Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
የዮናስ እና ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ ስንመረምር፣
ኢየሱስ ክርስቶስ ንስሐን ለመስበክ መቷል፤
ዮናስ ደግሞ ተልኮ ነበር፤ ነገር ግን አንድ ሰው የሚሆነውን ሳያውቅ ሸሸ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ለመዳን ንስሐን ሊሰጥ በፈቃዱ መጣ።
ዮናስ በመርከቡ ውስጥ ተኝቶ በማዕበል ባሕሩ መካከል እያንኮራፋ ነበር፣
ኢየሱስም ክርስቶስ ተኝቶ ሳለ፣ ባሕሩ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መነሳት ጀመረ፣
የተኛውንም ኃይል በቅደም ተከተል ያሳያል። እነሱም “ለምን ትተኛለህ?
ተነሥተህ አምላክህን ጥራ፤ እግዚአብሔር ያድነን ዘንድ አሉት፤
"በሌላው ጉዳይ ግን መምህሩን “ጌታ አድነን” አሉት።
ከዚያም “አምላክህን ጥራ” አሉት።
እዚህ “አድነኝ” ይላሉ፣ አንደኛው ግን፣ “ውሰደኝ፣ ወደ ባሕርም ጣልኝ” ይላል።
ባሕሩም ጸጥ ይላል፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
አንደኛው ወደ ዓሣ ነባሪ ሆድ ተጣለ፣ ሌላኛው ግን የማይታየው የሞት ዓሣ ነባሪ ባለበት በራሱ ፈቃድ ወረደ።
እንደ ተጻፈውም የበሉትን ሞት ያባርራቸው ዘንድ በገዛ ፈቃዱ ወረደ።
“ከመቃብር ኀይል እቤዣቸዋለሁ። ከሞትም እጅ እቤዣቸዋለሁ”
[ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ]
**ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡
በሦስት ቀን ጾም የነነዌን መዓት የመለሰ በሦስት ቀን ጾም የግብፅን ተራራ ያፈለሰ የነስምዖን አምላክ የእኛንም በደልና ኃጢያት በቸርነቱ ይቅር ይለን ዘንድ በልባችን ጉልበት እንስገድ ሰላሙን ያድልልን። መልካም ጾም ይሁንልን።**
**ነነዌ ሆይ፣ ማቅሽና አመድሽ የክብር መጎናጸፊያ ሆነሽ!
በእግዚአብሔር ፊት ራሷን ያዋረደች ከተማ የተባረከች ናት።
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ**
✥••┈• ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ፡፡” [መ/ዕዝ. ሱቱ. 2፡1] •┈••✥
በመላእክት ከተማ በራማ ካሉት ሦስት ነገዶች ውስጥ አንዱ ነገድ ሥልጣናት ይባላል፡፡ በሥልጣናት ላይ ከተሾሙ ሊቃነ መላእክት ውስጥ አንዱ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሱርያል ይባላል፡፡ ሱርያል የሚለው ስም በአንዳንድ ድርሳናት ካልሆነ በስተቀር እምብዛም አይታወቅም፡፡ ትርጉሙም ‹‹ዐለቴ እግዚአብሔር ነው›› ማለት ነው፡፡ ሱርያል የቅዱስ ዑራኤል ሌላ ስሙ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያንም በስፋት የሚተወቀው ስም ዑራኤል የሚለው ስም ነው፡፡ [ድርሳነ ዑራኤል 1991 ገጽ 14]
ዑራኤል ማለት “ብርሃነ እግዚአብሔር” ማለት ነው። “ዑራኤል ሥዩም ላዕለ ኵሎሙ ብርሃናት፤ ዑራኤል በብርሃናት ላይ ሁሉ የተሾመ ነው” እንዲሁም “ዑራኤል አሐዱ እመላእክት ቅዱሳን እስመ ዘረዓም ወዘረዓድ፤ ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ የተሾመ ነው” እንዲል፡፡ [ሄኖክ 6፥2] ከሊቃነ መላእክት አንዱ መሆኑንና ፍርሃት ረዓድ ላለባቸው ረዳታቸው እንደሆነ የመላእክትን ነገር የተናገረ ሄኖክ ነግሮናል፡፡ “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል” በማለት ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረ እግዚአብሔርን በሚፈሩና በሚያከብሩት ሰዎች ጭንቀት ጊዜ በመካከላቸው እየተገኘ ያጽናናቸዋል። [መዝ.33፥7]ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃቸዋል።
አንድም ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ኹለት ቃላት የተመሠረተ ነው። ዑራኤል ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ”፣ ”የአምላክ ብርሃን” ማለት (እግዚአብሔር ብርሃን ነው) ማለት ነው። "በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙ 7 መላእክትን ዐየሁ" [ራዕ. 8፡2] እንዳለ ሊቃነ መላእክት በቊጥር 7 ናቸው። ቅዱስ ዑራኤልም ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መ.ሄኖክ. 6፥2] ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ኁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። [መ.ሄኖክ 28፥13] “ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ፤ እውቀት ለተሰዎረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፤ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡
የመልአኩ ዓመታዊ ክብረ በዓላት
• ጥር 22 በዓለ ሲመቱ፣
• መጋቢት 27 የጌታችንን ክቡር የሆነ ወርቀ ደሙን ለዓለም የረጨበት ነው፡፡
• ሐምሌ 21 እና 22 ቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የእውቀት ጽዋ ያጠጣበት ቀን ነው።
አፈቅሮ ፈድፋደ፡- ዑራኤል ሆይ፣ ከመልኮች ሁሉ ይልቅ ያንተን መልክአ ጸሎት እወዳለሁ፡፡ የመልክህ ስነ ጸዳል በደመ ወልድ እግዚአብሔር የታተመ ነውና፡፡
ዑራኤል ሆይ፣ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽብን መልአከ ብርሃናት አንተ ነህ፡፡ በዕለተ ሥቅለት በደመ ወልድ ዓለምን ለመቀደስ ከሁሉ ይልቅ አንተ ተሰይመሃልና፡፡ ስለክብርህ የሰማይ መላእክት አደነቁ፡፡
ለተፈጥሮትከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ያለ መናገር በጥንት አርምሞ ከነፋስና ከእሳት ለተፈጠረ ተፈጥሮህ ሰላም እላለሁ፡፡ ዑራኤል ሆይ የተፈጥሮና የይቅርታና የቸርነት ክቡር መልአክ ነህና ስለኛ ስለሰው ልጆች ወደ ልዑል እግዚአብሔር ማልድ አማላጅነትህ ዘወትር ከጥፋት ያድናልና፡፡
ለዝክረ ስምከ፡-
ዑራኤል ሆይ፡- ከማርና ከወተት ይልቅ ለሚጥመው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡
ዑራኤል ሆይ፡- ክፍልህ /ክንፍህ/ በደመ ወልድ እግዚአብሔር የተከበረ /የታለለ/ ነውና፡፡ ለዓለሙ ሁሉ መድሃኒት ትሆን ዘንድ ግሩም የሚሆን የእግዚአብሔር ሥልጣን በክብር ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ [መልክአ ዑራኤል]
በአምላኩ አማላጅነቱን ኑና ተማጸኑት። በጸሎቱ ለተማጸነ ከአምላኩ በረከትን ምህረትን የሚያሰጥ አዛኝ እርሩህ መልአክ ነው። የቅዱስ ዑራኤል በረከት በኁላችንም ላይ ይደር!! አሜን።
✥••┈••●◉ ✞ ◉●••┈••✥
እመቤታችን ሆይ፣ የቅዱሳንና የምእመናንን ኹሉ ጸሎት በማዕጠንታቸው ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች አጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን። እንዲኹም ስምሽን በመጥራት የሰው ልጆችን ልመና ወደ ልዩ ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሳርጋሉ። የወገኖችሽንም ኅጢአት ታስተሠርዪ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተፈቅዶልሻልና። ለሰዎች ልጆች የዘለዓለም ሕይወት ድልድይ ትሆኝ ዘንድ የዓለም ኹሉ መድኃኒት ሆይ፣ ለምእመናን ወገኖችሽ መድኃኒታቸው ልትባይ ይገባል። ቅድስት ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን።
አንቀጸ ብርሃን
በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው። [ሄኖ.10:14]
ሰላም ለሰኰናከ
ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ።
በአንድ ወቅት በብዛትና በአንድነት ሲጠፉ ለምን ጠፍ ምክንያቱ ምንድን ነው ሳንል ራሳችንን አገልግሎታችንን ሳንፈትሽ ጸጥ ብለን በሆነ ወቅት ደሞ እነዛው የጠፉት መመለስ ሲጀምሮ የምን ማንጎራጎር ማብዛት ነው። አገልግሎት ምንድን ነው
አገልግሎት ማለት በፍቃደኝነት በተሰጠን ጸጋ(ስጦታ ) ልዑል እግዚአብሔርን ማገልገል ማለት አይደለምን? ለዚህ ደግሞ ሁሉም ተጠርቷል፡፡
አገልግሎት በእግዚአብሔር ጥሪ የሚጀመር መንፈሳዊ ተልዕኮ ነው፤
እግዚአብሔር ሰዎችን ያገለግሉት ዘንድና የፍቅሩ ተሳታፊዎች ይሆኑ ዘንድ ይጠራል፡፡
አግልግሎት በእግዚአብሔር እና በሰው ልጆች መካከል ያለ የፍቅር መግለጫ ነው፡፡
አግልግሎት ከእግዚአብሔር የተደረገልንን ውለታ ማሰብ ነው፡፡
አንድ አባት ”ቤተ ክርስቲያን አምጥታናለች፤ አስተምራናለች ለጌታችንም አንድንገዛ አድርጋናለች“ ብለዋል፡፡
አገልግሎት ማለት ያዩትን እና የሰሙትን የእግዚአብሔርን ቸርነት መመስከር ያወቁትን መንፈሳዊ ዕውቀት ላላወቀ ማሳወቅ ማለት ነው፡፡
የቤተ ክርስቲያን አገለግሎት ዋና ዓላማው የጠፋውን የሰው ልጅ ለድኀነት ማብቃት ነው፡፡ ሰው ለድኀነት የሚበቃው አዕማደ ምስጢራትን አምኖ ሲፈጽም በአመነበት እምነት ጸንቶ ከኃጢአት በመጠበቅ እግዚአብሔርን ሲያገልግል ነው፡፡ [2ኛ ጢሞ 2፤15 ”የእውነት ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ኾነኽ፥ የተፈተነውን ራስኽን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።"
ለመጣችሁም በመምጣት ሂደት ላይ ያላችሁም የምትመጡም እንኩዋን ወደ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችሁ ተመለሳችሁ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ደግሞም ያጽናችሁ።
ለምን ያህል ሰዓት ምግብ ከመብላት እንቆጠብ?
አንድ ሰው በጾም ወቅት ምግብ ከመብላት የሚቆጠብበት ጊዜ እንደ እድሜ፣ አቅም፣ የጤና ኹኔታ እና የሥራጫና የሚወሰን ነው፡፡ እነዚህን መሠረታዊ መስፈርቶች እንመልከታቸው፡፡
1. መንፈሳዊ አቅም/ብስለት [Spiritual Maturity] - አንድ ሰው ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ አቅም/ብስለት ካለው፤ ለረጅም ሰዓት ምግብ ሳይበላ መቆየት ይችላል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡- አንዳንድ ገዳማውያን እና ባህታዊያን በሦስት እና በአራት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ በጥቂቱ እየተመገቡ መቆየት ይችላሉ፡፡ ዝቅተኛ የሆነ መንፈሳዊ አቅም ያለን ግን በአቅማችን መጾም መቻል አለብን፡፡ ሌሎችን ዐይተን ‘ለምን ይበልጡናል’ በሚል ስሜት ብንንጠራራ ግን ራሳችንን እንጎዳለንእንጂ፤ መንፈሳዊ በረከትን አናገኝበትም፡፡
2. እድሜ [Age] - በጾም ወቅት የምናየው ኹለተኛ መስፈርት እድሜ ነው፡፡ አንድ ጾምን በመለማመድላይ ያለ የስምነት ዓመት ልጅ፣ ወደ ወጣትነት እየተሸጋገረ ያለ የዐሥራ ስድስት ዓመት ልጅ፣ የሃያ አራት ዓመት ወጣት፣ የአርባ ዓመት ጎልማሳ እና የሰባ ዓመት አዛውንት እኩል የሆነ የመጾም አቅም አይኖራቸውም፡፡ በመሆኑም የጾም ሰዓት ከእድሜ ጋር መገናዘብ አለበት፡፡ አንድን የስምንት ዓመት ልጅ እስከ ዐሥራ አንድ ካልጾምክ ብሎ ማስገደዱ ጾምን በልኩ እንዳይለማመድ ከማድረጉም በተጨማሪ፣ እየተሰላቸ እና እየተማረረ እንዲጾመው በማድረግ መንፈሳዊ በረከቱን እንዳያገኝ ሊያደርገው ይችላል፡፡
3. የጤና ኹኔታ [Status of Health] - ሌላው አጽንኦት የሚሰጠው ጉዳይ ደግሞ የጤና ኹኔታ ነው፡፡ በሕመም ከደከሙ ሰዎች ይልቅ ሲነጻጸር ፍጹም ጤናማ የሆነ ሰው በተሻለ ኹኔታ የመጾም ችሎታ ይኖረዋል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አስቸጋሪ የሆነ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር በመመካከር ለአጭር ሰዓት ብቻ ከጸሎት ጋር መጾም ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ‘አንድ ጊዜ እንዲህ አሞኝ ነበር፤ አሁንም ብጾም ሊያመኝ ይችላል’ በሚል ፍራቻብቻ ደግሞ ከጾም መሸሽ እንደማይገባ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
4.የሥራ ክብደት [Heaviness of Work] - አንድ ሰው የሚሠራው የሥራ ዓይነትም ግምት ውስጥ ይገባል፡፡አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ አካላዊ አቅም የሚጠይቅ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ብዙ አካላዊ እንቅስቃሴ የማያስፈልገውእና ቢሮ ውስጥ ቁጭ ተብሎ የሚሠራ ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ፡፡በዚህ ዓይነት ያሉ ኹለት ሰዎች እኩል ላይጾሙ ይችላሉ፡፡ የመጾም አቅማቸውም ከሥራቸው አኳያ ሊለያይ ይችላል፡፡
አካላቱን ዳሠሠው ፊቱንና ዓይኖቹን አሻሸው ጽድቁንም ዐውቆ << አባቴ በረከትህ ትድረሰኝ >> በማለት ተባርኳል፡፡
ትምህርተ ሃይማኖትን ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋራ ካጸና በኋላ ወደ ሀገረ መንበረ ሢመቱ ተመልሶ ካህናቱንና መንጋዎቹን ሁሉ ሰብስቦ ጸሎተ ሃይማኖትን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አነበበላቸው ይኅን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም አጽንተው እንዲጠብቁት አዘዛቸው፡፡ ጥቂት ዘመናትም ከኖረ በኋላ ቅዱስ ቶማስ ጵጵስና በተሾመ በ40 ዓመቱ ነሐሴ 24 አርፏል፡፡ የጻድቃንን የሰማዕታትን የሐዋርያትንና የሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል።
ምንጭ፦ ሐመር መጽሔት ሐምሌ 1-15/2014 ዓ.ም
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago