16 - ሚዲያ

Description
እንኳን ወደ አስራ ስድስት ሚዲያ ቴሌግራም ቻናል በሰላም መጡ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሊቀላቀለዉ የሚገባ ስለ ሀይማኖቱ ስርአት ስለ ቤተክርስቲያን መመሪያ ህግጋት በደንብ የምናስተምርበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ።
YOUTUBE ~> https://www.youtube.com/@16_media16
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago

1 month, 1 week ago

*🔰* በቤተክርስቲያን ያሉ ነገሮች ምሳሌዎቻቸው

፩/ቤተክርስቲያን_የመንግሥተ ሰማይ ምሳሌ
፪/መቅደስ_የቀራንዮ ምሳሌ
፫/ታቦት፣ መንበር____የእመቤታችን ምሳሌ
፬/ኲስኲስት__የእመቤታችን ምሳሌ
፭/ማይ__የማይ ሕይወት ክርስቶስ
፮/መሠረቱ___ከአዳም እስከ ኖኅ ያሉ የአስሩ አበው ምሳሌ

፯/ሦስት ደጃፍ___የሥላሴ ምሳሌ
፰/ትልልቅ መስኮቶች___የዐበይት ነቢያት ምሳሌ
፱/ትንንሽ መስኮቶች___የደቂቀ ነቢያት ምሳሌ
፲/የውስጥ አዕማድ __የሐዋርያት ምሳሌ
፲፩/የውጭ አዕማድ___የ፸፪ቱ አርድእት ምሳሌ
፲፪/ማዕዘን__የአራቱ ወንጌላውያን ፣የኪሩቤል ምሳሌ

፲፫/መብራት__የሊቃውንት ምሳሌ
፲፬/በሮች___የቅዱሳን አበው ምሳሌ
፲፭/ጠርብ___የሰማእታት ምሳሌ
፲፮/ማገር___የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ
፲፯/ሣሩ__ ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ምሳሌ
፲፰/መጋረጃ___የመላእክት ፣የረድኤተ እግዚአብሔር ምሳሌ

፲፱/የሰጎን እንቁላል___የተዘክሮ እግዚአብሔር ምሳሌ

፳/አፀደ ቤተክርስቲያን ፣ቅጽረ ቤተክርስቲያን___የመላእክት ምሳሌ

፳፩/ደጀ ሰላም___የገነት ምሳሌ
፳፪/ሁለት ቅጽር____አንዱ የናጌብ አንዱ የአድማስ ምሳሌ ናቸው።
ሁለት ቅጽር ማለት እንደ ጎንዴር ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን እንዴ አዲስ አበባ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሁለት ቅርጽ ያለው ቤተክርስቲያንን ያመለክታል።

ምንጭ:- ፲፬ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ አንድምታ ትርጓሜ

ወሰብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለ መስቀሉ ክቡር ይቆዬን አሜን ፫**

1 month, 1 week ago

ወደ እኔ ነይ

ታላቁ ጻድቅ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጸሎታቸው እንዲህ ይላል:

✝️በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ! ከነቢያት ማኅበር ሁሉ ጋር ወደ እኔ ነይ ፣ ከአንደበታቸው የወጣውን የምስጋናሽን ኃይለ ቃል ልብ ታስደርጊኝ ዘንድ።

✝️ድንግል ሆይ የቃልን ከአንቺ ሰው መሆን ሥጋ መልበሱንም ጽንፍ እስከ ጽንፍ ካስተማሩ፣ በልጅሽም ዕርፈ መስቀል የአሕዛብን ምድር ካረሱ፣ የቃሉንም ድልብ በምድር ሁሉ ከዘሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ጋር ወደ እኔ ነይ

✝️ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ በሥጋቸው የልጅሽን መከራ ከተሸከሙ የሰማዕትነታቸውን ደም ከተቀቡ ሰማዕት ከእነርሱም ማህበር ጋር ወደ እኔ ነይ

✝️ድንግል ሆይ በማመንዘር እድፍ ነፍሳቸውን እና ሥጋቸውን ካላረከሱ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ከሆኑ ንጹሐን ደናግል ማህበር ጋር በበረከትና በረድኤት ወደ እኔ ነይ

✝️ድንግል ሆይ ስለ መንግሥተ ሰማያት ራሳቸውን ጃንደረባ ካደረጉ ፍጹማን መነኮሳት ማኅበር ጋር በበረከት እና በረድኤት ወደ እኔ ነይ

✝️በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባልሽ የተመረጥሽ እመቤቴ  ቅድስተ ቅዱሳን  ድንግል ማርያም ሆይ በየጊዜው እና በየሰዓቱ ምስጋና እና ቅዳሴ ከማያቋርጡ ከትጉኃን መላዕክት ማህበር ጋር ለምህረት እና ለረድኤት ወደ እኔ ነይ።

ምንጭ አርጋኖን ዘዓርብ ምዕራፍ 1:1-6

✝️ በእውነቱ ይህ ታላቅ ጸሎት ነው እንደጸሎታቸውም አባታችን  አባ ጊዮርጊስ በእመብርሃን ተጎብኝተዋል፣ በእጆቿም ተባርከዋል። የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ  አባ ጊዮርጊስን እንደጎበኘሽ፣ቅድስት ኤልሳቤጥ ቤትም እንደገባሽ፣ በእኛም ቤት ግቢ፣ ባርኪን፣ ቀድሽን፣ ከልጅሽ አማልጂን፣ ወደ እኛም ነይልን።ወደ ኢትዮጵያ ነይልን**

✝️ እመብርሃን በየቤታችን ትግባ። የእናታችን የቅድስት ኄራኒ የዓመት ክብሯ በረከት በየቤታችን ይግባ። አሜን

1 month, 1 week ago

ዲ/ን ዳንኤል ክብረት:

ጊንጥ አና ጊንጠኞች!!

ብዙ ጊዜ ጊንጥ የሚለውን ቃል ስሰማ ብዙም ትኩረት አልሰጠውም ነበር ዛሬ ግን ጊንጥ አሪፍ ነገር አስተማረኝ፡፡ ይህንን እንድል ያስገደደኝ የዛሬው ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ አጭር ታሪክ ነው ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡
አንድ ሽማግሌ ውሃ ውስጥ ሊሰምጥ ያለ ጊንጥ ያዩና ሊያድኑት ይፈልጋሉ፡፡ ከዚያም ጊንጡን ከውሃው ለማውጣት እጃቸውን ዘርግተው አነሱት በዚህ ጊዜ ጊንጡ ነደፋቸው እሳቸውም ደንግጠው ለቀቁት ጊንጡም ተመልሶ ወደውሃው ገባ፡፡ ሽማግሌው አሁንም የጊንጡን ውሃ ውስጥ መስመጥ ተመልክተው ድጋሚ እጃቸውን ለእርዳታ ዘረጉለት አሁንም በድጋሚ ጊንጡ ነደፋቸው ሲለቁት አሁንም ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ ይህንን የሽማግሌውን ትእይንት የሚመለከት አንድ ሰው ወደ ሽማግሌው ጠጋ ይልና ‹‹ይህ እኮ ክፉ ፍጥረት ነው ጊንጥ እሱን ለማዳን ሲሉ እርሶ እየተጎዱ እኮ ነው›› አላቸው።
ሽማግሌውም እንዲህ ሲሉ መለሱ ‹‹የጊንጡ ተፈጥሮ መናደፍ ነው፡ የኔ ተፈጥሮ ደግሞ መርዳትና ማገዝ ነው፡ ስለዚህ ተፈጥሮዬ ክፉ አደለምና ጊንጡን ከመርዳት አላቋርጥም አረዳዴን ግን አስተካክላለሁ›› አሉና ጥቂት አሰብ አድርገው ተነስተው ከዛፉ ላይ አንድ ቅጠል ቀንጥሰው በቅጠሉ ጊንጡን ይዘው አወጡትና ህይወቱን አተረፉለት፡፡
እኛም እንዲህ ነን ሰውን ለመርዳት ስንሄድ ብዙ ጊንጦች ይነድፉናል፡ ደግ ልናደርግ ስንጓዝ ብዙ እንቅፋቶች ይመቱናል፡፡ ነገር ግን ጊንጡ እንዳይነድፈን እናደርጋለን እንጂ እንቅፋቱ እንዳይመታን እንጠነቀቃለን እንጂ እንዴት ደግ ማድረግ እናቆማለን ???
አንተም አንቺም ሁላችንም እዚህ ምድር ላይ ያለን ሰዎች በሙሉ ስንፈጠር ደግና መልካም ነን፡፡ ግን ሰውን ክፉ የሚያደርገው ተፈጥሮው ሳይሆን መጥፎ አጋጣሚ ነው፡፡ ለዛ እኮ ነው በነዚህ ጊንጦች ስለተነደፍን መልካም ለማድረግ ቅስቀሳ በጎ ለመስራት ማጣራት መጠራጠር በሌላ አይን መመልከት ጀመርን፡፡
እስኪ የዛሬዋን አዲስ ቀናችንን እንዲህ ብንውላትስ ሰው ስንረዳ እንደጊንጥ በሚሆኑ ሰዎች ተሸንፈን መልካም ከማድረግ ከምንቆጠብ የምንረዳበትን መንገድ ለይተን ብናውቅስ፡፡ በነገራችን ላይ ለሰው በጎ ማድረግ ሲባል በገንዘብ ብቻ ይመስለናል አይደለም በየቤቱ ገንዘብ ኖሮት ሰው የናፈቀው ህሊና አለ ስለዚህ አንዳንዶች ፈገግታችንን አንዳንዶች እኛነታችንን አንዳንዶች መሰማትን ይፈልጋሉና በየደረስንበት ለመልካም ነገር ጊንጥ ፈርተን እምቢ እንዳንል፡፡

መልካም የምታደርጉ ሁሉ ግን ጊንጡንም ቢሆን ከማዳን አትቦዝን

2 months, 2 weeks ago
3 months, 1 week ago
4 months, 2 weeks ago
4 months, 2 weeks ago

አዲስ መልካም ዜና**

◈ውድ ኦርቶዶክሳውያን መዝሙር የመልቀቅ ሐሳብ ያላችሁ ነገር ግን የሚዲያ አጋር ያጣችሁ ይኸው እኛ መፍትሄ አምጥተናል።

መዝሙራችሁን በራሳችሁ studio ውስጥ አሰርታችሁ በኛ ቻናል ልንለቅላችሁ አስበና።

ለማናገር ፦** @Official_scor

5 months, 3 weeks ago

አብነት ትምህርት (የየኔታ ትምህርት)

ውዳሴ ማርያም እና ዳዊት በግዕዝ በነፃ በቻናላችን

ጥቅሙ :- ለፀሎት እግዚአብሔርን ማመስገኛ
ቋንቋ :- በግዕዝ እና በትርጉም
ጊዜ :- የማይጋፋ በተመቸ ጊዜ መማር የሚቻል
በፅሁፍ ወይስ በድምፅ :- በሁለቱም
ክፍያ :- የለውም በነፃ በቻናላችን ብቻ

በተጨማሪም ከትርጉም ጋር ይቀርባል
ለመማር :- https://t.me/+vwK-CCz0VeQ2MjY8

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago