Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
?ቁርዐንን ጨምሮ ሁሉን በአንድ የያዘውን ሁለገብ ቻናላችንን ተጋበዙልኝ ?
?ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም?
?አነቃቂ ኢስላማዊ ሀዲሶችን ከውብ ቁርዓን ጋር የሚያደርስ የተመሰከረለት ምርጥ ቻናል ጋበዝኳችሁ❣
⛔️ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም ተቀላቀሉ⛔️
#ሷሊህ አስታጥቄ
አዲስ ጦሃ ሙስጠፋ #MEWELID
MEDINA||TUBE
@MEDINA_TUBE
አሏህ ለሉት የረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሙሂቦች ረጅም ሃያትትት ወደዛኛው ዓለም ለተሻገሩት ደሞ የአሏህ እዝናት በነሱ ላይ ይሁን #HAMESI MUBARAK @MEDINATUBE
አንድ የዕድሜ ባለፀጋ አልጄሪያዊ ሀጃጅ በሞት ያጡትን አባታቸውን የሚመስል ሌላ ሀጃጅ ስላዩ ወደ እሱ ሄዱ ሳሙት እና ማልቀስ ጀመሩ,,,,,,,,
በሞት ያጣቸውን አባት በጣም ከመመሳሰላቸው ስሜታቸውን መቆጣጠር ስላልቻሉ ራቅ ብለው ተመለከቱና ማልቀስ ጀመሩ።
@medinatube
ሀጂዬ እንኳን ለዐረፋ በዓል በሰላም አደረስዎ።እድሜዎ ይርዘም አባቴ!!! @medinatube
የሀበሻ መሻኢኽ ፈርጦችን የማክበር በረካ ይስጠን
የነቢዩን መስጂድ ሃረም የሚገኘው "ሁጅራ" ቁልፍ ያዥ ኢትዮጵያዊ ማን ናቸው?
"ሼክ ኑሪ" እየተባሉ በቁልምጫ እና በስስት የሚጠሩት ኢትዮጵያዊ በሳዑዲ
ኢትዮጵያ እና እስልምና ያላቸው ቁርኝት እጅግ የቆየ፣ ታሪካዊ እና አሁን በሚታየው ብቻ የማይበየን ስለመሆኑ ብዙ ማሳያዎች አሉ።
የነቢዩ መሐመድ (ሰ.አ.ወ) አሳዳጊ ኡሙ አይመን፣ ቀዳሚው ሙአዚን ቢላል ኢብኑ ረባህ እንዲሁም በቅዱስ ቁርአን የተከበሩት እና የተወደሱት፤ ህይወታቸው ካለፈ በኋላም የመጀመሪያው የሙት ሰላት (ሰላተል ጋይብ) እንደተደረገለቸው የሚነገረው ፍትሃዊው ንጉሥ ነጃሺ " ንጉሥ አርማህ" ኢትዮጵያ እና እስልምና ስለመተሳሰራቸው ዋነኞዎቹ ማሳያ ሆነው ሊጠቀሱ ይችላሉ።
ታዲያ ዛሬ ይህን ጥልቅ እና ብዙ ምርምር የሚፈልግ ጉዳይ ለመዳሰስ ሳይሆን አንድ የዚህ ታሪክ ሰበዝ ለማንሳት ነው።
የሳብናት ሰበዝም በጥቂቱ የምታስዳስሰን አባት ነብዩ መሀመድ (ሰ.አ.ወ) “አትንኳት“ ካሏት እንዲሁም በጭንቅ እና በስቃይ ወቅት የእስልምና እምነት ተከታይ ወዳጆቻቸውን (ሶሃባዎችን) ከላኩባት የኢትየጵያ ምድር የተገኙ ናቸው።
በሳዑዲ ዓረቢያ "በቅዱስ" ከተማዋ መዲና ኑሮዋቸውን ያደረጉት እኚህ አባት በመዲና የሚገኘውን የነቢዩ መስጅድ ሃረም ከ50 ዓመት ባላይ አገልግለዋል።
ዓለም ከጫፍ እስከ ጫፍ ለጸሎት የሚያቀናበት በመዲናው የነቢዩ መስጅድ ሃረም ውስጥ የሚገኘውን ሁጅራ ተብሎ የሚጠራው የቀብር ቦታ ብቸኛው ቁልፍ ያዠ ናቸው።
የሳዑዲው ንጉሥን ጨምሮ ሙስሊም መሪዎች ወደ መዲና ለዚያራ (ጸሎት) መጥተው ዋናውን የቀብር በር የሚከፍቱላቸው እኚህ የተከበሩ ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው።
በእስልምና ዕምነት ትልቅ ቦታ ከተሰጣቸው ኡሙ አይመንና ቢላል ሀገር የፈለቁት እኚህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ሼህ ኑረዲን መሀመድ አሊ ይባላሉ።
በአካባቢው ማህበረሰብ ተወዳጅ ከመሆናቸው የተነሳ በሙሉ ስማቸው አይጠሩም። "ሼክ ኑሪ"እየተባሉ በቁልምጫ እንደሚጠሩ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል ይገልጻሉ።
ሼክ ኑሪ በበርካታ ሀገራት በተለይም የሙስሊም ሀገራት ጉብኝት እንዲያደርጉ ተደጋጋሚ መንግሥታዊ ግብዣ ቢደረግላቸውም ስራቸው ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ የተወሰኑትን ብቻ ተቀብለው ሀገራትን ጎብኝተዋል።
ፓኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ኦማን እንዲሁም ዮርዳኖስ በሼክ ኑሪ ከተጎበኙ ሀገራት መካከል ይገኙበታል።
ወደ ሀገራቱ ሲያቀኑ ከአየር መንገድ ጀምሮ ደማቅ አቀባበል ይደረግላቸዋል። የሀገራቱ ሚድያዎችም ትኩረት በከፍተኛ ደረጃ ይስባሉ።
በቅርቡ የተጓዙባት ፓኪስታን ሚድያዎች የሼክ ኑሪን ወደ ሀገራቸው መግባት፤ "በሰበር ዜና" ጭምር ሽፋን መስጠታቸው ትልቅ ማሳያ ነው።
በእርግጥ ሼህ ኑሪ በተለያዩ ጊዜዎች ወደተለያዩ ሀገራት ያደረጏቸው ጉብኝቶች እንዳሉ ይታወቃል::
ሼህ ኑሪ መሀመድ አህመድ አሊ በአውሮፓውያኑ 2015 በሁለቱ "ቅዱስ" ቦታዎች ሃላፊ የመካው መከተል ሙከረማ ሀረም መስጅድ ዋና ኢማም ሼህ አብድረህማን ሱደይስ "የእድሜ ዘመን" ልዩ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል።
አሁን እርጅና የተጫነው የነቢዩን መስጂድ ሃረም የሚገኘው "ሁጅራ" ቁልፍ ያዥ ኢትዮጵያዊ አልፎ አልፎ ወደ ሀገራቸው ይመጣሉ።
"እኚህ የተከበሩ አባት ወደ ሀገራቸው ሲመጡ ቢያንስ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ደረጃ እንኳን አቀባበል አለመደረጉ አሳዛኝ ነው" ሲሉ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር አደም ካሚል በአንድ ወቅት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸው ነበር።
ጊዜው እንዳልረፈደ ያነሱት የታሪክ ተመራማሪው እኚህን ታላቅ ኢትዮጵያዊ የሚዘክር እስላማዊ ሙዚየም ቢገነባ እንደ ሀገርም ተጠቀሚ መሆን የሚቻልባቸው ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
@medinatube
በአብዱልአዚዝ ዩሱፍ
ምንጭ
ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ካርፖሬት Ebc
ለበይከላሁመ ለበይክ፣?
ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣?
ኢነል ሀምዳ ወኒዕመታ ለከ ወልሙልክ፣?
ላ ሸሪከለክ፣?
አብደላህ ኢብን ሙባረክ (ረሒመሁላህ) ለሐጅ ጉዞ ላይ ሳሉ ኩፋ ውስጥ በመንገድ ላይ አንዲት ሴት ከቆሻሻ ቦታ ላይ የሞተች ዳክዬ ስትቆራርጥ ያዩና ቆም ብለው ያናግሯታል። "የሞተ ነገር ምን ልታደርጊው ነው ይህኮ ሐራም ነው።"ይሏታል እሷም"ለኔና ለቤተሰቦቼ ምግብ ለመስራት ነው ምንም የምንበላው ነገር በቤት ውስጥ የለንም እስቲ ዞርከፊቴ ዘወር በልልኝ" ትላቸዋለች በብስጭት፤
በሌላ ዘገባም እንዲህ ማለቷ ተዘግቧል ፦"ለምን ይህን በክት ትበያለሽ !?" ብለው ሲጠይቋት" እኔና ወንድሜ የምንቀይረው ልብስ እንኳን የለንም አንዲት ልብስ ብቻ ነው ያለን የምንበላውም ምንም ስለሌለን ከቆሻሻ ስፍራ እየለቃቀምን ነው የምንበላው ሌላ ምግብ እስከምናገኝ ይህ ለኛ የተፈቀደና ሐላል ነው። አባታችን ሀብታም ነበር ንብረቱን ተዘርፎ እሱም ተገደለ ምን አማራጭ አለን።" በማለት ትመልሳለች።
ኢብን ሙባረክ ጊዜ አልፈጁም ቤተሰቦቿ የት እንደሚኖሩ አጠያይቀው በቀጥታ መንገድ መሪ ይዘው ወደ ቤቷ አመሩ እንደደረሱም ለሐጅ ጉዞ የጫኑትን ሁሉ አራገፉ ወደ ሀገራቸው መረው ለመመለስ ብቻ የሚያበቃቸውን ጥቂት ንብረት ብቻ በመያዝ ሐጁን ትተው ወደ ኋላ ሀገራቸው ተመለሱ። ለቤተሰብና አብረዋቸው ላሉትም አሉ፦"ዘንድሮ እኛ ከሐጅ ስራው ይህ ይበልጥብናል፣" በማለት አሳወቋቸው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
ሌሎች ጓደኞቻቸው ጉዟቸውን ጨራርሰው ከሐጅ ጉዞ ሲመለሱ ከዘየሯቸው በኋላ "እንዴት ነበር ሐጁ እያሉ ወግ ሊጀምሩ ሲሉ እሳቸው፦"እኔኮ ዘንድሮ ሐጅኮ አልሔድኩም ሰረዝኩት፣" አሏቸው። ጓደኞቻቸው ግራ በመጋባት መንፈስ ተያዩና ወዲያው አንደኛው "ምነው ከሚና ወደ አረፋ ስንጓዝ እንኳን የሀነ ዕቃዬን አንተ ጋር አስቀምጥልኝ ብዬ አልሰጠሁህም!?" አላቸው።
ሌላኛውም ቀበል አረገና "እንዴ! ከኔ ራሱኮ የሆነ ዕቃ ገዝተኸኛልኮ ረሳኸው!?" አላቸው። ኢብን ሙባረክ ግን ረገጥ አድርገው "እኔ ዘንድሮን ሐጅ አለማድረጌን ነው የማውቀው።" ሲሉ መለሱላቸው። ጓደኞቻቸው በጉዳዩ እየተገረሙ ተለያዩ።
የዛን ቀን ማታውኑ አብደላህ ኢብን ሙባረክ ህልም ያያሉ፦ድምፅ ወደሳቸው ይመጣል" አብደላህ ሆይ! እንኳን ደስ አለህ! ደስ ይበልህ! ባደረግከው በጎ ነገርና ሰደቃ ኢላህ ተደስቶብህ ተቀብሎኻል፣ ባንተ ቦታ ያንተን የሐጅ ስራ መላዒካ ከውኖልኻል፣" አላቸው የሰሙት ድምፅ።
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago