Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ትንሿ ቤተ-ክርስቲያን

Description
እኛስ በትዳር ከእግዚአብሔር ጋር እንተባበራለን።
ትንሿ ቤተክርስቲያንን እናይ፣እናውቅ እና እንወድ ዘንድ እንማማራለን።
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 2 days, 13 hours ago

2 weeks, 1 day ago

የእናት አስፈላጊነት

በልጆች አስተዳደግ ውስጥ እናት ያላት ድርሻ ጡት ከማጥባት ያለፈ ነው፡፡ እናት በልጆች ሕይወት ውስጥ በማትገኝበት ወይም እያለች ያላት ተሳትፎ ግን አናሳ በሚሆንበት ጊዜ በልጆቹ የስነ-ልቦናና ማሕበራዊ እድገት ላይ ትልቅ ቀውስ ይፈጥራል፡፡

ከእናት ውጪ ያደገች አንዲት ሴት ከሁኔታው ተገቢውን ፈውስ ካላገኘች ለበርካታ ቀውሶች ልትጋለጥ ትችላለች፡፡ ከእነዚህ ቀውሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

ድፍረትን ማጣት፣ ሰዎችን ማመን አለመቻል፣ የቀይ መስመርን (personal boundary) ለማስመር ያለመቻልና የሁሉ አስደሳች የመሆን ዝንባሌ፣ በራስ ላይ ያለ የተዛባ እይታ፣ ራስን ከሰዎች ማግለል፣ የስሜት ስስነትና በማይሆን ፍቅረኛ ላይ መውደቅ፡፡

ከእናት ውጪ ያደገ ወንድም ጉዳዩ ይለከተዋል፡፡ የእናት መገኘትና አለመገኘት በወንድ ልጅም ላይ እስከ መጨረሻው የሚዘልቅ አሉታዊ ተጽእኖ አለው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ወንድ ልጅ የመጀመሪያውን አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽእኖ የሚቀበለው ከእናቱ ነው፡፡ 

አንድ ወንድ ወደዚህች አለም ከተቀላቀለ በኋላ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያውቃት ሴት እናቱን ነው፡፡ ስለሆነም ከእናቱ ጋር ያለው የልጅነት ትውስታና ግንኙነት ወደፊት በሴቶች ላይ በሚኖረው አመለካከት ላይ ዘርን ጥሎ ማለፉ አይቀርም፡፡

በእናቱ አማካኝነት የደረሰበትን የመጣል፣ ችላ የመባልና የመሳሰሉት ባህሪዎችን ወደፊት በሚኖረው ግንኙነት ውስጥ የመፍራትን ዝንባሌ ሊያዳብር ይችላል፡፡ በእናቱ “በርታ” ተብሎ ያደገ ልጅና ያንን ሳያገኝ ወይም ተቃራኒን ሰምቶ ያደገ ወንድ ይህ ልምምዱ ወደፊት ከሴቶች ጋር በሚኖረው ግንኙነት ላይ የሚጫወተው ሚና ቀላል አይሆንም፡፡

አንዳንድ የእናትን ጣእም ሳያገኙ ያደጉ ወንዶች ፍቅረኛ ወደመያዝ ደረጃ ሲደርሱና በዚያ መስክ ሲሰማሩ ሳያውቁት ያንን በልጅነት ያጡትን የእናትነት ምስልና እንክብካቤ ፍለጋ ከእድሜያቸው በብዙ ወደሚበልጡ ሴቶች የመሳብ ዝንባሌ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሆኖም፣ የዚህን ዝንባሌና ተጽእኖ የሚያዩት በትዳር ውስጥ ከቆዩና የእድሜ ልዩነቱን በግላጭ ማየት ሲጀምሩ ነው፡፡

ከላይ በጥቂቱ ለመጠቃቀስ የሞከርናቸው ሃሳቦች የአባትንና የእናትን ተገቢ የሆነ ግንኙነት፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ሚና ሳያገኙ ያደጉ ልጆች ሊጋፈጧቸው የሚችሉትን ሞጋች ሁኔታዎች አመልካች ናቸው፡፡ እነዚህ ልጆች አድገው ወደ ወጣትነት፣ አልፎም ወደ አዋቂነት ሲሻገሩ ከተቃራኒ ጾታ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በምን አይነት ቅድመ-ምልከታ እንደሚቀርቡት የሚወስንላቸው ይህ በልጅነታቸው አመታት ቀምሰው ወይም ሳይቀምሱ ያደጉት የቤተሰብ ጣእም ነው፡፡
@TnshuaBetechrstian

2 weeks, 4 days ago

♡YAHWEH PROMOTION♡

ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
              ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
Tel      :- +251943686155
  :- +251977157265 📞 ያገኙናል
https://t.me/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ

Telegram

ሰአሊ ለነ ቅድስት

ፍቅር ግን ከሁሉ ይበልጣል

♡YAHWEH PROMOTION♡
1 month, 2 weeks ago
1 ጢሞቴዎስ 2 (1 Timothy)

1 ጢሞቴዎስ 2 (1 Timothy)
9-10፤ እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፥ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ።
ስለ ትንሿ ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

1 month, 2 weeks ago
ላላገቡ . . .

ላላገቡ . . .

ልጅ፡- “እማዬ፣ ሃብታም ሰው ባገባ ይሻላል ወይስ ቆንጆ ሰው ባገባ ይሻላል?”

እናት፡- “ልጄ፣ እውነተኛ ሰው አግቢ”!
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

1 month, 2 weeks ago
[#ስለ](?q=%23%E1%88%B5%E1%88%88) [#ሩካቤ](?q=%23%E1%88%A9%E1%8A%AB%E1%89%A4) [#ስጋ](?q=%23%E1%88%B5%E1%8C%8B)

#ስለ #ሩካቤ #ስጋ
ወደ ትዳር ስንገባ በጣም አስፈላጊው ነገር ልምድ አልባ መሆን ነው።ምንም እንኳን አንዳንድ ሰዎች የሩካቤ ፍላጎታቸውን ለመፈጸምና ድካማቸውን በምክንያት ለመሸፈን ሲሉ "እንደ ስራ ልምድ" ቢቆጥሩትም እውነታው ግን እንደዚያ አይደለም።አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወደ ትዳር ለመግባት የሩካቤ ልምድ አያስፈልገውም ኹለታችንም ልምድ አልባ ስንሆን የትዳር አጋሮቻችንን ከሌሎች ጋር አናነጻጽራቸውምና።አንዳችን ለአንዳችን የሚኖረን ፍቅርም ንጹህ እንዲሆን ያደርገዋል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ይህንን ሲያብራራው እንዲህ ይላል፦
"ድንግል ወንድ ድንግል ሴትን ማግባቱ ለትዳራቸው ጤናማነት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል እንደሆነ ታስባለህን? አይደለም!ድንግልናውን ለጠበቀ ወንድ ብቻ አይደለም ፤ድንግልናዋንም ለጠበቀች ልጃገረድም ጭምር እንጂ።ፍቅራቸው ፍጹም ንጹሕ አይሆንምን? ከሁሉ በላይስ እነዚህ ወጣቶች ንጽሕናቸውን ጠብቀው እንደ ሕጉና እንደ ስርአቱ ተጋብተው ስለ ተዋሐዱ ደስ ተሰኝቶ እግዚአብሔር  ትዳራቸውን ስፍር ቁጥር በሌለው በረከት አይሞላላቸውምን? አዎን እንደዚህ ሆነው ባል ለሚስቱ ያለውን ንጹሕ ፍቅር ዘወትር እንዲያስበው ያደርገዋል።ይህን አይነት መውደድ፣ይህን አይነት ፍቅርም ዘወትር እንዲያስበው ያደርገዋል።ይህንን አይነት መውደድ ይህን ፣አይነት ፍቅር አጽንቶ የያዘ እንደሆነም ከሚስቱ በቀር ወደ ሌላ ሴት ዓይኑን አያነሳም።"
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

1 month, 3 weeks ago
  • ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር:: 
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ::  በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ስለ #ትንሿ #ቤተክርስቲያን
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@TnshuaBetechrstian

2 months, 3 weeks ago

♡YAHWEH PROMOTION♡

ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።
  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ይስመዝግቡ
              ➱ 👉@ZEMARYAM_NEGN
Tel      :- +251943686155
  :- +251977157265 📞 ያገኙናል
https://t.me/Saint_Mary21 ይቀላቀሉ

3 months, 1 week ago

#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘእንዚናዙ ለንስሓ ልጁ #በሰርጓ ቀን መገኘት ባለመቻሉ የላከላት ደብዳቤ
“ልጄ! ለሰርግሽ የነፍስ አባትሽ እኔ ጐርጐርዮስ ይህን ግጥም ስጦታ አድርጌ ልኬልሻለሁ፡፡ አባት ለሚወዳት ልጁ ሊሰጣት የሚችለው የተሻለው ምክርም ይህ እንደ ኾነ አምናለሁ፡፡

“ኦሎምፒያታ ሆይ፥ እውነተኛ ክርስቲያን ለመኾን ያለሽን ፍላጎት ዐውቃለሁና በደንብ አድምጪኝ! እውነተኛ ክርስቲያን እንዲሁ መኾንን የሚመኝ ብቻ ሳይኾን እንደዚያ ለመኾን ሊጥር ይገባዋል፡፡

“ከኹሉም በላይ፥ እግዚአብሔርን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ከእርሱ ቀጥሎም በቅዱስ ወንጌል እንደ ታዘዘው እንደ ጌታችንና መድኃኒታችን [ኢየሱስ ክርስቶስ] አድርገሽ ባልሽን ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ ስለዚህ እጠይቅሻለሁ! ጌታዋንና ፈጣሪዋን [ኢየሱስ ክርስቶስን] የማታከብርና የማትወድ ሴት በዚህ መንገድ ባልዋን እንዴት አድርጋ ልታከብረውና ልትወደው ትችላለች?

“በጋብቻሽ ውስጥ የትዳር አጋርሽ ይኾን ዘንድ እግዚአብሔር መርጦ ለሰጠሽ ባል ያለሽ መውደድ፣ ስሜትና ፍቅር እጅግ ኃያል ሊኾን ይገባዋል፡፡ ይህ ሰው አሁን የሕይወትሽ ዓይን፣ የልብሽም ደስታ ነውና፡፡

“እግዚአብሔርን እንደምትወጂው፥ ባልሽንም ያለ ቅድመ ኹኔታ ልታከብሪውና ልትወጂው ይገባሻል፡፡ አንቺ ሴት እንደ ኾንሽና ታላቅ የኾነ ዓላማና ግብ እንዳለሽ፥ ኾኖም ዓላማሽና ግብሽ የቤትሽ ራስ ሊኾን ከሚገባው ባልሽ የተለየ እንደ ኾነ ዕወቂ፤ ተረጂም፡፡ ባንቺ ዕድሜ ላይ ያሉት አንዳንዶች ኹለቱም ፆታዎች እኩል [ራስ ናቸው] ብለው የሚሰብኩትን አትስሚ፤ የጋብቻንም ግዴታ [ወይም ዋና ዓላማ] አስቢ፡፡ እነዚህን ግዴታዎች [ወይም ዓላማዎች] ስታውቂ የቤተሰብሽን ተግባራት ለማከናወን እንደ ምን ያለ ትዕግሥትና ጽናት እንደሚያስፈልግሽ ታውቂያለሽና፡፡ እንደ ሚስት እጅግ ጥንካሬን ገንዘብ የምታደርጊውም በዚህ መንገድ ነው፡፡

“ወንዶች እንዴት በቀላሉ የሚቈጡ መኾናቸውን በርግጥ ልታውቂ ይገባሻል፡፡ አይችሉም፤ ብዙ ጊዜም እንደ በረኻ አንበሳ ይኾናሉ፡፡ እንግዲህ ሚስት ጸንታ ልትቆምና የነፍስ ልዕልናዋን ልታሳይ የሚገባት በዚህች ቅጽበት ነው፡፡ አንበሳን የማስለመድ ሥራ መሥራት አለብሽ፡፡ አንበሳን የሚያስለምድ ሰው አንበሳ ሲያገሳ የሚያደርገው ምንድን ነው? ከየትኛውም ጊዜ በላይ ዝም ጸጥ ይላል፡፡ በጸጥታውና በርጋታውም የአንበሳውን ቊጣ ይቈጣጠራል፡፡ በርጋታና በለሆሳስ ኾኖ ያናግረዋል፤ ይደባብሰዋል፤ በቀስታ ያሻሸዋል፤ በጥቂት በጥቂቱም አንበሳው ቊጣውን ይተዋል፡፡

“ባልሽ ስሕተት ሲሠራ በፍጹም ልትነቅፊው፣ ልትንቂው ወይም ልታስነውሪው አይገባም፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ መሥራት ያለበትን ነገር ባይሠራና ከዚሁ የተነሣም ውጤቱ ደስ የማያሰኝ ቢኾን፣ ወይም እጅግ የምትፈልጊውና አግባብ ነው ብለሽ የምታስቢውን ባያደርግ እንኳን ባልሽን መናቅ ከአንቺ ልታርቂ ይገባል፡፡ ክፉዎች አጋንንት ዘወትር ቤታችሁን ለማፍረስና የጥንዶች መንፈሳዊ አንድነትን ለመበተን እንደሚሞክሩ ዕወቂ፡፡”

(#ከገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ ከትንሿ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ የተወሰደ)

@TnshuaBetechrstian

3 months, 2 weeks ago

" እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:31)
@TnshuaBetechrstian

4 months, 3 weeks ago
ማንም ለገዛ አካሉ ትልቅ ፍቅር እንዳለው …

ማንም ለገዛ አካሉ ትልቅ ፍቅር እንዳለው ሁሉ እንዲሁ #ለሚስቱ #አካሉ #ናትና #ትልቅ #ፍቅር ሊኖረው ይገባል።
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@TnshuaBetechrstian

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 2 days, 13 hours ago