Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል

Description
قل عن أخيك" لا أدري لعله خير مني" فلا تقل كما قال إبليس"أنا خير منه"
@Nebil309

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

1 month, 3 weeks ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር 🌙

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

👆በ pdf ማንበብ ለምትፈልጉ ወንድምና እህቶች 👆

፨ እጅግ በጣም ጠቃሚ መልዕክት ስለሆነ በሰከነ መንፈስ እናብበው! 
ለሌሎችም ተደራሽ ይሆን ዘንድ share በማድረግ የኸይር ስራ ተቋዳሽ እንሁን!!

© Nebil alkeririy

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

1 month, 3 weeks ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙

*🖌 በሸይኽ በኢልያስ አሕመድ*

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
              ››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነው። ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ካልበዙ በስተቀር ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም!»

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445
____
@ustazilyas

1 month, 3 weeks ago

🔘-ሐሰን አል-በስሪ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፡-

"የአደም ልጅ ሆይ! ሳሊሆችን እወዳለው ብለህ ትሞግታለህ፣ ከስራዎቻቸውም ትርቃለህ። አመጸኞችን እንደምትጠላ ትሞግታለህ፣ ከነርሱ አንዱ ነህ። ስለርሱ እርግጠኛ ሆነህ ወንድምህንም በጥርጣሬ ጠልተሃል።”

📚(አዙህድ ሊሕመድ ኢብኑ ሐንበል - ክፍል አሥራ ዘጠኝ)

2 months ago
2 months ago
2 months ago
رحمة الله عليك يا شيخ أهل …

رحمة الله عليك يا شيخ أهل السنة

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

2 months, 1 week ago

«ዝክረ ረመዳን App»

√ ከጎግል ፕለይ ማውረድ ላልቻላችሁ Apk ፋይል አታች አድርገናል። ዝክረ ረመዳን፤ ከማስታወቂያ ነፃ ድንቅ የፆም ህግጋት መማሪያ አፕ በመጫን ረመዳንን በዕውቀት ይፁሙ!

@merkezuna

2 months, 1 week ago
2 months, 1 week ago

የጓደኝነት መስፈርቶች!!!

በ741 ዓ.ሂ የሞቱት ሙፈሲር ኢብኑ ልጁዘይ አልጙርናጢ እንዲህ ይላሉ፦

🌺ጓደኛ ሰባት መስፈርቶችን ሊያሟላ ይገባዋል

1⃣ ዐቂዳና አቋሙ ሱንና  ላይ የተመሰረተ፣

2⃣ አላህን የሚፈራ ሰው

✔️እምነቱ ላይ ቢድዓን የሚከተል ጌታውንም የማይፈራ ጓደኛ ከኖረው
ጓደኛውን ወደዛው መንገድ ሊያስገባው ወይም ሰዎች እሱም ልክ እንደጓደኛው ነው ብለው በመጥፎ ሊጠረጥሩት ይችላሉ። ምክንያቱም የሰው ልጅ የጓደኛው እምነትና አቋም ላይ ነውና የሚሆነው።

3⃣ አስተዋይ ሊሆን ይገባዋል! ሞኝን ጓደኛ ማድረግ ትልቅ አደጋ ነው።

*4⃣ስነ-ምግባሩ ያማረ ሊሆን ይገባዋል፣ ስነ-ምግባሩ የተበላሸ ጓደኛ በሂደት ጠላት ሊሆን ይችላል። ስነ-ምግባሩን ለመገምገም መጀመሪያ እሱን አስቆጥቶ ማየት አንዱ አማራጭ ነው፣ በቀላሉ የማይቆጣ ወይም ከቁጣው ቶሎ የሚመለስ ከሆነ ጓደኛ አድርገው።*

5⃣ ልቡ ንጹህና ሰላማዊ፣ ከሀሜትና ከምቀኝነት የራቀ፣ እንዲሁም ሁለት ፊት ያልሆነ፣ ተንኮልና ነገርን የማይፈልግ፤
*6⃣ቃልና መልካም ግንኙነቱ ላይ ጽናት ያለው የማይሰላችና ጸባዩ የማይቀያየር*፣

7⃣ አንተ ሃቁን እንደምትጠብቅለት ሁሉ እሱም ሃቅህን የሚጠብቅ ሊሆን ይገባዋል። ሃቄን እንደሚጠብቀው ሁሉ እኔም የሱን ሃቅ መጠበቅ አለብኝ የማይልን ሰው ጓደኛ ማድረግ ምንም ጥቅም አይኖረውም።»

{ምንጭ፦ "አልቀዋኒኑል-ፊቅሂያህ" ሊል-ኢማም ኢብኑ ጁዘይ}

🚫ማሳሰቢያ፥ ንግግሩ በወንድ ፆታ ቢሆንም መልእክቱ ግን ለሁሉም ነው!

🏷እነዚህንና መሰል መስፈርቶችን ከማያሟላ ሰው ጋር ከመቀራረብና ጓደኝነት ከመፍጠር ብቸኝነት ይሻላል!!
ለዲን ወይም ዲንን ሳይጎዳ ለዱኒያ እንጂ  ለሌላ ዓላማ ጓደኝነት ልንፈጥር አይገባም!!

🍀የሙእሚን ዋናው ጓደኛው ቁርኣን ነው!!

✍🏻ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
[ረቡዕ 27/12/1440ዓ.ሂ]

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

2 months, 1 week ago
ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago