LIJ MUAZ

Description
"አላማዬ ወጣቱን የጥሩ ስነ-ምግባር ባለቤት ማድረግ ነው"።

Tiktok👇
https://www.tiktok.com/@lij_muaz?_t=8Z1Zk6YYK1e&_r=1

Youtube👇
https://youtube.com/@lijmuaztube?si=2LRG82_zAugcNjjl

Facebook👇


Instagram 👇


እኔን ማግኘት ለምትፈልጉ @LijMuaz_bot
ማስታወቂያ ለማስነገር @MuazPlus
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

6 days, 19 hours ago

تفسير القرآن | ቁርአን ተፍሲር

💦

بأخينا : أبو حارس عبد الرحمان

ሸርርር .ያ ጀመኣ ባረከላሁ ፊኩም

https://t.me/Abuharisabdurahman?livestream=758aa45b9ed9422802

1 week ago

ያ!አላህ🤲 አርቆ የሚያስብ ጭንቅላት
ጥሩ የሚያስተዉል ልብ
ብዙ የሚችል ሆድ ያረቢ አንተው ስጠን
🤲 አሚን 🤲**

ልብ ትዝጋለች ፣ ብረት እንደሚዝገው ሁሉ ።
ማፅጃዋ #አሏህን ማውሳትና #ቁረአን መቅራት ናቸው ።

አሏህዬ የአንተን ውዴታ ወፍቀን።

ውሎህን በዚክር ጀምር

〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ #ፈዘኪር💐ሰባሃል .. ኸይር .. 🌸** @LIJ_MUAZ

1 week ago

**የሆነ ፍርሀት ይይዘኛል .....

በጀነት ቦታ የለህም እንዳልባል 🥀ወንጀሎቼ
ኸይር ስራዎቼን እንዳይበልጡ ብዬ በጣሙን
እፈራለዉ።ተስፋዬ አንድ ነዉ::የአላህዬእዝነት
መሀሪነቱ ከኔ ወንጀል በላይ ሰፊ መሆኑ ነው
ያረብ እዝነትህን

መልካም ምሽት👍......**@LIJ_MUAZ

1 week, 4 days ago

تفسير القرآن | ቁርአን ተፍሲር

💦

بأخينا : أبو حارس عبد الرحمان

ሸርርር .ያ ጀመኣ ባረከላሁ ፊኩም

https://t.me/Abuharisabdurahman?livestream=4f35271b5ef9aca7ce

1 week, 4 days ago

አንት የሱና ወጣት የት ላይ ነው ያለህው⁉️**

እየቀራህ ነው⁉️

እየተማርክ ነው⁉️

ቤትሰብ እየረደህ ነው⁉️

ትዳር እየመራህ ነው⁉️

ደዕዋ እያደክ ነው⁉️

እየነገድክ ነው⁉️

እያረስክ ነው⁉️

ሙያ እየለመድክ ነው⁉️

👉ወይስ👈

ቦዝነሃል⁉️

ስራ ፈተሃል⁉️

ቂርአት ትተሃል⁉️

ከመስጊድ ቀርተሃል⁉️

ደዕዋ አቁመሃል⁉️

ማንበብ ትተሃል⁉️

መማር ትተሃል⁉️

ትዳር ፈተሃል⁉️

በጥቅሉ>=

ጓደኛህ ማን ነው⁉️

ስራህ ምንድነው⁉️

መዋያህ የት ነው⁉️

ማደሪያህ የት ነው⁉️

አላማህ ምንድን ነው⁉️

መልስ ከሁላችንም ይጠበቅብናል አሁን ላይ ታውቃላቹህ ⁉️

የትምህርት ተቋማቶች ተዘግተው

መድረሳዎች ተዘግተው

አብዛኞቹ የስራ መስኮች ተዘግተው

የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው ነው ያሉት

ታዲያ በዚህ ጊዜ ቦዘኔው ስራ አጡ ሌባው አጭበርባሪው ይበዛል ያኔ ታዲያ አንተ ምን ማድረግ አለብህ⁉️

ጓደኛ መምረጥ

ትንሽም ብትሆን ስራ መፍጠር

ውስጥ ለውስጥም ቢሆን ደርሶችን አፈንፍነህ መከታተል

ዒባዳ ላይ ትኩረት ማድረግ ወደ አሏህ የሚያቃርብህን ነገር ፈልገህ መስራት ባገኘህው አጋጣሚ ሱናን ለህዝብህ ለማድረስ ቀና ደፋ በል

አሏህ በመልካም እንቅስቃሴዎች ሁሉ ይረዳሃል** @LIJ_MUAZ

1 week, 5 days ago

#ፈጅር ***ለፈጅር ሰላት ወደ መስጂድ ስትገባ ጥቂት ሰጋጆች ስትመለከት ዕወቅ ... አላህ ነው ከእነርሱ(ከባሮቹ) እንድትሆን የመረጠህና አመስግን!!

የፈጅርን ሰላት በጀምዓ ለመስገድ ስለበቃህ እንኳን ደስ አለህ!
በአላህ ጥበቃ ውስጥ ነህ .... በእውኑም በመንፈስም ቤትህ ከሌሎች ቤቶች ብርሀን ነው።

«ጌታዬ ሆይ ጉዳዮቼን ወደ አንተ አቀርባለሁ፣ እንደምታሳካልኝም ተስፋ አደርጋለሁ!» ከሚሉ ባሮቹ ውስጥ ያድርገን!!*** #ዳይወደሶላት@LIJ_MUAZ

2 weeks, 4 days ago

የ3 አመቷ ታዳጊ ልጄን አሳክሙልኝ ይላል አባት ሙነወር አህመዲን **

ህፃን ኢነብ ሙነወር አህመዲን ባጋጠማት የመቅኔ ችግር መቅኔዋ ደም አያመርትም እና በሰዉ ደም ነዉ ምትኖረው በየሳምንቱ ደም ይቀየርላታል አይመቻትም በአፋ እና ከተለያየ ቦታዋ ይወጣል በዛን ስዓት ለረጅም ስዓት እራሳን አታውቅም ህይወቷ እጅግ አስጊ በሆነ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን እና በመላው አለም ያላቹ ወገኖቼ የልጄን ህይወት በናንተ ተሣትፎ አድኑልኝ ይህ ጥያቄ ስጠይቅ ግን አንደበቴ ተሳስሮ ነው በርግጥ የሠው ፊት እንደማየት አስፈሪ ነገር የለም 15 ወራት ያለኝን አሟጥቼ ሥታገል የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ያለችበት ሁኔታ በሽታው እየጨመረ ስለሆነ የተሻለ ሕክምና ማድረግ እንዳለባት ሐኪሞች አረዱኝ:: የተጠየኩት የህክምኛዋ ወጪ ከአቅሜ በላይ ነው ህክምናውም በፍጥነት ህንድ ሀገር ሄዳ ካልታከመች ወደ ካንሠር ይቀየራል ተባልኩ
በጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያዎች እንደ መጨረሻ መፍትሄ የተደረሱበት ውሳኔ፤ በሽታው ከዚህ በላይ ሳይደርስ ወደ ካንሰር ሳይለውጥ በፊት ወደ ህንድ ሀገር ሄዳ እንድትታከም የሀኪሞች ቦርድ ወስኗል።

የታዳጊዋ ህይወት እጅግ አስጊ ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሀገር ሄዳ ሕክምናዋን እንድታገኝ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። ለህክምናው በአጠቃላይ ከ50,000 ዶላር (5 ሚሊዮን ብር) እንደሚያስፈልጋት ታውቋል። ይህን ለመሸፈን ደግሞ እጅግ በጣም ከአቅሜ በላይ ስለሆነብኝ ለአላህ ብላችሁ የልጄን ህይወት ታደጉልኝ ሰበብ እንድትሆኑና ወገናዊ ድጋፋችሁን እንድታደርጉልኝ ከልብ በሆነ ትህትና ጠይቀዋችኋል።
ሰዉ ለመርዳት ሰዉ መሆን ብቻ በቂ ነዉ
√ የአካውንት ቁጥሮች፦
1000665961242 ንግድ ባንክ
213116134 አቢሲኒያ ባንክ
0052261820101 ዘምዘም ባንክ

ተማም ሙዘሚል, ሳዲቅ አህመዲን እና ሙነወር አህመዲን

ስልክ፦0921339398 ሙነወር አህመዲን (አባት)

ስልክ :-0993468988 ተማም ሙዘሚል**https://t.me/+GVDu1cklUTkxYzc0

2 weeks, 4 days ago

**➻ለምን አታገባም?

⇝በዚህ ዘመን ያላገባ በሸይጣን መረብ ውስጥ መከራን ይጋታል!

❍ሸይኽ ሳሊህ አል'ፈውዛን፦

"ሴት ያለ ወንድ በመከራ ላይ ነች። ወንድም ያለ ሴት መከራ ውስጥ ነው። ተመጣጣኝ ጥንዶች በትዳር ከተቆራኙ የተሟላ ፀጋ ውስጥ ናቸው።"

[اعانة المستفد (2/220)]

➻አል' ኢማም አል' ጁወይኒይ አሽ ሻፊዒይ፦

"ላጤነት የእብደት ሰበብ እንደሆነ ሁሉ ኒካሕ እብደትን ከሚያስወግዱ ነገሮች አንዱ ነው።"

[نهاية المطلب (12/43)]

❍ኢብኑ ዓባስ፦

"አላህ ልጅ የሰጠው ሰው መልካም ስም ያውጣለት፤ በስነ ስርኣትም ኮትኩቶ ያሳድገው፤ ለአቅመ አዳም የደረሰ ግዜ ይዳረው!"

[رواه ابن ابي الدنيا في العيال (443/1)]

➻ሱለይማን አር'ሩሐይሊይ፦

"ያለ ምንም ምክንያት ከማግባት የሚያፈገፍግ ሰው ወደ ሐኪም ጎራ እንዲል እንመክረዋለን"

(منقول من محاضرة)

❍ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ፦

"እህትህን ወይም ሴት ልጅህን (ለጣሊበል ዒልም) የሸሪዓ እውቀት ተማሪ ለሆነ ወንድ መዳር ለአንተ ከዱንያና በውስጧ ካሉ ነገሮች ሁሉ በላጭ ነው!"

[البشائر في السماع المباشر ص 13 ]

➻ሸይኽ አሕመድ አን'ነጅሚይ፦

"ወንድ ልጅ መልካም ሴት ጋር ትዳር እስኪመሰርት ህይወቱ የተሟላና ደስተኛ አይሆንም። ሴትም እንደዛው።"

[تأسيس الاحكام (4/172) ]

❍ታላቁ ታቢዒይ ጣውስ ፦

"እስኪያገባ ድረስ የአንድ ወጣት ዒባዳ አይሟላም"
[السير (570/1)]

➻ታላቁ ታቢዒይ ኢብራሂም አን ነኸዒይ፦

"አግባ! ቤቷ ሆና የሚመግባት ጌታ በአንተም ቤት አንተንም እሷንም ይመግባቿል!"** @LIJ_MUAZ

2 weeks, 4 days ago

አላህን አመስግነው**

ያለ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ በዚህ ወቅት የቤቱ መሄጃ መንገድ እንኳ ጠፍቶት የሚደናበረውን፣ በግሮሰሪ ቤቶች ውስጥ ራሱን ስቶ የሚጨፍረውን፣ በተለያዩ የፈሳድ አይነቶች ተጠምዶ የሚገኘውን እትየለሌ ህዝብ አስበህ፤

አንተ ግን እስልምናን ጀሊሉ መርጦልህ ቤትህ ውስጥ በሰላም ከቤተሰብህ ጋር ቁጭ ብለህ ሐላል ነገር እየሠራህ ከሆነ አላህን አመስግነው።

«…الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي هَدَانَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِيَ لَوْلَا أَنْ هَدَانَا اللَّهُ!…»
«ለዚያም ወደዚህ ለመራን አላህ ምስጋና የተገባው ነው። አላህ ባልመራንም ኖሮ አንመራም ነበር።»
[አል-አዕራፍ: 43]** @LIJ_MUAZ

3 weeks, 4 days ago

*➡️አስተውል አንተ የአላህ ባሪያ‼️
💧*💧💧💧💧
💧💧💧
💧

💦 ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።

🌹 ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።

🌹 ሰወችን በመውደድ ብቻ ስትጠመድ የጌታህን ውዴታ እንዳትነፈግ ፍራ! ጥላቸው ማለት አይደለም ውዴታህ በልክ ይሁን!

💦 እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ እውነተኛ ሁን!

🌹 የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!

🌹 ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።

💦 ፍርድ ለመስጠት ከመወሰንህ በፊት ዳኛ ለመሆን አቅሙ እንዳለክ እራስክን ጠይቅ።

🍃 ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!

🍃ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!

🌹መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።

🌹 ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!

💦 ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።

💦መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ!!

📿ከተንኮል የፀዳ የተቀደሰ የሆነ አስተሳሰብ አላህ ይወፍቀን

በቴሌግራም ⤵️

::::::::::::: @LIJ_MUAZ :::::::::::::
::::::::::::: @LIJ_MUAZ :::::::::::::
★★★★★★★★★★★★★★**

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago