Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

Description
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
قناة رسمية
لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا
(أبو عبيدة) الدعوة السلفية

በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን
እንለቃለን
ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ
ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka
Advertising
We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 month, 2 weeks ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 3 weeks, 1 day ago

💫💫💫NGOjobs💫💫💫
🆕ማንኛውንም ስራ ከ 0 አመት ጀምሮ በየቀኑ እና በየሰአቱ
🆓 ነፃ የትምህርት እድሎች
✔️ስልጠናዎች
🌏 ለማስታወቂያ ወይንም ስራ ለማስነገር @promoter14 ላይ ያናግሩን !
Promotion የምትሰሩ አናግሩን @promoter14
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 2 weeks, 6 days ago

4 дня, 19 часов назад

የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ክፍል 26 የአላህ መልእክተኛ የመሀይማን ህዝቦችን ከተቃረኑባቸው ነጥብ መካከል አዩሁዶች ወደኛ የተወረዱ ናቸው በሚሏቸው ነብያት መልእክት አለመስራታቸው

5 дней, 11 часов назад

የአል ኢርሻድ ኪታብ ደርስ ክፍል 94 ከትንሹ ቂያማ የቀጠለ የሰው ሩሕ እንዴት እንደሚወጣና የት እንደሚሆን

6 дней, 10 часов назад

የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የማኢዳ ምእራፍ ክፍል አንድ የተለያዩ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች ያካተተ ምእራፍ

1 неделя, 4 дня назад

የመሳኢሉል ጃሂሊያ ኪታብ ደርስ ክፍል 25 የአላህ መልእክተኛ የጃሂሊያን ህዝቦች ከተቃረኑበት ነጥብ አንዱ የባጢል ኪታቦችን ፅፈው ከአላህ ነው ማለታቸው

1 неделя, 4 дня назад

🚫 የኢኽዋኖች ግብዝነት ለፍልስጢናዊያን እልቂት ግብአትነት ።

በተደጋጋሚ ለመግለፅ እንደተሞከረው ኢኽዋነል ሙስሊሚን የሚባለው የጥፋት ድርጅት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስካለንበት ደቂቃ ድረስ በዓለም ላይ ባሉ ሙስሊሞች ላይ ለሚደርሰው እልቂትና ሰቆቃ ምክንያቶች ናቸው ።
ኢስላም ወደር በሌለው መለኮታዊው የአላህ ቃል መመሪያነት ነገሮችን ይመዝናል ። አንድን ነገር ከመስራትም ሆነ ከመናገር በፊት ጥቅምና ጉዳቱን እንድናመዛዝን ያዛል ። ጥቅም እንጂ ጉዳት ከሌለው ወይም ከጉዳቱ ጥቅሙ ካመዘነ እንዲሰራ ያዛል ። ከጥቅሙ ጉዳቱ ካመዘነ ደግሞ መስራት ይከለክላል ።
ምክንያቱም የኢስላም ሸሪዓ ጉዳትን በማስወገድና ካልተቻለ በማቅለል በተቃራኒው ጥቅምን በማምጣትና በማብዛት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ነው ። ይህ መርህ በየዘመኑ የሚመጡ መለኮታዊው የአላህ ቃልና የነብዩ አስተምሮን የሚከተሉ ሊቃውንቶች የሚከተሉትና ሚዛን አድርገው ነገሮችን የሚለኩበት ነው ።
የቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶችን ታሪክ የሚያጣናና ፈለጋቸውን የሚከተል ሙስሊም ይህን እውነታ በግልፅ ያገኘዋል ። የቀደምቶችን ፈለግ የሚከተሉ በየዘመኑ የሚመጡ የኢስላም ሊሂቃን ይህን አበክረው አደራ ይላሉ ። ምክራቸውን የሰማ ራሱንም ሆነ ሌሎችን ወደ ጥፋት ከመንዳት ይጠበቃል ። አሻፈረኝ ያለ ሁሌም ለሙስሊሞች ሰቆቃና መከራ እንዲሁም እልቂት ሰበብ ይሆናል ።
ለዚህ ነው የኢኽዋን መሪዮች ሁሌም ለሙስሊም ሀገሮች መፍረስና ለሙስሊሞች እልቂትና ዋይታ ምክንያት የሚሆኑት ። ዐቅል ኖሯቸው በዐቅላቸው ወደ ሐቅ አይመሩ ልቦና ኖሯቸው የዑለሞችን ምክር አይቀበሉ የጥፋቱ ዶቭ ዝናብ ጥሎ ጎርፉ ሁሉን ነገር ጠራርጎ ከወሰደና ሀገርን ምድረበዳ ካደረገ በኋላ ከእንቅልፋቸው ይነቃሉ ። ሲነቁም በዐቅላቸው አይደለም ። ያን ሰቆቃና መከራ ለዲን የተከፈለ መሰዋእትነት ይላሉ ። በዚህ ቅዠት ውስጥ ሆነው ሁሌም የዋይታና ሶቆቃ ድምፅ ማጉያ ይሆናሉ ።
የአሜሪካና እስራኤል ፍልስጤንን ምድረበዳ የማድረግና ፍልስጢናዊያን ህፃናትና አረጋዊያን በቦምብ እሳት የማጋየትና ጀናዛቸው ከፍርስራሽ ስር እንዳይወጣ የማድረግ ዘመቻ ምክንያት የሓማሶቹ ኢኽዋኖች ናቸው ። እነዚህ የሓማስ ኢኽዋን መሪዮች ( አቡ ዑበይዳና የሕያ ሲንዋር ) የመሪዮቻቸውን ሐሰኑል በናና ሰይድ ቁጥብ መርህ ተከትለው ከአዩሁድና ራፊዳ ጋር አንድነት ፈጥረው ነው ለዛሬው የፍልስጢናዊያን እልቂት ምክንያት የሆኑት ።
ሓማስ የያሲር አራፋትን መንግስት ለማዳከም እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ታዛቢነት የፈበረኩት የኢኽዋን ድርጅት ነው ። እየአንዳንዱን የሓማስ እንቅስቃሴ አሜሪካም ሆነ እስራኤል እንዲሁም ኢራን ያውቁታል ። የጡፋኑል አቅሳ ድራማ ዋነኛ ተዋናይ ኢራን ስትሆን ደራሲዮቹ አሜሪካና እስራኤል ናቸው ። እነአቡ ዑበይዳና የሕያ ሲንዋር በሚፈልጉት መልኩ እነርሱ የቀረፁዋቸው ገፀ ባህሪዮች ናቸው ።
የሓማስ ተዋጊዮች የመጀመሪያው ቀን እርምጃ በደራሲዮቹ የተጠናና ለዛ ማጣፊያ የሚወሰደው እርምጃ የሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት ተመዝኖ ወደ ተግባር እንዲቀየር የተደረገ ነው ። ረቦቶቹ የሓማስ ገፀባህሪዮች ግን ጥቅምና ጉዳትን የሚያመዛዝኑበት ዐቅልም ይሁን ዑለሞችን ወይም በዚህ ዙሪያ በቂ ልምድ ያላቸውን የሀገር መሪዮች የሚያማክሩበት ልቦና አልነበራቸውም በተቀደደላቸው ቦይ መፍሰስ ነበር ብልሀታቸው ።
ሶሪያንና የመንን ምንነቱ ባልታወቀ መሳሪያ ያፈረሰችው ኢራን ሩቅ ሆና ድራማውን እያየች በፍልስጢናዊያን ላይ የሚዘንበውን የቦንብ እሳት እንዲጨምር ገፀባህሪዮቹን ደራሲዮቹ የዋጋቸውን ያገኛሉ በርቱ እያለች በእሳቱ ላይ ቤንዚን ስትጨምር ረቦቶቹ ( ግብዞቹ ) የሓማስ መሪዮች ኢራን በገንዘቧና በመሳሪያ እያገዘችን ነው እያሉ መድረክ ይደቀድቃሉ ።
የትኛው መሳሪያ እንደሆነ አላህ ይወቀው ያ በሶሪያ ሰማይ ላይ እያምቧረቀ ሶሪያን ምድረበዳ ያደረገው መሳሪያ ወይስ የመንን ያፈራረሰው ? የትኛው የኢራን መሳሪያ ነው የእስራኤልን ጀቶች ከፍልስጤን ሰማይ ላይ መቶ የጣለው ? ወይስ የኢኽዋን መሪዮችና ራፊዳዎች የፍልስጢንን ህዝብ የሚሸውዱበት የፖለቲካ ድራማ ?
እነዚህ የሓማስ መሪዮች የፍልስጢን ህዝብ በቦንብ እሳት ሲነድ ባዘጋጁት ጉድጓዳቸው ውስጥ ወላፈኑ ለብርድ መከላከያነት ይሞቁ ነበር ። በጣም የሚገርመው ዛሬም የታወቀ ከ40 ሺህ በላይ ህዝብ በፍርስራሽ ስር የቀረ አላህ ብቻ የሚያውቀው አልቆ ሀገሪቷ ምድረበዳ ሆኗ የድል ዜማ ያዜማሉ
ማንኛውም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አሁን የሚያስበው ፍልስጢን እንዴት ወደ ነበረችበት ትመለሳለች የሚል ነው ። ምናልባት ዐቅለቢስ የሆኑት በኢራን ፕሮግራምድ የተደረጉት የሓማስ ረቦቶች ካልሆኑ በስተቀር ።
የዚህ አይነቱ በኢኽዋኖች ምክንያት የሚከሰቱ የሙስሊም ሀገሮች ውድመትና የሙስሊሞች እልቂት የመጀመሪያ አይደለም ። ሊቢያ ፣ ሶሪያ ፣ የመን ፣ ግብፅ ፣ ቱኑስና ዒራቅ የመሳሰሉት የቅርብ ጊዜ ትዝታዎች ናቸው ። ማንኛውም የእነዚህ ሀገር ዜጋ ከንቅናቄው በፊትና አሁን ስላለው ቢጠየቅ የሚሰጠው መልስ ለየአንዳንዳችን ህሊና መተዉ ይሻላል ።

አላህ ከኢኽዋኖች ሽር ጠብቆ ምእራባዊያንን አዋርዶ የሙስሊሞችን ደም ይበቀልልን ። በግፍ የተቃጠሉትንና የተረሸኑትን በሸሂድነት ማእረግ ላይ ያስቀምጥልን ። እሱ ሁሉን ቻይና የሀይል ባለቤት ነውና ።

http://t.me/bahruteka

1 неделя, 4 дня назад

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

አስደሳች ዜና

🎤🎤 ታላቅ የደእዋ ፕሮግራም 🎤🎤
🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰

እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 04/09/2016 ዓ/ል ከወትሮው ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ  ታላቅ የደእዋ ፕሮግራም በቢላል  መስጅድ ስለተዘጋጀ ይህ ታላቅ እድል እንዳያመልጠዎት ስንል እርሰዎን  ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር  በአክብሮት ተጋብዘዋል።

የእለቱ ውድ ተጋባዥ ዳዒዎች
1ኛ  ውዱ ሸኻችን ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ኢብኑ ያሲን አል—ለተሚ

2⃣ኛ. ኡስታዝ ሀቢብ ሃፊዘሁሏህ

3⃣ኛ.ኡስታዝ  እእዘዲን ሃፊዘሁሏህ

ሌሎችም ተጋባዥ ዳዒዎች አሉ።

ሁሉም ርዕሶች በእለቱ ይገለፃሉ !!!!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል !!!!

🕌 አድራሻ፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን በምስራቅ ስልጢ ወረዳ ገርቤበር ከተማ ቢላል መስጂድ።

📅 ዕለተ፡-  እሁድ 04/09/2016

🧭 ሰዓት፡- ከጠዋቱ 2 : 30 ጀምሮ በሰዓቱ ይጀመራል ።

🌷ለሴቶችም በቂና ምቹ ቦታ ተዘጋጅቷል!!!!

ጥብቅ ማሳሰቢያ : –
▬▬▬▬▬▬▬
👉 ይህንን በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ የሆነ ፕሮግራም እንዳያመልጥዎት ፕሮግራሞትን ከወዲሁ በማመቻቸት ከቤተሰብዎ፣ ከጓደኛዎ፣ ከስራ ባልደረባዎ ጋር ለመታደም ቁጥር አንድ ፕሮግራምዎ አድርገው ይያዙ ።

👉 አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል !!!
ትልቁ ችግራችን ማርፈድ ነው ማርፈድን  እንቅረፍ

👉 ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው !!!

✍️አዘጋጅ፡- የገርቤበር ከተማ ቢላል መስጂድ ጀማዕ።

2 недели, 4 дня назад

👉 የኢኽዋን እምባ ጠባቂዎች ሹብሀ ( ብዥታ )

የሱሩርዮች እንባ ጠባቂው ዐልዩል ሐለብይ ያመጣቸውን ቀመሮች በመጠቀም ሀገራችን ላይ ኢልያስ አሕመድና ኢብኑ ሙነወር አብዛኛውን ምስኪን ጢብ ጢብ እየተጫወቱበት ይገኛሉ ።
ይህ የሐለብይ ቀመር ምን መሰላችሁ ከሙብተዲዕ መራቅ ፣ አለመቀማመጥ ፣ ኪታቡን አለማንበብ ፣ ትምህርቱን አለማዳመጥ የሰለፍያ ዳዕዋ አስል ( መሰረት )ና የሰለፎች መዝሀብ መሆኑን እናውቃለን ይላሉ ።
ነገር ግን ይህን መሰረት ለመናድና የሰለፎችን መዝሀብ ለማፍረስ ሌላ ቀመር ያመጣሉ እሱም ከሰለፎች ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ የዑለሞችን ስም እየጠሩ እገሌ የሚባል የሰለፍ ዓሊም እገሌ ከሚባል ሙብተዲዕ ጋር ተቀማምጧል ። ኪታቡን አንብቦ ከሱ ነቅል አድርጓል ። እገሌ የሚባልን ሙብተዲዕ አወድሷል ። ታዲያ እነዚህን ዑለሞች ምን ትሉዋቸዋላችሁ የሚል ነው ።
ድንቄም ሹብሀ !!!
🔹 ሐለብይ ይህን ቀመር ያመጣው ከሙሐመድ ሱሩር ዘይኑል ዓቢዲን ከነሰልማነል ዐውዳና አምሳያዎቹ ለመከላከል ነው ።
🔹ኢልያስ አሕመድ ከዶ/ር ጀይላንና ባልደረቦቹ ለመከላከል ።
🔹 ኢብኑ ሙነወር ከኢልያስ አሕመድና ከመርከዙ ሰዎች ለመከላከል ።
ስለመርከዙ ሰዎች ( ነሲሓዎች) ማንነት ከበቂ በላይ ስላየን አሁን መድገም አያስፈልግም ። ወደ ሹብሀዎቹ ስመለስ
🔹 እእነዚህ አካላት ከኛ ጋር የሚስማሙባቸው ነጥቦችን አሉ እነርሱን እንይ :–
– ሙብተዲዕን መጥላት ማኩረፍ ከሱ ጋር አለመቀማመጥ ፣ ኪታቡን አለማንበብ ፣ ትምህርቱን አለማዳመጥ ……… ወዘተ የሰለፎች መዝሀብ መሆኑን ማመን ።
– እነርሱ የሚከላከሉላቸው አካላት የሚቀማመጡዋቸው ፣ የሚያደንቁዋቸው ፣ አብረውዋቸው የሚሰሩዋቸው አካላት ሙብተዲዕ መሆናቸውን መቀበል ።
🔹 ከኛ ጋር የሚለያዩባቸው ነጥቦች
– ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ይቻላል ምክንያቱም እገሌ የሚባል የሰለፍ ዓሊም እገሌ ከሚባል ሙብተዲዕ ጋር ስለተቀማመጠ ። ኪታቡን ማንበብ ይቻላል ። አብሮ መብላት እሱን ማወደስ ይቻላል ። እገሌ የሚባል ዓሊም እገሌ የሚባል ሙብተዲዕን ኪታብ አንብቧል ። እገሌ የሚባለው የሰለፍይ ዓሊም እገሌ የሚባለውን ሙብተዲዕ አወድሷል ………… የመሳሰሉት መረጃዎች አሉ ።
🔹 የኛ መልስ
– አንደኛ : – ከሙብተዲዕ መራቅ አለመቀማመጥ የሰለፎች መዝሀብ መሆኑን እናምናለን እያሉ እገሌ? ስለሰራው ይቻላል ማለት እርስ በርሱ ይጋጫል ።
– ሁለተኛ :– በቁርኣን በሐዲስና በሰለፎች ስምምነት የተረጋገጠን አስል ( መሰረት) በሆነ ጊዜ የሆነ አካል በሰራው ስራ መረጃነት ማፍረስ በመሆኑ ።
– ሶስተኛ :– የዚህ ምሳሌው አንድ ሰው ዝሙት ፣ ስርቆት ፣ ኸምር መጠጣት ሐራም መሆኑን አውቃለሁ እያለ ነገር ግን የሆነ ሰው ቢጠጣ የጠጣውን አካል መወረፍ ብይን መስጠት ማራቅ አያስፈልግም ምክንያቱም እገሌ የሚባል ሰው በሆነ ዘመን ዝሙት ሰርቶ ፣ ሰርቆ ፣ ኸምር ጠጥቶ ነበር እንደማለት ነው ። ይህ ጤነኛ ዐቅል ያለው ሰው የሚለው አይደለም ። ምናልባት ዐቅሉ ላይ እንከን ያለበት ካልሆነ ።
– አራተኛ አንድ : – አንድ ሰው ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ሐራም ( የተከለከለ ) መሆኑን አውቃለሁ እያለና የሚቀማመጠው አካል ሙብተዲዕ መሆኑን እያወቀ እንዴት በዚህ አይነት ውዳቂ ስሌት መረጃነት ይቀማመጣል ?
– አምስተኛ : – እነዚያ ተቀማምጠዋል ፣ አወድሰዋል ፣ ኪታቡን አንብበዋል የተባሉት ዑለሞች እነዛ አካላት ሙብተዲዕ መሆናቸውን እያወቁ ለመሆኑ መረጃ አምጡ እንላለን ።
– ስድስተኛ :– በቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ስምምነት የፀደቀ መርህ በሆነ አካል ተግባር አይናድም ፣ አይሻርም ። ያ ዓሊም ተግባሩ ወደ ቁርኣንና ሐዲስ በሰለፎች ግንዛቤ መጥቶ ተመዝኖ ብይን ይሰጠዋል ። ትክክል ከሆነ ትክክል ነው ስህተት ከሆነ ስህተት ነው ይባላል ። ግለሰቡን በተመለከተ ሰለፎች ባስቀመጡት መርህ መሰረት መስፈርቱ ሲሟላ ከልካይ ሲወገድ ብይን ይሰጥበታል ።
– ሰባተኛ :– ከሰለፎች እንዲህ አይነት ስሌት ሰርቶ ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ ይቻላል ያለ ዓሊም አምጡ እንላለን ።
🔹 የሀገራችን የኢኽዋን እንባ ጠባቂዎች የሚከላከሉላቸው አካላት ሙብተዲዕ መሆናቸውን እያወቁ በመሆኑ ዑዝር የላቸውም ።

➡️ ማጠቃለያ :–

ኢልያስ አሕመድና ኢብኑ ሙነወር ቀጥተኛውን የሰለፎች ጎዳና ጥለው የቢዳዓ ቆንጥር ውስጥ ገብተው ወጣቱን ወደ ቆንጥሩ እየነዱት ነውና ወጣቶች ሆይ ነፍሳችሁን አድኑ ።

https://t.me/bahruteka

Telegram

ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም https://telegram.me/bahruteka

***👉*** የኢኽዋን እምባ ጠባቂዎች ሹብሀ ( ብዥታ )
2 недели, 5 дней назад

👉 የነሲሓዎች ምንነት በመረጃ ሲረጋገጥ

ክፍል አምስትና
የመጨረሻው ክፍል

የነሲሓዎች ማንነት ሐቅ ለሚፈልግ ከመጀመሪያ ጀምሮ እሳካሁን ባየናቸው ክፍሎች እንደጠዋት ፀሀይ ፍንተው ብለዋል ።
በዚህኛው ክፍል ለማጠቃለያ ያክል ኢልያስ አሕመድ አሁን የደረሰበት ደረጃ በሰለፍያ ሚዛን ለማሳየት የተወሰኑ ነጥቦችን እናያለን ።
የዛሬዎቹ ኢኽዋኖች ( ነሲሓዎችና ) እንባ ጠባቂዮቻቸው የምነወር ልጅና ግብረአበሮቹ ሙብተዲዕን መራቅና ማኩረፍ መጥላት የሰለፎች ሚንሀጅ መሆኑ እናምናለን ይላሉ ። ወደ ነባራዊው ሁኔታ ስንመጣ ተግባራቸው በተቃራኒው ነው ። ይህን መርህ ውድቅ የሚያደርጉ ስሌቶችና ቀመሮችን በመጠቀም ለሙብተዲዕ ጥብቅና ሲቆሙ እናያለን ። ይህ ምናልባት ከቁርኣንና ሐዲስ ከሰለፎች መዝሀብ ጋር ከማስተሳሰር ይልቅ ከራሳቸው ጋር ያስተሳሰሩትን ወጣት እንጂ ሌላውን ለመሸወድ አያስችልም ።
ነሲሓዎች ወጣቱን ከኢልያስ አሕመድ ጋር አስተሳሰሩት ። በመሆኑም እሱ የሚሰራውና የሚለውን ሁሉ ልክ ነው እኛ የማናውቀው ነገር ቢኖር ነው እንዲል አደረጉት ። በዚህም እነዶ/ር ጀይላን ሙሐመድ ሓሚዲን ፣ ካሚል ሸምሱ ፣ አቡ በከር አሕመድና ሓሚድ ሙሳ የመሳሰሉትን የኢኽዋን መሪዮችን ሰለፍዮች ናቸው አለ ተከትለውት አሉ ።
የሙነወር ልጅ የኢልያስ አሕመድና የነሲሓዎች ፀሀይ የሞቀው ሰው ያወቀው ኢኽዋንይነት የተለያዩ ስሌቶችን እያመጣ በማጣፋት ከደሙ ንፁህ ናቸው ለማለት ታተረ ። ነገር ግን የእነርሱ ማንነት በየቀኑ ገሀድ እየወጣ እነርሱም ኢኽዋንይነታቸው የሚያሳፍራቸው ሳይሆን ይልቁንም ሰለፍይነት ስሩርይነት ነው በሚል ስሜት ወደፊት ማለቱን ቀጠሉበት ።
የነሲሓዎች ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ እየሰራው ያለውና የሰለፎች በአህሉል ቢዳዓ ላይ ያለቸው አቋም ለማነፃፀር የተወሰኑትን እንይ : –

ሰለፎች ሙተዲዕን ማላቅና ለሱ ፈገግ ማለት እስልምናን በመናድ ላይ ተባብራል የሚል መርህ ነው ያላቸው ። ይህን አስመልክቶ ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል : –

يقول الفضيل بن عياض – رحمه الله –

" من عظم صاحب بدعة،  فقد أعان على هدم الإسلام،  ومن تبسم في وجه مبتدع،  فقذ استخف بما أنزل على محمد،  ومن زوج كرينته من مبتدع،  فقد قطع رحمها،  ومن تبع جنازة مبتدع لم يزل في سخط الله حتى يرجع ".

أخرجه  ابن الجوزي في تلبيس إبليس بسند صحيح

🔹 አሁንም ፉደይል ኢብኑ ዒያድ እንዲህ ይላል : –

" ሙብተዲዕን ያላ ሰው እስልምናን በመናድ ላይ በርግጥ ተባብሯል ።
በሙብተዲዕ ፊት ፈገግ ያለ አላህ በነብዩ ላይ ያወረደውን ቁርኣን ክብር ዝቅ አድርጓል ።
የተከበረች ሴት ልጁን ለሙብተዲዕ የዳረ ዝምድናዋን ቆርጧል ።
የሙብተዲዕን ጀናዛ የተከተለ ሰው በአላህ ቁጣ ላይ ነው እስኪመለስ ። "

የኢልያስ አሕመድን ተግባር እንይ በሚቀጥሉት ሊንኮች ተመልከቱ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/119ojuz_POBxulM9Zi4wAz_xLO87M5wbP/view?usp=drivesdk
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/1HVcSEMz2AtmT4wPmxzd-c3grzJoLzYFG/view?usp=drivesdk
ኢልያስ አሕመድ እያዋረዳቸው ፣ ፊቱን አጨፍግጎባቸው ነው ወይስ ፈገግ ብሎ እያላቃቸው ነው ? እነዚህ አካላት የቢዳዓ ባልተቤቶች ወይስ ሰለፍዮች ናቸው መልሱ ለናናተ ትቼዋለሁ ። ልብ በሉ ኢልያስ አሕመድ በውልባረግ ፕሮግራሙ ላይ ስለነአዩብና ቡሽራ መርከዙን ወክለው መደመር ሲጠየቅ እኔ ምናገባኝ የተካፈሉት ሁለቱ ናቸው ሌላው ለምን ይጠየቃል ነበር ያለው ። አሁንም እሱ ነሲሓን ወክሎ ነው ይህ ሁሉ ትርኢት ከኢኽዋኖች ጋር እየሰራ ያለው ። አሁንስ ምን ይል ይሆን ለሙሪዶቹ ?
ስለፎች ከሙብተዲዕ ጋር የሚቀማመጥ በኛ ላይ ከሙብተዲዕ በላይ ነው ይሉ ነበር ። ይህን አስመልክቶ ኢብኑ ዐውን እንዲህ ይላል : –

يقول ابن عون – رحمه الله –
" من يجالس أهل البدع أشد علينا من أهل البدع "

🔹 ኢብኑ ዐውን የተባለ የሰለፍ ሊቅ እንዲህ ይላል : –

" ከሙብተዲዕ ጋር የሚቀማመጥ በኛ ላይ ከሙብተዲዕ በላይ ነው "

የኢልያስን ተግባር በሚቀጥሉት ሊንኮች እንመልከትና በሰለፎች መዝሀብ እንመዝነው እንመልከት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1HWUfnITGHyqXU2x615ovQnA8d4_6o49H/view?usp=drivesdk
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/11925FhpYAEDi09TvicMHTtYj-MJtgDj_/view?usp=drivesdk
ኢልያስ አሕመድና የሱ እንባ ጠባቂዮች ምን ይሉ ይሆን ? ሰለፎች ሙተሸዲዶች ወሰን አላፊዮች ነበሩ ወይስ እነ ጣሃ ሀሩን ሰለፍዮች ናቸው ?
ሐቅ ለሚፈልግ እነዚህ ናቸው ነሲሓዎች ከእነርሱ ራሱን ያርቅ ካልሆነ ራሱን እንጂ ማንንም አይሸውድም ።
🔹 ክፍል አንድን ለማግኘት
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/bahruteka/4828
🔹 ክፍል ሁለትን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/4837
🔹 ክፍል ሶስትን ለማግኘት
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/bahruteka/4841
🔹 ክፍል አራትን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/bahruteka/4844

https://t.me/bahruteka

2 недели, 5 дней назад

أحد الإخوة من طلبة العلم من بلاد اليمن كان يتواصل معي من سنوات ثم يسر الله له الالتحاق بالجامعة الإسلامية في المدينة النبوية كتب لي لما جاءته دعوة حفل التخرج الذي سيقام للدفعة التي يدرس فيها هذه الرسالة :

الحمدلله أولا وآخرا

تخيل ياشيخ قبل مجيئي إلى المملكة
حفظها الله درست سنة في اليمن وتركت بسبب الظروف ماقدرت أواصل
والله أكرمني بالجامعة الإسلامية

لا أقول هذه الرسالة تزلفا أومن أي قبيل
ولكن من باب لا يشكر الله من لا يشكر الناس

تخيل يتكفلوا لك بالسكن والمصاريف
والأكل والشرب والإنترنت
وحق الطريق ذهاب وإياب
حق الكتب
ومقعد دراسي.

كل هذا بدون مقابل ...وفوقها لا يريدون منك جزاء ولا شكورا وإنما تؤدي الرسالة التي جئت من أجلها...

يعني بالله مثل هذه البلاد وهؤلاء الحكام
يحرض عليهم ويحقد عليهم ؟!!

أو شي أقسم بالله إنهم يعطوك أكثر من بلدك التي أنت تنتمي لها !!

خيرهم في كل مكان وإنما أسرد لك ما عشته في هذه السنوات

وبفضل الله ثم الجامعة بنيت وتزوجت والله إن هذه البلاد نعمة وخير

وطن من لا وطن له.
نصيحة والله حافظوا على بلادكم ودافعوا عنها وعن حكامها بكل ماتستطيعوا .

وربي إن هذه البلاد المهج ترخص لها ...

الله يديم هذي البلاد للمسلمين
تخيل أكثر من ١٠٠ جنسية في الجامعة

لما يرجعوا ينشروا الإسلام في ميزان حسنات هذه البلاد

يعني بالمختصر أقول لك : هذه البلاد والحكام ليس للسعودين فقط

خيرها لجميع المسلمين في كل مكان ولا ينكر هذا إلا من في قلبه مرض .

وقد استأذنته في نشر رسالته من باب ( وأما بنعمة ربك فحدث ) فأذن بذلك وفقه الله وجعله من أئمة المتقين وأنصار دعوة التوحيد والسنة
وجزى الله ولاة أمرنا عنا وعن المسلمين خير الجزاء وثبتهم على التوحيد والسنة وزادهم من فضله نصرة للدين وأهله .

وصلى الله وسلم على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين

كتبه :
محمد بن راشد الحبشان
20 شوال 1445

4 недели, 1 день назад

👉 የነሲሓዎች ማንነት በመረጃ ሲረጋገጥ

🔹 ክፍል ሶስት

በክፍል ሁለት ላይ ነሲሓዎች መጀመሪያ ወደ ሰለፍያ ዳዕዋ ይጣሩ እንደነበርና በኋላ ግን ይህ የማያወጣ ነው ብለው ከኢኽዋን ሱፍይና አሕባሽ ጋር እንደተደመሩ አይተናል ። አላህ ካለ በዚህኛው ክፍል ደግሞ ነሲሓዎች ሄደው በጉያቸው የገቡባቸውና መሪዮቻቸው አብረውዋቸው ዘና ፈታ የሚሉዋቸውን የኢኽዋኖችና የአሕባሽ መሪዮች ማንነት በመረጃ እናያለን ።
በመጀመሪያ የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት የሆነውና የነሲሀው ሸይኽ ኢሊያስ አሕመድ በሚሊኒየም ፕሮግራማቸው ላይ በክብር እንግድነት እንደፍቅረኛ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከአሕባሽ መሪዮች በአንዱ ታጅበው ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ያመሩትን ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ ማንነትና ለሰለፍያ ዳዕዋ ያለውን ቦታ በሚመለከተው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ : –
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/10xPY0-FlUGwoM3Qp10zqLC2zj4l1pOR9/view?usp=drivesdk
ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ሰለፍያ ተለጥፎብን የነበረ ታፔላ ነበር ገለን ቀብረነው ለቅሶውንም ጨርሰናል ይለናል ። ይህ ነበር ረመዳን መግቢያ ላይ ነሲሓዎች ባዘጋጁት የሚሊንየም አዳራሽ ፕሮግራም ላይ የክብር እንግዳና የኢልያስ አሕመድ ጓደኛ የነበረው ። አሁንም ይኸው የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት ጫትን አስመልክቶ ምን እንደሚል በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ : – 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/126kmMZiFWGK8_xdLHtlBW0QKwlBVMcrD/view?usp=drivesdk
ከኢኽዋን መሪዮች አንዱ የሆነው ሌላኛው ሙሐመድ ሓሚዲን የሀገራችን ሙስሊሞች ሁሉም ሱንዮች ናቸው ሀገራችን የአህሉ ሱና ሀገር ነች ይለናል ። ስለየትኛው ሀገር ይሆን የሚነግረን ? ለማንኛውም ንግግሩን በሚቀጥለው ሊንክ ያገኙታል : –
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/12EUA74JaGqwLJFs_vz_Z-oPbT6hEOiVa/view?usp=drivesdk
ሌላኛው የኢኽዋን መሪና የነሲሓዎች ዶክተር ( አዩብ ደርባቸው ዶክተራችን የሚለው) ዶ/ር ጀይላን ከአሕባሽና ሱፍዮች ጋር የሰለፍይ ወጣቶችን የሱፍይና የአሻዒራ መዝሀብ እንዲቀበልና ከጣሃ ኋላ እንዲሰግድ ምን መደረግ እንዳለበት ሲያሴር በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ያዳምጡ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/19vjzYzG__9bfQwd4ZH9mTze4rRB5kS4H/view?usp=drivesdk
ይኸው ደ/ር የሱፍይ ልጅ እንደሆነና ሁላችንም ሱፍዮች ነን ይላል ። ነሲሓዎች ተቀብለውት ተደምረዋል ። እኛ ግን አላህን እናስመሰክራለን ሰለፍዮች ነን ሱፍይ አይደለንም ። ከመሆንም በአላህ እነጠበቃለን ። ለማንኛውም ንግግሩን በሚቀጥለው ሊንክ ያገኙታል : –
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/19lzlIW2rSdgTQS1Zl4TlXPRwAv-_oEYJ/view?usp=drivesdk
ሌላኛው የኢኽዋን መሪና የመጅሊስ ባለስልጣን የሆነው የነሲሓዎች ጓደኛ ሓሚድ ሙሳ ስለመውሊድ ምን እንደሚል በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ስሙት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/10tmVvIxrJlOnsVbSBAmHiEo2Om0mts4Q/view?usp=drivesdk
አሁንም የነሲሓዎች ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ አብሮት ዘና ፈታ የሚለው የኢኽዋን መሪ አቡበከር አሕመድ ስለዒሳ ምን እንደሚል በሚቀጥለው ሊንክ ያገኙታል : –
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/128j6TXg7aMADMhSyFeCqop1zhFPf9tN4/view?usp=drivesdk
እንደገና ይኸው የጀነት ሙሽራ የሚባልለት የነሲሓዎች ጓደኛ አቡበከር አሕመድ ሁላችንም የፈጣሪ ልጆች ነን ሲል በሚቀጥለው ሊንክ ገብታችሁ ስሙት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1A-66qzb8kXkcZi5xlKqodfdlKd2tD4c-/view?usp=drivesdk
ሌላኛው የከሰረ የኢልያስ አሕመድ የጅማ ጉዞ ጓደኛ ያሲን ኑሩ ኢትዮዽያ ሀገር ሳትሆን እምነታችን ነች ሲል እስኪ ስሙት :–
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://drive.google.com/file/d/1A5lroest_2pSDZqRMPIQtqgfkweDnS8F/view?usp=drivesdk
እነዚህ ነሲሓዎች የተደመሩዋቸውና አብረውዋቸው በኢኽላስ በሚመስል መልኩ እየሰሩ ያሉት ከኢኽዋን መሪዮች ጥቂቶቹ ሲሆኑ ከአሕባሽ መሪዮች ዋነኛውና አሕባሽን ወክሎ በመጅሊሱ በምክትል ፕሬዝዳንትነት የተመረጠው ብዙ የቀብር አምልኮ ቦታዎችን በሀላፊነት የሚያስተዳድረው የዘቢሞላው ዐ/ከሪም ምንነት በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/117oHbpIziWHa4u42eN0yKvZmpjnhzB6s/view?usp=drivesdk

አላህ ካለ የነሲሓዎች ከእነዚህ አካላት ጋር አሁን ያላቸው ወዳጅነት በመረጃ በሚቀጥለው ይዤ እቀርባለሁ ።

https://t.me/bahruteka

We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 month, 2 weeks ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 3 weeks, 1 day ago

💫💫💫NGOjobs💫💫💫
🆕ማንኛውንም ስራ ከ 0 አመት ጀምሮ በየቀኑ እና በየሰአቱ
🆓 ነፃ የትምህርት እድሎች
✔️ስልጠናዎች
🌏 ለማስታወቂያ ወይንም ስራ ለማስነገር @promoter14 ላይ ያናግሩን !
Promotion የምትሰሩ አናግሩን @promoter14
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 2 weeks, 6 days ago