ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ

Description
╔════◈◉◈════╗
                     أهل السنة والجماعة
            ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⚪️አህለሱና ወልጀመዓህ ስንል የሰለፎችንና የኸለፎችን የግንዛቤ ዘይቤ የሚከተሉ ማለት ነው።

🔴ይህ መንገድ ሌሎች የኢስላም አስተሳሰብ ተከታዮችን አያከፍርም

🔎አመላካች የሰሪን ምንዳ ያገኛልና ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩልን

╚════◈◉◈════╝
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

2 weeks, 1 day ago

🛑🛑🛑 አህባሽ ⁉️

ክፍል አንድ

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على المعصوم محمد وعلى آله وصحبه أجمعين

أما بعد  نتكلم عن "مفاهيم يجب ان تصحح"
#ما_معنى_الاحباش

#አህባሽ ማለት ምን ማለት ነው?

#አህባሽ ማለት ቋንቋዊ ፍቹና ትርጉሙ ኢትዮጽያኖች  ማለት ሲሆን ካፊር ፣ ሙስሊም ይሁን ሙርተድ፣  ጼንጤም ይሁን #ኦርቶዶክስ ፣  አይሁድም ይሁን ሰይጣን አምላኪ ሁሉም ዜግነታቸው ኢትዮጽያዊ የሆኑ ማለት ነው።

#አህባሽ ማለት ሱፊ #ለማለት ነው የሚለው አባባል በቋንቋም በአገላለግጽም ኢትዮጽያዊ በሚለው በትክክል ለሚረዳ ትክክል እንዳልሆነ ግልጽ ነው።
ሊባል የሚገባው  አህባሾች ሱፍዮች እንጂ ሱፊይ  አህባሽ ብቻ አይደለም ።

#ምክንያቱም
💚💚  አረብ የሆኑም ኢትዮጲያዊ የሆኑም ሱፍዮች ስላሉ አህባሽ የሚለው ኢትዮጽያዊ ማለት ከሆነ ኢትዮጽያዊ ሱፊም አለ ጼንጤም አለ ሱፊ ያልሆነም አለ ሁሉም ኢትዮጽያውያን ከሆኑ አህባሽ ብሎ መጥራት ይቻላል።

☀️ኢትዮጲያዊ  ሱፍዮችን ለማለት ነው ከተባለ ደግሞ አረብኛው  " ሱፍየቱል አህባሽ" ( የሃበሻ ሱፊዮች)   ነው የሚሆነው ሌላው ሽወዳ የሃሰት ትርክት ለመሆኑ በ እንግሊዘኛም የተጻፉ የውጭ ጸሃፍያን የጻፉት ዊኪፒዲያም ላይ አህባሽ ብለን ስንጽፍ የሚመጣን ተጨባጭ ነገሩን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

❇️ መስተካከል ያለበት አረዳድ

ይህን ስያሜ  የተጠቀምነው ወሃቢዮች አህባሽ ሲሉ ሱፍዮችን ለማለት ነውና እኛ አህባሽ ነን  ከሆነ   , ውሃብያ በዚህ አግባብ የሚረዳው የአላዋቂነት ምልክት ነውና የመሃይም ንግግርን #እንደ ትልቅ ነገር በመውሰድ ለራስ አገልግሎት መውሰድ #የቂሎች ተባባሪነት ስለሆነ በዚህ አረዳድ መረዳት አግባብ አይደለም፡፡

#አሊሞች አህባሽ የሚለውን ትርክት ሲመጣ ትርጉሙ በአረብኛ ቋንቋ ደረጃ ኢትዪጲያውያን ማለት ሲሆን ይህም በዜግነት ኢትዮጽያዊ የሆኑትን ሁሉ ማለትም ጴንጤዎችንም ሙስሊሞችንም አይሁዶችንም ኦርቶዶክሱንም ሰይጣን አምላኪውንም ጭምር ያካትታል ነገር ግን የእምነት ስም አይደለም በማለት አላዋቂ ለሆኑ ሰዎች መለስ ሰጥተዋል።

#የሚያሳዝነው ግን #አላዋቂዋች ያነሱትን ሃሳብ ለአንድ ወገን ሰዎች ብቻ በመውሰድ #ሱፍዮች ጋር በማስታከክ #አህባሽ ማለት ሱፍያ ነው እንዲባል ልዩ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች አሉ።

#ምን_አይነት_ሰዎች_ናቸው_ያላዋቂዎችን_ትርክት_እንደ_አድቫንቴጅ_በመውሰድ_ሊጠቀሙበት_የቋመጡ_ስዎች?

#መልስ

አንደኛው ቡድን

አህባሽ ቡድን ተብለው ራሳቸውን የሰየሙ ቡድኖችና ማህበር አባላት ኢትዮጽያ ሲገቡ መሃይሞች ያሰራጩትን ትርክት እንደ እድል በመጠቀም #አህባሽ እኮ #ሱፍያ ነው ወደሚል #የመሃይም_አረዳድ ወስደውታል፣  በዚህም እኔ አህባሽ ነኝ ፣ ሃበሽይ ነኝ፣  ሃበሺያ ናት እያሉ የቡድንተኝነት መገለጫ አድርገውታል ለዚህ ምስክሩ በfb ላይ profile name የሚያደርጉትን ሰዎች ማየት በቂ ነው ፡፡

#ችግሩ ሃበሺይ ነኝ ፣ ሃበሺያ ናት በሚለው ላይ ሳይሆን ትርጉሙ ኢትዮጽያውያን ኡትዮጽያዊት ማለቱ በኢትዮጽያውነት ራስን መግልጽ የሚያኮራ ሆኖ እያለ ግን #ወሃብይ_አይደለሁም ለማለት የሚጠቀሙበት ሆኖ መገኘቱ #የእምነት መለያ መደረጉ ነው፡፡

♻️ሁለተኛው ቡድን

🟢 ወሃቢዮች ሲሆኑ አህባሽ የሚለውን ስም ወደ #ሱፍያ ብቻ የሚሆን እንደሆነ በሃሰት በመንዛት ሃሳቡን በማሳጠር ስም የማጠልሽት ተግባርን በማሰራጨት #መሻይኾችንና አቂዳቸውን #በማህበረሰቡ ውስጥ #ተቀባይነት ለማሳጠት የተፈጸመ ነበር፡፡

🟡 የሚገርመው ሃሳባቸው ብዙ ያልተሳካው ውሽት የተጨመረበት ስለነበር ለአብነትም ሶላት  ሁለት ብቻ ነው  ብለዋል  የሚለው ይጠቀሳል፡፡

         ይቀጥላል ▪️▪️▪️
https://t.me/sufiyahlesuna

2 weeks, 2 days ago

ነዋፊል በሆኑ ጾሞች ፣ ሰላቶች ፣ እንዲሁም ዚክሮች ከመጠመድ በዒልም ጊዜን ማሳለፍ በላጭ በመሆኑ ላይ ተስማምተዋል (ዑለሞች)።

አል መጅሙዕ (ኢ ፡አንነወዊ)
https://t.me/sufiyahlesuna

2 weeks, 3 days ago

መስጂድ ውስጥ ለብቻ ከመስገድ ከመስጂድ ውጭ በህብረት መስገድ በላጭ ነው ፤ ቤት ውስጥ በብዙ ስብስብ ከመስገድ መስጂድ ውስጥ በትንሽ ስብስብ መስገድ በላጭ ነው

ዶ/ር ለቢብ ነጂብ

الجماعة بغير المسجد أفضل من الانفراد فيه، والجماعة القليلة في المسجد أفضل من الكثيرة في البيت

3 weeks, 1 day ago

ፎቅ ገንብተዋል ያልከው : በቅድሚያ ይህን ሁሉ የስም ማጥፋት ዘመቻ የሚያካሄዱት ሙፍቲ ሀጅ ዑመር ከሚወክሉት የቀድሞው የዑለሞች መንገድ ጋር በሀሳብ የማይስማሙ አካላት ናቸው ፤ የስም ማጥፋቱ መነሻ የፊቅህና የዐቂዳ አስተሳሰብ ልዩነት መሆኑን በደንብ አስምርበት ፤ በአሁኖቹና በዱሮዎቹ ዑለሞች መካከል ያለውን ልዩነት አንተም በተወሰነ መልኩ አይተሀዋል ።

እነዚህ አካላት የሙፍቲን ስም ሲያጠፋ መነሻቸው ይህ ልዩነት እንጂ የምር ሙፍቲ ስልጣን ወዳድ ወይም ሌባ ስለሆኑ አይደለም ይህን ደግሞ ከርሳቸው ጋር በሀሳብ የሚለያዩት እነ አቡበከር አህመድ እንኳ መጀመሪያ አካባቢ የመሰከሩት ጉዳይ ነው።

አንድን ወገን በሀሳብ ስለተለያዩት ብቻ የውሸት ፍረጃዎችን መደርደር ከሙስሊም የማይጠበቅ ጉዳይ ነው ፣ ስለ ሀብታቸው ያነሳሀው ነጥብ የምር ይገርማል ፣ ዐሊም ደሀ ይሁን ፣ ሀብት አያፍራ ብሎ የወሰነው ማነው ? ሙፍቲ ነጋዴ እንደነበሩና የሀብታም ልጅ እንደነበሩ ደጋግመው ተናግረዋል ፣ ሰርተው ማግኘታቸው ምን ያስገርማል ?

የተወሰኑ ኢኽዋኖችን ጠቀስኩለትና እገሌ እገሌ በጣም የለጠጡ ባለሀብቶች ናቸዉ ነገር ግን እኔ በሀሳብ ስለምቃረናቸው ብቻ ይህን ሀብት ሰርቀው ፣ ህዝብ አጭበርብረው ነው ያገኙት ማለት አልችልም ።

በመጨረሻ የምመክርህ አንተ እንዲህ አይነት ነገር ውስጥ አትግባ ፣ ስራህን ስራ ፣ ሰላትህን ስገድ ፣ ከሀራም ተከልከል ፣ የቻልከውን ያክል ሱና ዒባዳ አብዛ ።

ፅሁፋ ረዘመ አይደል ? አፍወን ሰሞኑን ፈተና ላይ ስለሆንኩ እዚያ ላይ ለምዶብኝ ነው 😁

3 weeks, 2 days ago

እቃ
~ ~

አንድ ቤት ለኒካህ ሄደን ቤቱ 5ሰው ከገባ በኃል ሞላ ስለዚህ በረንዳ ላይ ለመቀመጥ ተገደድን
ቤቱን ሳየው ጠባብ ሚባል አደለም ነገር ግን የእቃ አይነት ዘብ ብሎበታል ። አንዳንዴ ቤትና ሀገር ለምን እንደተሰሩ ግራ ይገባኛል ?ቤትም በተመሳሳይ ሀገርም የተሰሩትም የተፈጠሩትም ለሰው ነው እቃ ውስጥ አስቀምጦ ሰውን ውጪ ማስቀመጠ ብዙም ስሜት አይሰጥም ቤት ያለ ሰው ሀገር ያለ ህዝብ አፈር ከመሆን ውጪ ትርጉም አይሰጥም ።እቃ እንግዛ ነገር ግን ቤቱን የሚመጥን ይሁን ቤቱን እቃ ጥቅ አድርገን ሰው መቀመጫ ካጣ ቤት ሳይሆን ያለን መጋዘን ነው።

ዘ.ሐ

3 weeks, 2 days ago

ኢማም አል ገዛሊይ እና ፍልስፍና
——————————————-

👉 ኩፍርን ባካተቱ የፍልስፍና አስተሳሰቦች የተጠቁ ቀደምትና ዘመናዊ ሙስሊም ተብዬ ወገኖች ኢማም አል- ገዛሊን የመቻቻል እሴትን የማይቀበሉና የፍልስፍና ጠላት አድርገው ይስሏቸዋል ፤ ይህም ሁሉም ሙስሊም የሚስማማባቸው ዐቂዳዊ ጉዳዮችን የካዱ ሙስሊም ፈላስፎችን ስላከፈሩ ነው ።

👉 በተቃራኒው እነ- ጅላንፎ “ ኢማም አል ገዛሊ ፍልስፍና ውስጥ ሰምጠው መውጣት ያቃታቸው ናቸው “ ብለው እኚህን ብርቅዬ ዐሊም ለመወረፍ ይሞክራሉ

❇️ የሚገርመው ከጅላንፎዎቹ ይልቅ ፈላስፎቹ ኢማም አል ገዛሊን በደንብ ተረድተዋቸዋል ፤ ፍልስፍናን ተጠቅመው በፍልስፍና ውስጥ የነበሩ የኩፍር አስተሳሰቦችን በመዋጋታቸው እንደ ትልቅ ውስጣዊ ጠላት ይመለከቷቸዋል
https://t.me/sufiyahlesuna

4 weeks ago

ኢማም አዝዘሀቢ “ሲየር አዕላም አንኑበላእ “ ላይ ኢማሙ ማሊክ ስለ ሙተሻቢህ አንቀፆች እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል :-

“ እንደመጣው (ቃሉ) ያለ ፍቺ አሳልፋት “

4 weeks, 1 day ago

በቅርቡ ካለፋ የወሀቢያ መሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አልባኒ ከላይ ባልለው የድምፅ ቅጂ ላይ እንዲህ ይላል :-

“ እኛ አህመዲዮች አይደለንም ( የኢማሙ አህመድ ተከታዮች ) ፣ የዐቂዳችንንም ሆነ የአስተሳሰባችንን መሪነት ለነዚህ አኢማዎች አሳልፈን አንሰጥም “

👉 ሰለፍ ሰለፍ የምትለዋ ጉረራ እዚህ ጋር ታበቃለች ፣ አልባኒና መሰሎቹ ዘንድ “ ቁርአንና ሀዲስ በሰለፎች ግንዛቤ መከተል “ የምትለው መፈክር ተራውን ህዝብ ማታለያ እንጂ የእውነት ሰለፎችን እንደማይከተሉ ይህ ንግግር በግልፅ ያሳየናል

4 weeks, 1 day ago

ነቢያቶች አለይሂሙስሰላቱ ወሰላም ላይ እንደ ረሀብ ፣ ጥማት፣ ቁጣ ፣ እንቅልፍ ፣ ሞት የመሳሰሉ ክብራቸውንና ደረጃቸውን ወደ ማሳነስ የማያደርሱ ሰዋዊ ክስተቶች ያመችባቸዋል / ይከሰትባቸዋል / ።

1 month ago

ከሞተ ሰውም ይሁን በህይወት ካለ ሰው የሆነ የሰውነት ክፍሉን ወስዶ ለሌላ ህመምተኛ ሰው መትከል እንደ መጅመዕ አል ፊቅህ አል- ኢስላሚይ ፣ የዮርዳኖስ የፈትዋ ኮሚቴ ፣ የግብፅ የፈትዋ ኮሚቴን የመሳሰሉ አብዛኞቹ የዘመናችን ኢስላማዊ የፈትዋ ተቋማት የደገፋት ተግባር ነው ።

ሆኖም ዝርዝር የሆኑ መስፈርቶችን ስላስቀመጡ ይህ ጉዳይ ያጋጠመው ሰው ዝርዝሮቹን ወደ ዑለሞች ጠጋ ብሎ መጠየቅ አለበት

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago