አስኳላ-💚💛❤️

Description
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው።


Comment▹ @Meklite21
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

1 month, 3 weeks ago
"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር ጋር ጥሩ ታሪክ …

"ምከረኝ" አለችኝ "ከመምከር  ጋር ጥሩ ታሪክ የለኝም" አልኳት ።

አላመነችኝም ... ለማሳመን አልጣርኩም።
"ምራኝ እሺ " አለችኝ "ሲከተሉኝ እፈራለሁ ቀድሞ ግራ ይሂድ ቀኝ ይሂድ ሳሰላስል እደናበራለሁ" አልኳት ።
ትህትና መሰላት ።

"መንገድ የጠፋበት ሰው ቢመራ የት ያደርሳል?" አልኳት
"አለማወቅ ምቾት አለው" አለችኝ።
"አለማወቅን ካላወቅን ነው ምቾት ያለው"  አልኳት።

"እንደምትወደኝ ንገረኝ" አለችኝ።

"እወድሻለሁ" 
"እሺ ምከረኝ" አለችኝ ።
ድንገት ጭንቅላቴ ላይ ከመምከር ጋር ያለኝ ታሪክ መጣብኝ...

ጓደኛዬ ነበረች ፤ ሃዘን ገጠማት  የምትወደው ሰው፣ አንድ ያላት ሰው ሞተባት። መሰበሯ ሲጠነክር መከርኳት።
"ሃኪም ነኝ፤ የሞተ ሰው በየቀኑ አያለሁ ፣ ሲሰቃዩ የነበሩ ሰዎች፣ መኖር ሰፈልጉ የነበሩ ሰዎች፣ መዳን ብቻ የሚፈልጉ ሰዎች ሲሞቱ አያለው።

ሲሞቱ ትክ ብዬ አያቸዋለሁ፣ ህመማቸው ነው የሚቋጨው ፣ ትግላቸው ነው የሚቀርላቸው ፣ መሞት ለሟቹ እረፍት ነው የሚመስለኝ" ብዬ ገጠመኜን እያጣቀስኩ ነገርኳት .....
በሳምንቱ ሞተች እራሷን ገድላ።

ለማኖር ነበር የመከርኳት ፤ አይኗን በልቅጣ ቀልቧን ሰጥታኝ ስትሰማኝ ሞት እረፍት ነው ብላ እንድትጠነክር ነበር ። ግን መኖርን ነበር የቀማኋት  መሰለኝ.......

የቱ አፋፍ ላይ ቆማ ሰምታኝ ይሆን ?
'ለምንናገረው  ይሁን እንዴት ሰምተውን ለሚተረጉሙት ትርጓሜ ኋላፊነት መውሰድ ይቻለናል ?'  አያልኩ መብከንከን ፀፀትም ተከተለኝ።

በሃሳብ ጭልጥ ስል አይታ "አትመክረኝም?" አለች ።
ፈገግ አልኩ ...

**ይልቅ እንጠጣ እስኪ።

......✍️©Adhanom Mitiku
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢   
💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asresee ** https://t.me/Asresee

1 month, 3 weeks ago

በረከቶችህን አትግፋ!.........

ችግሮችህን  ስትቆጥር በረከቶችህ አያምልጡህ። የትም ብትሔድ፣ ማንንም ብትጠይቅ የማታጣው ነገር ቢኖር ችግሩን የሚተርክልህ ሰው ነው። "የኔ ችግር ይለያል" የሚልህ ሰው ብዛቱ ያንተን ችግር እንድትረሳ ሊያደርግህም ይችላል። ቸግሩን ሲያወራ በረከቶቹን የሚረሳም ብዙ ሰው አለ። በረከት፣ ፀጋ፣ ስጦታ ተነፍጎ በችግር፣ በመከራና በስቃይ ብቻ የተከበበ ሰው የለም። አንተ አላየሀውም ማለት ስጦታ የለህም ማለት አይደለም፤ አንተ አታውቀውም ማለት ክህሎት አልባ በረከት የተነፈክ ነህ ማለት አይደለም።
አዎ! ጀግናዬ..! ቸግሮችህን እያጎላህ በረከቶችህን አትግፋእንዳለህ ባለማወቅህ ብቻ እንደሌለህ አትናገር። እራስን ላለማወቅ ተጠያቂው እራሱ ባለቤቱ ነው። ፀጋህን አለማወቅህ ያለመኖሩ ማረጋገጫ አይደለም። ሁሉም ሰው ከችግሩ በላይ በረከቶች አሉት። የምናስበውን ያለመለየት ጉዳይ ነው እንጂ መልካሙን የሚያስብ፣ በጎውን የሚመኝ ችግሮቹ ላይ መንገሱ አይቀርም። "ይሔ ችግር አለብኝ" ከማለት በላይ "ይሔ በረከት ተሰቶኛል" ማለት ነገሮችን የማስተካከል አቅም አለው። ከፈለከው ታገኘዋለህ፤ ካተኮርክበት ይገለጥልሃል፤ ጊዜ ከሰጠሀው በእርግጥም ትደርስበታለህ። ያንተ ሆኖ የማታውቀው፣ ተሰቶህ የሚሸሸግብህ ስጦታ አይኖርም።

አዎ! እንኳን የቅርቡን የራስህን ይቅርና የሩቁን፣ በሰዎች ላይ ያለውን መመልከት ትችላለህና ለእራስህ ሲሆን አትስነፍ፤ አትድከም። ችግሩን የሚያወራ ብቻ ሳይሆን ችግሩን የሚፈታ ማንነትም እንዳለህ አስታውስ። ማንም ስለሆክ ችግር አንተጋር ብቻ አይመጣም። ማንኛውም ሰው የእራሱ የግል ሸክም፤ የእራሱ አስጨናቂ ሃሳብ አለበት። የሌላው ጉዳይ ያንተ አይደለም፤ ማንም ሰው የእራሱን ፈተና የመወጣት አቅም አለው። የዚህ ንደፈ\-ሃሳብ እውነታ አንተም ጋር ይሰራል። ችግርህን መቁጠር ትርፍ አልባ ነው፤ በረከትህን መቁጠር ግን ሰላም፣ ፍቅር፣ እርካታ አለው። ባታውቀው እንጂ ብታውቀው ከችግር በላይ ነህና ተስፋህን ተንከባከብ፤ አንተነትህን ውደድ፤ ፀጋህን አጎልብት፤ በበረከቶችህ አመስግን፤ እንዲኖርህ የምትፈልገውን ውብ ስብዕና ከሚያጎናፅፍህ ሰላም አንፃር ከውስጥህ ፈልገህ አግኘው።

........✍️(Epha A.)
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢   
Telegram channel
👇*👇*👇
💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asresee ** https://t.me/Asresee

1 month, 3 weeks ago
**“ዕቃ የጠፋን ያህል እንኳን ፈጣሪን ብንፈልገው …

“ዕቃ የጠፋን ያህል እንኳን ፈጣሪን ብንፈልገው ምንኛ መልካም ነበር፤ እቃ የጠፋን ያህል ብንፈልገው.. ሰው የገዛ ሞባይሉ ቢጠፋ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ገለባብጦ ነው የሚፈልገው። ፈጣሪያችንን ሳናገኝ ግን ውለን እናድራለን። ፈጣሪን በማጣታችን ነፍሳችን ደግሞ ጥያቄዋ አያርፍም። ሁልጊዜ ሰው አይረካም፤ ስለማይረካም ነው ይገላል ይቀማል፤ ተሹሞ መሾም ይፈልጋል፤ አግብቶ ማግባት ይፈልጋል፤ ይዞ መያዝ ይፈልጋል። ሰው ለምንድነው ልቡ የማያርፍለት ካላችሁኝ የልብ ማረፊያው ፈጣሪ ስለሆነ ነው።”.... :- አባ ገብረ ኪዳን

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢   
Telegram channel
👇*👇*👇
💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asresee ** https://t.me/Asresee

1 month, 4 weeks ago

ትናንት ከእሱ ጋር ስሆን የሚያየኝ ስንት ሰው አዝኖ
አይመጥንሽም እያለ መክሮኛል፡፡ ሐሳባቸውን የጫጫታ ያህል እንኳን ቦታ አልሰጠሁትም ነበር።

እሱ ግን ካደኝ!.......

አጣጥለው ሲያዋሩት፣ ሲቀልዱበት እና ሲያሳንሱት ከስንቱ ጋ ተሟገትኩ? ከስንቱ ተጣላሁ? ጭሎ አድርገውት እኩዮቹ ሲልኩት፤ ታናናሾቹ ሲያሳንሱት ስንት ቀን ቀና እንዲል ባተልኩ። ወደ በጎ መለወጥ ብዙ ጠመዝማዛ መንገድ አለው። እንደ መበላሸት ቀላል አይደለም። እሱን ለመለወጥ ስንት መጽሐፍ አነበብኩ? ስንት ስልጠና አስገባሁት? እሱን ለመቀየር ሰንት ቀፋፊ ስፍራዎች ዋልኩ???

ከማይረባ _ ሰው ጋር ሆንሽ በሚል ቤተሰቦቼ መከሩኝ፣ ጨቀጨቁኝ፣ ተጣሉኝ። እኔ ግን ተጋፈጥኩ፡፡

እሱ ካደኝ እንጂ!!........

ሱስ አሸንፎት ምን ያልሸጠብኝ ነገር _ ነበር?? _ ከቤተሰቦቼ የተቀበልኳቸው ስጦታዎች እጄ ላይ መቼ አሉና?...መቀየሩ ስጦታዬ ይሆናል ብዬ ነበር የታገስኩት፡፡ ለምንፈልገው ነገር ዋጋ ካልከፈልን የምንፈልገውን ነገር መቼ እናገኛለን!

እሱ ግን ካደኝ!......

ተነጫናጭ፣ ግትር ነሽ ይለኛል። ነገር ግን ያኔ ንፁሕ ወዳጆች ሳለን ጭምር አስቸጋሪነትሽ ለታገሰሽ ደቂቃዎች እንኳን አይከርምም ይለኝ አልነበር? ትናንት አሜን ያለውን ማንነቴን ዛሬ ጎረበጠኝ አለ።...

ይሄን ማንነቴን እያወቀ እና እያየ እኮ ነው ከመጠንኩሽ ፍቀረኛ ካልሆንን ያለኝ፡፡

ዛሬ ከሱሱ ሲላቀቅ፣ ሲያምርበት፣ ጥሩ ደመወዝ ሲያገኝ፣ አለቃ ሲሆን ትናንት በደከመበት ወራት የተቀበለው ማንነቴ ኮሰኮሰው::

ሕሊናው ሲጠይቀው፣ ሲሞግተው ያሳለፍናቸውን ጥልፍልፍ መንገዶች ለማያውቁ፣ ለማይሞግቱ ሰዎች ጥሩ ሰው ነች ግን ካድኳት ብሎ ጆሮ ሲሰጡት ኃጥያቴን አግዝፎ እና አለስልሶ ያትታል። የውስጥ እውነት በጭብጨባ ሆነ በእርግማን ብዛት የሚዛነፍ መስሎት። ኢየሱስን የከሰሱት እና የሰቀሉት እኮ ያልደረሰባቸው እና የፈወሳቸው ናቸው፤ ሰቃይ እና ከሳሾቹ ሲጠየቁ የሚሉት መች አጡ???

እሱ ግን ትዝታችን ይበቃኛል ያልኩትን አላመነኝም!........

📓ርዕስ፦ አዎ! እሱጋ ያመኛል
...................ደራሲ፦አድኃኖም ምትኩ

..................... @Meklite21
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢   
Telegram channel
👇*👇*👇
💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asresee ** https://t.me/Asresee

2 months ago

ተናግረን ከልባችን ባልነበሩት እና
ከልባችን ኖረው መናገር ባቃቱን መሀል
ብዙ የጠፉ ፍቅሮች አሉ።
.ብዙ ብዙ...................
..............

*👉 https://t.me/Asresee 👉*** https://t.me/Asresee

2 months ago
2 months ago
`ያ ዕለት ከአንደበትሽ የወጡት

ያ ዕለት ከአንደበትሽ የወጡት የተበታተኑና ፍቺያቸው የራቁ ቃላት የመጨረሻ ንግግርሽ መሆኑን ባውቅ ጆሮዬን ከአንደበትሽ አልነቅልም፣በዚያች ቅፅበት ምድር ብትንቀጠቀጥ፣ሰማይ ቢደረመስ፣ ከዋክብት ቢረግፉ የመጨረሻ ንግግርሽን ከመስማት የበለጠ አያስፈሩኝም ነበረ። . ያ ዕለት ዐይኖችሽ ከሩቅ ሲከተሉኝ የስንብት ዕይታ መሆናቸውን ቢገባኝ አንገትሽ ሥር ገብቼ የልብ ምቴን እስክትሰሚው አቅፌ እሰናበትሽ ነበር። በወግ የመሰናበቱን ትርጉም ያስተማረኝ ያለመሰናበት ፀፀት ነው። . ያ ዕለት በሕይወታችን አንዱ አስከፊው ግን የምናልፈው ቀን መሰለኝ። አቃጥሎ የሚሰወር ክቡድ ድባብ የተጠናወተው ቀን መሰለኝ። ታገልኩ። ታተርኩ። በዚያ ትግል ውስጥ የሚወዱትን የመሰናበት ወግ አመለጠኝ። እየቆየ የሚጠዘጥዝ ጠባሳ፣ ቀን እየጠበቀ የሚያገረሽ ደዌ ተነቀስኩ። "ሕይወት ይቀጥላል"ብለው ሲያፅናኑ "መቀጠሉ ያማል" የሚል ምላሽ ፈጠርኩ።

🌹🌹 https://t.me/Asresee 🌹🌹
🌹🌹 https://t.me/Asresee 🌹🌹
🌹🌹 https://t.me/Asresee 🌹🌹

2 months ago
**ሳልነግርሽ**….......

ሳልነግርሽ….......
.
.
አፍቅሬ እንዳጣሁሽ… በነብያቶች አፍ፣ ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ ታምር የሚሰራ… ጎትቶ ጎትቶ ፣ በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡ በሰባራ መርፌ…. ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ ይኸው እደክማለሁ… ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡ ………………………………….
ሳልነግርሽ
የኔ አለም ያላንቺ ፣እንደሆነ ራቁት ባንቺ እንደነበር ፤ ቀንና ሌሊቴ የሚፈራረቁት፡፡ እንደተለየሽኝ … አለም ባዶ ሆና ፣ መኖር እንዳስጠላኝ ፍቅርሽ እከክ ሆኖ… በልቤ ተተክሎ ፣ ነፍሴን እንደበላኝ፡፡ …………………………………
ሳልነግርሽ….
የነብያት ትንቢት ፣ በኔ መፈፀሙን ታምሪያለሽ ›እያልሁኝ ፣‹ተአምር› ማክተሙን የተለየሽኝ ለት… ምፅአት መምጣቱን ፣ የኔ አለም መቆሙን፡፡ …………………………………………
ሳልነግርሽ....….
ካጣሁሽ በኋላ…. ባለፍኩት ጭንቅ ዓለም ፣ የስቃዬን መአት አፍቅሮ ማጣት ነው… በሰባራ መርፌ፣ እውነትን መስፋት ነው ፣ ለካንስ ምፅአት፡፡
;
:
:
**➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢   

Tiktok channel👇👇https://www.tiktok.com/@tamrat624?_t=8kb1090E501&_r=1 Telegram channel 👇👇👇
https://t.me/Asresee https://t.me/Asresee ➱** https://t.me/Asresee

2 months, 1 week ago

🤕#ክፉ አይንካሽ
....ነዋይ ደበበ

5 months ago

ላንቺ ይሁንልኝ!!`ያኔ በርረሽ የትም መድረስ የምትችዪ የሚመስልሽ ልጅነትሽ ውስጥ ብዙ ህልም የነበረሽ ፣ <ሳድግ የምሆናት> ብለሽ አርቀሽ የሰቀልሻት አንቺ የነበረችሽ ፣ እደምቅበታለው ያልሽው መክሊት እና ችሎታ የነበረሽ ………

ከዛ ግን ዓመታት ነጉደው ስትነቂ ክንፍሽ የተሰበረ ዓይነት ስሜት ያለው ……..

~ አግብተሽ ወልደሽ ….. በልጆችሽ ፍቅር ውስጥ ጠፍተሽ …. ምናልባትም ባልበሰለ ውሳኔሽ የተሳሳተ አጋር መርጠሽ ያዘመመ ትዳር እየመራሽ …… የእለት ተዕለት ኑሮን ለማስኬድ እጅሽ የደረሰበትን ስራ እየሰራሽ በኑሮ ትግል ደብዝዘሽ …….  ህልምሽ ተዘንግቶሽ ….. ሳድግ የምሆናት ካልሻት አንቺ የልጆችሽን ማደግ አስቀድመሽ …. ከራስሽ ጋር የምታወሪበት ፋታ ስታገኚ

«በቃ?!! ህይወቴ ይሄ ነው በቃ?!! ህልሜ ፣ ምኞቴ ቅዠት ብቻ ነበር?!!» የምትይበት ዝቅታ ለሚሰማሽ

~ደግሞ ለቤተሰቦችሽ ወይም ለልጅሽ ቀን ላውጣላቸው ብለሽ ተሰደሽ በሰው ሀገር ስትለፊ ያንቺ ቀን ያለፈ ለሚመስልሽ ፣ በትከሻሽ ተሸክመሽ ባህር ያቋረጥሽውን ሀላፊነት ቀስ በቀስ ስትንጂ …. ወንድምሽ አግብቶ የራሱን ቤተሰብ መምራት ሲጀምር ፣ ለአባትሽ ቤት ከገዛሽ ኋላ ፣ እህትሽ ትምህርቷን ስትጨርስ ….. ለምትወጃቸው <ቆይ ይሄን አድርጌ> እያልሽ ዓመት ዓመትን ሲደርብ ….. <አሁን ለራሴ መኖር ልጀምር !> ስትዪ እድሜሽም ሄዶ ፣ ድሮ ያስቀመጥሽውን አንስተሽ መቀጠል እንዳትችዪ ሆኖ ተቀያይሮ … ከዚህ በኋላ ገና ተምሬ? ከዚህ በኋላ ገና ፍቅር ፈልጌ? ከዚህ በኋላ ምንስ ብጀምር እስክጨርሰው የትዬለሌ …… ብለሽ ቀኑ የሰጠሽን ተቀብለሽ «በቃ! አሁንማ አበቃ!! ድሮ ነበር!» የምትይበትን ዝቅታ ለነካሽ

~ ደግሞ ላንቺ …. በአደባባይ <እሷን ባደረገኝ> የሚባልልሽ ስኬታማ ፣ በመንገድሽ ላገኘሽው ሁሉ ብርታት እና ንቃትን የምታጋቢ ፣ ለልጆችሽ፣ ለጓደኞችሽ ፣ ለቤተሰቦችሽ እና በዙሪያሽ ላሉ ሁሉ በሳቅሽ ቀናቸውን የምታፈኪ ፣ በአደባባይ የዋጥሽው እንባ ብቻሽን ስትሆኚ የሚገነፍልብሽ ፣ እቤትሽ የምታነክሽበት ጉድለትሽ እንስ አድርጎ የሚያኮማትርሽ ….. <እስከመቼ ነው እንዲህ ባዶነት የሚፈረካክሰኝ? በቃ ህይወቴ እንዲህ ነው የሚቀጥለው? ያ ሁሉ የወጣሁ የወረድኩት ለዚህ ባዶነት ነው?> የምትይበትን ዝቅታ ለነካሽ``ታውቂዋለሽኮ የመጨረሻ የዝቅታ ወለል ላይ ስትሆኚ ያለሽ ምርጫ ሁለት ብቻ ነው!! ወይ ወደላይ (ወደከፍታ) መሄድ ወይ ደግሞ እዛው መቆየት ነው። ምክንያቱም ከመጨረሻው ወለል ወደየትም ዝቅ አትይማ!!

እዛው መቆየት ያንቺ ምርጫ አይሆንምኣ? <በቃ! አከተመ! > የሚባልበት እድሜም ሁኔታም የለምኮ!! ረስተሽው ወይ እየደቆሰሽ ባለፈ አስቸጋሪ ቀን የተሟጠጠ መስሎሽ እንጂ እንኳን አንድ ያንቺን የሌላውን ደርበሽ አቀበቱን የምትወጪበት ጉልበትኮ ነው ያለሽ!! ለምን አንድ ዓመት አይሆንም የቀረሽ የእድሜ ዘመን? እየሞከርሽ ፣ እያለምሽ ፣ መራመድ ባትችዪ እየተንከብለልሽ ዘመንሽ ይለቅ!! ምክንያቱም ስኬትኮ የተራራው ጫፍ አይደለም!! ጉዞውም የስኬትሽ አካል ነው!! መፍጨርጨር እና እየወደቁ መነሳቱምኮ ወደ ህልምሽ መቅረቢያ መንገዱ ነው!! የህልምሽ አካል ነው!!በቀንሽ መጨረሻ ምን ዓይነት ሴት ሆነሽ ማለፍ ነው የምትፈልጊው? ምን አይነት አሻራ ጥለሽ ነው ማለፍ የምትፈልጊው? ሁሉ ነገር ሲመቻች ብቻ አይደለም ያቺን ራስሽን የምትሰሪው ፤ አሁን ባለሽበት ዝቅታሽ ውስጥ ..... በኑሮ ውጣ ውረድ በደበዘዘ ነገሽ.....  ምንም ተስፋ የሚሰጥ ጭላንጭል ብርሃን ባይታይሽም ራስሽን ስሪ ፣ ነገ የእኔ ቀን ሲመጣ የማጌጥበት ነው ብለሽ መክሊትሽን አዳብሪ!! አታስቀምጪው (አትደብቂው)!! እጅ አትስጪ እንጂ ያ ቀን ይመጣል!! አድካሚም ቢሆን ያ ያንቺ ቀን ይመጣል!!
እየተዘጋጀሽ ፣ እያደግሽ ፣ እየተለማመድሽ ካልቆየሽኮ ግን ያ ቀንሽ ቢመጣም አትደምቂበትም! ምክንያቱም ተስፋ ቆርጠሽ ቀን እስኪመጣ የጣልሽው ህልም ነው ያለሽ እንጂ የምትሰጪው ወይ የምታሳዪው ነገር አይኖርሽም!!` ደግሞ ከሁሉ በላይ የሰማዩ አምላክ አለ አይደል? ለእያንዳንዷ ለዘራሻት ፍቅር ፣ ለሞላሽው ጉድለት ፣ ላበስሽው እንባ ፣ ቀና ላደረግሽው አንገት …….. ይሄን ሁሉ ብድራትሽን ሊከፍልሽ ሳለ የምን እጅ መስጠት ነው? <አበርታኝ> በይው!! አንድ ለመራመድ የዘረጋሽው እግርሽ አስር ተራምዶ ታገኚዋለሽ!! እመኚኝ አልፎ ወደኋላሽ ዞረሽ ስታዪው እንዳለፈ ውሃ ነው!!!!...
         ደሞ በተረፈው እኔ እወድሽ የለ?
❤️*❤️*

ውብ ቀን ውብኛ አዋዋል ዋሉልኝ!!! ❤️❤️❤️

(ወንዶች ካነበባችሁት ምናልባት ሊያስፈልጋት ስለሚችል ለሚስትህ አንብብላት ወይም ስደት ላለች እህትህ........!!!
.........ኸረ እኔ የለሁበትም! ያላችሁ እንተላለፍ !! )**

የእናቴ ልጅ-(Tame)
........................... @Meklite21

??Telegram channel ??
✍️ https://t.me/Asresee *✍️
✍️ https://t.me/Asresee ✍️
✍️ https://t.me/Asresee ✍️***

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago