Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

E4J ስነ ፅሑፍ

Description
በተሰጠን ፀጋ እግዚአብሔርን እናገልግል
የተለያዩ መንፈሳዊ የስነ ፅሑፍ ስራዎችን የሚያገኙበት Channel @e4jgxm
❤️መንፈሳዊ መፅሐፍት
❤️ግጥሞች
❤️ወግ
እና
❤️ሌሎች መንፈሳዊ ፅሑፎች ይገኙበታል

ዋናውን ግሩፕ ለማግኘት
👇👇👇👇
❤️ @e4jesus❤️
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago

4 months, 2 weeks ago

ሰላም ለእናንተ ይሁን
የኢትዮጵያን ለኢየሱስ የግጥም ቤተሰቦች
ይሄን ቻናል ስለ ማንጠቀም እዚህ ይለቀቁ የነበሩት በሙሉ የሕብረቱ ቻናል @e4jsong ላይ ስለ ሚለቀቅ እስከ አሁን ቻናሉን ያልተቀላቀላችሁ ትቀላቀሉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያን ለኢየሱስ
የቴሌግራም ግሩፕ @e4jesus
ቻናል @e4jsong

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ (E4J)

4 months, 3 weeks ago

ርዕስ፦ ፍቅር እኛን አለ

እንኳን ለጌታችንና ና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ

እንኳን በክርስቶስ መወለድ ሆነልን

🥰🥰🥰🎄🎄🎄
💥💥
መልካም በዓል

@e4jesus
@e4jgixm
@e4jsong

6 months, 2 weeks ago
***✍*** መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ …

   መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ በኢትዮጵያን ለኢየሱስ ግሩፕ ( @e4jesus ) እሁድ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ  ኑ አብረን እንማማር

እንዲሁም ግጥም ይኖረናል ከE4J ገጣሚያን ጋር

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ

❤️ @e4jesus(ዋና ግሩፕ)
❤️ @e4jsong(መዝሙር ብቻ)
❤️ @e4jgxm (ግጥም)

7 months, 2 weeks ago

ማን ያንከባለዋል?🤔😔

በጠንካራ ድንጋይ ታትሞ የኖረ፤
አንከባላይ ጠፍቶ ተደፍኖ የቀረ፤
ማን ያንከባለዋል?
ይህን ሸህም ድንጋይ
ጥበቆች ዝምአሉ፤
መላዕክ እስኪወርድ
እስኪመጣ ከላይ፤
እስኪ ያንከባለው
ማህተሙን ድንጋይ፤
ምስጢሩ ይገለጥ በማለዳ ይታይ፤

👆👆👆
🙏🙏🙏

📖በሰብለ እዳኤ✍️

7 months, 2 weeks ago

ማንንም አይንቅም የተባለለት እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ሲንቅ እናያለን በሰው ፊት እየተከበሩ በእግዚአብሔር ከሚናቁ ወይም በሰው ፊት ቢናቁም ባይናቁም በእግዚአብሔር ከሚከበሩ ሰዎች አንዱ ለመሆን ምርጫው የኛ ነው
ከትልቅነቱ የተነሳ አይተኬ ከትንሽነቱ የተነሳ አይጠቅሜ ሰው በእግዚአብሔር ቤት የለም
ሁሉ ቦታ አለው ነገር ግን ሁሌም ሰው ብቻ መሆናችንን ማስታወስ ልካችንን ማወቅ ይህንን ለሚያስገነዝቡን ሰዎች ቦታ መስጠት ( ማክበር ) ከምንም በላይ ደግሞ ቅዱሱን መንፈስ ማድመጥ ይበጀናል የእግዚአብሔርን ስራ ለስማችን ማስጠሪያ እንዳናደርገው መጠንቀቅ ይኖርብናል እራሳችንን ከፍ ከፍ እንድናደርግና ሁሉ በእኛ የተደረገ እንዲመስለን ማድረግ ከሚቃጣቸው ሰዎችም መሸሽም ደግ ነው
ጳውሎስ ፍቃዱ

በቸር ዋሉ🙏

9 months, 1 week ago

#ይሰበር ብልቃጡ

እሩቅ በተባለች ቢታንያ ሀገር፤
ኢየሱስ ሲገባ በትንሿ መንደር፤
ከፈሪሳዊው ቤት ግብዣ ለመታደም
የድግሱ ተስካር፤
ምርጫውም አልነበር፤
ጣፋጭ ህይወት ሊቸር፤
የእርሱማ ቁም ነገር፤

ጎራ ሲል ወደቤት፤
ወደ ታደመበት፤

አስተናጋጅ ጠፍቶ ሀጥዕ በሞላበት
ድንገት ከተፍ አለ ህዝብ ወደሞላበት፤
ድግሱን ታዳሚ
ይመስላል ሲቀመጥ፤
ዙሪያውን ቢያማትር ወደ ግራና ቀኝ
እራሱን እሚገልጥ አጣ እኔነኝ ባይ

አንዲት ሴት ተነሳች ጌታ ማረኝ ብላ
የያዘችው ብልቃጥ በሽቶው የሞላ
በፊቱ ሰበረች፤
እግሩንም በጸጉሯ እየደባበሰች፤
የእንባዋን መንታ ከአኖቿ እየቀዳች፤
ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ፤
እኔን ማረኝ አለች፤
ዝግት ባለ ልሳን ስቅ ስቅ እያለች
የድንጋይ ውርምታ
የሰዎች ጫጫታ
ዙሪያዋን ቢከባት
ነፃነቷ እንጂ እሚሰጣት ህይወት
ፃድቅ ፊት ልትቀርብ፤
ምንም እንኳ ባይኖር፤
ልቧንም ሰብራለች ውድ ስጦታዋን
የስምዖን ደስታ፤
አይጠቅመው ለጌታ፤
ለጊዜው ነው እንጂ
አያልፍም ከማታ፤

ብልቃጡ ይሰበር

ይታይ የእኛ ደስታ

📖በሰብሊ✍️

9 months, 2 weeks ago

#አይቆጨኝም

መንገድእናእውነት
ህይወትንማወቄ፤
መከተል ብጀምር የመዳኔን ፅድቄ፤
ሀጥዕ ሥሬን ሳይሰድ
ጉልበቴ ሳይላላ፤

አይቆጨኝም እኔ፤

በወላፈን እሳት በእቶን ብበላ፤
መንገዱ እኔነኝ ልጄ ካለኝማ፤
ተዉኝልከተለው ምንም ሳላቅማማ፤
የህይወት ሚዛኔ የኔነቴ ካስማ፤
ሽቶዬ ቢያርሰው፤
የእግሮቹንም ወዝ
ፀጉሬ ቢያብሰው፤

በቃ አይቆጨኝም ግራ መጋባቱ፤

መስማማትን መረጥኩ፤
ልቤን ካሸፈተው ከዚህ ክንደብርቱ፤
እራሴን ብሰጠው አትርፌ ከእሳቱ፤
ከሲዖል ይሻላል
ሰማይን መምረጡ፤
የምድር ደስታ ፌሽታ
ባይገባኝም እዛ፤
ፍፁም አይቆጨኝም
ብመስል ፈዛዛ፤
ብባል እመርጣለሁ
እማይገባት ጌጃ፤
እርድና እማታውቅ
እንሰሳ ናትእንጃ፤

ቢሉኝ
ቢያሾፉብኝ፤

ምንም አልቆጭም፤

ለታወረባቸው፤
ሞኝ ለመሰልኳቸው፤
ምነው ባይነካኩኝ፤
አባሱት ንዳዴን ይልቅ ቆሰቆሱኝ፤
መንደዴን ቀጠልኩኝ፤
ማንስ ሊያዳፍነኝ፤
ጠፍቷል እሚያጠፋኝ፤

አይቆጨኝም እኔን

መዳኔን መምረጤ
ይብላኝ ለአባጆች ለእነ ምናምንቴ፤
በአዳኙ አምላክ ድናለች ህይወቴ፤

@e4jesus🇪🇹
@e4jsong🇪🇹
@e4jgxm🇪🇹

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹

📖በሰብለ እዳኦ✍️

10 months ago
[#እኔነኝ](?q=%23%E1%8A%A5%E1%8A%94%E1%8A%90%E1%8A%9D) በጊቷ

#እኔነኝ በጊቷ

ሁሉ ከሞላበት ከአባቴ ቤት ርቄ፤
በድፍርሱ ውሀ ላልጠራ ጠልቄ፤
ውስጠቴ ቆሽሾ ተጨመላልቄ፤
በሀጢአት አሻራ ወድቄ ዘፍቄ፤

መልኬን ሲያበላሸው የራሴ እኔነት
የተመካሁበት
የእኔ ያልኩት ጉልበት፤
አውቃለሁ ባይነት፤
የእኔ ጠባብነት፤

ግድፈቴ ላይጠራ፤
ጉድለቴ ላይሞላ፤
ያተረፍኩ ሲመስለኝ
ጥብቀቴ ሲላላ፤
ለካስ ፈላጊዬ መተሀል ከኋላ፤
ጥበቃህ በዛልኝ በአውሬ ላልበላ፤
አመሰግናለሁ አባቴ ከለላ፤
አሮጠህ ታደግኸኝ አንተ ባለመላ፤
እኔ ነኝ በጊቷ የታሰብኩትማ፤
🙏😥😥🙏

መልካም.......

@e4jesus🇪🇹
@e4jsong🇪🇹
@e4jgxm🇪🇹

ኢትዮጵያን ለኢየሱስ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹

✍️ ሰብለ እዳኦ📖

10 months ago
[#ሰማራዊቷ](?q=%23%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%88%AB%E1%8B%8A%E1%89%B7) ነኝ

#ሰማራዊቷ ነኝ

ውሀዬን ልቀዳ ገንቦዬን ሸክፌ፤
ማዶማዶ እያዩ ሲያማትሩ አይኖቼ

ከጉድጓድ አጠገብ
አንድ ሰው ተቀምጧል፤
ደቀ መዛሙርቱ ትተውት ሔደዋል

ገና ጎንበስ ብዬ፤
ውሀ ከመቅዳቴ፤
ከጥሙ እንዲረካ፤
ሲጠይቀኝ ለአፍታ፤
ቀድቼ ሰጠሁት የውሀ ጠብታ፤

ሰማራዊነቱ ግራ ቢያጋባኝም፤

ጥያቄ ጠየኩት፤
አንተማነህ አልኩት፤
ጥያቄ ተሞልቶ የእኔነት አንደበት፤

ደግሜ ጠየቅሁት
አንተአይሁዳዊ፤
ከእኔ ሰማራዊት ምን ትፈልጋለህ፤
እንዴት ከመንደሬ ውሀ ትለምናለህ
ብዬ ከማለቴ፤
እርሱም መለሰልኝ
በጥያቄ ብዛት ውስጥሽን ስታኪ፤
ብዙ ከነበሩት በአንዱ ሳትረኪ፤

ግድ ነበር የኔ በበርሽ ማለፌ፤
ወደ ባዶነትሽ ወደ አንቺ መቅረቤ፤
ከጉድጓዱበታች
ቢመስልሽም ቀልቤ፤
ይህ የእኔ አይደለም ሀሳቤ የልቤ፤
የአንቺ እርካታ እንጂ የኔ እርካታዬ

✍️ ሰብለ እዳኦ📖

10 months ago

#ድርሻችን የቱ ነው?

የአደባባይ ጩኸት ሆኖ ፀሎተችን፤

ቂምና አድመኝነት ተሞልቶ ልባችን፤

አመፅን በክፋት ወርሶትውልዳችን፤

እንዴት እንመለስ ታውሮ ልባችን፤

ሰማያዊው ቀረ የእኛ መክሊታችን፤

ሻማውም ቀለጠ ጠፋ ብርሀናችን፤

በማይመጥን ምኞት ስልጣናችንበዝቶ፤

በወኔያችን ላይ ደርበን ብትቶ፤

ውስጣዊው ፀጋችን፤

በሸረሪት ብልጠትድርንም አድርቶ፤

ሻገተ እንጀራችን እሚበላው ጠፍቶ፤

አንቅረን ጥለናል ከቤታችን ሸቶ፤

እንቅቡም አረጀተጠቃሚው ጠፍቶ፤

ለአምላክ ሳናስተውል፤
ትዕዛዙን ሳንፈፅም፤

ቃላችን ታጠፈ ኪዳናችን የለም፤

እንዴት እንፈወስ፤
ማንስ እኛን ያክም፤

ውስጣችን ባዶነው፤

መፍትሔ ያጣ ህመም፤

ወላፈኑ በዝቶ በእሳት ስንፋጅ፤

ምልጃና ፀሎቱ፤
ሲርቀን ከእኛውደጅ፤

ማን ደፍሮ ይመስክር፤
ማንስ ይበል አዋጅ፤

በአደባባይ ቀርቶ የእኛ ጩኸትማ፤
እንዴት አንድ እንሁን
እንዴት እንስማማ፤

ወንጌሉን ጥለናል እግዜ/ን ሳንሰማ
ይህ ጭካኔያችን አርጎናል ጨለማ፤
እስኪ እንመለስ ልባችን አይድማ፤

ድርሻችንን አውቀን
የእውነት ክርስትና፤
መባል ይበጀናል
የወንጌል ባለአደራ፤
እንንቀ እንቸኩል ጌታ ይመጣልና፤
💔🙏🙏

✍️ ሰብለ እዳኦ📖

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago