Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
አግዝዮ ስለሷ
እንዴትስ አስቻለሽ እንዴትስ ቻልሽበት
እንደ ምን አይተሽው በምንስ ኖርሽበት
አታውቂም...
ብታውቂማ ኖሮ መቻል ላልቻለበት
መኖርን ሳያውቀው ቀን ለነገሰበት
ብታውቂማ ኖሮ ማየት ካንቺ ሌላ
እንደታወርኩልሽ ሆነሽ አይነ ጥላ
ላንቺ ከምለፍፍ ለደራሲው ላውራ
እግዝዮ ላንተ ላውራ..
ምን እሾ በቅሎ ነው የቱስ አሜኬላ
በእሾ እንደወደቀ እንደባከነ ዘር ፍሬው ሳይበላ
ሳናበራ ጠፋን ጥሩ ሳኖን ከፋን
ሳንበቅል ደረቅን ሳናብብ ከሰምን
ሄደን ሳናውቅ ቀሩ ላይመጡ ቀጠሩ
መዋደድ ሳያውቁ ፍቅርን ተፋቀሩ
ተብሎ ተወራ አግዝዮ ላንተ ላውራ..
ማስመሰል በእውነት ሀዘኔታን ፍቅር
እያልኩኝ ተክቼ ከሷ በቀር ይቅር
ፍቅርን መስጠት ነው መቀበል ሳያሻኝ
ለፍቅር ስዋደቅ ምነው እሷን ነሳኝ
ከካፌው ገብቼ ሲለኝ ምን ልታዘዝ
ትዝታን አምጣልኝ በደንብ ያለ ቀዝቀዝ
ፀሀዬን አምጣልኝ ፍቅር ማንነቴን ብዬ ተማፀንኩት
ልመናን በትዛዝ መስዬ አዘዝኩት
ፍቅሬን አምጣልኝ ስለው አይቶኝ ይስቅብኛል
ደግሞ ደጋግሞ ደግሞ ምን ልታዘዝ ይለኛል
ሰውኔቴን ትቼ ትዝታን ስለብሰው
ሰው ጠፋ እስኪሉ ቅኔዋን ስዘርፈው
መጥፎ ቅኔ ለቀልድ ጥሩውን አግዝፌ
ለመፍታት ስኳትን ወርቄን እኔው ጽፌ
አግዝዮ ስለቅኔ አግዝዮ ስለ ያኔ አግዝዮ ስለ እኔ...
ለካ ጣት ለፃፈው ልብ አይመሰክርም
ለካ ሆድ ያባውን ጣት አያወጣውም
በጣት ከንቱ ግብር ሰውነት መሰዋት
በዘመን ተለክፎ የሰው ዘመን ማጥላት
አፈቀርኩህ መባል መፈቀርም አይደል
ወደድኩ ናፈኩ በኢምንት ይካዳል
እንዴት ቃል እረክሶ በቃል ቃል ይናዳል
አግዝዮ ለቃል ነበር ለቃል ፍቅር ጌታ
ለምንስ ዝም አለ ለፍቅርስ ወርዶ ለፍቅር ስረታ
ላልበላ ታጥቤ መዳፌን ሳነጣው
በትዝታ ጅራፍ ፊቴን ላገረጣው
ሳትመጪ የሄድሽው ሳላገኝ ያጣሁሽ
አንቺን የምትመስል አንድ ሀገር አለችሽ
ሳትመጣ የሄደች ሳትበላ ያገሳች
ሳትከብድ የቀለለች ሳታለቅስ ያነባች
አንድ ምስኪን አለች..
እኔ አቅልሀለው ዘመን ያሳደፋት
ያላዋቂ ሳሚ ምራቅ ያከረፋት
ልጆቿ ባንድ ላይ ቀጥረዋት የጠፉ
በዘመን ቀጠሮ ዘመን ያሳደፉ
አዎ ሀገር አለች ጋን አስከ ድፍድፉ
ሳምኩዋት የሚል በዛ እየተናከሰ
ላነገሰው ሆዱ ክብር እያረከሰ
እግዝዮ ስለክብር አግዝዮ ስለ እናት
ዛሬስ ልማዱ ነው ነገን ማን ያዝንላት
ለቀስተኛው አሽሙር አባባዩም ዲስኩር
ማባበያው በደል ማንስ ከማን ይማር
ገና ሳይጎርሰው ነው እጇን የሚነክሰው
ምናል ቢታገሰው አስከምታጎርሰው
ምናልባት ቢሆንስ ጉርሻው ለጥያቄ
መልሱን ያዘለለት ሳይሄድ ለአረቄ
አግዝዮ ስለ ትግስት አግዝዮ ስለማግስት
ካስጨበጥሺው ብሩሽ ካስነከርሽው ቀለም
የርሱ ብሶት አንጂ ያንቺ ስዕል የለም
ፈገግ ያልሽ እንደሆን ጥርስሽ ያስታውቃል
ትቢያ ካንቺ ሰዶ ከራሱ ይፍቃል
አግዚዮ ማርና ኢትዮጵያን
እባክህ አላህ ሆይ በእዝነትህ ታረቀን
እንቅፋት ሲመታ ወደ ኃላ አይጥል
ያረቢ አንበል እምነትን አንጣል
መውደቅ መነሳት ነው ለፍሬው ጥፍጥና
ከስቃይ አመሻሽ ኃላ ደስታ አለና
ምንም አይደል ለኔ ከጣቶቼ መሀል ስጋዬ መላሙ
ወትሮውንስ ቢሆን ባንቺው አልጋ አይደል ወይ ህልሜ መታለሙ
አግዝዮ ስለ አለሜ አግዝዮ ስለ ህልሜ
ይህን ለመረዳት ትንሽ ብቻ ወኔ
ከዛም ማስተዋል ነው የሽመናን ቅኔ
በቀኝ በግራ እየወረወረ የሚቀባበለው መወርወሪያ ብሎ ስሙን የሰየመው
ሀገሬ እኮ አሷ ናት በቀኝ በግራ ምንቀባበላት
ወድቃ እንዳትሰበር የምሰስትላት ሀገሬ እኮ እሷ ናት
አርቡ ላይ ወጥሮ የሚያሽከረክረው ማዳወሪያ ብሎ
ከሸማኔው ዋለ በክር ተመስሎ
ሀገሬ ክር ናት
ወይ ልንበጥሳት ወይ ልንዋብባት
የምንታገላት ሀገሬ ቀጭን ናት
እግዝዮ ስለ እሷ አግዝዮ ለተዋበው ለጥበብ ቀሚሷ
ደግሞም ሳይታክተው ሸማኔው ያደራል
ያደራውን ድርም አጥብቆ ይቋጥራል
ድሩም ተስፋችን ነው ሁሌ ሚለመልም
ቋጠሮ ነገ ነው ለነገ ሚፈታ ዛሬ ማይታለም
አርቡ ሳይኖር ጥልፉ ሳይደወር ጥለት
ሳይገፉ ድልም ሳይሞቱ ነፃነት
ድሩም ሳይደራ አንዝርቱንም ሳይዞር
መች ለውጥ ይገኛል ካላሉ ዞር ዞር
ጥበብ ማለት አሷ ጠቢብ ማለት ህዝቧ
አግዜር የፈጠራት ቢሆንም ጠቢቧ
ጥበብን የቸራት እንድትኖር ተጠባ
የንጉሶች ጥለት ያውም የድንጉዛ
ማጌጧ ማይቀር ነው አበሳው ቢበዛ
ሀገሬ አንቺ ነሽ ሳላገኝ ያጣሁሽ
አንቺን የምትመስል አንድ ሀገር አለችሽ
ሌላ ሀገር አትስሩ ጋራ ሸንተረሩን ምናብ አትሳሉ
ሀገሬ እኮ ሰው ነው ሰውነት አምሳሉ
ይቺ ስም ማንስ ናት ይላል ብለው ካሉ
የነገስታቶቹ የቅኔዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት በሉ
ይቀመጣል እንደደላዉ
ህመም ጎኑን እየበላዉ
ይፈግጋል የሞት ሞቱን
ማን አይቶለተ ስውር ምቱን
እያነቡ እንደመሳቅ
ከሰዉ ኑሮ ከራስ መራቅ
ቃልአብ አፀደ
ይቀመጣል እንደደላዉ
ህመም ጎኑን እየበላዉ
ይፈግጋል የሞት ሞቱን
ማን አይቶለተ ስውር ምቱን
እያነቡ እንደመሳቅ
ከሰዉ ኑሮ ከራስ መራቅ
ቃልአብ አፀደ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад