Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Bakos Book Store 📚 ባኮስ መጻሕፍት መደብር

Description
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!

ለበለጠ መረጃ በ0920888887 ይደውሉ።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month, 2 weeks ago
ዛ ሬ ይ ጠ ና ቀ …

ዛ ሬ ይ ጠ ና ቀ ቃ ል

#ትንሿን_ቤተ_ክርስቲያን መጽሐፍ በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀው የመጻሕፍት ዐውደ ርእይ #በ700 ብር ብቻ ያገኟታል

ያስተውሉ ከዐውደ ርእዩ ውጭ በዚህ ዋጋ አያገኙም

ከ5 በላይ መጻሕፍት ለሚገዙን ያዘጋጀነው ሽልማትም እንደ ተጠበቀ ነው

1 month, 3 weeks ago
ታ ላ ቅ ቅ ና ሽ …

ታ ላ ቅ ቅ ና ሽ

ለ ዛ ሬ ና ለ ነ ገ ቅ ዳ ሜ ብ ቻ

#ትንሿን_ቤተ_ክርስቲያን መጽሐፍ በስካይላይት ሆቴል በተዘጋጀው የመጻሕፍት ዐውደ ርእይ #በ700 ብር ብቻ ያገኟታል!

ያስተውሉ ከዐውደ ርእዩ ውጭ በዚህ ዋጋ አያገኙም

በተጨማሪም ከ5 በላይ መጻሕፍት ለሚገዙን ሽልማት አዘጋጅተናል!

1 month, 3 weeks ago
ከስመ ጥሩ ካህን ቀሲስ ታድሮስ ማላቲ …

ከስመ ጥሩ ካህን ቀሲስ ታድሮስ ማላቲ ላቅ ያለ ጠቀሜታ ያላቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትረካዎች ባማረ ሁኔታ ተጠናቅረው በእነዚህ ሁለት መጻሕፍት ቀርበዋል።

እነዚህ መጻሕፍት ከሕፃናት ጀምሮ እስከ ወላጆች እንዲሁም በወጣቶች ሃይማኖታዊ ትምህርት ላይ አደራና ኃላፊነት እስካለበት ማንኛውም ሰው ድረስ ብሉይንና ሐዲስ ኪዳንን እንደዚሁም በውስጡ የተካተቱትን እጅግ ወሳኝ ታላላቅ ክስተቶች በአስደናቂ ሁኔታ የያዘ በሁሉም ዕድሜዎች ለሚገኙ ሁሉ የሚጠቅሙ መጻሕፍት ናቸው፡፡

እነዚህ የከበሩ መጻሕፍት አማርኛው ለሁሉም በሚገባ መልኩ የተዘጋጁና በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ በደስታ እንድንጓዝ የሚጋብዙ ሲሆኑ ለበርካታ ቀጣይ ትውልዶችም ትልቅ ዋጋ ያላቸው ሐብቶች ናቸው፡፡

ባ ኮ ስ መ ጻ ሕ ፍ ት መ ደ ብ ር

1 month, 4 weeks ago
[#የዕለቱ\_ምርጥ\_መጽሐፍ](?q=%23%E1%8B%A8%E1%8B%95%E1%88%88%E1%89%B1_%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%A5_%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%90%E1%8D%8D)

#የዕለቱ_ምርጥ_መጽሐፍ
📚 የመጽሐፉ ርእስ፦ ኦሪት ዘፍጥረት - 4ኛ ኅትም
📚 አዘጋጅ፦ ቅዱስ ዮሐንስ እንዳስተማረው
📚 ትርጉም፦ ገብረእግዚአብሔር ኪደ
📚 ይዘት፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራርያ
📚 የገጽ ብዛት፦ 347
📚 የሽፋን ዋጋው፦ 450 ብር
📚 ለዛሬ የተተመነለት ዋጋ፦ 340 ብር
-------------------
👉 ይጎብኙን - ለዐቢይ ፆም ሙሉ በምናወጣቸው የየዕለቱ ቅናሾች ተጠቃሚ ይኹኑ!
-------------
👉 አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ፥ አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ስ.ቁ. 0920888887
-----------------
https://t.me/Bakosbookstore

1 month, 4 weeks ago
ኦሪት ዘፍጥረት ቅጽ ፩ - 4ኛ …

ኦሪት ዘፍጥረት ቅጽ ፩ - 4ኛ ኅትም በሽሮ ከለር ወረቀት ጥሩ ኾኖ ታትሟል!

የሽፋን ዋጋ 450 ብር

_________
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!

ለበለጠ መረጃ በ0920888887 ይደውሉ።

2 months ago

⭐️ሰፌልያ⭐️

የመጽሐፍ ዳሰሳ/ Book review

ሰፌልያ የተዘጋጀው በሰባኬ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን ሲሆን የሕትመት ዘመኑ ደግሞ ኅዳር 2016 ዓ.ም ነው። ሰፌልያ የንዑድ ቅዱስ ጳውሎስን ሕይወት፣ ማንነትና ያደረጋቸውን ሐዋርያዊ ጉዞዎች ያስቃኛል። መጽሐፉ መዶሻ (ሰፌልያ) ስለተባለው ሐዋርያ በአምስት ምዕራፎች የተደላደለ ጥልቅ ሐቲት (discourse) ለመስጠትም ይሞክራል።

የመጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ የቅዱስ ጳውሎስን የቀደመ ግለ ታሪክ፣ የተወለደበትን ስፍራ፣ የቤተሰቦቹን ማንነት፣ ያደገበትን ሁኔታ፣ ዜግነቱን፣ ቋንቋውን፣ ትምህርቱን፣ ሙያውን፣ የቤተ ክርስቲያን ያሳዳጅነት ዘመኑን፣ ወደ ክርስትና ስለመጠራቱ፣ ወደ ሐናንያ ስለማምራቱ፣ በቅርጫት ስለማምለጡ፣ ወደ አረብ ሀገር ስለማቅናቱ፣ ኬፋን ሊጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ስለመውጣቱ፣ ስለእስጢፋኖስ ማኅበር መበተን፣ በርናባስ ወደ አንጾኪያ ስለመላኩ፣ ስለአጋቦስ ትንቢት... ሌሎችም ዝርዝር ጉዳዮችን ይተርካል።

ሰፌልያ በሁለተኛው ምዕራፍ የቅዱስ ጳውሎስንና የበርናባስን ለአገልግሎት መመረጥ፣ ወደ ቆጵሮስ ስለማቅናታቸው፣ ስለጳፋው ጠንቋይና ሐሰተኛው ነቢይ፣ በጲስዲያ አንጾኪያ ስለነበረው አገልግሎት፣ በቆጵሮስ ስለሰበኩት የምስራች፣ ስለትንሣኤው ምሥጢር፣ ስለአይሁድ ቅናት፣ ስለኢቆንዮን፣ ስለሊቃኦንያ ከተሞች፣ ስላልተገባ መሥዋዕት ስላቀረቡት ተግሣጽ፣ ስለጳውሎስ መከራ መቀበል፣ ወደ ደርቤን ስለመውጣታቸው፣ በኢየሩሳሌም በግዝረት ጉዳይ ስለተደረገ ክርክር... ጉዞው ስለሸፈናቸው አጠቃላይ ነገሮች በጥልቀት ይተነትናል።

ሦስተኛው የሰፌልያ ምዕራፍ ቅዱስ ጳውሎስ ከጢሞቴዎስ ጋር ስለተተዋወቀበት አጋጣሚ፣ ስለጢሞቴዎስ ማንነት፣ ቀኖና ትሁፊትን መጠበቅ እንዲገባ፣ በእስያ ቃሉን እንዳይናገሩ በመንፈስ ቅዱስ ስለመከልከላቸው፣ ጳውሎስ ስላየው ራእይ፣ ወደ መቄዶንያ ስለመሻገራቸው፣ ስለልድያ፣ ከምዋርተኝነት ስለፈወሷት አንዲት ሴት፣ ጳውሎስና ሲላስ በእስር ሳሉ ስለገጠማቸው ክስተት፣ ስለውኅኒ ቤቱ ጠባቂ፣ በሥውር ስለመፈታታቸው፣ ስለአቴና ከተማ፣ ስለአርዮስ ፋጎስ ሸንጎ፣ ስለቆሮንቶስ.... እና ጉዞ ስለሸፈናቸው ቦታዎችና፣ በጉዞው ስለተጻፉ መልእክቶች፣ ስለተመዘገቡ ሁነቶች በዝርዝር ይተርካል።

ሰፌልያ በአራተኛው ምዕራፍ ስለኤፌሶን፣ ስለአጵሎስ፣ እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ስለሠራው ሥራ፣ ስለአስቄዋ ልጆች፣ ስለቆሮንቶስ መልእክት፣ በኤፌሶን ስለተነሣው ታላቅ ሁከት፣ ስለአርጤምስ፣ በእፉኝት ስለመነደፉ፣ ሮም ስለመድረሱ፣ ቅዱስ ጳውሎስ የአይሁድ ታላላቆችን ስለመጥራቱ፣ ስለገላቲያ እና ስለሮሜ መልእክት፣ ስለአጋቦስ፣ ስለቅዱስ ጳውሎስ መታሠር፤ ስለፊሊጲስዩስ፣ ስለኤፌሶን፣ ስለቆላይሰስ፣ ስለፊልሞና እና ስለዕብራውያን መልእክት እንዲሁም እስከ መጨረሻው ድረስ ቅዱስ ጳውሎስ ስላስተናገዳቸው ሁነቶች በጥልቀት ያነሣል።

በአምስተኛውና በመጨረሻው የመጽሐፉ ምዕራፍ ቅዱስ ጳውሎስ በቁም እስር ሁለት ዓመት ተቀምጦ ስላስተማረው ትምህርት፤ ለጢሞቴዎስ፣ ለቲቶ ስለጻፋቸው መልእክቶች እና በኔሮን ቄሣር ትዕዛዝ ስለተቀበለው ሰማዕትነት በሰፊው ያስረዳል።

ሰፌልያ ለየት ባለ መልኩ አንባቢው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክታቱን የጻፈባቸውን ስፍራዎቹን መከታተልና የጉዞውንም ጠባይ ከአጭር ገለጻው መረዳት እንዲችል፣ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ላይ በቀጥታ ወደ ሐዋርያው ጉዞ ከመግባቱ በፊት አጭር የጉዞ መግለጫና የጉዞውን መዳረሻ ከተማዎችን የሚያሳይ ካርታ ተያይዟል፣ ይህም ተገቢውን ማብራሪያ (counter argument) ይሰጣል።

በአጠቃላይ ሰፌልያ በጥልቅ የነገረ መለኮት ግንዛቤ የተቃኘና ሊያነጥር ያነሣቸውን ሐሳቦች ከግብ ሳያደርስ የማይተው ተሻጋሪ (transcendental) የምርምር ሥራ ነው። ጥብቅ አስተውሎትን የሚጠይቁ ቦታዎች ስላሉት እንዲሁ በዋዛ ሳይሆን ደግመን ደጋግመን እንድናነበው ያስፈልጋል። አባታችን መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገ/ መድኅን አገልግሎትህን ይቀበልልህ፣ በእንዲህ መሰል (priceless) ገጸ በረከት ዳግም ያምጣልን።
________
ፍጹም አብርሃም እንደ ጻፈው
________
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!

ለበለጠ መረጃ በ0920888887 ይደውሉ።

2 months ago
Bakos Book Store 📚 ባኮስ መጻሕፍት …
2 months ago
ከኹለቱ አራት አራት ፍሬዎች አግኝተናል!

ከኹለቱ አራት አራት ፍሬዎች አግኝተናል!

ይጎብኙን!!!

2 months ago
[#የዕለቱ\_ስፔሻል](?q=%23%E1%8B%A8%E1%8B%95%E1%88%88%E1%89%B1_%E1%88%B5%E1%8D%94%E1%88%BB%E1%88%8D)

#የዕለቱ_ስፔሻል
📚 የመጽሐፉ ርእስ፦ ፍኖተ ሊቃውንት ቅጽ ፩
📚 አዘጋጅ፦ ዲ/ን አሻግሬ አምጤ
📚 ይዘት፦ ነገረ አበው
📚 የገጽ ብዛት፦ 503
📚 የሽፋን ዋጋ፦ 700 ብር
📚 ለዛሬ የተተመነለት ዋጋ፦ 670 ብር
-------------------
📍 ማስታወሻ፦ ይህ ቅናሽ ለዛሬ ብቻና ባኮስ መጻሕፍት መደብርን ብቻ የሚመለከት ነው።
-----------------
ይጎብኙን - ለዐቢይ ፆም ሙሉ በምናወጣቸው የየዕለቱ ቅናሾች ተጠቃሚ ይኹኑ!
-------------
አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ፥ አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ስ.ቁ. 0920888887
-----------------
https://t.me/Bakosbookstore

2 months, 1 week ago
[#የቅበላ\_ስፔሻል](?q=%23%E1%8B%A8%E1%89%85%E1%89%A0%E1%88%8B_%E1%88%B5%E1%8D%94%E1%88%BB%E1%88%8D) ፪

#የቅበላ_ስፔሻል
📚 የመጽሐፉ ርእስ፦ የሰው ልጅ ማን ነው?
📚 ጸሐፊ፦መምህር ሲሳይ ተስፋ
📚 ይዘት፦ ነገረ ክርስቶስን መሠረት ያደረገ ዕቅበተ እምነት
📚 የገጽ ብዛት፦ 375
📚 የሽፋን ዋጋ፦ 450 ብር
📚 ለቅበላው የተተመነለት ዋጋ፦ 340 ብር
-------------------
📍 ይህ መጽሐፍ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን ሳይቀበሉ በዕውቀት ያልበሰሉ (በተለይ የግቢ ጉባኤ ተማሪ የኾኑ) ኦርቶዶክሳውያንን ግራ ለማጋባት ለሚሞክሩ ለእስልምና ለፕ.ሮ.ቴ.ስ.ታ.ን.ቶ.ች. የተዘጋጀ ነው። ያመኑትን እያጸና ለሎችም መልስ የሚኾን ነው።
-----------------
ይጎብኙን - ለዐቢይ ፆም ሙሉ በምናወጣቸው የየዕለቱ ቅናሾች ተጠቃሚ ይኹኑ!
-------------
አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ፥ አሐዱ ባንክ ፊት ለፊት
ስ.ቁ. 0920888887
-----------------
https://t.me/Bakosbookstore

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago