ከፍልስፍና ዓለም (The world of philosophy)

Description
ይህ ቻናል ማንኛውም ፍልስፍና ተኮር የሆኑ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ነው ። ፍልስፍናን እንደነብሴ እወዳለሁ ያለ ሁሉ ይቀላቀለንና አብሮን ፍልስፍናን ይኮምኩም...
ፍልስፍና ሁሉ ነገር ነው ።
ፍልስፍና ህይወት ነው ። @filsfina

ግሩፓችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @booksforall32
ለአስታየት እና ለCross @simba23 ወይም @Eftah32
የሴክስ ኖትፊኬሽን ያለው ፕሮሞ አንቀበልም!!
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

4 years, 1 month ago

ዶክተርስ ኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ፕሮግራም

[በኢትዮጵያ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ሃኪሞች ላይቭ(Live) ህክምና የሚያገኙበት በ ሀገራችን የመጀመሪያው ከየትኛውም ሀገር online ህክምና የሚያገኙበት

ዘወትር አርብ ምሽት 3:20 በ ፋና ቴሌቪዥን
በተለያዮ ስፔሻሊስት ሃኪሞች ቤቶ ሆነዉ ህክምና ሚያገኙበት

ባዘጋጀኘው አዝናኝ ውድድሮች እስከ ነፃ ህክምና ሽልማቶች ስላዘጋጀን አሁኑኑ ቻናላችንን ይቀላቀሉ](https://t.me/joinchat/AAAAAEGvgnYXOueEE2wSKg)

ነፃ ህክምና ያግኙ
???????????
https://t.me/joinchat/AAAAAEGvgnYXOueEE2wSKg

4 years, 11 months ago

ተሸካሚ በሌለበት ሸክም የለም...!!

፨፨፨

<< አንድ ነገር የሚታየው በሌላ አካል ለመታየት ስለሚችል ሳይሆን ነገር ግን ሌላ አካል ስላየው ነገሩ ሊታይ ቻለ፤ ወይም አንድ ነገር ተመሪ የሚሆነው መሪ ስላለው እንጂ ነገሩ ተመሪ ስለሆነ አይደለም። አንድ ነገር ሸክም የሆነው ተሸካሚ ስላለው እንጂ ነገሩ በራሱ ሸክም ሆኖ አይደለም። ይኽ ማለት አንድ ውጤት በራሱ ልቆ የወጣበት አካል ውጤቱ የራሱ ሳይሆን ምክንያት ስላለው ነው። ውጤት የሆነ ነገር በራሱ ውጤት አያመጣምና። ቅድስናም እንዲሁ ቅዱስ የሚሆነው አማልክት ስለሚወዱት እንጂ በራሱ ቅዱስ ስለሆነ አይደለም። >>

/ ሶቅራጥስ /

ከፍልስፍና ዓለም

@filsfina @filsfina

4 years, 11 months ago
ከፍልስፍና ዓለም (The world of philosophy)
4 years, 11 months ago

ስለ ታገቱት እህቶቻችን...
( ፍትሕ ለእህቶቻችን )

፨፨፨

ነግ በኔ ነውና ሁላችንም ዝም ማለት የለብንም...
ልጅን በተለይም ሴት ልጅን አስተምሮ ለቁምነገር ማብቃት እና ዩኒቨርስቲ ደረጃ ማድረስ ቀላል እንዳልሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው። ልጄ ትማርልኛለች ብሎ ዩኒቨርስቲ የሰደደ ወላጅ ደግሞ ዛሬ የልጁን መታገት ሰምቶ በሃዘን እና በስጋት ተቆራምዶ በጭንቀት ተውጦ ከማየት በላይ ልብን የሚያቆስል ነገር የለም።

የናንተን ባላውቅም እኔ የሚታየኝ አንድ ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ የልጆቹን ሰላም መመለስ በየቀኑ ፈጣሪን የሚማፀን አባት ነው። እኔ ሁሌም የምስለው በሀዘን ተቆራምዳ እራሷን የጣለች እና ምግብ እንኳን ከአፏ አልወርድላት ያለ በድሀ ጎኗ ያሳደገቻት ልጇን በአይኗ እስከምታይ እንባዋ አልቆም ያለ እናትን ነው ።

አባካችሁ እስቲ ሁላችንም እንጩህ ይሄ የብሔር እና የሃይማኖት ጉዳይ አይደለም ይህ የሰብአዊነት ጉዳይ ነው። ሁላችንም እንደየእምነታችን ወደ ፈጣሪ እንጩህላቸው። ሁላችንም ሰው እንደመሆናችን በሰውአዊነት የእህቶቼ መታገቴ የ'ኔም ነው እንበል። ሁላችንም ድርጊቱን በማውገዝ ብቻ ሳይሆን ተገቢውን ፍትሕ አጊንተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ይመለሱ ዘንድ ድምጽ እንሁናቸው ።

ባገኘንው አጋጣሚ ሁሉ ስለታገቱ እህቶቻችን እንጩህ...ፍትሕ እስከሚያገኙ ድረስ ዝም አንበል።
"የራስህ ሕመም ከተሰማህ በሕይወት አለህ ማለት ነው፤ የሰው ህመም ከተሰማህ #ሰው ነህ ማለት ነው።"
አሁን #ሰው ሆነ መገኘት ያለብን ጊዜ ነው
ፍትሕ
ፍትሕ
ፍትሕ
ለ እህቶቻችን...!!

እህቶቻችን መልሱልን
(Bring Back Our Sisters)

ንባብ ለሕይወት እንዲሁም ከፍልስፍና ዓለም ቴሌግራም ቻናሎች...

@filsfina @books4all32

4 years, 11 months ago
ከፍልስፍና ዓለም (The world of philosophy)
4 years, 11 months ago

ዛሬ እኛው እንፈላሰፍ እስኪ...

<< መጥፎ አጋጣሚ ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ይመጣል ብለህ አታስብ...የመጥፎ አጋጣሚ ሁሉ መነሻ አእምሮህ ነው፤ ከምታየው ዓለም መጥፎ አጋጣሚ ሁሉ ራስህን ጋርደህ ውስጣዊ አዕምሮህን ነፃ ብትለቀው ድርጊትህ ሁሉ የሞኝ ስራ ይሆናል >>
/ ጉተማ ቡደሀ /

ምን ለማለት ፈልጎ ይመስላችኋል ቡድሀ?
በራሱ ወደኛ የሚመጣ የክፋት ተግባር የለም እኛ የምንፈጥረው ጭንቀት እና ፍርሃት ያንን ተግባር እንደማግኔት ወደኛ ስቦ ያመጣዋል ለማለት ፈልጎ ይሆን ወይስ ሌላ...? ምናልባት ይሄንን እሳቤውን ሳይኮሎጂውም እንዲህ ሲል ይጋራዋል "...Your Mind is like a magnet..." ይላልና ። አስተሳሰባችንን ከጭንቀትና ከአጋጅ ነገሮች ጋርደን ነፃ ስናወጣው እያንዳንዱ ድርጊታችን ነፃ ይሆናል ለማለት ፈልጎ ይሆን...? ወይስ ሌላም እሳቤ አለው...?
ሲጀመር የሰው ልጅስ አስተሳሰቡን ነፃ ይለቅ ዘንድ ይችላል ወይ...?

ሀሳባችሁን ለማካፈል @Eftah32 ላይ አለሁ...

Tip ፦ #ቡደሀ ትክክለኛ ስሙ #ሲዳሀርታ ነበር። ከብዙ መንፈሳዊ ጥልቅ ማሰላሰል(Meditation) በኋላ በ35 ዓመቱ ቡድሃ እንደሆነ መዛግብት ይናገራሉ። ቡድሃ ማለትም (The Enlightened one) ያወቀ፣ የነቃ ወይም የበራለት ማለት ነው።

ከፍልስፍና ዓለም

@filsfina @filsfina

4 years, 11 months ago

የፈላስፋው ፍርድ

"የሰው ልጅ #ለተፈጥሯዊው_ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ #በዓለማዊው_ሕግ በከለው"

/ ላኦ-ዙ /

???

.....ላዎ-ዙ በመላዋ ቻይና ጠቢብ ለመሆኑ በተመሰከረለት ዘመን ላይ ቆሞ ነበር ። ይኸን የሰማው የቻይና ንጉስ ላኦ-ዙን አስጠርቶ በታላቅ ትህትና ከተቀበለው በኋላ ..."እባክህ!የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳኛ እንድትሆን እለምንሀለሁ?"ሲል የሹመት ጥያቄ አቀረበለት ።
፨ ላኦ-ዙ ግን "ንጉስ ሆይ! ተሳስተሀል!ለዚህ ቦታ የሚሆን ትክክለኛው ሰው እኔ አይደለሁም ፤ ልቅርብህ...ሌላ ሰው ፈልግ!" አለው ።
ንጉሱ ግን የላዎ-ዙን እምቢታ መቀበል ቀርቶ መስማት እንደማይፈልግ ነገረው፦"ከአንተ በቀር ማንንም ሰው በዚህ ወንበር ላይ ማስቀመጥ አይቻልምና የሰጠሁህን ሥልጣን ግድ መቀበል አለብህ"ሲል ወተወተው ።

፨ ላዎ-ዙም፦ "እንግዲ አልሰማህም የምትል ከሆነ በመጀመሪያው ቀን ችሎት የምፈፅመውን ስትመለከት መሳሳትህ ይገባሀል ። ከትህትና በመነጨ ወይም ለአንተ ካለኝ አክብሮት ለቦታው የምገባ አለመሆኔን ነገርኩህ እንጂ ፣ እውነቱ ግን መንግስትህ የዘረጋው ሥርዓት የተሳሳተ መሆኑን ማወቄ ነው!እናም በቦታው ላይ ወይ እኔ እኖራለው ፤ ወይም ደግሞ የአንተ ህግና ሥርዓት። ፣ እንዲሁም እሱን የሚከተለው ሕዝብህ ይኖራል"በማለት ሥልጣኑን ለመቀበል ተስማማ ።
፨ ላዎ-ዙ ጊዜ ሳያባክን በነጋታው ችሎት ተቀመጠ ። ተከሻሱ ሰው በቻይና ዝነኛ ከነበረ ሀብታም ብዙ ገንዘብ ዘርፏል ተብሎ ከፊቱ ቀረበ። ላዎ-ዙ የተከሳሹን ወንጀል አድምጦ ሲያበቃ ፍርድ ሰጠ ። "ከሳሽም ተከሳሽም እያንዳንዳቸው በስድስት ወር እስራት እንዲቀጡ ፈርጃለሁ"።

ከሳሽ የሰማውን ማመን አልቻለም ። ምናልባት ላኦ-ዙ ክሱ አልገባው ይሆናል ፤ አልያም እርጅና እየተጫጫነው ስለሆነ መርሳት ጀምሮት ይሆናል ፥ ወይም ደግሞ ለስራው አዲስ ስለሆነ ...ብቻ አስቦ ሲጨርስ ፈገግ ብሎ፦"ክቡር ዳኛ!ምን እያሉ ነው? ገንዘቤን የተዘረፍኩት እኮ እኔ ነኝ ፤ ይሄ ምን አይነት ፍርድ ነው? ሀብቴን ተዘርፌ እንዴት እንደገና ከዘረፈህ ሰው ጋር አብረህ ወህኒ ውረድ እባላለው ? ግዴለም የሆነ ቦታ አልገባዎትምና ያልተገባ ፍርድዎን ያስተካክሉልኝ!"

፨ላዎ-ዙ ፈገግ ብሎ ምክንያቱን አስረዳው፦"ይልቁንስ ያልገባህ አንተ ነህ!ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁ መስሎህ ከታየህ ምናልባት ያልተገባ ፍርድ የሰጠሁትም ገንዘብህን ዘርፏል በተባለው ሰው ላይ ነው ። የአንተ ወህኒ መውረድ ግን ከሌባው በላይ የተገባ ሆኖ አግኝቼዋለው ። ምክንያቱም አንተ የበዛ ሀብት ለራስህ ያከማቸኽው ፥ ሌላው ሰው ማግኘት የሚገባውን እያሳጣህ ነው...ብዙዎች በችግር የሚማቅቁባት በዚህች ሀገር አንተ ገንዘብ በገንዘብ ላይ ታከማቻለህ ። ለምን ይሆን? አየህ! የአንተ ከልክ ያለፈ ስግብግብ ባህሪህ እነዚህን ሌቦች ፈጠረ! ስለሆነም ሌባው በድርጊቱ ፤ አንተ ደግሞ ሌባ በመፍጠርህ እኩል ፍርድ ይገባችኋል ! የመጀመሪያው ወንጀል ፈጣሪ ግን አንተ ነህ ።

ላዎ-ዙ፦"የሰውን ልጅ ዓለማዊው እውቀትና ሕግ ሳይሆን የተፈጥሮ ሕግ ሊገዛው ይገባዋል" የሚለው ለዚህ ይመስላል ። ይህ ከላይ የተሰጠው ፍርድ መለስ ብለን ብንቃኝ የሰው ልጅ ተፈጥሮ በውስጡ ያስቀመጠችውን የእኩልነት ፣ የመፋቀር ፣ የመተሳሰብ ፡ባህሪይ እንዲጥል ያደረገው ራስ ወዳድነት በመስፈኑ ነው ። የራስ ወዳድነት ምንጩ ደግሞ ይህንን ስሜቱን የሚጠብቅለት ሰው ሰራሽ ሕግ መፈጠሩ ነው ። ሀብትን ለማንም ሳታካፍል ማከማቸት እንደምትችል እርግጠኛ ያደረገህ ማንም እንደማይወስድብህ የሚጠብቅልህ ሰው ሰራሽ ሕግ መኖሩ ነው ። ለዚያም ነው "የሰው ልጅ ለተፈጥሯዊው ሕግ የሚገዛበትን አዕምሮ በዓለማዊው ሕግ በከለው/corrupt አደረገው" የሚለን ላዎ-ዙ ።

???

ምንጭ ፦ ኃይለጊዮርጊስ ማሞ-ፍትህ መፅሔት ቁ.57(የተወሰደ)

ከፍልስፍና ዓለም

@filsfina @filsfina

4 years, 11 months ago
ከፍልስፍና ዓለም (The world of philosophy)
4 years, 11 months ago

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የቻናላችን ታዳሚዎች ሁሉ መልካም የጥምቀት በዓል ስንል መልእክታችንን እናስተላልፋለን...

መልካም ቀን ለሁላችሁ በያላችሁበት

ከፍልስፍና ዓለም

@filsfina @filsfina

4 years, 11 months ago

የኒቼ እና የኦሾ ቅራኔ ምን ነበር...?

፨፨፨

በፍልስፍናው ዓለም በሃይማኖት እይታ ላይ ጥሩ ነገር ያላበረከቱ ወይም ክፉኛ ሃይማኖትን እና አምላክን ተዳፍረው አልፈዋል ከሚባሉት ፈላስፋዎች መሃል

ፍሬድሪክ ኒቼ እና ራጅናሽ ኦሾ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው ።

ፍሬድሪክ ኒቼ ምን ነበር ያለው...?

" አምላክ ሞቷል(God is dead) ዛሬ እናንተ አምላክ የምትሉት በሰዎች አስተሳሰብ ውስጥ ተፈጥሮ አድጎና ጎልምሶ እንዲሁም አርጅቶ ያለፈ አስተሳሰብ ነው። "

በነገራችን ላይ ፍሬድሪክ ኒቼ የሱ ቀዳሚ የነበረው ፈላስፋ #አርተር ሾፐንሀወር አድናቂ ነበር እንዲሁም በፍልስፍና እይታዎቹ ላይም የሱ ተጽእኖ አለበት ይባላል...አርተር ሾፐን ሀወርም በፈጣሪ ህልውና የማያምን እንዲሁም ለስነ መለኮት መምህራን ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት የነበረው ፈላስፋ ነበር ።

ኒቼ ይህንን ሃሳብ ማለትም "God is Dead" የሚለውን እይታውን "Joyful wisdom" በሚለው መጽሐፉ ላይ ለሕትመት ባበቃ ሰአት ከብዙ የሃይማኖት ተከታዮች ተቃውሞ ደርሶበት ነበር...ይህንን ንግግሩንም አንስቶ ራጅናሽ ኦሾ እኔም በጊዜው ብኖር እቃወመው ነበር ይለናል።

ይህንን እይታም ያስቀምጣል...
<< ፍሬድሪክ ኒቼ አምላክ ሞቷል ሲል ብዙ እምነቶች ተቃውሞ አንስተውበት ነበር። እኔም እቃወመዋለሁ ምክንያቱም እኔ ደግሞ የምለው እንኳን ሊሞት መጀመርያም #አልነበረም ነውና >> ይለናል ይህንን ንግግሩን ብርሃነ ኅሊና የሚለው መጽሐፍ ላይ እናገኘዋለን ።

ባብዛኛው ሰዎች ራጅናሽ ኦሾን የሳይኮሎጂስቱን ሲግመን ፍሩድ እና ፍሬድሪክ ኒቼን ፍልስፍናዎች ያስተጋባ ብለው የሃሰት ካባ ሊያለብሱት ቢሞክሩም እሱ ግን ከነሱም የተለየ አስተሳሰብ እንደነበረ ካሳየባቸው ንግግሮቹ አንዱ ይህ ነበር ።

#አሁን ታድያ ማን ይፍረድ እንደ ኒቼ የፈጣሪን ህልውና የተገዳደረ ፈላስፋ የለም የሚባለው ሚዛን ይደፋ ይሆን የኦሾን አይን ያወጣ #ክህደት በሉት #እውነት አፍጥጠን ስናይ...?

መልሱን ለህሊናችሁ...!!
፨ የዚህ ጽሑፍ አላማ የፈጣሪን መኖር መካድ ሳይሆን በሁለቱ ፈላስፎች መሃከል በሀለዎተ ፈጣሪ ዙርያ ያለውን እይታ ማሳወቅ ነው። በሌላ እንዳይተረጎም...

ግብዓት ምንጮች ፦ ጥበብ ከጲላጦስ እንዲሁም ብርኀነ ኅሊና መጽሐፍት

ከፍልስፍና ዓለም

@filsfina @filsfina

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago