Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
- ويروي أصحاب طبقات الصوفية أن علي بن محمد الدينوري أوتي حرف [كن] لكنه قال ((تركت قولي للشيء كن فيكون تأدبا مع الله))
جامع كرامات الأولياء 2: 158.
ዐስሀቡል ጠበቃት ሚለው የሱፍያ ኪታብ
ላይ እንዲህ ይላል:-
አሊ ብኑ ሙሀመድ
ሚባለው ወልይ እንዲህ ይላል:-
#ኩን (كن) ምትለው ሀርፍ ተሰጥታኛለች አንድን ነገር ሁን ስለው ይሆናል ነገር ግን አሁን ትቻታለው ከአላህ ጋር አደብ እንዲኖረኝ ፈልጌ ።
አብዱልጀባር ሙሀመድ ኑር
https://t.me/abduljebarmohammednur
ረውደቱል አንዋር #በአማርኛ በ PDF
የነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የህይወት ታሪክ
“አንዳንድ የስሜት ተከታዮችና ብልሹ አላማ ያነገቡ ሰዎች ይህን የተውሒድን ለሶስት መከፈል ይቃወማሉ፡፡ ፈጠራ እንደሆነም ይገልፃሉ፡፡ ይሄ ከንቱ ማሳሳቻ ነው፡፡ ይሄ አከፋፈል ፈጠራ ከሆነ በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች፣ በተለያዩ ርእሶችና የአሕካም ስያሜዎች ላይ የሚገኙ ከዑለማእ የተላለፉ ክፍፍሎች ሁሉ ፈጠራ ናቸው ማለት ነው፡፡ እውቀቶቹ በተጨባጭ በነብዩ ዘመን የነበሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን የአከፋፈሉ ስያሜዎችና ሙያዊ ቃላት አልነበሩም፡፡ ልክ እንዲሁ የተውሒድ ክፍሎችም ሁላቸውም በቁርኣንና በሱናህ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ያም ሆኖ ግን ሙያዊ ቃላቱ ማለትም ተውሒድ ለዚህ ለዚህ ከፈላልየሚለው በነዚህገለፃዎች መግለፁአዲስ ነው፡፡”[ሸርሑ ተድሙሪያህ፡47]
በተለያዩየእውቀት ዘርፎችብናስስ ተመሳሳይክፍፍሎች ይገኛሉ፡፡በሶላት፣ በውዱእ፣በዘካህ፣ በፆም፣በሐጅና በሌሎችምየፊቅህ ብይኖችብንገባ በቁርኣንናበሐዲስ ቃል በቃልያልተጠቀሱ በተለያዩቁጥርና ስያሜ የተገደቡመስፈርቶችን፣ ግዴታዎችን፣ህግጋትና ደንቦችን፣ሙስተሐቦችን የሚጠቁሙክፍፍሎችንና ሙያዊ ቃላትንበብዛት ማገኘትይቻላል፡፡ ይህን እውነታጀማሪ ደረጃ ላይ የሚገኙኪታቦችን ያንቧተረሁሉ አያጣውም፡፡እነኚህን ክፍፍሎችሲመለከት ማንም የቢድዐህአጀንዳ ውል አይልበትም፡፡ምክንያቱም በቁርኣንናበሱናህ ውስጥ በተጨባጭየሚገኙ እውነታዎችንለማስተማር በሚመችመልኩ ተንትኖመመደብ እንጂ ማስረጃውስጥ የሌሉ ጉዳዮችንመሰንቀር እንዳልሆነግልፅ ነውና፡፡ተውሒድን ለሶስትስንከፍልም በተመሳሳይ፣ቁርኣንና ሱናህ ውስጥያሉ የተውሒድመልእክቶችን በሶስትመደብ ማስቀመጥእንጂ አዲስ ፈሊጥመፍጠር አይደልም፡፡ስለዚህ በየትኛውም
የእውቀትዘርፍ “ይህን ያህልክፍሎች አሉት”፣“ይህን ያህል መስፈርቶችአሉት”፣ “የሚያበላሹትይህን ያህል ናቸው” … ማለት እውቀትንአመቺና ቀላል በሆነመልኩ ለማቅረብእንጂ ቁጥሮቹበራሳቸው አምልኮትሆነው አይደለም፡፡እናም ክፍፍሉየአቀራረብ ስልት እንጂበራሱ ግብ አይደለም፡፡ታ ዲያ እውነታውይህ ሆኖ ሳለአንዳንድ በተውሒድትምህርት ላይ ቂምያረገዙ አካላትያለወትሯቸው ቢድዐንየሚዋጉ በመምሰልየተውሒድን ለሶስትመከፈል ከፈጠራጋር በማቆራኘትአልፎም ከስላሴጋር በማመሳሰልሲያወግዙ ማየት የሚደንቅነው፡፡ ምነው ደግሞወጥ በሆነ መልኩሁሉንም ቢድዐ በየእርከኑበተዋጉ፡፡ ይበልጥግልፅ ለማድረግበሌላ መልኩ እንመልከተው፡፡ሶስቱም የተውሒድክፍሎች በተቃራኒያቸውየበለጠ ግልፅ ይሆናሉ፡፡የነኝህ የተውሒድክፍሎች ተቃራኒሶስት መልክ ያለውሺርክ ወይም ክህደትነው፡፡ በነዚህየተውሒድ ክፍሎችመልእክቶች የማያምንያለጥርጥር ከተቃራኒያቸውላይ ይወድቃል፡፡የነኝህን የተውሒድክፍሎች መልእክትሙስሊም ሆኖ የሚያስተባብልአይገኝም፡፡ በአላህብቸኛ ፈጣሪነት፣በብቸኛ አምላክነቱናልዩ በሆኑ ስሞቹናመገለጫዎቹ የሚያስተባብልሙስሊም ከቶ ከወዴትይገኛል?! እንዲያውም“ላኢላሃ ኢለላህ” የምትለዋ ቃለ-ተውሒድሶስቱንም የተውሒድክፍሎች ጠቅልላእንደያዘች ኢብኑ ተይሚያህረሒመሁላህ ይናገራሉ፡፡ከአላህ ሌላ በሐቅየሚመለክ አምላክአለመኖሩን ማሳየቷየተውሒዱል ኡሉሂያንመልእክት በቀጥታያመላክታል፡፡ የተውሒዱሩቡቢያን መልእክትምእንዲሁ በውስጧአቅፋ ይዛለች፡፡መፍጠር፣ መለገስ፣ማቀናበር፣… የማይችልአምላክ እውነተኛአምላክ ሊሆን አይችልምና፡፡ተውሒዱልአስማእ ወስሲፋትንምእንዲሁ ታመላክታለች፡፡መልካም ስሞችናሙሉእ የሆኑ መገለጫዎችየሌለው ሙሉእ አይደለምና፡፡ሙሉእ ካልሆነደግሞ እውነተኛአምላክም ፈጣሪምሊሆን አይችልም፡፡[አልሙኽተሶሩልሙፊድ፡ 24]
አሁንደግሞ የተውሒድንለሶስት መከፈልከጠቆሙ ዑለማዎችውስጥ ጥቂቶቹንእንጥቀስ፡፡
1. አቡሙሐመድ ዐብዱላህኢብኒ ሙሐመድአንነይሳቡሪይ አልሒሪይረሒመሁላህ (328 ሂ.)፡-
“የተውሒድመሰረቶች ሶስት ናቸው፡አላህን በጌትነቱማወቅ፤ በአንድነቱለሱ ማፅደቅእና በጥቅሉከሱ ባላንጣዎችንመንሳት” ይላሉ፡፡[አልሒልያህ፡ 10/356]
2. ኢብኑበጧህ አልዑክበሪ(387 ሂ.) እንዲህይላሉ፡-
“በፍጡርላይ ግዴታ የሆነውበአላህ ላይ የማመንመሰረቱ ሶስት ነገርነው፡፡ አንደኛ፡ባሪያው የአላህንጌትነት በማመንበፈጣሪ መኖር ከማያምኑአራቋቾች የተለየሊሆን ነው፡፡ሁለተኛ፡ የአላህንአንድነት በማመንበፈጣሪ መኖር አምነውግን ከሱ ጋርተጋሪ ካደረጉትአጋሪዎች የተለየሊሆን ነው፡፡ሶስተኛ፡ አላህ እራሱንየገለፀባቸው እንደ እውቀት፣ችሎታ፣ ጥበብናሌሎችም መገለጫዎችባለቤት እንደሆነማመን፡፡” [አልኢባናህ፡693-694]
3. አቡበክርአጥጦርጡሺ ረሒመሁላህ(520 ሂ.)፡-
“በጌትነቱ፣በብቸኛነቱ እንዲሁምለራሱ በመሰከረባቸውመልካም ስሞቹ፣በላቁ መገለጫዎቹእና በሙሉእመታወቂያዎቹ እንመሰክራለን” ይላሉ፡፡ [ሲራጁልሙሉክ፡1/7]
እነዚህሶስቱም ዐሊሞችበ728 ዓ.ሂ. ከሞቱት ኢብኑ ተይሚያበብዙ ዘመን የቀደሙመሆናቸው “ተውሒድንለሶስት መክፈልበኢብኑ ተይሚያየተጀመረ ነው” የሚሉሰዎች ሙግት ከንቱቅጥፈት እንደሆነየሚያጋልጥ ነው፡፡
4. ኢብኑአቢልዒዝ አልሐነፊይረሒመሁላህ (792 ሂ.) እንዲህይላሉ፡-
“ተውሒድሶስት ክፍሎችንያካትታል፡፡ አንዱ የአላህመገለጫዎችን የሚመለከትርእስ ነው፡፡ሁለተኛው ጌትነቱንየሚመለከት ተውሒድሲሆን አላህ ብቻየሁሉ ነገር ፈጣሪእንደሆነ መግለፅነው፡፡ ሶስተኛውየአምልኮቱ ተውሒድነው፡፡ እሱም ጥራትይገባውና የላቀውአምላክ በብቸኝነትሊመለክ ባለ ሐቅመሆኑንና ተጋሪ እንደሌለውየሚገልፀው ነው፡፡” [ሸርሑ አጥጦሓውያህ፡1/77]
በነገራችንላይ እነዚህየተውሒድን ለሶስትመከፈል የሚቃወሙሰዎች መልኩንይቀይራሉ እንጂ እነሱም ተውሒድንይከፍላሉ፡፡ ለምሳሌከዒልመል ከላም አንጃዎችውስጥ “ተውሒዱንፊዝዛት”፣ “ተውሒዱንፊስሲፋት” እና “ተውሒዱንፊልአፍዓል” ብለው ለሶስትየሚከፍሉ አሉ፡፡[አልሚለል ወንኒሐል፡1/42]፤ [ሪሳላህፊ ዒልሚትተውሒድ፡40]፣ [ኒሃየቱልኢቅዳም፡90]
ሌሎችምእንዲሁ “የተራውህዝብ ተውሒድ”፣“የልዩዎች ተውሒድ” እና “የእጅግልዩዎች ተውሒድ” ብለው ለሶስትመደብ የሚከፍሉአሉ፡፡ ለእንዲህአይነቱ ብልሹ አከፋፈልየዝሆን ጆሮ ይስጠንያሉ ሰዎች ቁርኣንእና ሱናን መሰረትበማድረግ እንዲሁምታላላቅ ዑለማዎችንበመከተል ተውሒድንለሶስት መክፈልንሲቃወሙ ማየት እጅጉንየሚደንቅ ነገር ነው፡፡የአላህ ፈቃዱ ከሆነበቀጣይ በሌላ ርእስእንገናኛለን፡፡
ኢብኑ ሙነወር (አስ ሱንና መጽሔት ግንቦት 2009 የተወሰደ)
ተውሒድን በ3 መክፈል ቢድዐ ነው ?
ተውሒድ“ተውሒዱ ሩቡቢያ”፣“ተውሒዱል ኡሉሂያ” እና “ተውሒዱልአስማእ ወስሲፋት” የተሰኙ ሶስት ክፍሎችእንዳሉት በሰፊውይታወቃል ፡፡ ይሁንእንጂ አንዳንድሰዎች አንዳንድየስሜት ተከታዮችየተውሒድን በዚህ መልኩለሶስት መከፈል“መጤ ቢድዐህነው” በማለት በፅኑሲያወግዙ ይታያሉ፡፡አንዳንዶቹም የዚህ ክፍፍልጠንሳሽ ኢብኑ ተይሚያረሒመሁላህ እንደሆኑይሞግታሉ ፡፡በርግጥየተውሒድን ለሶስትመከፈል የሚቃወሙሰዎች የተቃውሟቸውቀዳሚ ሰበብ በተውሒዱልኡሉሂያህ እና በተውሒዱልአስማእ ወስሲፋትላይ ያላቸውብልሹ አቋም እርቃኑንእንዳይቀር መስጋትነው፡፡ ብዙዎቹእነዚህ አካላት በሚሰቀጥጥመልኩ የሙታንአምልኮ ውስጥ የተነከሩናቸው፡፡ ከዚህምአልፎ በአላህስሞችና መገለጫዎችጉዳይ ከጥንቶቹ ጀህሚያህእና ከሙዕተዚላህጥመቶች በሰፊውይጋራሉ፡፡ ስለዚህእነዚህን ጥፋቶችእንደ ፅድቅ የሚቆጥርአካል በቅጡ ባልያዘውየተውሒድ ትምህርትላይ ትችት ቢሰነዝርብዙም የሚደንቅአይደለም ነገር ግንመታወቅ ያለበት‘ተውሒድ ለሶስትይከፈላል’ የሚሉ ሰዎችማስረጃዎችን ተከትለውከማስተጋባታቸው ባለፈ በምንምመልኩ ኢስላምውስጥ አዲስ
ነገርአለመጨመራቸው ነው፡፡ያለውን አልካዱም፡፡የሌለንም አልጨመሩም፡፡ለነኚህ የተውሒድንለሶስት መከፈልበፅኑ ለሚያወግዙሰዎች ጠቅለልያለ መልስ መስጠትይቻላል፡፡
ሶስቱምየተውሒድ ክፍሎችቁርኣን ውስጥ ያሉናቸው እርግጥቃል በቃል “ተውሒድለሶስት ይከፈላል” የሚል የቁርኣንአንቀፅ ወይም ሐዲሥየለም፡፡ ይሁን እንጂቁርኣንን እናሱናን በጥሞናለሚከታተል የሶስቱምየተውሒድ ክፍሎችመልእክት ፍንትውብሎ ይታያል፡፡(አላህ የሁሉምነገር ፈጣሪ ነው፡ ) (ያ ትፈሩት ዘንድ እናንተንም ከናንተ በፊት የነበሩትንም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ያ ለናንተ ምድርን ምንጣፍ ሰማይን ጣራ ያደረገላችሁ፣ ከሰማይም ውሃን ያወረደላችሁ፤በሱም ለናንተ ሲሳይ ይሆን ዘንድ ከሰብል ያበቀለላችሁ ነው) እናየመሳሰሉ ስለ አላህፈጣሪነት፣ ስለ ስልጣኑ፣ስለ ሲሳይ ሰጪነቱ፣ስለ ሁሉን አስተናባሪነቱየሚያትቱት ማስረጃዎች"የተውሒዱ ሩቡቢያን" መልእክት እንደያዙህሊና ላለው ሁሉአይሰወርም፡፡
(ሀይማኖትን ለሱ ጥርት አድርገው አላህን እንዲያመልኩት እንጂ አልታዘዙም፡፡)አላህን አምልኩ ከሱ ሌላ አምላክ የላችሁም)፤ (በየህዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣኦትንም ራቁ፡፡ በማለት በርግጥም መልእክተኛን ልከናል፡፡) (አንተን ብቻ ነው የምናመልከው ባንተ ብቻም ነው የምንታገዘው) የሚሉትና መሰል መልእክት የያዙ አንቀፆች “ተውሒዱል ኡሉሂያ”የሚባለውን የተውሒድ ክፍል እንደያዙ ግልፅ ነው፡፡
(የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡)(በል “እሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደም፡፡ ለእሱም አንድም ብጤ የለውም” የሚሉትና መሰል አንቀፆች የተውሒዱል አስማእ ወሰሲፋትን መልእክት እንደያዙ ለማን ይሰወራል?!
ታዲያ የትኛው የተውሒድ ክፍል ነው በቁርኣንም በሱናም ውስጥ የሌለው? የነዚህ ሰዎች ተቃውሞ
ቁርኣን ውስጥ የሚገኙ ምእራፎችን ቆጥሮ114 እንደሆኑ መናገር“ቢድዐህ ነው፡፡ ቁርኣን ውስጥ 114 ሱራዎች አሉ የሚል ቃል የለምና” ከማለት ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት ሂሳብ በህሊና ላይ ማመፅ እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም፡፡ እንጂማ ጌታችን አላህ የሶስቱንም የተውሒድ ክፍሎች መልእክት ደግሞ ደጋግሞ በቁርኣኑ ላይ ገልጿል፡፡
ለምሳሌ ሶስቱም የተውሒድ ክፍሎች በአንድ አንቀፅ ላይ የተገለፁበትን እንመልከት፡፡ “(እሱ) የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ላለው ጌታ ነው፡፡ ስለሆነም ተገዛው፤ እሱን በመገዛትም ላይ ታገስ፡፡ ለእሱ አምሳያ ታውቅለታለህን?” [መርየም፡ 65]
ያስተውሉ!!! በመጀመሪያው አረፍተ-ነገር ላይ የጌትነቱ ተውሒድ አለ፡፡ በሁለተኛው ላይ ደግሞ የአምልኮት ተውሒድ አለ፡፡ በሶስተኛው ላይ ደግሞ የስሞቹና የመገለጫዎቹ ተውሒድ አለ፡፡ ስለዚህ “ተውሒድ ለሶስት ይከፈላል” ሲባል ቁርኣን ውስጥ ያሉ ተውሒድ-ነክ ማስረጃዎችን መርምሮ ሶስት መልክ እንዳላቸው ማስፈር እንጂ ያለ ማስረጃ አዲስ ትምህርት መፍጠር አይደለም፡፡ ይህን አስመልክተው ሸይኽ አብዱርረሕማን ኢብኒ ናሲር አልበራክ እንዲህ ይላሉ፡-
የኢብኑ ሰዒድን አዲስ ቻናል ይቀላቀሉ !
*?* (ረድ በአህባሾች ላይ)
هذا كشف شبهات الأحباش في ترويجهم لتحريف معنى استوى إلى استولى ناقلة عن يحيى بن المبارك المتوفى ٢٣٧ هجري
የሚያመጡትን ማምታቻ ዉድቅ ማድረግ
?በኡስታዝ ኸድር ቢን አህመድ አል-ከሚሴ ( አቡ ሓቲም )**t.me/UstazKedirAhmedt.me/UstazKedirAhmedt.me/UstazKedirAhmed
ጨረቃ በመታየቱ ነገ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያው ቀን ይሆናል። ሁላችንም ኸይር ስራ ላይ እንበርታ ! አሏህ ኸይር ከሚሰሩት ..ሰርተው ደግሞ ከሚጠቀሙት ያድርገን !
...አሚን...
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/ibnuseiid
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад