ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot
⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu
ስልክ ቁጥር +251911857852
Last updated 19 hours ago
–The Best Arsenal Football Club Telegram Channel in Ethiopia.
–በኢትዮጵያ ትልቁ የአርሰናል ቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ አርሰናል አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ፣ ዜናዎች ፣ኃይላይቶች፣ቪዲዬች፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ። ____________________
📥 ለማስታወቂያ ስራ : @Mex_classic
https://telega.io/c/ETHIO_ARSENAL
Last updated 2 months ago
ዐሹራእ ደረሰ
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
ዐሹራእ ምንድነው?
ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡
ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡
ለምን ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡ ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡
ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡
መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሁክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
ዓኢሻህ(ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡
መቼ እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ሰኞ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱቱ አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ከ እሁድ-ማቅሰኞ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡
ለ. እሁድና ሰኞ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡
ሐ. ሰኞና መቅሰኞ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
መ. ሰኞን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ነው፡፡
አላህ ይወፍቀን
Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder
USTAZ Abu Heydar
USTAZ Abu Heydar. 247,384 likes · 5,527 talking about this. Interest
ተክቢራ☝️
اﷲ اكبر ! اﷲ اكبر ! اﷲ اكبر .........
?? عيد مبارك ??
تقبل الله منا ومنكم كل عام وأنتم بخير
?? عيدُُ سعيد ??
?ውብ የጁምዓ ኹጥባ?
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
?አል በቀራህ 183?
t.me/joinchat/AAAAAERWlA2VEv32NugvJQ
شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ …»
(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው…»
?አል በቀራህ 185?
?ውብ የጁምዓ ኹጥባ?
أَقِمِ الصَّلَاةَ لِدُلُوكِ الشَّمْسِ إِلَىٰ غَسَقِ اللَّيْلِ وَقُرْآنَ الْفَجْرِ ۖ إِنَّ قُرْآنَ الْفَجْرِ كَانَ مَشْهُودًا
ሶላትን ከፀሐይ መዘንበል እስከ ሌሊት ጨለማ ድረስ ስገድ፡፡ የጎህንም ሶላት ስገድ፡፡ የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና፡፡
ኢስራእ 78?
?ሱብሕን የሰገደ በአላህ ጥበቃ ስር ነው” ረሱል ﷺ
【ሙስሊም】
?ዒሻእን በጀማዐህ የሰገደ ግማሽ ሌሊትን በሶላት እንደቆመ ነው፡፡ ረሱል ﷺ?
?ሱብሕን በጀማዐህ የሰገደ ደግሞ ሌሊቱን በሙሉ እንደቆመ ነው”
ረሱል ﷺ 【ሙስሊም】
?ሱብሕን ለሰገድ መላእክት ይመሰክሩለታል፡፡
ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- [በናንተ ውስጥ የሌሊት
መላእክትና የቀን መላእክት ይተካካሉ፡፡
[✅በፈጅር ሶላት እና
በዐስር ሶላት ላይ ይሰባሰባሉ፡፡
?ከዚያም እነዚያ በናንተ ዘንድ ያደሩት
☝️ወደ ሰማይ☝️ ይወጣሉ፡፡](https://t.me/kedibntebrahim/5090)
ይህኔም ጌታቸው በነሱ
ሁኔታ አዋቂ ሆኖ ሳለ “ባሪያዎቼን በምን ሁኔታ ላይ
ተዋቸኋቸው?”
ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ “እነሱ እየሰገዱ ነው
የተውናቸው፡፡ እየሰገዱም ነው የመጣናቸው” ይላሉ፡፡
?ቡኻሪና ሙስሊም?
በየሳምንቱ ውብ የሆኑ ኹጥባዎችን ለሌሎቹም ለማካፈል ሼር..ሼር?
https://t.me/joinchat/AAAAAERWlA2VEv32NugvJQ
ፅሁፍ እንዳላበዛባችሁ ሙሉ ኹጥባውን አዳምጡ?✅
Telegram
attach 📎
ረጀብ 27ኛው ቀን በኢስላም መከበር አለበት ወይስ የለበትም❓
?ፔጅ 134 (አል አንዓም 53-59)?
እነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት (ወደ አንተ) በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው»
ብዙ ሙስሊም እህቶቻችን ቀሚስን አሳጥረው የመልበስ እና ሰውነታቸውን
የሚያጣብቅና ሰውነታቸውን የሚያሳይ ልብስ መልበሳቸው ከሸሪያ አንፃር እንዴት
ይታያል?
«ሴቶች የቀሚሳቸውን ጫፍ እንዴት ማድረግ አለባቸው?
የሴት ልጅ እግርና ተረከዝ መሸፈን ካለበት ክፍሎች አንዱ ነው።
ኡሙ ሰለማ እንዲህ ስትል የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ጠየቀች፦
«ሴቶች የቀሚሳቸውን ጫፍ እንዴት ማድረግ አለባቸው?
የአላህ መልዕክተኛም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው መለሱላት፦
«ወደታች አንድ ስንዝር ዝቅ ታድርግ»እሷም እንዲህ ስትል ጠየቀች «እንዲያም ሆኖ ተረከዛቸው የተገለጠ ከሆነስ?» የአላህ መልዕክተኛም (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው መለሱላት፦ «አንድ ክንድ ዝቅ ያድርጉ ከዚህ በላይ አይጨምሩ»
[አልባኒ ሰሂህ ብለውታል]
እስኪ ጎንበስ በይና የራስሽን ልብስ ተመልከቺው! አንድ ክንድ ወደታች ለቀሽዋል ወይስ ወደላይ ሰቅለሽዋል?
ሌላው ደግሞ ጉርድ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ከጉልበታቸው በታች እራቁታቸውን ናቸው፣ ሙሉ ቀሚስ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን ከመወጣጠሩ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ሙሉ
ለሙሉ ያሳያል፣ ሲላቸውም ደረታቸውና የወገባቸው ክፍል የማይሸፍንም ይለብሳሉ፣ ሻርፕ ለብሰናል ይላሉ ነገር ግን አስሬ የምትወርድ ወይም ለሳንፕል እዩልኝ በሚል መልኩ ይለብሳሉ። ሌላም ሌላም ጉድ የሚሳኝ አይነት ምናልባትም ሙስሊም ያልሆኑት ከሚለብሱትና ከሚያስከፈ መልኩ ለብሰው እያየን ነው።
"ሁለት ክፍሎች የእሳት ናቸው። እነሱንም አላየኃቸውም። አንዶቹ የከብት ጅራት የመሰለ አለንጋ ይዘው በዚያ የአላህን ባሮች የሚገርፉ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ የለባሽ እርዘኛ
(ለብሳ ያለበሰች)፣ ተዝንባዩች እና አዘንባዩች እራሳቸው እንደ ከሳ ግመል ሻኛ የሆኑ በፍፁም ጀነት አይገቡም፤ አረ እንዳውም ሽታውንም አያገኙም። የጀነት ሽታ ከዚያ ወደዚያ(ከረጅም ርቀት) የሚገኝ ሆኖ ሳለ።" (ሙስሊም 2128፣ አህመድ 440/2)
እኔ እምልሽ የኔ እህት! እጣ ፈንታሽ ይሄ እንዲሆን ትፈልጊያለሽን?! ለዲንሽ ዋጋ
ስጪ!! ወንድሜ ሆይ! ባለቤትህ ወርዳና ተዋርዳ ስትወጣ ዝም ማለት ያንተ ባልነት ምኑ ጋር ነው? አባት ሆይ! ልጅህ የአደባባይ መነጋገሪያ እስክትሆን ያንተ ሚና ምን እንደሆነ ረሰሀውን? አንተስ ወንድሜ እህትን መቆጣጠር ምንተሳነህ? ስህተት/ጥፋት እያየን ዝም ካልን አላህ እንዴት ነስሩን ይስጠን? የእስካዛሬው ይብቃ! ዛሬውኑ ቤታችንን በዲን እናፅዳ! አላህ ያግራልን!
ሰባት ምክሮች የሰራባቸው
/////////////////////////////
_በእርግጥ ታድሏል_
…………………………………
قال أَحْمَدُ بْنُ أَبِي الْحَوَارِيِّ
=>አህመድ የአቢ ልኸዋሪ ልጅ የሆነው እነዲህ ይላል_
ﻗﻠﺖ ﻷﺑﻲ ﺳﻠﻴﻤﺎﻥ اﻟﺪاﺭاﻧﻲ ﺃﻭﺻﻨﻲ
=>ለአቢ ሱለይማን አደራኒ ምከረኝ አልኩት ይለናል_
. ﻓﻘﺎﻝ: ﺃﻣﺴﺘﻮﺹ ﺃﻧﺖ؟
=>አንተ በመከርኩህ ነገር ትሰራበታለህ?_
ﻓﻘﻠﺖ نعم إن شاءالله تعالى
=>አዎን እሰራበታለው የአላህ ፍቃድ ከሆነ>
ﻓﻘﺎﻝ:
=>እንዲህ ብሎም መከረው_
?(1) ﺧﺎﻟﻒ ﻧﻔﺴﻚ ﻓﻲ ﻛﻞ ﻣﺮاﺩ ﻟﻬﺎ ; ﻓﺈﻧﻬﺎ اﻷﻣﺎﺭﺓ ﺑﺎﻟﺴﻮء،
=>የነፍሲያህ ተቃራኒ ሁን በሁሉም ፍላግትዋ እስዋ እኮ በመጥፎ ነው ምታዘው_
?(2)ﻭﺇﻳﺎﻙ ﺃﻥ ﺗﺤﻘﺮ ﺃﺣﺪا ﻣﻦ اﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ،
=>ከሙስሊሞች አንዱንም ከመናቅ ተጠንቀቅ_
?(3)ﻭاﺟﻌﻞ ﻃﺎﻋﺔ اﻟﻠﻪ ﺩﺛﺎﺭا،
=>ጌታህን አላህን መታዘዝን ልብስህ አድርገህ ያዘው
?(4)ﻭاﻟﺨﻮﻑ ﻣﻨﻪ ﺷﻌﺎﺭا،
=>አላህን መፍራት ላንተ አርማህ ( መለያህ) አደርገው
?(5)ﻭاﻹﺧﻼﺹ ﺯاﺩا،
=>ኢባዳህ ጥርት አድርገህ መያዝህ ስንቅህ አድርገው
?(6)ﻭاﻟﺼﺪﻕ حسنة،
=>እውነት መናገርህ መልካም ሰራ አድርገህ ቁጠረው
ﻭاﻗﺒﻞ ﻣﻨﻲ ﻫﺬﻩ اﻟﻜﻠﻤﺔ اﻟﻮاﺣﺪﺓ ﻭﻻ ﺗﻔﺎﺭﻗﻬﺎ ﻭﻻ ﺗﻐﻔﻞ ﻋﻨﻬﺎ:
ይህችን አንድት ንግግር ከኔ ተቀበል ከሷም እንዳትለያት እንዲሁም ከሷም እንዳትዘናጋ
?(7) ﺇﻧﻪ ﻣﻦ اﺳﺘﺤﻴﻰ ﻣﻦ اﻟﻠﻪ ﻓﻲ ﻛﻞ ﺃﻭﻗﺎﺗﻪ ﻭﺃﺣﻮاﻟﻪ ﻭﺃﻓﻌﺎﻟﻪ ﺑﻠﻐﻪ ﺇﻟﻰ ﻣﻘﺎﻡ اﻷﻭﻟﻴﺎء ﻣﻦ ﻋﺒﺎﺩﻩ
=>ነገሩ እኮ በሁሉም ወቅት አላህን ያፈረ በሁሉም ግዜው በሁኔታው እንዲሁም በሁለም ስራው አላህን ያፈረ ሥራው በራሱ ከወልዮች ደረጃ ዘንድ ያደርሰዋል።
ﻗﺎﻝ: ﻓﺠﻌﻠﺖ ﻫﺬﻩ اﻟﻜﻠﻤﺎﺕ ﺃﻣﺎﻣﻲ، ﻓﻔﻲ ﻛﻞ ﻭﻗﺖ ﺃﺫﻛﺮﻫﺎ ﻭﺃﻃﺎﻟﺐ نفسي بها
البداية والنهاية449/14
=>አህመድም እንዲህ አለ እነዚህ ንግግሮች ፊት ለፊቴ አደረግኩኝ
ነፍሴን ይህን ነገር እንድታደርግ አስታውሳታለው በተግባር እንድታሳይ ሁልግዜ እፈልጋለው ።
አላህ ሆይ የነዚህ ድንቅ ሰለፎች ትክክለኛ ተከታይ አድርገን አሚን
•════•••???•••════•
JOIN→ https://t.me/Ketibeb
JOIN→ https://t.me/Ketibeb
┄┄┉┉✽̶»̶̥✿»̶̥✽̶┉┉┄┄
https://t.me/joinchat/AAAAAEeo-fc3TF1FQ-jMAw
┄┄┉┉✽̶»̶̥✿»̶̥✽̶┉┉┄┄
Telegram
ጥበበ ሉቅማን/Luqman Tube
❥ሁሌም ቢሆን ለዲነህ ትልቁን ቦታህን ስጥ!! ❥አንብብ ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል ያን ደግሞ በተግባር አሳይ። LEAVE ከማለት ይልቅ ***👉*** @ketibebot ይችን ጫን በማድረግ የተሰማዎት ይፃፉልን። Promotion– @kedir2 For Le ወንድም channeል ለፈገግታ @ethio\_keld
?በመልካም ነገር መረዳዳት?
✅በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ አል ማኢዳህ 2?
የዙል ቀርነይን ታሪክ↴
قَالُوا يَا ذَا الْقَرْنَيْنِ إِنَّ يَأْجُوجَ وَمَأْجُوجَ مُفْسِدُونَ فِي الْأَرْضِ فَهَلْ نَجْعَلُ لَكَ خَرْجًا عَلَىٰ أَن تَجْعَلَ بَيْنَنَا وَبَيْنَهُمْ سَدًّا
«ዙልቀርነይን ሆይ! የእጁጅና መእጁጅ በምድር ላይ አበላሺዎች ናቸውና በእኛና በእነሱ መካከል ግድብን ታደርግልን ዘንድ ግብርን እናድርግልህን» አሉ፡፡
قَالَ مَا مَكَّنِّي فِيهِ رَبِّي خَيْرٌ فَأَعِينُونِي بِقُوَّةٍ أَجْعَلْ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُمْ رَدْمًا
አለ «ጌታዬ በእርሱ ያስመቸኝ ሀብት (ከናንተ ግብር) በላጭ ነው፡፡ ስለዚህ በጉልበት እገዙኝ፡፡ በእናንተና በእነሱ መካከል ብርቱን ግድብ አደርጋለሁና፡፡
آتُونِي زُبَرَ الْحَدِيدِ ۖ حَتَّىٰ إِذَا سَاوَىٰ بَيْنَ الصَّدَفَيْنِ قَالَ انفُخُوا ۖ حَتَّىٰ إِذَا جَعَلَهُ نَارًا قَالَ آتُونِي أُفْرِغْ عَلَيْهِ قِطْرًا
فَمَا اسْطَاعُوا أَن يَظْهَرُوهُ وَمَا اسْتَطَاعُوا لَهُ نَقْبًا
(የእጁጅና መእጁጅ) ሊወጡትም አልቻሉም፡፡ ለእርሱ መሸንቆርንም አልቻሉም።
Telegram
attach 📎
ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot
⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል
የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና
ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu
ስልክ ቁጥር +251911857852
Last updated 19 hours ago
–The Best Arsenal Football Club Telegram Channel in Ethiopia.
–በኢትዮጵያ ትልቁ የአርሰናል ቴሌግራም ቻናል ነው። ስለ አርሰናል አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ፣ ዜናዎች ፣ኃይላይቶች፣ቪዲዬች፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ። ____________________
📥 ለማስታወቂያ ስራ : @Mex_classic
https://telega.io/c/ETHIO_ARSENAL
Last updated 2 months ago