ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል

Description
قل عن أخيك" لا أدري لعله خير مني" فلا تقل كما قال إبليس"أنا خير منه"
@Nebil309

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 3 days, 21 hours ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 months ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 4 weeks ago

5 days, 19 hours ago
6 days, 2 hours ago

🌺▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂🌺

👆تعليم سورة البلد مع القارئ الشيخ محمود خليل الحصري

🌺▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂🌺

👆ለአዋቂም ለልጆችም የሚጠቅም የቁርኣን ትምህርት በተጅዊድ!
ከእውቁ የቁርኣን ቃሪእ ማሕሙድ ኸሊል አልሁሶሪ ጋራ ሱረቱል በለድ!

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

@ibnuljezeriy

6 days, 8 hours ago
1 week, 6 days ago
የቀበጡ ለታ!

የቀበጡ ለታ!

1 week, 6 days ago
***🕋*** **በቀንም በማታም ድምቀት የተሞላበት ቦታ**!

🕋 በቀንም በማታም ድምቀት የተሞላበት ቦታ!

#حرم
#الكعبة

2 weeks ago
ኢብኑል ጀዘሪይ የቁርአን ትምህርት ማዕከል
3 weeks, 2 days ago
  1. ሌላው ችግራቸው ደዕዋቸው አብዛኛውን ኢስላማዊ ድንጋጌዎች ችላ በማለት የተወሰኑ ጉዳዮች ላይ #ብቻ መገደቡ ነው። የጠራውና ከፍ ያለው አላህ ደግሞ {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ኢስላም ጥቅልል ብላችሁ ግቡ} ይላል። ኢስላምን ከሁሉም አቅጣጫው ያዙት እያለ ነው። በርካታ ታላላቅ ዓሊሞች ደዕዋቸውን የሚተቹት በዚህ ሳቢያ ነው። እርግጥ ችሎታው በሌላቸው ነገር ውስጥ እንዲያወሩ ልናስገድዳቸው አይደለም። እንዲያውም በማያውቁት ነገር እንዲያወሩም አንፈቅድላቸውም። …
  2. ሌላኛው ችግራቸው ደካማ የሆኑ፣ ቅጥፈት እንደሆኑ የተደረሰባቸው፣ መሰረተ ቢስ ሐዲሦችን ማውራት ነው። መልእክተኛው ﷺ “ከኔ ብዙ ማውራትን ተጠንቀቁ! ያላልኩትን በኔ ላይ የተናገረ መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ይላሉ።…” (ከሸይኽ ሙቅቢል “አልመኽረጅ ሚነል ፊትናህ” ኪታብ ተነካክቶ የተወሰደ።) [ገፅ፡ 95-97]
    አንዳንዱ “አኽላቅ አላቸው” ይላል። ወንድሞች እንዲህ እያልን እነሱንም አናስተኛቸው። ሌሎችም በነሱ እንዲሸወዱ መንገድ አንጥረግ።
  3. አኽላቅ የሚጀምረው ከተውሒድና ከሱና ነው። የአላህን ሐቅ ሳያከብሩ ለፍጡር አንገት ቢሰባብሩ ምን ዋጋ አለው? ሙስሊምን ‘ሙስሊም’ ያሰኘው ከአኽላቁ በፊት ዐቂዳው ነው። ያለበለዚያማ ሁሉም ሃይማኖቶች ወደ መልካም ስነ ምግባር ይጣራሉ እኮ! መልኩና አፈፃፀሙ ላይ ልዩነት ቢኖርም።
  4. ደግሞስ እስኪ በአኽላቅ ወደ ተውሒድና ወደሱና ጥሯቸውና የሚሰጧችሁን መልስ እዩት። እኔ ተግባራዊ ምሳሌ አለኝ። ከነሱ ለስልሶ በተጨባጭ ያየባቸውን የዐቂዳ ክፍተት ሊያርማቸው የሞከረን ወንድም “እንወያይ” ብለው ሌላ ክፍል ወስደው ድብደባ ነበር የጀመሩት። የሆነ ጊዜም እነሱ ኹሩጅ ከወጡበት መስጂድ ሌላ ሰው ደዕዋ ሲያደርግ ሲረብሹ አይቻለሁ። የሚገርመው ተቃውሞ ሲያሰሙ ይሰጥ የነበረው ደዕዋ ስለ አኽላቅ ነበር። ይበልጥ የሚደንቀው ደግሞ ካንቀሳቃሾቻቸው አንዱ በእድሜ በሰል ያለ ነው ቁርኣን ቢያጣቅሱለት “የፈለጋችሁትን ቁርኣን ብትጠቅሱ አልቀበልም!” ብሎ በድፍረት አሳቀቀን። ይሄስ አኽላቅ ነው?
  5. እኛ እነሱ ጋር “ጭራሽ ምንም ኸይር የለም” አንልም። የትኛውንም ሃይማኖት ብንመለከት በእርግጠኝነት ከሌሎች ጋር የሚያጋራቸው የሆነ ኸይር አይጠፋም። ሆኖም ግን የምናየው ኸይር በተጨባጭ ያለውን ጥፋት ዝም እንድንል አያደርገንም። ጴንጤዎች ጋር የምናየው የሆነ መልካም ባህሪ ስለነሱ እንድንከላከል እንደማያደርገን ማለቴ ነው። (ድንበር ተሻግሮ “እያከ - ፈርክ ነው” የሚለኝ እንደማይኖር ተስፋ አደርጋለሁ።)
  6. “ዓሊም ምንጭ ነው ዳዒ ግን ደመና ነው። የተጠሙ ሰዎችን ካሉበት እየተንቀሳቀሰ (ኹሩጅ እያደረገ) ያደርሳል” እያሉ የራሳቸውን ሚና ከዓሊሞቹ ሚና በላይ ሲያደርጉ በኪታብ ነበር ያነበብኩት። አሁን ግን ወላሂ ባይኔ አየሁኝ በጆሮዬ ሰማሁኝ። ግን ይሄ አኽላቅ ነው ኢኽወቲ ፊላህ?

ዑለማዎች ስለተብሊግ ምን አሉ
~
ምናልባት ተብሊግን መቃወም ለኡማው አንድነት አለመጨነቅ፣ ህዝቡን ለመበታተን ከጠላት ጋር መተባበር የሚመስለው ቢኖር አይገርምም። ምክንያቱም በማስረጃ ከመነጋገር ይልቅ የተቃወማቸውን ሁሉ በዚህ መልኩ ማጠልሸትና ማሳጣት የሚቀናቸው ሰዎች በርክተዋልና። ለማንኛውን አስተዋይ የሆነ፣ ለዲኑ ዋጋ የሚሰጥና ነገሮችን በእርጋታ የሚመረምር ሰው ይጠቀም ዘንድ ዓሊሞች ምን እንዳሉ የጥቂቶቹን አባባል ልጥቀስ:-

  1. ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአልባኒ ረሒመሁላህ፡- “እኔ የማምነው የተብሊግ ደዕዋ በአላህ ኪታብና በመልእክተኛው ﷺ ሱና ላይ ያልተመሰረተ ዘመናዊ ሱፊያ እንደሆነ ነው። የሚገርመኝ ለደዕዋ ብቁ እንዳልሆኑ እራሳቸው እያመኑ ደዕዋ ሊያደርጉ መውጣታቸው ነው። ደዕዋ ላይ መሰማራት ያለባቸው የእውቀት ባለቤቶች ናቸው። ልክ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከሰሐቦቻቸው መልእክተኞችን ሲልኩ ያደርጉ እንደነበረው። ከታላላቅ ሶሐቦቻቸው ዑለማዎቹን ፉቀሃኦቹን መርጠው ነበር ሰዎችን ስለዲን ስለ ኢስላም እንዲያስተምሩ ይልኩ የነበረው…”

  2. ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ብኑ ባዝ ረሒመሁላህ “የተብሊግና የኢኽዋን ቡድኖች ከሰባ ሁለቱ ጠፊ አንጃዎች ውስጥ ይገባሉ ወይ” ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ብለው ነው የመለሱት፡- “አዎ ከሰባ ሁለቱ ውስጥ ይገባሉ። የአህሉ ሱናን ዐቂዳ የሚቃወም ከሰባ ሁለቱ ውስጥ ይገባል።”

  3. ሸይኽ ሐሙድ ቱወይጂሪ ረሒመሁላህ ስለ ተብሊግ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፡- “እኔ ጠያቂውንም ዲናቸው ከሺርክ ቆሻሻዎች፣ ድንበር ከማለፍ፣ ከቢደዕና ከኹራፋት ሰላም እንዲሆን የሚጓጉ ሌሎችንም የምመክረው ከተብሊጎች ጋር እንዳይቆራኙ ነው። ሰዑዲ ውስጥ ይሁን ሌላ ሀገር ፍፁም ከነሱ ጋር እንዳይወጡ። ምክንያቱም ቀለለ ቢባል በዐቂዳቸውም በአካሄዳቸውም የቢድዐ፣ የጥመትና የድንቁርና ባለቤቶች ናቸውና። በእንዲህ ዓይነት ክፉ ሁኔታ ላይ ከሆኑ ደግሞ ያለጥርጥር ሰላም ያለው እነሱን በመራቅ ነው።”

  4. ሸይኽ ዑበይድ አልጃቢሪ፡- “የተብሊግ ቡድን የተከናነበ ሱፊያ ነው። ወደ አላህ በመጣራት ስም የሚያንፀባርቀው ነገር የሱፊያና የቡድናዊ መጋረጃው ነው። ለዚህም ነው ከረጂም ጊዜ ጥናት በኋላ በአራቱ የሱፍያ ጦሪቃዎች (ነቅሸበንዲያህ፣ ቃዲሪያህ፣ ሰህረወርዲያህ እና ጂሽቲያህ) ቃልኪዳን የሚያስገቡት። የቡድኑ አካሄድ ተከታዮቹን በእውቀት እንዲጠቀሙ አያደርግም። እውቀት ያለው ከውስጣቸው ከተገኘ ያገኘው ከነሱ አይደለም። ጤነኛ አቂዳ ያለው ከተገኘም ይህን የተማረው ከነሱ አይደለም። … እኔ ባስተዋልኩት መሰረት ቡድኑ አራት እርከኖች አሉት። የመጀመሪያው እርከን፡- የሱፊያ ቁንጮዎች ናቸው። መሪዎቻቸውና ለነሱ ቃል ኪዳን የገቡት።
    ሁለተኛው እርከን፡- የተታለሉ ዓሊሞችና ተማሪዎች ናቸው። ቡድኑ በጎን በሚያንፀባርቀው መልካም ገፅታ የተሸወዱ።
    ሶስተኛው እርከን፡- ተራው ሰው ነው መሃይማኑ። እስከማውቀው ብዙሃኑ የቡድኑ ተከታዮች እነዚህ ናቸው።
    አራተኛው እርከን፡- ፈር ለቀው የነበሩ የሙስሊሞች ልጆች ናቸው። በየባሩ፣ በየቡና ቤቱ … ሲልከሰከሱ ቆይተው የዚህ ቡድን አባላት ቀድመው ደርሰው የያዟቸውና ያደራጇቸው በቡድኑ እንደተቀኑ የሚያስቡ ናቸው። የመጀመሪያውን እርከን በተመለከተ አላህ ካልሻላቸው በስተቀር የመመለሳቸው ነገር ተስፋ አስቆራጭ ይመስለኛል። ቀሪዎቹ ሶስቱ እርከኖች ግን ልንመክራቸው እውነቱን ግልፅ ልናደርግላቸው ግዴታ አለብን እላለሁ። ብዙዎቹ እውነቱ ሲገለፅላቸውና ሲያውቁት የቡድኑን ክፍተቶችም ሲረዱ ይተዋቸዋልና።…” (ከካሴት የተወሰደ ነው)

  5. ሸይኽ ዘይድ ብኑ ሃዲ ረሒመሁላህ፡- “የተብሊግ ቡድንን በተመለከተ ወላሂ እኛ የአላህ ዲን 24 ሰዐት ሙሉ ወደ ህዝብ ቢደረስ እንወዳለን። ባይሆን ሰዎችን እንዴት ነው የምናስተምረው ጤነኛ የሆነን እውቀት ትክክለኛውን መንገድ ነው ልናስተምር የሚገባው።… ላኢላሃኢለላህን አሳምረው ሳይዙ በየአፅናፉ መውጣቱንና መዝመቱን ግን ይህን ነው የጠላንባቸው።…"

እነኚህንና ተጨማሪ ፈትዋዎችን
1. “አልጀዋቡል በሊግ” የሚል ኪታብ ላይ ማግኘት ይቻላል። ይበልጥ ማንበብ ከፈለጉ እነኚህን ኪታቦች ያገላብጡ
2. አልቀውሉልበሊግ ፊተሕዚር ሚንጀማዓቲ ተብሊግ- ሐሙድ አቱወይጂሪ
3. አልጀማዓቱል ኢስላሚያህ (471-538)- ሰሊም አልሂላሊ
እና ሌሎችም እንደ ተቅዩዲን አልሂላሊ፣ ሰዕድ አልሑሰይን የፃፏቸውን ኪታቦች ብናነብ መልካም ነው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 29/2006)

3 weeks, 2 days ago

ጥቂት ስለ ተብሊጎች
~
ሰሞኑን የተብሊግ ደዕዋ በተደጋጋሚ እያጋጠመኝ ነው። ታዲያ ግርም የሚለኝ ኹሩጅ የወጣው ሁሉ ተረኛ እየሆነ ሲናገር በአንድ አይነት ነገር መጀመራቸው ነው። “እና ምን ችግር አለው ነብዩ ﷺ በኹጥበተል ሐጃ እንዲጀመር አስተምረው የለ?” እንዳይባል። በሱ ቢጀምሩማ እንዴት በታደልነው?! እንዲያውም የነብዩ ﷺ ኹጥባ መክፈቻ ውስጥ ያለውን “መጤ ነገር ሁሉ ቢድዐ ነው። ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው። ጥመት ሁሉ ወደ እሳት ነው” የሚለውን ሲሰሙ ውስጣቸው የሚጓሸው ቀላል አይደሉም። ልክ የኛ ንግግር የሆነ ይመስል። ብቻ አሁን ከሰሞኑን እያጋጠመኝ ያለው ነገር አንዱ ይነሳና “ኢንሻአላህ የዒሻ ሶላትን በጀማዐ አሰጋገደን፤ ልናመሰግነው ይገባል። ኢንሻአላህ ካመሰገናችሁኝ እጨምራችኋለሁ፤ ከካዳችሁ ግን ኢንሻአላህ አያያዜ የበረታ ነው ይላል ኢንሻአላህ። ስለዚህ አልሐምዱሊላህ ማለት አለብን።” ከዚያ በጀማዓ “አልሐምዱሊላህ” ይላሉ። “ኢንሻአላህ አዛን የተደረገው ለሁሉም ሰው ነበር። የመጣነው ግን እኛ ብቻ ነን። እኛ ብልጥ ስለሆን አይደለም ኢንሻአላህ። እኛ ጀሃነምን ስለፈራን ጀነትን ስለፈለግን አይደለም የመጣነው ኢንሻአላህ። አላህ መርጦን ነው በተውፊቁ ነው ያመጣን ኢንሻአላህ።” “እሳት ለማቃጠል የአላህ ፍቃድ ያስፈልገዋል ኢንሻአላህ፤ ቢላዋ ለመቁረጥ ኢንሻአላህ የአላህ ፍቃድ ያስፈልገዋል።” ይቀጥላሉ። “ኢንሻአላህ ወንድሞቼ ሰማዩን የፈጠረው አላህ ነው ኢንሻአላህ ተራራውንም ባህሩንም መሬቱንም የፈጠረው ኢንሻአላህ አላህ ነው። የሚረዝቀን አላህ ነው ኢንሻአላህ።”
በዚህ አይነት ቋንቋ ሰርክ ሲደጋግሙ አስቡት። 0ስርም፣ መግሪብም፣ ዒሻም ላይ የተነሳው ያለምንም መሰልቸት እንዲሁ ይላል። ሱብሐነላህ! አንዳንዶቹ “ይህን የሰጠን አላህ፤ ይህን የሰጠን አላህ” እያሉ አይናቸውን፣ አፍንጫቸውን… ተመስጠው ይነካካሉ። እስኪ አሁን ይሄ ማስተማር ነው ማስተኛት? ሸይኽ ሙቅቢልን አላህ ይማራቸውና የነኚህን ሰዎች ደዕዋ “የሞተ ደዕዋ ነው” ይላሉ። እንጂማ ይህንን እውነታ እነ አቡ ጀህልስ መቼ ዘነጉት? ይሄው እኮ ቁርኣን ላይ እየተገረ!
{“ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው? መስሚያዎችንና መመልከቻዎችንስ የሚቆጣጠረው ማነው? ህያውን ከሙት ሙቱን ከህያው የሚያወጣውስ? ነገርን ሁሉ የሚያስተናብረውስ ማነው?” በላቸው። “አላህ ነው” ይሉሃል። “ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) እሱን አትፈሩትምን?” በላቸው።} [ዩኑስ፡ 31]
{ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በርግጥም “አላህ ነው” ይሉሃል።} [ዙኽሩፍ፡ 87]
* {“ሰማያትንና ምድርንም ማን ፈጠራቸው?” ብለህ ብትጠይቃቸው “አሸናፊው ጥበበኛው (አላህ) በርግጥም ፈጠራቸው” ይላሉ።} [ዙኽሩፍ፡ 9]

ወንድሜ ሆይ! ከንዲህ አይነት የቢድዐ አካሄድ ራስህን አርቅ። ያለበለዚያ በዲንህም በዐቅልህም ላይ ስትቀልድ ነው የምትኖረው። ወላሂ በያገሩ መዞርህን እንደ ስኬት አትቁጠረው። ለዲንህ ከተቆረቆርክ ቁጭ ብለህ ተማር። ከዚያም አላህ ካገራልህ 3 ቀን፣ 40 ቀን በሚል ካሪኩለም ሳትገደብ ወጥተህ አስተምር። ስለዲንህ ምንም የማታውቅ ሆነህ ሳለህ “ኹሩጅ እወጣለሁ” ካልክ ግን 40 ቀን አይደለም 40 አመት ብትዞር ዐቂዳህን አታሻሽልም። እንዲያውም ይበልጥ ጥፋትህን እንደ ልማት የምታይ፣ ለሱና ውስጥህ የሚደፈርስ፣ ስሜትህን የሚነኩ የቁርኣን አያዎችና ሐዲሦች ሲነገሩ በጥላቻ የምትሞላ፣ ቢድዐ የማይጎረብጥህ አደገኛ ፍጡር ነው የምትሆነው። ከውስጥ ያየሃቸው ነገሮች እንዳያማልሉህ። ኢብኑ ወዷሕ ረሒመሁላህ “ቀደምቶች ዘንድ ከአላህ በሚያርቀው ነገር ወደሱ ሊቃረብ የሚተጋ ስንት አለ?! እያንዳንዱ ቢድዐ ውብና አንፀባራቂ ነው (አማላይ ነው)” ይላሉ። ሱፍያኑ ሠውሪይም ረሒመሁላህ እንዲሁ “በላዩ ላይ ውበት የሌለበት ቢድዐ የለም” ይላሉ። ባይሆንማ፣ የሚያማልል ነገር ባይኖረውማ ቢድዐን ማን ቁም-ነገር ብሎ ይይዘው ነበር?! ወንድሜ! ነገሩ በዲን ስም ስለሚሰራ አይሸውድህ። ቢድዐንኮ ቢድዐ ያሰኘው በዲን ስም መሰራቱ ነው፣ እንደ ዒባዳ መያዙ። ቢድዐንኮ ይበልጥ አደገኛ የሚያደርገው በዲን ስም ስለሚሰራ የገባበት ሰው በላሉ አለመንቃቱ ነው። ይህን እውነታ ተረድተው እኮ ነው ሱፍያኑ ሠውሪይ ረሒመሁላህ “ቢድዐ ሸይጣን ዘንድ ግልፅ ከሆነ ወንጀል ይበልጥ የተወደደ ነው። ምክንያቱም ከወንጀል ሰዎች የመመለስ እድላቸው ሰፊ ነው። ከቢድዐ ግን የመመለስ እድላቸው ጠባብ ነው” ያሉት። ዝሙት የሚሰራ ሰው በጥፋቱ “አጅር አገኛለሁ” ብሎ አያልምም። ቢድዐ የሚሰራ ሰው ግን በዲን ስም ስለሚሰራው ወደ አላህ “ያቃርበኛል” ብሎ ይጠብቃል። ታዲያ ከሁለቱ የመንቃት እድል ያለው ማንኛው ነው? ሐጃጅ ብኑ ዩሱፍ ቃላት ከሚገልጸው በላይ እጅግ አረመኔ ነበር፣ ስንት ታላላቆችን የጨረሰ ጨፍጫፊና ሰው በላ። ዐምር ብኑ ዑበይድ ደግሞ የጠማማው ሙዕተዚላ አንጃ ቁንጮ ነበር። የበስራው ታላቅ ዓሊም ሰላም ብኑ አቢ ሙጢዕ ረሒመሁላህ “ከአላህ ጋር በዐምር ብኑ ዑበይድ የስራ መዝገብ ከምገናኝ ይልቅ በሐጃጅ መዝገብ ብገናኘው እመርጣለሁ”ይላሉ። የምታስተውል ከሆንክ እንዲህ ዓይነቱን የቀደምቶች አባባል ስትመለከት ለቢድዐ ያለህ ተገቢ ያልሆነ እይታ እንደገና ያስደነግጥሃል። አዎ የቢድዐው መልክና መጠን ሊለያይ ይችላል። ቢሆንም ቀደምቶቻችን እንድናስተውል እየጋበዙን ነውና ግብዣውን እንቀበል። ይሄው ደግሞ ሌላኛው ምን እንደሚሉ “መስጂድ ውስጥ ማስቆም የማልችለው ቢድዐ ከማይ ማጥፋት የማልችለው እሳት ባይ እመርጣለሁ።”
ወንድሜ ሆይ ከቢድዐ ራቅ። ከተብሊግ ተጠንቀቅ። ወላሂ ላስከፋህ አይደለም ይህን የምፅፈው። ጉዳይህ ቢያስጨንቀኝ የዐቂዳህ ነገር ቢያሳስበኝ ነው። እነሱ ጋር ሆነህ ተውሒድህ አይስተካከልም። ይሄ የኔ አባባል አይደለም ይሄውና ዓሊሞቹ ምን እንደሚሉ፡-

  • “ተብሊጎች ከሚተቹበት ነገር
  • አንዱ ለዐቂዳ ትኩረት አለመስጠታቸው ነው። አንድ ሰው ከነሱ ጋር አርባ አመት ተቆራኝቶ ከቢድዐና ከሺርክ እምነቱ የማይላቀቅ አለ። ይሄ ከሱና ተፃራሪ የሆነ አካሄድ ነው። ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት ነብዩ ﷺ ሙዓዝን ወደ የመን ሲልኩት ሰዎችን ከአላህ ውጭ በሐቅ ሊያመልኩት የሚገባ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ በማስተማር እንዲጀምር ነው በእርግጥም ያዘዙት። ከዚህ የምንረዳው ወደ ተውሒድ መጣራት ከሁሉም ነገር እንደሚቀድም ነው። ለተውሒድ እጅ የሚሰጥ ሰው ከሸሪዐ ጋር የሚፃረሩ ነገሮችን በሙሉ ለማራገፍ ዝግጁ ነው።
  • ሌላው ችግራቸው ለዒልም ትኩረት አለመስጠታቸው ነው። ለምሳሌ ከነሱ ጋር ሃያ አመት ያሳለፈ ታገኛለህ። ነገር ግን በጅህልናው ላይ እንዳለ ነው። ከዒልም ችላ ማለት ከኸይር ችላ ማለት ነው። ነብዩ ﷺ “#አላህ_መልካም_የሻለትን_ሰው_ዲኑን_ያሳውቀዋል” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] ወደ አላህ የሚጣራ ሰው ከሌሎች በበለጠ ጠቃሚ ለሆነ እውቀት ይጓጓል። ለምን? ሰዎችን በእውቀት ላይ ሆኖ መጣራት ይችል ዘንድ። ከፍ ያለው ጌታ እንዲህ ይላል፦ {“ይቺ መንገዴ ናት፤ #በግልፅ_ማስረጃ ላይ ሆኜ ወደ አላህ እጣራለሁ፤ እኔም የተከተለኝም እንዲሁ” በል።} [ዩሱፍ፡ 108] የአንድ ዓሊም መድረክ ከመቶ ጃሂል መድረክ የተሻለ ነው።
3 weeks, 2 days ago

https://t.me/DrMelihaMedicalCenter/19888

👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ስለ ኪንታሮት አጭርና ጠቃሚ ገለፃ ስለሆነ ሊንኩን ተጫኑና አንብቡት! ይጠቅማችኋል።

አላህ ከመሰል በሽታዎች ይጠብቀን🤲

2 months, 3 weeks ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር 🌙

ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

👆በ pdf ማንበብ ለምትፈልጉ ወንድምና እህቶች 👆

፨ እጅግ በጣም ጠቃሚ መልዕክት ስለሆነ በሰከነ መንፈስ እናብበው! 
ለሌሎችም ተደራሽ ይሆን ዘንድ share በማድረግ የኸይር ስራ ተቋዳሽ እንሁን!!

© Nebil alkeririy

#أبو_عبد_الله_نبيل_الكريري

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 3 days, 21 hours ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 months ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 5 months, 4 weeks ago