Natnael Dagnaw| ናትናኤል ዳኛው

Description
አጫጭር ልብ-ወለዶች|Short Stories| መጣጥፎች|Essays 'n' Articles| እይታዎች perspectives|

መጻሕፍት፦ •ወደ 'ራስ•| የአጫጭር ልብ ወለዶች መድበል
እና •ጉራማይሌ| የዘመናችን አጫጭር ታሪኮች• ከሌሎች ደራስያን ጋር፡፡

Any Comments☞ https://t.me/NattyDM2
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

2 Jahre, 8 Monate her

ሕይወት ውስጥ ሞት የለም? ሕይወት ውስጥ ሕልም፣ ሕልም ውስጥ ሕይወት የሉም? ንቃት ምንድር ናት? ማለም ምንድር ነው? መኖር የምንለው ሕልማችንን ቢሆንስ? ሕይወት ወደ ሞት መንቃት ናትና 'ከዚህ ሕልም የመውጫ ብቸኛው መንገድ ወደ ሞት ማደግ ይሆናል፡፡'*
የሰው መኖር ዓመታት ናቸው ደቂቃዎች? ሰከም ሰከም እያልን በአደባባይ ስንተያይ ይመስለናል አይደል በሕይወት ያለን? መኖር የሞት መንገድ ናትና፤ በየቀኑ ነው የምንሞተው፡፡ መኖራችን ከደቂቃ አታልፍም፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ ስንት ጊዜ በሕይወትና ሞት መሐል እንመላለሳለን? የምንኖረው ወደ ሁዋላ፥ ሞታችን ደግሞ አሁን ነው፡፡ ሕልው ነኝ የሚል ሁሉ ቅድምና አሁን መሐል ዥዋዥዌ የሚሰራ ክላውን ነው፤ ጊዜና እግዜር እየተቀባበሉ አብዶ የሚሰሩት፡፡

  • 'The only way to get out of this dream is to awaken into death.' Danilo Kis, The Legend of sleepers

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 8 Monate her

°°አንድ እሁድ በተጋደምንበት የድሮ ነገር ተነሳና ስለፃፍናቸውና ስለተፃፉልን ደብዳቤዎች ስናወራ ፥ የፃፍካቸውን ካላየሁ ስትል የድሮ የፎቶ አልበም ጋር ያስቀመጥኳቸውን አንድ ሁለት ደብዳቤዎች አሳየሁዋት፡፡ ደብዳቤዎቹ በጥቂት ዓመታት ልዩነት ትዕግስትና ፍሬ ለተባሉ ሁለት ሴቶች የተፃፉ ናቸው፡፡ እየሳቀችም እየተገረመችም እያየሁዋት አነበበቻቸው፡፡ 'ፍሬ ላይ አድገሃል..' አለች፡፡ እውነቷንም ነበር፤ ትዕግስት ላይ ልጅ ነበርኩ፤ ደግሞ ከሷ የማስታውሰው ቤታቸው ሄጄ የጠጣሁትን የሚጥም ሻይ ብቻ፣ ድንክ ቡፌያቸው ላይ በፍሬም የተቀመጠ መለስ ዜናዊ አባቷን መስሎ እያስፈራራኝ(ልንገረሽ አባትሽን ካድሬ ነው እንዴ? ብያለሁ በልቤ፤ ልጆቹ አያታቸው ወይ አጎታቸው መስሏቸው ቢያድጉ ቅር አይለውም? ብያለሁ በልቤ) ፤ ክብሳት የመሰለ ፣ ከብርቱካናማ ከናቴራዋ በላይ ቀስቱ የተወደረ ጡቷን እንዳላይ እያጉረጠረጠብኝ... ውስጤ የቀረ ይሄ ብቻ መሆኑ ያሳዝነኛል፤ ጡቶችሽን አስተውል ነበርና እንደ አባይ የሚሞሉበትና የሚጎድሉበት ወቅት እንዳለቸው አስባለሁ፡፡ ሲሞሉ እየማለልኩ፥ በውስጤ ይቺ ልጅ ቆልቷታል፣ ይቺ ልጅ አፍልታለች እል ነበር... የሆነው ሆኖ ሰላም ላንቺ ባለሽበት እህቴ... ሰላም ለጡቶችሽ ልጅና ባል ምገዋቸው ለተዘለሱ፣ ሰላም ለጣቶችሽ ያን የሚጥም ሻይ ላፈሉልኝ (ምን ነበረ ያልኩሽ? በሻይ የሴት ልጅን ሙያ መለካት ይቻላል? አዎ አልሽ የዋህ እህቴ ከጎኔ ተቀምጠሽ ፎቶዎች እያሳየሽኝ፥ እና ልንገርሽ የዛኔ የሰጠሽኝ ፎቶሽ ዛሬም እኔ ጋ አለ፣ ሰገን አይታው እህትህ ጸደይን ትመስላለች አለችኝ፣ መች ነግሬያት አንቺ መሆንሽን)፣ ሰላም ለሮማን ዓይኖችሽ ሆነ ብዬ አላይሽ ስል እይታየን ፍለጋ ለተንከራተቱት፣ ሰላም ለአፍሮሽ 'ሄይ ዘሪቱ ከበደ' አስብሎ በጎረምሳ ላስተረበሽ፣ ሰላም ላለምኩት ግን ላላየሁት በጭኖችሽ መሐል ላለ ደናኪል (ይመስለኛል እንደ ከንፈሮችሽ ጠይም ወዛም)፡፡

የገረመኝ ግን ሰገን ቀናች ፥ ቅናቷ አጉል ስለሆነባት 'አይ ኖው ልክ አይደለሁም ግን ቀንቻለሁ!' አለች በከፋው ገፇ ለመሳቅ እየሞከረች፡፡ አቅፌ ደረቴ ላይ አስጠጋሁዋትና ላንች ከፍሬ የተሻለ እጽፍልሻለሁ አልኳት ግንባሯን ስሜ፡፡ 'የሴቶችህ ስም ግን ሲገርም' አለች 'ትዕግስት፣ ፍሬ... አባባል ይሰራል'ኮ ትዕግስት መራራ ናት ፍሬዋ ግን ምናምን...' ተያይዝን በሳቅ ጠፋን፡፡ አልኳትም 'አንቺ ግን ሰገን ነሽና ማረፊያ... ሰገነት እጸ-ገነት' ከፍስሃ ጋር ደረቴ ላይ ተለጥፋ የተኛነውን ከ'ናት ግት እንደሳቡት ወለላ አስበዋለሁ፡፡ °°

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 8 Monate her

°°የቴአትር ቤቱ በረንዳ ደረጃ ላይ ለፎቶ የሚመቻች ጎልማሳ መነጽር ያደረገ ሰው ይታየኛል፡፡ በጎኔ የሚያልፉ ሰዎች በተለይ ሴቶች ቆም እያሉ ያዩታል፡፡ አንዷ ሴት 'እይ አዳምዬ እኮ ነው ደራሲው' ስትል ሰማሁዋት፡፡ በውስጤ እዚህ ሀገር አዳም የሚባል ታዋቂ ደራሲ አለ? እላለሁ፡፡ ከሴቷ ጋር የነበረች ሌላ ወጣት ሴት 'He seems a bit depressed!' አለች በአፈ ፈረንጅ፡፡ ሌላኛዋ
'ቢሆን አይገርምም፡፡ ግን አያምርም?' አለች
ያቺኛዋ 'ነይ ባክሽ!' እያለች እጇን ይዛ ጎተተቻት፡፡ ጸሐፊውን ፎቶ ያነሳው ወጣት እያሳየው የሆነ ነገር ያወራዋል፤ ሰውየው በኃይል ሳቀ፥ ሲስቅ ልጅቷ ካለችው የበለጠ ዲፕረስድ ይመስላል፡፡ የደረበውን ጥቁር ጃኬት እያወለቀ አልፈውኝ ወደ ራስ ሆቴል በሚወስደው መንገድ መራመድ ሲጀምሩ ትኩረቴን ግድግዳው ላይ ወደ ተለጠፉት ፖስተሮች መለሰኩ፡፡ ፖስተሮቹን አንብቤ ወደ ሔዱበት አቅጣጫ ሳይ የፀሐፊው እጅ ላይ የተለኮሰች ሲጋራና ከሷ እየተንበለበለ የሚወጣ ጭስ ታዩኝ፡፡°°
/ከተረክ/

©ናትናኤል ዳኛው

2 Jahre, 9 Monate her

°°ለድሆች እየታገለ ድሃ ሚስትና ልጆቹን ከበደለ፤ ስለተራቡትና ስለተገፉት እታገላለሁ እያለ ልጆቹን ለርሃብና ሞት ገፍቶ ከሰጠ ማርክስ በተባለ ፂማም ሽማግሌ ወንጌል የተጠመቁ ለሀገራችን እያሉ ሀገራቸውን የበሉ፣ ለትውልዳችን እያሉ ትውልዳቸውን የጨረሱ ይብልዎ አባቶች ፥ ዛሬም ወንጌላቸው በሌላ ወንጌል ተሽሮም ያልቀዘቀዙ፣ ሥህተት ያላስተማራቸው በነሱ ልክ እኛን ሊሰፉ ይታትራሉ፡፡ ግን ትናንትም ዛሬም ሥህተት ናቸው፡፡ አንድ ልክነታቸው ከስህተታቸው አይማሩም፡፡ የተጠመቁት በእሳት ይመስላል፤ የማርክስ ብዕር ትባላለች፡፡ ዘ ኮምዩኒስት ማኒፌስቶ ከአዲስ ኪዳን ይልቅ ያጸናል፡፡ ከማርክስና ከክርስቶስ በአማኞቹ ልብ ጸንቶ የሚኖረው ማን ነው?°°

/ከተረክ/

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 9 Monate her

°°እሷ እህቴ እንደኔው ሺህ ችግሮች እንዳሉባት አውቄ እንዳዝንላት ስንት ሕይወት ያስፈልገኛል? የሚያውቁትም የማያውቁትም ፍርሃት ልባቼውን ያጎበጠባቸው ናቸውና ወንድሞቼ ብልህ ብሆን ፈገግ ልልላቸውና ላፍታ ሸክማቸውን ላቀል በተገባ፡፡ በራሴ የ'ነኝ'ና ልምድ ቅርፊት ተከልዬ ሌላውን ልዳኝና ልፈርድበት ስቸኩል ያን ጊዜ እውነት ከኔ ራቀች፡፡ ይቺ እህቴ እንዲህ እንድትሰራ በየት እንዴት አለፈች? ያሰረኝ አስሯታል፣ የጠለፈኝ ጠልፏታል፣ያስፈራኝ አስፈርቷታል ታዲያ ለምን ለራሴ ሳዝን ለሷ ማዘን ተሳነኝ!
የሰው ልጅ የሚያውቀውም የማያውቀውም ኃይል የሚነዳው መጻጉዕ ነው፡፡ የገዘፈ መስሎ ከላባ የሚቀልል፣ አዋቂ መስሎ ጉንዳን በብልህነት የምትልቀው፣ ትጉህ መስሎ ንብ በበረከት የምትተርፈው...°°

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 9 Monate her

°°ግድግዳው ላይ የተሰቀለ ስዕል ይታየኛል፡፡ የሚማርክ ዓይነት ነገር ስላለው ቀርቤ ላየው ፈለግኩ፡፡ ርእሱ "Conversion of saint paul" ይላል፡፡ ሰዓሊው ካራቫጂኦ የሚባል ፈረንጅ እንደሆነ ተጽፏል፡፡ ፈረንጅ ልበል እንጅ ሰውዬው ነጭ ይሁን ጥቁር አላውቅም፡፡ ስሙና ስዕሉ ግራ ነው፤ ሰውዬውም ግራ ይሆናል፡፡ ዘወር ዘወር እያልኩ ቤቱን ለማየት ሞከርኩ ቤቱም እሱን ይመስላል፤ በሚወዳቸው ነገሮች የተገጤ ነው፡፡ ስዕሎች፣ መጻሕፍት፣ የሙዚቃ ማጫወቻ ሸክላ... በረንዳውም ውስጡም በእንጨት ቤት የቆሙ ተክሎች ሞልተውታል፡፡

በረንዳው ላይ ቆሜ አሻግሬ ውጩን እያየሁ ሳለ "ሶሪ ዲር! ዘገየሁ አይደል!" እያለ መጣ፤ ዘወር ብዬ ሳየው አልኮል የሞላቸው ሁለት ጠርሙሶች ይዟል፡፡ የሸሚዙን እጅጌ ስላጠፋቸው ስስ ፀጉር የሸፈነው ክንዱ ይታያል፡፡ አጥንቱ ሰፊ ነው፡፡
ፈገግ አልኩለት፥ በምንም አይደል ዓይነት፡፡ "ውስኪ መግዛት ረስቼ አላውቅም ነበር!" አለ እሱም እየፈገገ፡፡ ወደ'ሱ በቀስታ እየተራመድኩ እሰማዋለሁ፡፡ "ደግሞ ጠጭ እንዳልመስልሽ አለ!"
"Aren't We?" አልኩ ራሴን ጨምሬ
ሳቀ፥ ደጋግሞ "ባንሸልልበትም ነን መሰለኝ!"

አንዱ ጠርሙስ ከፍቶ የወርቅ ቀለም ባላቸው ሁለት ብርጭቆዎች ቀዳና አንዱን አቀበለኝ፡፡ በስሱ ገጫ አድርገን ሳብንለት፡፡
"ቤትህ ውብ ነው!" አልኩት መጥቶ ጎኔ ሲቆም፡፡
"ኔቨር፥ ሴት የሌለችባቸው ቤትና ልብ ውብ ሆነው አያውቁም!"አለ
በመደነቅ ዓይነት አየት አደረግኩት
"የቱንም ያህል በምወዳቸው ነገሮች ባስጌጠውም ረክቼበት አላውቅም፡፡"

"ታዲያ ለምን አታገባም?" አልኩ ኮስተር ብዬ
አየት አደረገኝና ፈገግ ብሎ "እስከቅርብ ማግባት የምፈልጋትን አላውቅም ነበር"
ልቤ ስትሽኮረመም ታወቀኝ "አሁን አውቀሃታል ማለት ነው?"
ሳይመልስልኝ ቆይ አንዴ ብሎኝ ወደ ሳሎን ተመለሰ፡፡ አሻግሬ እያየሁ አስባለሁ፥ ገብቶኛል አልገባኝምም ዓይነት፡፡ ከተዋወቅን እንኳ ገና ሁለት ወራችን ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ቤቴ ወስጀዋለሁ፥ የእሱ ቤት ስመጣ ዛሬ የመጀመሪያየ ነው፡፡ የተዋወቅነው የጋራ ወዳጅ የራት ግብዣ ዝግጅት ላይ ነበር፡፡ ከነበሩት ሰዎች ብቸኛ የዩኒቨርስቲ መምህር ያልነበረው ሰው እሱ ነበር፡፡ ግን አንዳች የተለየ ነገር ነበረው፤ ሳላየው የአካሉን ፈርጣማነትና ነጋዴነቱን ብቻ ቢያወሩልኝ የምንቀው ዓይነት ወንድ ይሆን ነበር፡፡ እዛ ዝግጅት ላይ ለማርፈዱ ይቅርታ እየጠየቀ ሲቀላቀለን ነው የገባኝ፤ ሞገሱ! ሞገሱ ልዩ ነበር፡፡ የአካሉ ፈርጣማነት እንኳ ከግልብነት ጋር የሚያያይዘው ነገር የለም፡፡ ከውኃ መሳይ የመነጽር ሌንሶቹ ማዶ ያሉ ዓይኖቹ የሚናገሩት ይዘት አለ፡፡ መሐላችን በተቀላቀለባት ቅጽበት አየት አድርጌው ለራሴ 'የእረፍት ጊዜ ደረሰ' አልኩ በልቤ፡፡ ምን እንደዛ አስባለኝ?
ከአፉ በቀልድ እርሾ ፋፍተው የሚወጡት ቃላት ሁሉ ውብ ነበሩ፡፡ ብልግናን የሚኳሹ ውበቶች ከአፉ ሲዘንቡ አመሹ፡፡ የዩኒቨርስቲ የስራ አጋሮቼ እሱ ሲያወራ ሲተያዩ አያቸዋለሁ፡፡ መደነቅ እነሱንም አግኝቷቸዋል፡፡ ዝግጅቱ አልቆ ስንወጣ ቃል ሳላወጣ ቢዝነስ ካርዴን ሰጥቸው ሄድኩ፡፡ በሁለተኛው ቀን ደውለ፡፡ ለዛው ከስልክ ማዶም ያው ነው፡፡
----
ከተዋጥኩበት ሙዚቃ ተሰማኝ፡፡ ዘወር ብዬ ሳየው እየተወዛወዘ ወደ'ኔ ሲመጣ አየሁት፡፡
"Is that wanda jackson?" አልኩ፥ ብርጭቆየን ላስቀምጥ ወደ ጠረጴዛ እየተጠጋሁ
"Yes, My dear!" አለ በደንብ እየቀረበኝ፡፡...°°

/ከተረክ/

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 9 Monate her

°°እንዴት ነው ደራሲ በድርሰቱ የማስተማር ግዴታ የለበትም የሚሉን? ግድ የለም ማስተማር የሚለው ይቅር ድርሰት ግን የሆነ ዓይነት የባሕል-ረብ (Cultural significance) ሊኖረው አይገባም!?በተለይ እንደኛ ዓይነት ከብዙ ሰው-ፈጠር ጠቃሚ ባሕሎች አምልጦ ለሚኖር ሕዝብ፡፡ ባሕል ዓይነት ዓይነት አለውና እዚህ ላይ ስጠቅሰው ያለንን እና ከኛ ወዲያ ለአሳር የሚያስብለንን ብቻ ለመወከል አይደለም፡፡ እንላለን እኮ የንባብ ባሕላችን ገና አላደገም ምናምን፤ በሐሳብና በእስክርቢቶ የማውራት ባሕላችን ለዜሮ የተጠጋ ነው፣ ኪነ-ጥበብ በራሷ ባሕላችን ልትሆንና የአኗኗር ዘይቤያችን ውስጥ ልትገባ ይገባል፡፡ ምኁራኖቻችን ከሐሜት ወጥተው በተጠረዘ መጽሐፍ ሊነጋገሩና በሐልዮት የመፋለም ምሕዳር (Theory fighting ecosystem) ባሕል ሊሰሩልን ይገባል፣ የፖለቲካ ላብራቶሪስ ሊኖረን አያሻም ወገኖቼ? ፖለቲከኞቻችንን መዝነው የሚያገዝፉና የሚያቀሉ የፖለቲካዊ ሐቲት(Political Theory) መፈብረኪያ ተቋሞች ፥እንደ ማኅበረሰብ ማን ለምን ብሎ የመመተር ልማድን የሚሰጡ ተቋሞች አያስፈልጉንም? ሐቅ እንነጋገር ከተባለ ሐቅ ነውና እኔ ፈረንጅንም ሆነ ኢምፔሪያሊዝምን ለመተቸትና ለማንቋሸሽ የአፌንም የብዕሬንም ምላስ አልስልም፤ እሱ ለነጠቃ ተዘጋጅቶ ሲመጣ እኔ የት ነበርኩ? እንበል፣ ምን እየሰራሁ በምን እየተመሰጥሁ አገኘኝ እንበል፥ የዛኔ የባሕል ምኅዳራችን ክሽፈት ሐሜት ላይ አሰልፎን በስንፍና እንዳገኙን ይገባናል፡፡ ብዙ ጊዜ የምናጠፋበት ያ ባሕላችን ነው!

ምን ልል ነው እንዲህ እንዲህ ዓይነቱን ነገር ለመፍጠር ጊዜና ሒደት ይፈልጋል፡፡ በማኅበረሰብ መረብ ውስጥ ገብቶ ራሱን እንዲያደራጅ ደግሞ ይሆነኝ ብሎ የሚያነሳው ተርብ ይሻል፡፡ ለዚህም ነው በግሉ የዚህ ዓይነቱ ባሕል አድናቂና ተቆርቋሪ የሆነው ደራሲ የራሱ በሆነው ነፃ የወረቀት ማኅበረሰብ ውስጥ ሊፈበርከውና ወደ እውናዊው ማኅበረሰብ ሊያስገባው የሚገባው፡፡ ከዚህ በላይ ጠቀሜታ(Significance) ይኖር እንደሆነ አላውቅም!...°°

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 9 Monate her

°°አባቴ የታሸገ ዘይት አንጥልጥሎ እየገባ "ቱ! ኢምፔሪያሊዝም፤ ሆዳም ካፒታሊዝም!" ይላል፡፡ እናቴ በተቀመጠችበት አየት አድርጋው እየሳቀች"መጣህ? ቆየህ እኮ!" አለች

ራመድ ብሎ የዘይት ኮዳውን ጠረጴዛ ላይ እያስቀመጠ "አንቺ ምናለብሽ!" ይላል፡፡ እኔ እያፈራረቅኩ አያቸዋለሁ፡፡

"ድሮ እናቴ የሚያብለጨልጭ ጠርሙስና አምስት ብር አስጨብጣ ነበር ወደ 'ዋለ ዘይት' የምትልከኝ፡፡ ለያውም 'ይሄው ቆሜ እያየውህ ነው ሮጠህ!' ብላ፡፡ እኔም ጠርሙስ ሙሉ ዓይኔ እያየ የተጨመቀ የኑግ ዘይቴንና መልሴን ይዤ በመልሱ ስለሚገዛልኝ ጠጠር ከረሜላ እየጎመዠሁ ነበር ምራቋ ሳይደርቅ የምመለስ፡፡ ዛሬ ሰሊጥ ይሁን ዘንጋዳ የማናውቀውን ወገብ ሰባሪ ፈሳሽ ለመግዛት ሰዓታት የምንሰለፍበት ዘመን መጣ፤ ለያውም ደሞዝ የሚያስደነግጥ ብር ተከፍሎ.. አይ ካፒታሊዝም፤ ብሽቅ ኢምፔሪያሊስቶች ድድብናችንን ተጠቅመው ሰሩልን! ይበለን በማያራኩተው ስንራኮት፣ በማያወዳድረው ስንሸቀዳደም፣ ድል በማያስገኘው ስንራኮት፤ ከጓሯችን አጭደው ከፋብሪካቸው ሸጡልን፡፡ ፓ ንቃት ለዘላለም ይኑር!"

ይህን እያወራ ጫማውን አውልቆ ሶፋ ላይ ተጋደመ፡፡

እናቴ ዘይቱን አንስታ ወደ ጓዳ ስትራመድ

"መድኅን እሙች ከዛሬ በሁዋላ ዘይት ግዛ ከምትይኝ ያለዘይት ወጥ የመስሪያ ዘዴ ፈልስፍ ብትይኝ ይቀለኛል፡፡ "
አየት አድርጋው  " መግዣው አይጥፋ በል ጌታዬ" አለች

እኔ ባባባሉ እየሳቅኩ ካፒታሊዝም ምንድን ነው? ኢምፔሪያሊስት የሚላቸው እነማንን ነው? እላለሁ፡፡

ስስቅ ዘዎር ብሎ አየኝና "ስማ ጌታው ድሮ ዘይት ያንተ እኩዮች የሚገዙት ቀላል እቃ ነበር፡፡ ዛሬ ባንተ ቢቀይሩኝ ያዋጣኛል" አለ እሱም እየሳቀ፡፡°°

©ናትናኤል ዳ.

2 Jahre, 9 Monate her

°ምን አጥብቄ እንደምጠላ ታውቃለህ?°° አለ

°°Easy money and Easy pussy. ወዳጆቼ ትኮፈሳለህ ይላሉ፤ ለተዘረጋልኝ ሁሉ እጄን ስለማልዘረጋ፡፡ እድል የሚባል ነገር ቢኖር እንኳ አርቄ ያስቀመጥኩትና ከ'ሱ ለመድረስ የማልተጋለት ነገር ከሌለ የመኖር ትርጉም አይገባኝም፡፡ ሴት መቀያየር አልወድም፤ ግንኙነት ስጀምር ዘግይቼ ስወጣም እርግጠኛ ሆኜ ነው፡፡ ስለ ገንዘብ ያለኝ አቋምም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ሁለቱንም ተንጠራርቼ ስይዛቼው ነው ስሜት የሚሰጡኝ፡፡ እሴት የሌለው ገንዘብን አልወድም፤ ያልመረጥኳት ሴት ጋር አልተኛም፡፡ ዙሪያየን የከበቡኝ ግን ትራሽ* ካሽና ካሽ አሳዳጅ ፑሲዎች ናቸው፡፡°°

ከሚያማቸው ጋር ለምን ይኖራል? እላለሁ፡፡ ርቆ መጓዝና ይመስሉኛል በሚላቸው መሐል መኖር እየቻለ፤ መጓዝን ፈርቶ ለምን ራሱን ያደማል? እላለሁ፡፡ ሐሳቤን ያነበበ ይመስል፦

°° ልጅነትና ጉርምስናዬ በዚህ ቀዬ በነዚህ ሰዎች የተዋበ ነው፡፡ ጉልምስናዬና እርጅናዬም በፊታቸው እንዲሆን እሻለሁ፡፡°° ይላል

°°ታውቃለህ ዘፋኟ 'ሀገርም እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ?' ያለችው ወድዳ አይደለም፡፡ ሰውንም ያለ ጊዜና ቦታ አታስበውም፡፡ ለእኔ ይህ ተወልጄ ያደግኩበት ሰፈርና ያሳደጉኝ ሰዎች የማይለቁ እድፎቼ ናቸው፡፡ መቼ ሾልኬ የማማቸው ልጃቸው እንደሆንኩ አላውቅም፡፡ 'ምኁሩ' ይሉኛል፤ 'ሐኪሙ ልጃችን፤ ያስተማሩኝን አልከዳም ብሎ እኮ ነው እንጅ ፈረንጅ ሀገር መሔድ እየቻለ' እያሉ ያዝኑልኛል፤ እናቶች፡፡ እያከምኳቸው ግን እተቻቸዋለሁ፤ ድሮ ታምሜው ያለፍኩትን ዛሬ የልጅ ልጆቻቸው ታመውት ሳይ እበሳጫለሁ፡፡ እጅን ታጥቦ መብላት፣ የልጅን እጅ ማጠብ ስራ ሆኖ ነው? እላቸዋለሁ፡፡ እኔ እድል ቀንቶኝ ኮሌጅ ስገባ እዚሁ ቀርተው ጎጆ ያቆሙ ልጅ የወለዱ እኩዮቸን ተራ ገንዘብና ተራ ወሲብ አሳዳጅ እላቸዋለሁ፡፡ አብሬያቸው ተቀምጬ የሚጠጡትን እየጠጣሁ የሚያሙትን እያማሁ ብቻዬን ስሆን ደግሞ እነሱን አማቸዋለሁ፡፡ የተጓዝኩበት ቅያስ ድንገት ከነሱ መንገድ እንዳስወጣኝ አላወቅኩም ወይም መቀበል አልፈለግኩም፤ ሰው የመንገድና ጉዞው ውጤት ነውና ለልጆቻችሁ ተጠንቀቁ እያልኩ ግን እመክራለሁ፤ ተረስቶኛል እንዲህ ለመሰራት የተጓዝኩት፡፡ ዛሬ ተራ የምለው ትናንት ኮሌጅ ሆኜ ብር የላከልኝን ነው፡፡ አላስታውስም ይህ ብሩ የዛኔ እንደዛሬው ቆሽሾብኝ ያውቅ እንደሆን፡፡°°

/ከተረክ/

©ናትናኤል ዳ.

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад