Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
ሙሣፊር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
4፥101 "በምድርም ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ያውኩናል ብላችሁ
ብትፈሩ ከሶላት ባለ አራት ረክዓት የኾኑትን ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት
የለም"፡፡ ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺿَﺮَﺑْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺟُﻨَﺎﺡٌ ﺃَﻥ ﺗَﻘْﺼُﺮُﻭﺍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓِ ﺇِﻥْ ﺧِﻔْﺘُﻢْ ﺃَﻥ
ﻳَﻔْﺘِﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ
"ሙሣፊር" ﻣُﺴﺎﻓِﺮ የሚለው ቃል "ሣፈረ " ﺳَﺎﻓَﺮَ ማለትም "ተጓዘ" ከሚል ሥርወ-ቃል
የመጣ ሲሆን "ተጓዥ" "መንገደኛ" ማለት ነው፥ ዱዓቸው አሏህ ዘንድ መቅቡል
ከሆኑት ሦስት ሰዎች መካከል አንዱ የሙሣፊር ዱዓእ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 36
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም " ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ሦስት
ልመናዎች ያለጥርጥር ተቀባነት አላቸው፥ እነርሱም፦ የተበዳይ ልመና፣ የመንገደኛ
ልመና እና ወላጅ ለልጁ የሚያደርገው ልመና ናቸው"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﻗَﺎﻝَ ﻗَﺎﻝَ
ﺭَﺳُﻮﻝُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ " ﺛَﻼَﺙُ ﺩَﻋَﻮَﺍﺕٍ ﻳُﺴْﺘَﺠَﺎﺏُ ﻟَﻬُﻦَّ ﻻَ ﺷَﻚَّ ﻓِﻴﻬِﻦَّ ﺩَﻋْﻮَﺓُ
ﺍﻟْﻤَﻈْﻠُﻮﻡِ ﻭَﺩَﻋْﻮَﺓُ ﺍﻟْﻤُﺴَﺎﻓِﺮِ ﻭَﺩَﻋْﻮَﺓُ ﺍﻟْﻮَﺍﻟِﺪِ ﻟِﻮَﻟَﺪِﻩِ "
አምላካችን አሏህ ሙሣፊርን "ኢብኑ አሥ-ሠቢል " ﭐﺑْﻦ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞ ማለትም "የመንገድ
ልጅ" ይላቸዋል፥ "ኢብን " ﭐﺑْﻦ ማለት "ልጅ" ማለት እንደሆነ ልብ አድርግ! ዘካህ እና
ሶዶቃህ ከሚገባቸው አንዱ ሙሣፊሮች ናቸው፦
9፥60 ግዴታ ምጽዋቶች የሚከፈሉት ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ
ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም በኢሥላም ለሚለማመዱት፣ በባርነት
ተገዢዎችን ነጻ በማውጣት፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣
በመንገደኛም ብቻ ነው"፡፡ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟﺼَّﺪَﻗَﺎﺕُ ﻟِﻠْﻔُﻘَﺮَﺍﺀِ ﻭَﺍﻟْﻤَﺴَﺎﻛِﻴﻦِ ﻭَﺍﻟْﻌَﺎﻣِﻠِﻴﻦَ ﻋَﻠَﻴْﻬَﺎ ﻭَﺍﻟْﻤُﺆَﻟَّﻔَﺔِ
ﻗُﻠُﻮﺑُﻬُﻢْ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟﺮِّﻗَﺎﺏِ ﻭَﺍﻟْﻐَﺎﺭِﻣِﻴﻦَ ﻭَﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻞِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺍﺑْﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ
2፥215 "ምንን ለማንም እንደሚለግሱ ይጠይቁካል፥ "ከመልካም ነገር
የምትለግሱት ለወላጆች፣ ለቅርብ ዘመዶች፣ ለየቲሞችም፣ ለድሆችም እና
ለመንገደኞች ነው" በላቸው፡፡ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻮﻧَﻚَ ﻣَﺎﺫَﺍ ﻳُﻨﻔِﻘُﻮﻥَ ۖ ﻗُﻞْ ﻣَﺎ ﺃَﻧﻔَﻘْﺘُﻢ ﻣِّﻦْ ﺧَﻴْﺮٍ ﻓَﻠِﻠْﻮَﺍﻟِﺪَﻱْﻥِ
ﻭَﺍﻟْﺄَﻗْﺮَﺑِﻴﻦَ ﻭَﺍﻟْﻴَﺘَﺎﻣَﻰٰ ﻭَﺍﻟْﻤَﺴَﺎﻛِﻴﻦِ ﻭَﺍﺑْﻦِ ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞِ
እነዚህ አናቅጽ ላይ "መንገደኞች" ለሚለው የገባው ቃል "ኢብኑ አሥ-ሠቢል " ﭐﺑْﻦ
ﺍﻟﺴَّﺒِﻴﻞ መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል። "ቀስር " ﻗَﺼْﺮ የሚለው ቃል "ቀሶረ " ﻗَﺼَﺮَ
ማለትም "አጠረ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አጭር" ማለት ነው፥
የሙሣፊ ሶላት "ሶላቱል ቀስር " ﺻَّﻠَﺎﺓ ﺍﻟﻘَﺼْﺮ ይባላል። አንድ ሙሣፊር በመንገድ ላይ
እያለ ባለ አራት ረክዓት የነበሩት ሶላት ባለ ሁለት ረከዓት በመሆን ያጥራሉ፦
4፥101 "በምድርም ላይ በተጓዛችሁ ጊዜ እነዚያ የካዱት ያውኩናል ብላችሁ
ብትፈሩ ከሶላት ባለ አራት ረክዓት የኾኑትን ብታሳጥሩ በእናንተ ላይ ኃጢአት
የለም"፡፡ ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺿَﺮَﺑْﺘُﻢْ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺟُﻨَﺎﺡٌ ﺃَﻥ ﺗَﻘْﺼُﺮُﻭﺍ ﻣِﻦَ ﺍﻟﺼَّﻠَﺎﺓِ ﺇِﻥْ ﺧِﻔْﺘُﻢْ ﺃَﻥ
ﻳَﻔْﺘِﻨَﻜُﻢُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻛَﻔَﺮُﻭﺍ
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 5, ሐዲስ 1121
ኢብኑ ዐባሥ እንደተናገረው፦ "አሏህ በነቢያችሁ " ﷺ " ልሣን ግዳጅ ያረገው
በከተማ መኖሪያ አራት ረክዓትን ሲሆን በመንገድ ደግሞ ሁለት ረክዓትን ነው"።
ﻋَﻦِ ﺍﺑْﻦِ ﻋَﺒَّﺎﺱٍ، ﻗَﺎﻝَ ﺍﻓْﺘَﺮَﺽَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺍﻟﺼَّﻼَﺓَ ﻋَﻠَﻰ ﻟِﺴَﺎﻥِ ﻧَﺒِﻴِّﻜُﻢْ ـ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ـ ﻓِﻲ ﺍﻟْﺤَﻀَﺮِ
ﺃَﺭْﺑَﻌًﺎ ﻭَﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻔَﺮِ ﺭَﻛْﻌَﺘَﻴْﻦِ
"ረክዓህ" ﺭَﻛْﻌَﺔ ማለት "ዙር" ማለት ሲሆን የረክዓህ ብዙ ቁጥር ደግሞ "ረክዓት "
ﺭَﻛْﻌَﺖ ነው፥ በሙሰና ሲመጣ ደግሞ "ረክዐተይን " ﺭَﻛْﻌَﺘَﻴْﻦ ነው። የሙሣፊር ሶላት
ዙህር 4 ረክዓት እና ዐስር 4 በጥቅሉ 8 ረክዓት የነበረው ዙህር አዛን ካለበት
እስከ ዐስር ባለው ጊዜ ዙህር ሁለት ዐስር ሁለት ሆኖ 4 ረክዓት ይሰገዳል፥
እንዲሁ መግሪብ 3 ረክዓት እና ዒሻእ 4 በጥቅሉ 7 ረክዓት የነበረው መግሪብ
አዛን ካለበት እስከ ዒሻእ ባለው ጊዜ መግሪብ ሦስት ዒሻእ ሁለት ሆኖ 5 ረክዓት
ይሰገዳል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 19, ሐዲስ 52
ዐምር እንደተረከው፦ አቡ አሽ-ሸዕሳእ ሲናገር ሰማሁኝ፥ ጃቢር ሲናገር ኢብኑ
አባሥ"ረ.ዐ." እንደሰማሁት እርሱም እንዲህ አለ፦ "ከአሏህ መልእክተኛ " ﷺ" ጋር
ስምንት ረክዓት በአንድ ላይ እንዲሁ ሰባት ረክዓት በአንድ ላይ ሰገድኩኝ"። ﻋَﻦْ
ﻋَﻤْﺮٍﻭ، ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺃَﺑَﺎ ﺍﻟﺸَّﻌْﺜَﺎﺀِ، ﺟَﺎﺑِﺮًﺍ ﻗَﺎﻝَ ﺳَﻤِﻌْﺖُ ﺍﺑْﻦَ ﻋَﺒَّﺎﺱٍ ـ ﺭﺿﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ـ ﻗَﺎﻝَ ﺻَﻠَّﻴْﺖُ
ﻣَﻊَ ﺭَﺳُﻮﻝِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﺛَﻤَﺎﻧِﻴًﺎ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﺳَﺒْﻌًﺎ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ .
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 6, ሐዲስ 62
ሙዓዝ እንደተረከው፦ "ከአሏህ መልእክተኛ " ﷺ " ጋር በተቡክ ጉዞ ተጓዝን፥
እርሳቸውም ዙህርን እና ዐስርን አንድ ላይ እንዲሁ መግሪብን እና ዒሻእን በአንድ
ላይ ሰገዱ"። ﻋَﻦْ ﻣُﻌَﺎﺫٍ، ﻗَﺎﻝَ ﺧَﺮَﺟْﻨَﺎ ﻣَﻊَ ﺭَﺳُﻮﻝِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ﻓِﻲ ﻏَﺰْﻭَﺓِ ﺗَﺒُﻮﻙَ
ﻓَﻜَﺎﻥَ ﻳُﺼَﻠِّﻲ ﺍﻟﻈُّﻬْﺮَ ﻭَﺍﻟْﻌَﺼْﺮَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﻭَﺍﻟْﻤَﻐْﺮِﺏَ ﻭَﺍﻟْﻌِﺸَﺎﺀَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ .
የዐስርን ሶላት ዙህር አዛን ባለበት ሰዓቱ ላይ እንዲሁ የዒሻእን ሶላት መግሪብ
አዛን ባለበት ሰዓቱ ላይ መስገድ ተመራጭ ሲሆን በዙህር እና በዐስር መካከል
እንዲሁ በመግሪብ እና በዒሻእ መካከል ማሠላመት እንዳለ መዘንጋት የለበትም።
አንድ ሰው በጉዞ ላይ እያለ በረመዷን ፆም ወቅት አለመፆም ይችላል፥ ነገር ግን
ሙቂም ሲሆን ከፋራህ ያወጣል፦
2፥185 "በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን
በልኩ መጾም አለበት! አላህ በእናንተ ገሩን ነገር ይሻል፥ በእናንተም ችግሩን
አይሻም"*፡፡ ﻭَﻣَﻦ ﻛَﺎﻥَ ﻣَﺮِﻳﻀًﺎ ﺃَﻭْ ﻋَﻠَﻰٰ ﺳَﻔَﺮٍ ﻓَﻌِﺪَّﺓٌ ﻣِّﻦْ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﺃُﺧَﺮَ ۗ ﻳُﺮِﻳﺪُ ﺍﻟﻠَّﻪُ ﺑِﻜُﻢُ ﺍﻟْﻴُﺴْﺮَ ﻭَﻟَﺎ ﻳُﺮِﻳﺪُ
ﺑِﻜُﻢُ ﺍﻟْﻌُﺴْﺮَ
አንድ ሰው በአንድ ከተማ ከተወለደ ወይም ከከተመ "ሙቂም " ﻣُﻘِﻴﻢ ሲባል
የተወለደበት ወይም የከተመበት ደግሞ "ኢቃማህ " ﺇِﻗَﺎﻣَﺔ ይባላል፥ በተቃራኒው
አንድ ሰው ከሚኖርበት ቀዬ ከተጓዘ "ሙሣፊር " ﻣُﺴﺎﻓِﺮ ሲባል ጉዞው ደግሞ
"ሠፈር" ﺳَﻔَﺮ ይባላል። ስለ ሙሣፊር በግርድፉ እና በሌጣው ይህንን ይመስላል
# እንዴት_ታዝናለህ !...
ሌላው ለሌላ አካል እያጎበደደ፤አላህ አንተን መርጦ
እስልምናን ሰቶ ለርሱ ብቻ እንድታጎበድድ ፈቀደልህ!
እንዴት ታዝናለህ!...
ስንቱ በተከበረበት ተዋርዶ፤ረበል ዓለሚን ያንተን ወንጀልህንና ነውርህን ደብቆልህ
ለምን ታዝናለህ!...
ስንቱ ነው አንድ አፉን ሚመገበው ጎኑን
ሚያሳርፍበት ማደሪያ የሌለው፤አዛኙ ጌታህ ቤትህን በምግብና በመጠጥ
ሞልቶልህ ማደሪያ ሰጠህ
ስለምንስ ታዝናለህ!
ስንቱ ጤናውን አቶል ፤ራህማኑ አንተን ሰላም አደረገህ
አትዘን!
የሰው ፊት የሚገርፈው ሚለምን ስንቱ መሰለህ!?
ጀልሉ ግን አንተን ከሰዎች አብቃቃህ!
በፍፁም እንዳታዝን!
ከህመም ብዛት በስቃይ አይኑን ሳይከድን የተኛ ስንቱ መሰለህ!?፤ወዱዱ ላንተ
ሰላማዊ እንቅልፍን
ሰጠህ
ያጣሀውን አትመልከት ፤ያለህን ተመልከትና
(አልሃምዱሊላህ) በልና አላህም እንህ
ካላቸው ሰዎች ሁን....
" ﻭَﻗَﻠِﻴﻞٌ ﻣِّﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ ﺍﻟﺸَّﻜُﻮﺭُ "
"ከባሮቼ በጣም አመስጋኞቹም ጥቂቶች ናቸው፡፡"
[ሱረቱ ሰበዕ:13]
ጌታዬ አላህ ሆይ! ከመጥፎ ጎረቤትና እድሜዬ ሳይደርስ እንድሸብት
ከምታደርገኝ ሚስት በአንተ እጠበቃለሁ»።
ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም
አስ ሶሒሀህ (3137)
_አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል ሶስት_________
https://t.me/httpstmejoinchatAAMuktarhussen
ገንዘባችንን ካላመጠህ እንገድልሃለን ፣እንሰቅልሃለን እያሉ ሲያስጨንቁት የነበረ
አንድ ሰው አይታ አሳዘናትና ገንዘቡን ካላገኙ የሚገድሉት መስሏት የተሰጣትን
ገንዘብ ከመስጠት ከሞት ታድነዋለች ።ሰዉዬዉም እዳዬን ከፍለሽ ከሞት
ስላዳንሽኝ ካልሸኛሁሽ እያለ ይከተላታል።ልሸኝሽ ልከተልሽ ሲላት የአጅነቢይ ኸይር
የለዉምና አልፈልግም አለች ።እሱ ደግሞ ዉለታዋን የሚከፍል መስሎ ለሷ
አሳቢና ተቆርቋሪ በመምሰል ቢከተላትም አጅነቢ ነበርና እሱም የዋለችለትን
በመርሳትና ቃሉን በማፍረስ ቦታና ሁኔታ አመቻችቶ ብትጮህ ረዳት የማታገኝበት
ቦታ ሲደርሱ አላህ የጠላውን ነገር ይጠይቃታል ።።<<ገንዘቤን ከፍዬ ከሞት
አድኜህ ለኔ የተቆረቆርክ መስለህ የዚህ አይነት ጥያቄ ትጠይቀኛለህ ?፣ይህ ነው
ወለታዬ?በጣም አዝናለሁ ፣ጥያቄህ እንደማይሳካ ተስፋ ቁረጥ>>ትለዋለች
።ይህንኑ እየተመላለሱ ከዋናው መንገድ ዳር ደርሰው ነበርና ሰዎች ሲያገኝ
<<አንዲት ባሪያ አለችኝ ፤ልሸጣት እፈልጋለሁ ግዙኝ>>ብሎ ይጠይቃል ።ሰዉን
ባሪያ ነው ብሎ መሸጥ በጊዜው የነበረ ስርአት ነበርና ይህቺን በደለኛ ሲያዩ
ወደዷት ፤እሷም <<ባሪያ አይደለሁም >>ብትል ማን ሰምቷት፤ከእነሱ ጋር ዋጋ
ጨርሶ በ300ዲናር ይሸጣተል።ደግማደ ደጋግማ ራሷን ለማደን <<እኔ ጨዋ ነኝ
ባሪያ አይደለሁም >>ብትል <<እኛ ገዝተናል አያገባንም >>በማለት በጃልባ
ይዘዋት ይሄዳሉ ።ጀልባው ላይ ሆነዉ ባለመብት ነኝ ባዩ <<ከአሁን ጀምሮ የኔ
ባሪያ ነሽ >>እያለ ሊያቅፋትና ሊስማት እጁን ይዘረጋል ።<<አላህን ፍራ>>እያለች
ብትጮህም አትጩሂ ብሎ በጥፊ ይመታታል ።በዚህ ላይ እንዳሉ ማዕበል ተነስቶ
የነበሩበት ጀልባ ትገለበጣለች ።እሷም አላህ ጠብቋት ዋኝታ ወዳላሰበችዉና
ወደማታውቀው ባህር ዳርቻ ላይ ስትወጣ ከሷ ጋር በጀልባ የነበሩት ሰዎችም
ተበታትነው በተለያየ መንገድ ከባህሩ ይወጣሉ ።እሷ ከባህሩ በወጣችበት
አቅጣጫ አንድ አህለል ኸይር የጎሳ መሪ የሆነን ሰው ንጉሥ ታገኛለሽ።ታሪኳን
ስትነግረው በጣም ስላሳዘነችዉ ባለቤቷ ከሐጅ ተመልሶ ሀገሩ እስከሚገባ
ያለምንም ችግር ለብቻ ቤት ተሰጥቷት እንድትኖር ያደርጋል ።ቤቱ የአላህን ፈሪ
ቤት ስለነበር ተረጋግታ እየጾመች አላህን መለመን ትጀምራለች ____ክፍል
አራት በአላህ ፍቃድ ነገ ይቃጥለል ሼር ይደረግ ።
አላህን ፈሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል አምስት _______
https://t.me/httpstmejoinchatAAMuktarhussen
ሁሉም በአንድ ላይ በአንድ ቀን የአላህ ፍቃድ ሆነና ተያይዘው እሷ ዘንድ ደረሱ
።እሷም ታሪካዊ ጠላቶቿን ገና ከመድረሳቸው ሁሉንም አዉቃቸዉ ነበር ።እናም
ሁሉንም በአንድ ላይ ግቡ አለቻቸው ።እሷ ከመጋረጃ ጀርባ ስለነበረች አትታይም
።አትታወቅም ሁሉንም ከገቡ በኃላ እንዲህ አለች ፤<<ስራዉን ያጋለጠ ዱአ
ይደረግለታል ።እያንዳንዳችሁ እንዴት እንዲህ አይነት በሽታ ሊያጋጥማችሁ
እንደቻለ ተናገሩ ፤ችግሩን ያልተነገረ መፍትሄ አይገኝለትም ዱአም
አላደርግለትም>>ትላለች። በዚህ ግዜ የባለቤቷ ወንድም<<እኔ ጥፋቴን
በወንድሜ ፊት አልናገርም አፍራለሁ ወንድሜ ባለበት አልናገርም >>ሲል
ወንድሙ <<ምንም አይደል ተናገር የአንተን መዳን ነው የምፈልገው >>አለው
አልናገርም ተናገር አልናገርም ተናገረ እየተበበለ በመጨረሻ ደፍሮ <<እንግዳውስ
ይቅርታ አድርግልኝ ሚስትህን ያባረርኳት እኔ ነኝ፤ደብድቤያታለሁ፣በህይወት ትኑር
ትሙት አላዉቅም ።ላንተ ትነግርብኛለች በሚል ስጋት ዝሙት እንደሰራች
አስመስክሬባታለሁ>>በማለት ራሱን አጋለጠ ።ወንድምያዉ ምን ያክል ሊሰማዉ
እንደሚችል መገመት ይከብዳል ።ያልጠበቀው አሳዛኝ መርዶ ሲያረደዉ በድንጋጤ
እንደ እንጨት ደርቆ ቀረ።። ከዚያም ምስክሮቹም እንዲሁ ገንዘብ ሰጥቶን በሀሰት
መስክሩ ብሎን ከመሰከርን በኃላ ነው ለዚህ አይነት ችግር የተጋለጥነዉ በማለት
ራሳቸውን ያጋልጣሉ ።
ሌላዉም በተራው አንዲት ሴት አስፈራራለሁ ብሎ ህፃን ልጅ እንደገደለና ሌላ
እንደማያውቅ ተናገረ ።ሌለው ደግሞ ከሞት የዳነችውን ጨዋይቱን ሴት
300(ሶስት መቶ ዲናር)የሸጠ መሆኑን ና የገዛትም እንደዚሁ ባሪያዬ ናት ብሎ
ሲስማት በመርከቡ መገልበጡን ከዛ ዉጭ ምንም እንደማያዉቁ-----ሁሉንም ተራ
በተራ ካናዘዘች በኃላ ማንነቷን ሳትነግረዉ ከሀጅ የመጣውን ባለቤቷን ወደ
መጋረጃው ውስጥ (እሷ ወዳለችበት ክፍል )እንዲገባ ትነግረዋለች ።እሱም
ተስፋ ቆርጦ ስለነበር ባለቤቴ ትሆናለች የሚል እሳቤም ስላልነበረው <<እኔ
አጅነቢ ጋር አልገባም >>ይላል::__________ክፍል ስድስት እና የመጨረሻው
ክፍል በአላህ ፍቃድ ነገ ይቀጥላል ሼር አድርጉ።
«አንድ ሰው 3 ሴት ልጆች ኑረውት ከሚችለው ካበላቸው፣ ካጠጣቸው
እንዲሁም ካለበሳቸው የቂያማ ቀን ለሱ ከጀሀነም እሳት ከለላ ይሆኑለታል»።
◦•●◉✿ ነቢዩ ﷺ ስለአሏሁ አለይሂ ወሰለም ✿◉●•◦
ምንጭ:- ኢብኑ ማጀህ (2974)
የአላህ መልእክተኛ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
የአማኝ የሆነ ሰው ነገሩ ያስገርማል (ግሩም)ነው አማኝ የሆነ ሰው ነገሩ ሁሉ
የተሻለ ነው
ይህ ኸይር ነገር ለአማኝ ካልሆነ ለማንም አይሆንም
ሚያስደስት ነገር ሲያገኘው አላህን ያመሰግናል ለሱ የተሻለ ነው ችግር
ሲገጥመው ይታገሳል ይህ ለሱ የተሻለ ነው።
መልካም ነገር ሲያገኙ ከሚያመሰግኑ ሲቸገሩ ከሚታገሱ ወንጀል ላይ ሲወድቁ
ምህረት ከሚጠይቁ ባርያዎች ያድርገን አላሁ አሚን።
በአሸባሪዋ እስራኤል ውስጥ ከ1100 አመት በፊት የተቀበረ የወርቅ ሳንቲም
ተገኘ !! በሳንቲሙ ላይ
ﻻﺇﻟﻪ ﺍﻻ ﺍﻟﻠﻪ ﻣﺤﻤﺪ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ
ከአላህ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም
ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛው ነው። የሚል ጹሁፍ አለው !
https://www.timesofisrael.com/pure-gold-425-islamic-coins-
from-1100-years-ago-found-at-israel-dig/
ታሪክ ይናገራል ። ፍልስጤም ታሪክሽ ይህ ነው።
The Times of Israel
Pure gold: Teens find 425 Islamic coins from 1,100 years ago at Israel dig
Rare trove 'in excellent condition' includes a coin fragment, cut to make 'small change,' that shows a connection between Abbasid Caliphate and rival Byzantine empire
__ አላህን ፍሪዋ ሴት ታሪክ ክፍል አንድ ____
በበኒ እስራኤል ዘመን የነበረች የአንድ ሰው ሚስት ታሪክ ሲሆን ወደ ሀጅ ለመሄድ
አሰብና የሚወዱትን ባለቤቱን ብቻዋን ስለነበረች አይዞሽ እንዲላትና ችግር
እንዳይደርስባት በቅርብ የነበረው ወንድሙን አደራ በማለት ይሄዳል ።ከቀናት በኃላ
አጅነብይ ነበርና ሰይጣን በዚያም በዚህ ብሎ ያልሆነ ነገር እንዲጠይቃት
ይወሰዉሰዋል።እሱም ስሜቱንና የሰይጣኑን ጉትጐታ መቋቋም አቅቶት የወንድሙን
አደራ በመጣስ ያልሆነ ነገር ሲጠይቃት ሴትዮዋ በሀይመኖቷ ጠንካራ ነበረችና
<<የወንድምህን አደራ አትብላ ከሌባ ጠብቅ ብትባል አንተው ሌባ ትሆናለህ
በማለት ቁርጥ አቋሟን ስትነግረው ፣እንደማትቀመስ ስታስረዳዉ ዝሙት
ፈፅማለች በማለት ክብርሽን በማጉደፍ አዋርድሸለሁ እያለ ለማስፈራራት
ቢሞክርም እሷ ግን የፈለከውን ነገር አድርግ አላህ ምንግዜም ከእኔ ጋር ነው
አለችው ።የፈለገው ነገር ባለመሳካቱ ለግዜው በፊቷ አፍሮ ቢመለስም ሰይጣን
አቅጣጫውን ቀይሮ ላይሆንልህ ነገር ጠይቀህ ቀርቶብህ ቢሆን ይሻልህ ነበር
ወንድምህ ሲመጣ ልትነግርብህ ነው ያንተ ነገር አለቀለት ዋልህ ባይሆን
መፍትሄው ልንገርህ ዝሙት ስትሰራ አገኘኃት በልና ደብድባት፤ህይወቷ
እንዳይተርፍ አድርገህ በመደብደብ ከቤት አዉጥተህ ሌላ ቦታ ለብልግና ሄዳ
ችግር እንደደረሰበት በማስመሰል ሌላ ሰፈር ወስደህ ጠላት ሲለው ምክሩን
በመተግበር እንዳለው ያደርጋል ።ከዚህም በኃላ ከቤት ወጥታ እንደባለገች
በማስወራት የሀሰት ምስክር ሁለት ሰዎችን ቀጥሮ እየወጣች ታድራለች፤ከብዙ
ሰዎች ጋር ስትማግጥ አይተናታል ብለው እንዲመሰክሩ በማድረግ ወንድሙ
ሲመጣ ለማሳመን ይበጀናል ያለዉን መረጃ ሁሉ ይዞ ይጠብቀዋል ።እሷም
ከወደቀችበት መንደር ላይ ስታንቋርር(ስታጣጥር) ያየ ሰው ሁኔታዋ አሳዝኖት
ከወደቀችበት አንስቶ እቤቱ ይወስዳታል ____እንሻ አላህ ክፍል ሁለት ነገ
ይቀጥላል ሼር ይደረግ ።
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን፡ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ
ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-
"እስክታምኑ ድረስ ጀነትን አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ደግሞ
አላመናችሁም፡፡ ታዲያ ከሰራችሁት ሊያዋድዳችሁ የሚችል ነገርን
ልጠቁማችሁን? በመሀከላችሁ ሰላምታን አብዙ"
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 101
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago