Bakos Book Store - ባኮስ መጻሕፍት መደብር

Description
ይጎብኙን - ደርዛቸውን የጠበቁ አዳዲስና ነባር ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍትን ያገኛሉ!

ለበለጠ መረጃ በ0920888887 ይደውሉ።
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

3 weeks ago

#ጉባኤያት

በወንድማችን ዲያቆን አዶንያስ ብርሃነ የተጻፈውና ብዙ የተደከመት ይህ መጽሐፍ፡ ከጌታችን ዕርነት በኋላ ከተጠራው የሐዋርያት ጉባኤ (ሲኖዶስ) ጀምሮ እስከ ገባኤ ቊስጥንጥንያ ድረስ (AD 381) የተከናወኑ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ቀኖናትን አስደናቂ በሆነ መልኩ አቅርቦልናል፡፡ ዲያዞን አዶንያስ ስመ ጥር የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች (አውሳብዮስ ዘቂሳርያ፡ ሩፈኖስ፣ ሶቅርጥስ ወዘተ) የጻፏቸውን ጥንታውያን የታሪክ መዛግበት በልዩ ትጋት እያጣቀሰና ከተጨማሪ የግእዝ ምንጮች ጋር እያመሳከረ የጥንቷን ቤተ ከርስቲያን ታሪክ እንድንማር ይጋብዘናል። በየገጹ የተጠቀስት የኅዳግ ማስታወሻዎችና ዋቢ መጻሕፍት እንዲሁም ደራሲው የተከተለው ምሁራዊ የአጻጸፍ ዘዴ መጽሐፉ በሥነ መለኮት ተቋማት ውስጥ የደቀ መዛሙርት ማስተማሪያ ሆኖ እንዲመረጥ ያደርጉታል ብዬ አምናለሁ::

ይህን መጽሐፍ የሚያብቡ አፍቀርያነ መጻሕፍት፡ አንዲት፡ ቅድስት፡ ኵላዊትና ሐዋርያዊት የሆነችው የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የተነሡባትን ኑት ለመመከት ያደረገችውን ታላቅ ተጋድሎ እየተደመሙ ይማሩብታል፡፡ ኑት*ን መቃወም ብቻ ሳይሆን፡ የእምነት አርበኞች የሆኑት የቤተ ከርስቲያን ታላላቅ አባቶች ቅዱሱን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ አርቶዶክሳዊውን አስተምህሮ በማያሻማ መልኩ የገለጹበት ሂደትም በዚህ መጽሐፍ በዝርዝር ስለተዳሰስ፡ መጽሐፉ የእናት ቤተ ከርስቲያናቸውን ትምህርተ ሃይማኖት በተሻለ መልኩ ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ጠቀሜታው እጅግ ከፍ ያለ ነው::

ከዚህ በተጨማሪ ስለ ምሥጢረ ጥምቀት፤ ሥርዓተ ቊርባን፡ የክህነት አገልግሎት (መዓርጋት ከህነት) ከጋብቻና ፍቺ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የጌታ ዐበይት በዓላት አከባበር፡ ከአማንያን ኅብረት (ቤተ ከርስቲያን) በኑቄ* ምክንያት ስለተለዩ ሰዎችና በንስሐ ስለሚመለሱባቸው መንገዶች ጥናት ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት የሚጠቀስ ነው:: ዲያቆን አዶንያስ በገባልን ቃል መሠረት የመጽሐፉን ሁለተኛ ክፍል በቅርቡ እንደሚያስነብበን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ (ዮአከቴተ ቊርባን መጽሐፍ ደራሲ)
_ _
አሳታሚና አከፋፋይ፥ ባኮስ መጻሕፍት መደብር

#ጊዜያዊ_አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ ምስራች ማእከል አጠገብ በሚገኘው የገበያ ማእከል ውስጥ፥ የሱቅ ቁጥር 20
ለበለጠ መረጃ 0920888887

https://t.me/Bakosbookstore

3 weeks ago
Bakos Book Store - ባኮስ መጻሕፍት …
3 weeks, 3 days ago

#ጉባኤያት

የቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጻሕፍት፥ በቀድሞ ዘመን ለመምህራን ብቻ አለፍ ሲልም ለካህናት ብቻ እንጂ ለሁሉ የሚነገሩ የሚተረጉሙ አልነበሩም። መጽሐፍቱም ምናልባት በገዳማትና ታላላቅ አድባራት ወይም በአብያተ መጻሕፍትና በጳጳሳት ዘንድ እንጂ በካህናት እጅ እንኳ ኣይገኙም ነበር። ባለንበት ዘመን ግን መጻሕፍተ ቀኖናት (ሲኖዶስ፡ ፍትሐ ነገሥት) በመጽሐፍና በዘመኑ ቴክኖሎጂ ምክንያት በስስ ቅጂም ጭምር እየተዘጋጁ በቀላሉ በየሰዉ እጅ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህም አንባቢ ንባቡን ብቻ ተመልክቶ የራሱን አስተያየት እየሰጠ ከሚተረጕም፥ ምን እንደሚሉ፣ ለምን እና እንዴት የተወሰኑ መሆናቸውን አስቀድሞ ማሳየት የተገባ ነው። ይህን ለማድረግም የተጻፉ አያሌ መጻሕፍት አሉ፡፡ ለምሳሌ፦ ዶክተር ዲበኵሉ ዘውዱ፡ “ፍትሐ ነገሥት ብሔረ ሕግ ወቀኖና” ፤ መምህር በጽሐ ዓለሙ፣ “ፍትሐ ነገሥት ምን አለ?" ፤ መጋቤ ምስጢር ስማቸው ንጋቱ፥ “መጽሐፈ ሲኖዶስ ዘሐዋርያት" ወዘተ መጥቀስ ይቻላል።

ይህ የዲያቆን አዶንያስ ብርሃነ መጽሐፍም፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ቀኖናዎች የተወሰኑባቸውን ዐበይት ጉባኤዎችና አበው ታሪክና ቀኖና ብቻ ሳይሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነትን ያገኙ እንደ ሎዶቅያ፣ ዕንቆራ፣ ጋንግራ፥ የመሳሰሉ ንኡሳን ጉባኤዎችን ታሪክና ቀኖናዎቻቸው ምን እንደሚሉ፣ የቀኖናዎቹ ሐሳብ ምን እንደሆነ፣ ቀኖና ያልተሠራላቸው በየጉባኤው የተወሰኑ ጉዳዮችን እንዲሁም ሌሎች ቁምነገሮችን በዝርዝር አካትቶ የያዘ ነው፡፡ መጽሐፉ በዘመን ቅደም ተከተል የተዘጋጀ ሆኖ፥ አከፋፈሉም ጉባኤ ኒቅያን ማእከል አድርጎ፥ ከቅድመ ኒቅያ እስከ ድኅረ ኒቅያና ድኅረ ሎዶቅያ እስከ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ ዋዜማ ድረስ ያለውን የሸፈነ ነው።

መጽሐፉ፥ ለረጅም ጊዜ ከገበያ ጠፍቶ በመቆየቱ አንባብያን ድጋሚ እንድናሳትምላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁን ቆይተዋል። ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር እንዲል እነሆ አሁን በባኮስ መጻሕፍት መደብር አሳታሚነትና አከፋፋይነት እንደ ገና የኅትመት ብርሃን አግኝቶ በቀጣይ ማክሰኞ ይወጣል። ትጠቀሙበት ዘንድም ግብዣችን ነው።
_#ጊዜያዊ_አድራሻችን፦ አምስት ኪሎ ምስራች ማእከል አጠገብ በሚገኘው የገበያ ማእከል ውስጥ፥ የሱቅ ቁጥር 20

https://t.me/Bakosbookstore

3 months, 2 weeks ago

ቤተሰብ ነክ የኾኑ ጉዳዮች የሚማርክዎት ከኾነ፥ ይህን መጽሐፍ ያነቡት ዘንድ እንጋብዝዎታለን።
______
ከመግቢያው የተቀነጨበ አሳብም እነሆ፦

"የዛሬ 17 ዓመት በአገራችን የመጀመሪያው የሥነ-ልቦና ማማከር እና ሥልጠና አገልገሎት ለመጀመር 'ዕርቅ ማዕድ' የሚል አሳብ ይዘን መጥተን ስንሠራ በተለያዩ የሥነልቦና ጉዳዮች እና በቤተሰብ ዙሪያ አገልግሎት መስጠት ጀመርን፡፡ በጋብቻ ዙሪያ፥ በኋላ ላይ ደግሞ 'ዕእርቅ ማዕድ' የሬዲዮ ፕሮግራም ላይም የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ ነበር በዋነኝነት የምንሠራው፡፡ በመካከላቸው ያሉ ግንኙነቶችን የሚያሳሱ፣ ፍቅራቸውን የሚበርዙ፤ አብሮነታቸውን የሚያዳክሙ እክሎች ሲገጥሟቸው ወደ እኛ እየመጡ ስሜታቸውን ማድመጥና ወደ ሰላም እንዲመጡ በማደራደር (me- diation ማድረግ ) ነበር፡፡ በዚያ ወቅት የገጠሙን ሁለት ዋና ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ አንዱ በምናያቸው አብዛኞቹ ባለትዳሮች የፀብ ታሪካቸው የሚጀምረው ዛሬ ሳይሆን ከ5 እና 7 ዓመት ፣ እንደውም ጭራሹን ከመጋባታቸው በፊት ካለው ግንኙነታቸው ጋር የተያያዘ ሆኖ መገኘቱ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ዕርቅ ከወረደ በኋላ የተስማሙበት ጉደይ ወይም ችግሩ እንደ ገና ተመልሶ ማገርሸቱ ነበር፡፡

"በዚህ ሁኔታ በጣም ግራ እንጋባ ነበረ። በምክክር አገልግሎት ወቅት ቀጥታ የምንገናኘው ከደንበኞቻችን ዛሬ ጋር አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሚስት ባሌ 'የቤት ወጪ / ኪራይ በጊዜ አይሰጠኝም' ብላን ብትከስ የባልየው ታሪክ የሚጀምረው በዚህ ወር ሳይሆን ከ 8/11 ዓመት በፊት ሆኖ ይገኛል፡፡ ክሱ ሲታይ የዚህ ወር ይምሰል እንጂ ከ10 ዓመት በፊት፣ ገና እንደ ተጋቡ ወይም ሳይጋቡ በፊት ጀምሮ ያለው የኋሊት ታሪክ ነው የሚመዘዘው፡፡ ጉዳዩን ቀረብና ጠለቅ እያልን ስንሄድ ደግሞ ጭራሹም ጉዳዩ ከባለ ታሪኮቹ ልጅነት ጋር የተሳሰረ ሆኖ ይገኛል፡፡ የተጣሉትን እናስማማለን፤ እናስታርቃለን፡፡ ግን ተመልስው ወደ ኋላ ይሄዳሉ፡፡ የጠባቸው ቀስቃሽ ምክንያት ለእኛ ትንሽና ለጠብ የማያበቃ ይሆንብናል፡፡ በዚህ ግራ እየተጋባሁ ባለሁበት ወቅት ነው ስለ አዕምሮ ቁስለት የሰማሁት።

  • ምን ሆኛለሁ?
    በትዕግሥት ዋልተ ንጉሥ
    ________
    መጽሐፉን በመጽሐፍ መደብራችን ያገኙታል!
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago