር እንታገል።
እኔ የራሴን ድክመቶች በመመልከት ድንገት የመጣልኝን ነው የፃፍኩት። ሁሉም ነገን አስቦ ዛሬ ራሱን ይመልከት።
﴿بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَى نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ﴾
"በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡" [አልቂያመህ ፡ 14]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago