A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 1 day, 21 hours ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 3 months, 1 week ago
🔷 የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው
ክፍል ሰባት
ዳዕዋ ኢለላህ
የተብሊግ ጀማዓ አጠቃላይ እንቅስ ቃሴያቸውን በህይት አንድ ጊዜ አራት ወር ፣ በአመት አርባ ቀን ፣ በወር ሶስት ቀንና በአካባቢ መቃሚና ኢንቲቃሊይ ፣ እንዲሁም በአካባቢ መስጂድ ላይ ተዕሊም በሳምንት ጀውላ በሚል ይከፋፍላሉታል ።
በቁጥር ስድስት ላይ እንዳየነው አንድን ሰው አሳምነው ይዘውት ለሶስት ቀን ካወጡት በኋላ ሰው ፊት ቆመህ አስተምር አላህ ያናግርሀል ይሉታል ። ከላይ ያየናቸው በህይወት ፣ በአመትና በወር የሚሉ ክፍልፍሎች ምንም መረጃ የሌላቸው ሲሆን የዳዕዋ መሻኢኾት ተርቲብ ነው ይላሉ ።
በወር ለሶስት ቀን ሲወጡ በየምደባቸው ከአሚራቸው ጋር ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የ24 ሰአት የስራ ምደባ ያደርጋሉ ። በዚህ ምደባ ኻዲም ይመደባል ፣ ኢዕላን የሚያደርግ ይመደባል ፣ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በያን ( ሙሓደራ ) የሚያደርግ በመመደብ ይከፋፈላል ። ዐስር ሶላት ላይ ከጀማዐው አንዱ ተነስቶ " ዛሬ በአዱንያ ነገ በአኼራ ፈላሕና ነጃ የምንወጣው የአላህን ትእዛዝ በነብዩ መንገድ በመፈፀም ነው " ይህን በተመለከተ ከሶላት በኋላ በያን ተደርጎልን ጀውላ እናደርጋለን እኛ ሙሀጂሮች እናንተ አንሷሮች ሆነን በጋራ እንሰራለን ለአካባቢው እውሮች ስለሆንን የማይሰግዱና የታመሙ ሰዎች ቤትና እንዲሁም የአዛውንትና ዑለሞች ቤት የሚያዘይረን እንፈልጋለን ይላል ። ከሶላት በኋላ ለጀውላ ( አጃባቢ ላይ ለመዞር) ሰው ይመደባል ።
ጀማዓው በሶስት ወይም በአራት ተከፍሎ አሚር ፣ ደሊል ( ቤት የሚያሳይ)ና ሙተከሊም ( ተናጋሪ ) ተብሎ ይሄዳል ። ለዚህ ለወጣው ጀማዓ ኢስቲጝፋርና ዱዓእ የሚያደርግ አንድ ሰው ተመድቦ መስጂድ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ይህ የተቀመጠው ሰው ለወጣው ጀማዓ እንደ ዲናሞ ( አንቀሳቃሽ ) ነው የሚል እምነት አለ ። በዚህ ሰውና በወጣው ጀማዓ መካከል ተዋሱል ( በውስጥ መገናኘት) አለ ይላሉ ። የወጣው ጀማዓ የሆነ ችግር ከገጠመው ሞተሩ ጠፍቷል ፣ እንቅልፍ ወስዶታል ፣ ወይም ወሬ እያወራ ነው ሶኬቱ ተነቅሏል ብለው ያምናሉ ።
የዚህ አይነቱ እምነት ዐቂዳን የሚነካ ከባድ ሽርክ ነው ። ከዚህም ውጪ በቀዳእና ቀደር እምነት ላይ አደጋ ነው ። ማንኛውም ነገር የሚሆነው በአላህ ውሳኔ ሲሆን የእገሌ መተኛት ወይም ወሬ ማውራት ውጤት ከዚህ ጋር ግንኙነት የለውም ። በውስጥ መገናኘት የሚባል እምነት የሱፍዮች ሲሆን ከእስልምና አስተምሮ የራቀ ነው ።
ተመድቦ የወጣው ጀማዓ በሄደበት ቦታ ምንም አይነት ሙንከር ቢያይ ኢንካር ማድረግ አይችልም ። ለምሳሌ ወንድና ሴት አንድ ላይ ቁጭ ብለው ሙዚቃ ከፍተው ጫት ሲቅሙ ቢያዩ ይሄ ተግባር ክልክል ነው አይሉም ምክንያቱ ደግሞ በዳዕዋ አዳብ አይፈቀድም የሚል ነው ።‼ ይህን ሙንከር እያዩ ዛሬ በአዱንያ ነገ በአኼራ ፈላሕና ነጃ የምንወጣው ብለው ይህን በተመለከተ ከመጝሪብ በኋላ በያን ስላለ ብትመጡ ምን ይመስላችኋል ይላሉ ። ቶሎ በሄዱልን የሚሉት ጎረምሶች ኢን ሻ አላህ ብለው በመጮ ቶሎ ሂዱልን ብቻ የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ ። ይህ ደግሞ የእስልምናን ትልቅ መርህ የሚጥስ ነው ። አላህ በተከበረው ቃሉ ስለ ነብዩ ኡማህ ምርጥነትና ምርጥ ያደረገው ምን እንደሆነ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎ ነግሮናል :–
« كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ ۗ وَلَوْ آمَنَ أَهْلُ الْكِتَابِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُم ۚ مِّنْهُمُ الْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ الْفَاسِقُونَ »
آل عمران
" ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ ፡፡ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር ፡፡ ከነርሱ አማኞች አሉ ፡፡ አብዛኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው "፡፡
የተብሊግ ጀማዓዎች ይህንና መሰል አንቀፆች ቦታ አይሰጡዋቸውም ። ከዚህ ይልቅ መሻኢኽ የሚሏቸው የሚናገሩትን ነው ቦታ ሰጥተው ስራ ላይ የሚያውሉት ። ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በሚደረገው ሙሓደራ አላህ ያናግርሀል የተባለው ስው ፊት ቆሞ ላብ በላብ ሆኖ ፀጉሩን እያከከ ምንም አላውቅም የአሚር ትእዛዝ ሆኖብኝ ነው የተነሳሁት ሲል ጀማዓው አላህ እንዲያናግረው ሁሉም አይኑን ጨፍኖ አስተጝፊሩላህ ይላል ።‼
ምናልባት የተመደበው ሰው የሶሓባ ባህሪይ የሚሏቸውን ስድስቱ ነጥቦች የሸመደደ ከሆነ የነጥቦቹን ቱሩፋቶች እየዘረዘረ ስድስተኛው ላይ ሲደርስ የቻለውን ሁሉ ብሎ ለዳዕዋ እንዲነይቱ ያደርጋል ። በፈላ ውሃ የገባው በሚቀጥለው ዙር ህዝብ ፊት ቆመህ ተናገር ሊባል ይችላል ።
ይህ የተብሊግ ጀማዓ የዳዕዋ ነጥብ ያየንበት ሲሆን 20 አዳብ የሚባሉትን ጀማዓው እንዳጠቃላይ የሚመራበት መርህ አላህ ካለ በሚቀጥለው የምናየው ይሆናል ።
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
ያለፉትን ክፍሎች ለማግኘት
አስሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
አዲስ ኦንላይን (የቀጥታ ስርጭት)የቂርኣት ፕሮግራም ለሴቶች ብቻ ከአልኢስላሕ መድረሳ
እነሆ አልኢስላሕ መድረሳ በተለያዩ ቦታዎች ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሚገኙና በአካል ደርስ መከታተል ለማይችሉ እህቶች በቴሌግራም የቀጥታ ስርጭት (ኦንላይን) ደርስ አዘጋጅቶ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም በቀጥታ ስርጭቱ ደርስ ተሳትፋችሁ መማር የምትችሉ እህቶች መድረሳው በሚያስቀምጠው መስፈርት ተመዝግባችሁ መማር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።
አጠቃላይ የኪታብ ማስተማሪያ ግሩፑ ከታች ያለው ሲሆን የእያንዳንዱ ሙስተዋ ተማሪ የራሱ ግሩፕ ይኖረዋል።
https://t.me/alislaahwomenonlineders
**ማስታወሻ:-
1) ይህ የቂርኣት ፕሮግራም በአልኢስላሕ መድረሳ አስተባባሪነት የመድረሳውን ትምህርቶች በአካል መከታተል ለማይችሉ እህቶች የተዘጋጀ ነው።
2) በዚህ ቂርኣት ፕሮግራም የሚሳተፉት ሴቶች ብቻ ናቸው።
3) በዚህ ፕሮግራም ኦንላይን የሚሰጡ ቂርአቶችን ከሚማሩ ተማሪዎች ምንም አይነት ክፍያ መድረሳው አይጠይቅም። አይሰበስብም።
4) ማንኛዋም ተማሪ መድረሳው በሚሰጠው ትምህርት ላይ ለመሳተፍ መመዝገብ ግዴታ ነው። ያልተመዘገበ ተማሪ አይማርም።
5) ማንኛውዋም ተማሪ የምትማረው ያለችበት የቂርኣት ደረጃ (ሙስተዋ) ተለይቶ ስለሆነ ትክክለኛ ያለችበትን ሙስተዋ ለመለየት እንዲያግዝ ስለራሷ የቂርኣት ደረጃ ትክክለኛ መረጃ መስጠት አለባት።
6) በጠቅላላ ሁሉንም ሙስተዋ የሚመለከቱ የኪታብ ደርሶች የሚሰጡት በወንድ ኡስታዞች ይሆናል።
7) የቁርኣን፣ የተጅዊድና ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ቂርአቶች የሚሰጡት በሴት አሳቲዛዎች ብቻ ይሆናል።
8) ተማሪዎች በየጊዜው የሚሰጠውን የሙከራ ፈተና በስርዓት መፈተን ይኖርባቸዋል።
ለመመዝገብና ለመማር የምትፈልግ ማንኛዋም ተማሪ ከታች ያለውን ፎርም በትክክል በመሙላት መላክ ይኖርባታል። 👇*👇*👇
https://docs.google.com/forms/d/1PJwh0gz-gENe7JABvDeXlYjx3r0YvBc3979-OnoN-eI/edit?usp=drivesdk
🔷 የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው
ክፍል ስድስት
ዳዕዋ ኢለላህ
የተብሊግ ጀማዓዎች ትልቁ ትኩረታቸው ኹሩጅ ፊ ሰቢሊላህ የሚል ነው ። እንደሚታወቀው እነዚህ ጀማዓዎች የዳዕዋቸው ዋናው ነጥብ ፈዳኢልን ( ቱሩፋትን ) ማሳወቅ ነው ። ዳዕዋቸው ትኩረቱ ፈዳኢል ላይ ያተኩራል ። ይህ ማለት ደግሞ አላህ የሰው ልጆችን ከኩፍርና ሽርክ ጨለማ ለማውጣት 124 ሺህ ነብያት የላከበትን መርህ ይቃረናል ። ምክንያቱም አላህ ነብያቶች የላከው ለህዝቦቻቸው አልህን ብቻ እንዲያመልኩና ጣኦታትን እንዲርቁ እንዲያስተምሩ ስለሆነ ነው ። ይህን አስመልክቶ ቁጥር ስፍር የሌለው የቁርኣን አንቀፆች መጥቷል ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን እንይ : –
« وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ ۚ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ »
النحل ( 36 )
" በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል ፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ "፡፡
« لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ »
الأعراف ( 59 )
ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»
« وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ فَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ »
الأعراف ( 85 )
" ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው ፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም ፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች ፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው ፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው ፡፡»
« وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ »
هود ( 61 )
" ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን) ፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው " ፡፡
እነዚህ ከብዙ ነብያቶች ለምን እንደተላኩ ከሚገልፁ አንቀፆች ጥቂቶቹ ናቸው ። ነብያቶች ስራቸው ዳዕዋ ነበር ስለዚ ዳዕዋ አደርጋለሁ የሚል አካል ዳዕዋው ነብያቶች ያደረጉት ዳዕዋ መሆን ይነርበታል ። ወደ ተውሒድ መጣራትና ከሽርክ ማስጠንቀቅ ። የተብሊግ ጀማዓዎች ግን በተቃራኒው ወደ ተውሒድ የሚጣሩትን ጠላት አድርገው ሰው እንዳይሰማቸው ያስጠነቅቃሉ ። ወሀብይ እያሉ ያጠለሻሉ ። ዳዕዋ ብለው ይወጡና መሻኢኾች ያስቀመጡት አዳብ ብለው በስድስቱ የሶሓባ ባህሪይ በሚሉዋቸው ነጥቦች ብቻ ሙሓደራ ያደርጋሉ ።
አብዛኞቹ ዳዕዋ ብለው የሚወጡ ሰዎች ከተለያየ ቦታ የሚሰበሰቡ ስለሆኑ ስለእስልምና እንኳን በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው ። እነዚህ ሰዎችን አሳምነው እንዲወጡ ያደርጉዋቸውና ተመድበው የሆነ መስጂድ ይሄዳሉ ። እዛ ከደረሱ በኋላ አሚር ተብሎ በተመደበው ሰው አማካይነት የስራ ክፍፍል ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ የወጣውን ሰው ዛሬ በያን ( ሙሓደራ) አንተ ታደርጋለህ ይባላል ። ሰውየው ላብ በላብ ሆኖ እኔ ምንም አላውቅም እንዴት ሰው ፊት እቆማለሁ ሲል አብሽር አላህ ያናግርሃል መርሀባ በል የአሚር ትእዛዝ ነው ይባላል ። ‼
አላህ ካለ ይቀጥላል ።
ክፍል አንድን ለማግኘት
ክፍል ሁለትን ለማግኘት
ክፍል ሶስትን ለማግኘት
ክፍል አራትን ለማግኘት
ክፍል አምስትን ለማግኘት
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ
የማኢዳ ምእራፍ ክፍል 11
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ማንኛውንም ነገር ዝም ብላችሁ አትጠይቁ ግልፅ ቢሆንላችሁ ያስከፋችኋልና የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት
من وصايا سفيان الثوري رحمه الله تعالى:
" إيّاك أن تخون مؤمنا، فمن خان مؤمنا فقد خان الله ورسوله، وإذا أحببت أخاك في الله؛ فابذل له نفسك ومالك.
وإيّاك والخصومات والجدال والمراء، فإنك تصير ظلوماً خواناً أثيماً، وعليك بالصبر في المواطن كلها، فإنّ الصبر يجرّ إلى البرّ، والبرّ يجرّ إلى الجنة ".
[حلية الأولياء(٨٢/٧)]
**قال ابن مسعود رضي الله عنه؛
لأَنْ أَعُضَّ على جَمْرَة حتى تَبْرُدَ .
أَحَبُّ إليّ من أن أقول لِشيء قد قَضاه الله .
لَيْتَه لم يَكُن.
?أبوداود في الزهد١٢٨**
?የሙስሊሞች የእምነት ደረጃዎች
አሏህ - ዓዘ ወጀልለ - በተከበረው ቁርዓን የሚከተለውን ተናግሯል:-
" أَوْرَثْنَا ٱلْكِتَٰبَ ٱلَّذِينَ ٱصْطَفَيْنَا مِنْ عِبَادِنَا ۖ فَمِنْهُمْ ظَالِمٌ لِّنَفْسِهِۦ وَمِنْهُم مُّقْتَصِدٌ وَمِنْهُمْ سَابِقٌۢ بِٱلْخَيْرَٰتِ بِإِذْنِ ٱللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ" (فاطر :٣٢)
"ከዚያም እነዚያን ከባሮቻችን የመረጥናቸውን መጽሐፉን አወረስናቸው። ከእነርሱም ነፍሱን በዳይ አልለ። ከእነርሱም መካከለኛ አልለ። ከእነርሱም መካከል በአላህ ፈቃድ በበጎ ስራዎች ተቀዳሚ አልለ።" (ፋጢር :32)
እነዚህ ሶስቱም ክፍሎች ሙስሊሞች ናቸው። ነገር ግን በመካከላቸው የኢማን መበላለጥ አልለ።
?የመጀመሪያው ክፍል ነፍሱን በዳይ ነው :- እርሱ ሙስሊም ቢሆንም የተወሰኑ ጉድለቶች ከእርሱ ላይ ይስተዋሉበታል።
አንዳንድ ሐራም (እርም) ነገሮችን ይዳፈራል ፣ በአንዳንድ ዋጅቦች (ግዴታዎች) ላይ ጉድለቶችን ይፈጽማል።
?ሁለተኛው ክፍል መካከለኛው ነው :- ዋጅባቶችን (ግዴታዎችን) ይፈጽማል። ሀራም (እርም) ነገሮችን ይርቃል። ነገር ግን ሱናዎችና ተወዳጅ (ሙስተሐብ) ተግባራቶች ላይ ትኩረቱ ቀላል ነው። አንዳንድ የተጠሉ (ከረሐ) ተግባራትን ይፈጽማል።
?ሶስተኛው ክፍል ለመልካም ተግባራት የሚሽቀዳደም ነው : ፈርዶችንና ሱናዎችን በአግባቡ ይፈጽማል። እርም የተደረጉና የተጠሉ ተግባራትን ይርቃል። የተጠሉ ተግባራት (ከረሐ) ማለት ከሐራም ደረጃ ያልደረሱ ክልክል ነገሮች ሲሆኑ እነርሱን የተገበረ የማይቀጣበት ፣ ለአላህ ብሎ የተዋቸው ደግሞ የሚመነዳበት ማለት ነው።
በመልካም ተግባራት ቀዳሚ የሆኑ ሰዎች እርም ነገሮችም ይሁኑ የተጠሉ በአጠቃላይ ክልክል ነገሮችን በየደረጃቸው ይርቃሉ ፤ግዴታዎችን ይፈጽማሉ፤ ትርፍ ስራዎችን ወይም ሱናዎችን በብዛት ይፈጽማሉ። ይሁን እንጅ ድንበር አያልፉም።
ለምሳሌ : አንዳንድ ሰዎች "እኔ ዘዎትር እንቅልፍ ሳልተኛ ሌሊት ቆሜ አድራሁ" ፤ "ሳላፈጥር ዘዎትር እጾማለሁ" ፤ "ሴት ከነአካቴው አላገባም" ይላሉ።
ይህ በኢስላም ላይ ድንበር ማለፍ ፣ የነብዩን ሱና መጣስ ፣ ከነብዩ ሱና መራቅ ነው።
እንዲህ አይነቱን ተግባር የአላህ መልክተኛ - አለይሂሶላቱ ወሰላም - በሚከተለው ሐዲሳቸው አውግዘውታል:-
فمَن رغِب عن سنَّتي فليس منِّي
"ከሱናዬ ያፈነገጠ ፣ ከእኔ አይደለም"
እኛስ ከሶስቱ የሙስሊም ደረጃዎች ከየትኛው እንመደብ ይሆን?
አሏህ በእምነት ከቀዳሚዎች ያድርገን!
كن على بصير
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የማኢዳ ምእራፍ ክፍል 10
እናንተ ያመናችሁ ሆይ የሚያሰክር መጠጥ ቁማር ጣኦታት አዝላም ( በእጣ ገድ ማየት) እርክሰትና የሸይጣን ተግባር ነው ራቁት የሚለው አንቀፅና ሌሎችም የተብራሩበት ።
? ከቀደምት ሊቃውንቶች ምርጥ ንግግር
"خلق الله الملائكة عقولاً بلا شهوة ، وخلق البهائم شهوة بلا عقول، وخلق ابن آدم وركب فيه العقل والشهوة ، فمن غلب عقله شهوته التحق بالملائكة ، ومن غلبت شهوته عقله التحق بالبهائم " .
"አላህ መላኢካን ዐቅል ሰጥቶ ያለ ስሜት ፈጠራቸው። እንሰሳትን ደግሞ ስሜት ሰጥቶ ያለ ዐቅል ፈጠራቸው። የሰውን ልጅ ፈጥሮ ዐቅልና ስሜት አደረገለት። ዐቅሉ ስሜቱን ያሸነፈለት ሰው ወደ መላኢካ ይጠጋል። ስሜቱ ዐቅሉን ያሸነፈበት ሰው ደግሞ ወደ እንሰሳ ይጠጋል ‼።
የቁርኣን ትርጉም ማብራሪያ የማኢዳ ምእራፍ ክፍል 09 እነዚያ አላህ ማለት እሱ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው ያሉት በርግጥ ከፍረዋል የሚለውና ሌሎችም አንቀፆች የተብራሩበት ።
A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 1 day, 21 hours ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 3 months, 1 week ago