ከመጽሐፍት መንደር💠💫

Description
አንብብ አዕምሮህ ልክ አንደባህር ይሰፋል። ወንዞችም ለአንተ መገበር ይጀምራሉ። አንተ ወደ ሰዎች ሳይሆን ሰዎችም ወደአንተ ይመጣሉ። ማንብብ ሙሉ ሰው ያደርጋል!! አንብብ ብታነብ የሚቀርብህ ድንቁርና
🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩
🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨🟨
🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥🟥

ለማንኛውም አስተያየት
@manbabemuluyadergal_bot
We recommend to visit

#ZENBILL_STORE
በኢትዮጲያ ውስጥ ትልቁ የመገበያያ የቴሌግራም መድረክ ነው።

? ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይግዙ!

ካሉበት ሆነው ይዘዙን

Last updated 2 years, 10 months ago

ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል

✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211

💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot

Last updated 8 months, 2 weeks ago

?Quotes

“Life is generally meaningless beyond the choice we have to assign how meaningful it can be. I don’t fear death because I know this and therefore am able to live with peace of mind.”
@Quote_U
...

Last updated 3 years, 8 months ago

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago

ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሀያ

‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡
‹‹ለምን መሰለህ የጠየቅኩህ..?እንዲሁ ሳስበው አንተን ያገባች ሴት በጣም እድለኛ ትመስለኛለች….፡፡››
‹‹ምን አልባት ልትሆን ትችላለች ..እስከአሁን ግን አለገባሁምም አረ እንደውም ፍቅረኛም የለኝም››
ፈገግ አሉ….‹‹ሸክላ ሰሪ በገል ይበላልል›› አሉ…ብዙ ማወቅም እኮ መጥፎ ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹የምትፈልገውን ሁሉ የምታሟላ ሴት ለማግኘት በጣም ይከብድሀላ…ሁሉን ነገር አሟልታ ጥንቅቅ ያለች ሴት አታገኝም..በዛ እርግጠኛ ሆኜ ልነግርህ እችላለው…ግን ምትወድህና ምትወዳት ልጅ ሆና እራሷን ለመለወጥና ለማሻሻል የምትጥር ከሆነ በቂ ነው…አንተ ጎበዝ አንደበተ ርትኡ ባለሞያ ስለሆንክ መስመር ታስይዛታለህ››
እንዴት ብሎ መምከሩን ትቶ ተመካሪ እንደሆነ አልገባውም፡፡‹‹እሺ…የእናንተን ጉዳይ ከዳር ካደረስኩ በኃላ አስብበታለው….ምን አልባት እናንተ ትሆናላችሁ የምትድሩኝ…››
‹‹ለዛውም ድል ባለ ድግስ ነዋ››

‹‹እሺ..አሁን ይበቃናል…የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ወደሳሎን እንሂድ››
‹‹አዎ ..ይበቃናል..ይሄኔ ኃይሌ ብቻውን ደብሮታል››
ፈገግ እለ ….. ከመቀመጫው ተነሳና ወደውጭ መራመድ ጀመረ…ወ.ሮ ስንዱም ተከተሉት፡፡

ከሳምንት በኃላ……..
በቢሾፍቱ ቆይታቸው በባልና ሚስቶቹ መካከል አስገራሚ የሚባል ለውጥ ነው የታየው፡፡ቢያንስ እረስ በርስ በመሀከላቸው ያለ ንግግር የጥሩ ጓደኛሞች መምሰል ከጀመረ ሰነባብቷል…ይሄ ለውጥ ሰለሞንን ይበልጥ እንዲበረታታ እና ሙሉ ኃይሉን ስራው ላይ እንዲያውል አግዞታል፡፡
‹‹እንግዲህ ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው ነገ ወደአዲስአባ እንመለሳለን…ሶስት ቀን እረፍት እንወስድና ምን አልባትም ለመጨረሻ ጊዜ ለሌላ 15 ቀን ወደሌላ መዝናኛ ቦታ እንሄዳለን፡፡በቀጣይ የምንሄድበት ከዚህ የተለየ ነው…ሌሎች ሰዎች ማለቴ ጎብኚዎች የሚኖሩበት ቦታ ነው…እዛ ምንሄደው ነፃ ሆናችሁ እንድትዝናኑ ነው..እኔም አብሬያችሁ ኖራለው ግን ነፃ ናችሁ…እዚህ እንዳለው ብዙ ማዕቀብና እገዳ የለም…ስልካችሁን እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ.ሰሻል ሚዲያ ቴሌቪዝን ማየት ትችላላችሁ …ከሰው መተዋወቅና መገባበዝ ትችላላችሁ..አንድ ማትችሉት ነገር መለያየት ብቻ ነው….ለ15 ቀን የምታደርጉትን ሁሉ አብራችሁ ታደርጋላችሁ..››
‹‹ገባን ..ያልከው 15 ቀን የመጨረሻችን ይመስለኛል››
አዎ እኔም እንደዛ ነው የማስበው..በእውነት እዚህ ባሳለፍነው 15 ቀን ሁለታችሁም ካሰብኩት በላይ ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኃል …እናም ትልቅ ለውጥ እንዳመጣችሁም ይሰማኛል…እናንሰትስ ምን ይሰማችኃል…?አቶ ኃይለልኡል እስኪ ከእርሶ ልጀምር፡፡

‹‹እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ…እስከዛሬ ሚሲቴን ብቻ የምበድል መስሎ ነበር የሚሰማኝ ለካ ልጄንም ራሴንም ጭምር ነበር እያሰቃየው የነበረው….እውነት አንተና ልጄ የእድሜ ልክ ባለውለታዎቼ ናችሁ››
ፊቱን ወደወ.ሮ ስንዱ ዞረና ተመሳሳዩን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
‹‹አዎ…ኃይሌ እንዳለው ደስተኛ ነን…በፊት ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ገዳም ገብቼ መመልኮስ ነበር ምኞቴ ..ምክንያቱም ህይወት አስጠልታኝ ነበር…ቤቴም ኑሮዬም ይቀፈኝ ነበር…ጨለማ የሆነ ሀዘን ውስጥ ገብቼ ነበር..አንድ ያለችኝ አስደሳች ነገር ልጄ ብቼ ነበረች
..እሷም ከጠፋች በኃላ ደግሞ ነገሮች ለእኔ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው…አሁን ግን እንደዛ አይደለም የሚሰማኝ….ደግመኛ እንደመወለድ አይነት የመታደስ ስሜት እየተሰማኝ ነው…የመከራና የሀዘን ቆዳዬን ከላዬ ገፍፌ ጥዬ በአዲስ ተስፋና ፍቅር ተወልጄለሁ..አሁን ቤቴም ባሌም ይናፍቁኛል….ሃይሌን ከዚህ በፊት ለሆነው ሁሉ ይቅር ባዬዋለሁ.. እሱም ይቅር እንደለኝ ገምታለው፡፡››
ኃይለልኡል ተፈናጥረው ከመቀመጫቸው ተነሱና ሚስታቸው ላይ ተጠመጠሙ…ሁለቱም ተቃቅፈው መላቀስ ሲጀምሩ….ሰለሞንንም ስሜታዊ አደረጉት፡፡ተላቀው ወደቦታቸው ለመመለስ..ከ10 ደቂቃ በላይ ፈጅቶባቸዋል፡፡
ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ‹‹ጥሩ እንግዲህ… እዚህ ደረጃ ላይ ከደረስን አንዳንድ አጠቃላይ ስለሆኑ ነገሮች እናውራ፡፡ያው እናንተ በጋብቻ ውስጥ ረጅም እድሜ ስለአሰለፋችሁ ከእኔ የበለጠ ልምድ እንዳላችሁ አውቃለሁ....አሁን የማወራው የምታውቁትን ነገር ነው…ላሳውቃችሁ ሳይሆን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው››
‹‹ጥሩ እየሰማንህ ነው ….ቀጥል››
‹‹እንግዲህ እቤት የባል ብቻ አይደለም፣የሚስትም ብቻ አይደለም፣ እቤት የልጆችም ጭምር ነው።በዚህ ምክንያት ለሁሉም ኑዎሪዎች እኩል ምቹ መሆን አለበት።እናንተ ከአሁን ወዲያ በቤታችሁ የሚዘረጋው ስርአት ህግና የአኗኗር ዘየ..ሶስታችሁን በእኩል ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡ሌላው ንብረታችሁን በተመለከተ የእኔ የሚለውን ቃል ከመጠቀም የእኛ የሚለውን የጋራ ቃል መጠቀም የተሻለ ነው።የእኛ ቲቪ..የእኛ ቤት...የእኛ ጊቢ የእኛ ፋብሪካ፣ብሎ የመናገር ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።እያንዳንድ የቤተሰብ አባል የእዛ ቤተሠብ

የአክሰዬን ባለድርሻ ናቸው።ያንን ደግሞ በተግባርም በስነ-ልቦናም መረጋገጥ አለበት።በቤተሰብ ቢዝነስ ውስጥ ስለሚፈጠር ዋና ዋና ክስተት ስለትርፍም ሆነ ኪሳራ ሁሉም ሰው በተገቢው መጠን መረጃ ሊኖረው ይገባል….ሁሉንም ኃላፊነት አንዱ አካል ብቻ ጠቅልሎ መውሰድ የለበትም…እዚህ ላይ በተለይ አቶ ኃይለልኡል ብዙ ነገር ማስተካከል የሚጠበቅቦት ይመስለኛል››
‹‹ገብቶኛል..እሺ…አስተካክላለው፡፡››

‹‹ሌላውና ወሳኙ … የተለየ ችግር ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስት መኝታ ክፍላቸውንም ሆነ አልጋቸውን መለየት የለበቸውም…በተጨማሪም ባልና ሚስት በምንም አይነት ሁኔታ ወደመኝታቸው ሲሄድ አኩርፈውና በውስጣቸው ተበሳጭተው ወይ ቂም ይዘው መሆን የለበትም።መኝታ ክፍል ለባለትዳሮች እንደቤተመቅደስ ነው መሆን ያለበት ። የሚሳሳሙበት... የሚተቃቀፉበት.... የሚዋደድበትና የሚፋቀሩበት ….ስለጋብቻቸው እና ስለልጆቻቸው ደህንነትና ሰላም የሚማከሩበትና የሚፀልዩበት የገመና መክተቻ ቦታቸው ነው መሆን ያለበት ። ስለዚህ ... ቅያሜያቸውን ሆነ ቅሬታቸውን ሳሎን ጨርሰው ለጭቅጭቃቸው መፍትሄ አበጅተውለት እና ይቅር ተባብለው ነው በሳቅና በፈገግታ ወደመኝታቸው መሄድ ያለባቸው። አዎ ወደመኝታ ክፍላቸው ሲያመሩ በፍፁም ሰላምና ፍቅርና መሆን አለበት...የበለጠ ለመፍቀር...የበለጠ ለማረፍና ..የበለጠ ለመታደስ ።ይሄ ሁለታችሁንም በእኩል ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡››
ሁቱም አንገታቸውን እላይ እታች በማነቃነቅ መስማማታቸውን ገለፁ ‹‹ሌላው በቤት ውስጥ አንደኛው ሌለኛውን ማገልገል አለበት...ማገልገል ማለት በፍፅም ፍቃደኝነትና ፍላጎት አንደኛው ሌላኛውን መርዳት ማለት ነው።ባል የቤቱ ንጉስ ከሆነ ሚስት ደግሞ ንግስት ነች ማለት ነው ልጆች ደግሞ ልኡላን ናቸው።ማንም ከማንም የበለጠ አስፈላጊ አይደለም...ማንም ከሌላኛው ያነሰ አይደለም።ለቤቱ ሙሉነትና ፍፁምነት ሁሉም የየራሱ ኃላፊነትና ድርሻ አለው።በፍቅርና በጋብቻ ህይወት ውስጥ እርስ በርስ ያለ መከባበር በጣም ወሳኝ ነው።አንድ ለሌላዎ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሲኖሩት በትህትና እና ክብር በተሞላ ሁኔታ ጥያቄውን ማቅረብ አለብት።እርስ በርስ ያለ ግንኙነት የማስመስል መሆን የለበትም...እንግዳ ሲኖር የሚደረግ አርቴፊሻል የማስመሰል እንክብክቤ እና አክብሮት

2 months, 2 weeks ago

በነጭ ምዕመናን ታቦቷ ታጀበ
ዲያቆኑ ተነሳ ሊቃችን ወረበ

ጭብጫቦ እልልታው
     ዝማሬው ይበልጣል
ማርያም ማርያም ሲባል
      ስምሽ ይጣፍጣል።

ማርያም

ዮኒ
    ኣታን #yonatoz

5 months, 1 week ago
5 months, 1 week ago

ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)
ምዕራፍ-20
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ

ከምስራቅ ካር ስምምነት ላይ ከደረሱ በኃላ ይገጥመናል ከሉት በላይ በጣም የተወሳሰበው ነገር ነበር የገጠማቸው፡፡በመጀመሪያ የት እንደተወሰዱ ያለማወቃቸው ነበር ከባድ ነገር፡፡ መስታወቱ ደፍን ጥቁር ሆኖ ወደውጭ በማያሳይ መኪና ውስጥ ተከተው…ለአንድ ሰዓት ለበለጠ ጊዜ ሲጓዙ ከቆ በኃላ መኪናዋ ቆመችና ሲወርዱ አምስት የሚሆኑ ባለአምስት ፎቅ ዘመናው ህንፃዎች ያሉበት የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፤ የመረብ ኳስ እና የመሳሰሉት ሜዳዎች ያሉበት ዙሪያውን በደን የተሸፈነ እና ቢያንስ 3 ሜትር ሚሆን ከኮንክሪትና ከብሎኬት የተሰራ አጥር ….በአጥሩ ጫፍ ላይ አደገኛ ሽቦ የተጠመጠመበት በጣም አስፈሪ ድባብ የተላበሰ ግዙፍ ስፍራ ነው፡፡በዛ ላይ  .በተወሰነ ሜትር ርቀት በየሰዓቱ በሚቀያየሩ ቆፍጣና የጥበቃ ወታደሮች የሚታዩበት አስፈሪ ግቢ ውስጥ ነው ይዘዋቸው የገቡት፡፡
ይዞቸው ከመጡት መካከል አንድ ወደአንደኛው ፎቅ ይዟቸው ሄደና ወዳአንድ ቢሮ  አስገባቸውና  ምንነቱን ያለወቁት የሆነ ወረቀት አስፈርሞ በማስረከብ ቀሪውን ያዘና አነሱንም ልክ እንደወረቀቱ እዛው ጥሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ከዛ ከእነሱ ስለሚጠበቀው ነገር፤ ስለዋና ዋና የግቢው ህግ፤ማድረግ ስለሚገባቸው መድረግ ስለሌለባቸው ነገር የአንድ ሰዓት ገለፃ ከተሰጣቸው በኃላ ናኦል ወደ ወንዶች ህንፃ ኑሀሚም ወደ ሴቶች ህንጻ ተወሰድና ከሌላ ከአንድ ሰው ጋር የሚጋሩት የራሳቸው መኝታ ቤት ተሰጣቸው፡፡በዚህ ሁኔታ አዲሱን ህይወታቸውን አህዱ ብለው ጀመሩ፡፡
ወደእዛ ግቢ ገብቶ በቃችሁ ውጡ ከመባሉ በፊት ለመውጣት መሞከር መጨረሻው ሞት ብቻ እንደሆነ ያወቁት ግቢውን በረገጡ በቀናቶች ውስጥ ነበር፡፡እንደተባለውም ስልጠናው የተለየ እና በእነሱ ዕድሜ ደረጃ ላለ ወጣት ይቅርና ለሙሉ ወጣትም የማይሞከር ነበር….ግን ስልጠናውን በቃኝ አልቻልኩም ማለት እራስን ለሞት አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ሌላ የሚያሰገኘው ነገር የለም፡፡ስለዚህ የማይቻለን መቻል የግዳቸው ነበር፡፡ወታደራዊ ስልጠናው ብቻ ሳይሆን መደበኛ ትምህርቱ እራሱ በጣም ጥብቅ በሆነ ስነምግባር የሚሰጥ ነበር፡፡አንድ ልጅ እዛ ግቢ ሲገባ ሶስተኛ ክፍልም ይሁን ስድስታኛ ክፍል የ5 አመቱን የሥልጠና ጊዜ ጨርሷ ከዛ ጊቢ ተመርቆ ሲወጣ የ12ተኛ ክፍል ማትሪክ ወስዶ መሆን አለበት ፡፡በዛ የተነሳ በአመት ሁለት ክፍሎችን መማር የግድ ይላል፡፡ደግነቱ የትምህርት አሰጣጡ እጅግ ዘመናዊና ሁሉ ነገር የተሞላለት አስተማሪዎቹ ልክ እንደእነሱ በልዩ ችሎታቸውና ብቃታቸው የተመረጡ ጂኒዬሶችና ነገሮችን በቀላሉ በማስረዳት ችሎታቸው የተመሰከረላቸውና ስለሆኑ ጫናዎቹ የሚጠበቀውን ያህል እንዳይከብዳቸው ያግዛቸዋል፡፡በዛ ላይ እያንዳንዱ ሰልጣኝ እንደ ዝንባሌው በተለያዩ የስፖርት አይነቶቹ መሳተፍና የቋንቋ ስልጠናውም በተመሳሳይ ሁኔታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡በተለይ ከውጭ ቋንቋ እንግሊዘኛና አረብኛ ሲማሩ ከሀገር ውስጥ እንደየ ምርጫቸው ከሚያውቁት በተጨማሪ ሁለት ቋንቋ እንዲማሩ ይደረጋል፡፡
ይሄ በሀገሪቱ የደህነነት መስሪያ ቤት በልዩ ፕሮጀክት እቅድ ተነድፎለት በጀት ተይዞለት እየተካሄደው ያለው ልዩ ስልጠና ለመጀመሪያው አንድ አመት ለሁሉም ተማሪዎች በጣም ከባድ አካልንም መንፈስንም በእኩል ደረጃ የሚያዝል ነበር፡፡ለዚህም ማሳያ በተቀመጠው ክራይቴሪያ ከተለያ ቦታ በተለያየ ዘዴ ተሰብስበው ከገቡ 80 ተማሪዎች መካከል በአመቱ መጨረሻ 17 ቱ መቋቋም አቅቶቸው ሞተው ነበረ፡፡ናኦልም እህቱ ከጎኑ ኖራ በየጊዜው ብርታት ባትሰጠው ኖሮ ከሞቾቹ መካከል መሰለፉ አይቀርም ነበር፡፡ለዚህ ነው መጀመሪያውኑ ሰልጣኞቹ ሲመለመሉ  አስፈላጊው ክራይቴሪያ ዘመድና ጠያቂ የሌላቸው እንዲሆኑ የሚፈለገው፡፡
ኑሀሚ ግን ከሶስት ወር በላይ አልተቸገረችም ነበር….ካዛ በኃላ በየዲሲፕሊኑ ከፉክከሩ መድረክ ከፊት የምትሰለፍ፤ ለሁሉም ሰልጣኞች ምሳሌና ብርታት ሆና ነበረ የቀጠለችው፡፡አመስት አመቱ አልቆ ሲመረቁ ከአንድ ወንድ ጋር በእኩል ነጥብ አንደኛ በመሆን የወርቅ ዋናጫውን ተቀበለች፡፡ወንድሟ ናኦል 53 ተኛ ወጥቶ ተመረቀ፡፡እና 5 አመት ከኖሩበት ከእዛ ማሳልጠኛ ውስጥ ልክ እንደአገባባቸው በጨለማ መኪና ውስጥ ተሳፍረው እንዲወጡ ተደረገ.፡፡ከሰዕታት ጉዞ በኃላ ግን ልክ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናዋ ቆማ ስታወርዳቸው የተቀበለቻቸው ምስራቅ ነበረች፡፡
በወቅቱ ሁለቱም ያለልዩነት ነበር የተጠመጠሙባት፡፡እሷም በደስታ እና በከፍተኛ እርካታ ነበር የተቀበለቻቸው፡፡ስታያቸው ከበፊቱ በጣም አድገው ሙሉ ወጣት ሆነው ስላየቻቸው እጅግ ተደስታ ነበር፡፡ከዛ መኪና ውስጥ አስገባቻቸውና ቀጥታ ወደወላጆቻቸው ቤት ነበር የወሰደቻቸው፡፡ከመኪና ስትወርድ አብረዋት ወረዱ…ሰፈሩን ሲያዩና የቆሙበትን ሲረዳ ሁለቱም ደንዝዘው ነበር..ቀጥታ ሁለቱንም መሀከላቸው ገባችና ግራና ቀኝ እጃቸውን ይዛ ወደ ግቢው በራፍ ይዛቸው ሄደች…ሁለቱም በዝምታና በድንዛዜ ተከተሏት..ካዛ አንኳኩታ ሰውዬው ሲወጣ የሆነ ነገር ትለዋለች ብለው ሲጠብቁ..ኪሶ ገባችና ቁልፍ በማውጣት..‹‹ይሄው ቃል በገባሁት መሰረት የወላጆቻችሁ ቤት ቁልፍ ››ብላ ኑሀሚ እጅ ላይ አስቀመጠችላት፡፡ኑሀሚ አላመነችም፡፡ በድንዛዛ እጇን አንቀሳቀሰችና ቁልፉን ከፈተች.. አሸከረከረች… ተከፈተ.. ተንደርድራ ወደውስጥ ገባች፡፡ ወንድሟም ተከተላት፡፡ በረንዳው ላይ እስኪደርሱ አልቆሙም…የሳሎኑን በራፍ ስትገፋው ተዘግቷል፡፡ እጆ ላይ ባለው ቁልፍ ሞከረች ፤ተከፈተ……፡፡ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እነሱ ምንም ሳይለፉና ሳይጥሩ ነበር በምስራቅና በደህንነት መስሪያ ቤቱ ጥረት የወላጆቻቸው ቤት የተረከቡት፡፡
ከዛ ሁለት ወር ሰይቆይ ኑሀሚ በስልጠናዋ ባስመዘገበችው ብቃት ምክንያት ለተጨማሪ የሶስት አመት ስልጠና ወደ ራሺያ ተላከች፡፡
ናኦል ደግሞ ቤተሰቦቹ ቤት እየኖረ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ ትምህርቱን እየተማረ በተደራቢነት ከምስራቅ  በሚሰጠው መመሪያና ተልዕኮ መሰረት የፊልድ ስረዎችን እንዲላመድ ተደረገ፡፡
ናኦል ከትዝታው ባኖ ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ሰዓት ሲያይ በጣም ነበር የተገረመው….ከለሊቱ10፡20 ሆኗል …ላለፉት አራት ሰዓት በላይ ባለፈ ታሪኩ ውስጥ ሰምጦ በትዝታ ሲዋልል ነበረ፡፡አካሉም ብቻ ሳይሆን አእምሮውም ዝሏ ነበር ፡፡
/////
ኮሎምቢያ/አሞዞን ደን ውስጥ
ካርሎስ ከጥልቅ እንቅልፉ ባነነ እና አይኖቹን ገለጠ፡፡በድቅድቁ ጨለማ በአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ግዙፍ ዛፍ ላይ ቆንጆና ወጣት ልጅ ደረቱ ላይ ተኝታ ነው ያገኘው…ያለበትን ሁኔታ አሰበና ፈገግ አለ፡፡ቀስ ብሎ ከደረቱ ላይ ቀና አድርጎ ሲያስነሳት ነበር ከገባችበት ጥልቅ ትዝታ የነቃችው፡፡
‹‹ወይ ሀሳቤን ጥዬ ተንፈላሰስኩብህ አይደል?››አለችው፡፡

‹‹አይ የተፈጥሮ ጥሪ አጨናንቆኝ ነው››

‹‹ማለት?››

‹‹ሽንቴን…ኩላሊቴ ልትፈነዳ ነው››

‹‹እ ..ነው..ወርደህ ልትሸና ነው?፡፡

‹‹አይ ምን አስወረደኝ..ብወርድ ሽንት ቤት የለ ..ሜዳ ላይ ነው የምሸናው፡፡ ማይደብርሽ ከሆነ እዚሁ ሆኜ ልለቀው ነው፡፡››
በጨለማ ውስጥ የማይታየውን ፈገግታዋን እየለገሰችው‹‹ምን ቸገረኝ..ልቀቀው.››አለችው

‹‹አመሰግናለው ››አለና ቆመ፡፡ ዚፕን መክፈት ሲጀመር.

‹‹እንዴ…››ብላ አጉረመረመች

‹‹ምነው?››

‹‹ቢያንስ ፊትህን ወደእዛ አዙር እንጂ››

5 months, 1 week ago
8 months, 1 week ago
8 months, 1 week ago
8 months, 1 week ago
8 months, 1 week ago

እኔ ብቻ መስሎኝ እንደዛ ምወደው
ካላየሁት ብዬ የምጨናነቀው
በጠዋት በማታ ሁሌ ምናፍቀው

ዛሬ እዛነው ሲሉ ልሄድ የም መኘው
ዛሬ እዚህ ነው ሲሉ የምጠባ በቀው
እንደዚ ምወደው እኔ ምን ሆኜ ነው??
እኔ ብቻ መስሎኝ ይሁንልኝ ያልኩት
ለካስ ሁሉም ሰው ነው እንደኔ ሚወዱት
ቢሆንልኝ ብለው ሁልጊዜ ሚ መኙት
ለብቻዬ ላደርግ እንዲያ የደከምኩት
በጣም ትክክል ነኝ መውደ ዴን ወደድኩት
ለካስ እልፍ ሰው ነው --ኑሮን -የሚወዱት??

ኑሮ ተወደደደደ.......
ለካስ
?

We recommend to visit

#ZENBILL_STORE
በኢትዮጲያ ውስጥ ትልቁ የመገበያያ የቴሌግራም መድረክ ነው።

? ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ይግዙ!

ካሉበት ሆነው ይዘዙን

Last updated 2 years, 10 months ago

ማራኪ ცЯムŋの የጫማ መሸጫ ቻናል

✔ማራኪ ብራንድ የፈለጉትን ጫማ በፈለጉት ሳይዝ እና ጥራት እናቀርባለን!
With free delivery
🔰Contact me
👉 @Maraki2211 or Call 0913321831
Admin
@maraki2211

💯Spammed users⚠
@Marakibrand2bot

Last updated 8 months, 2 weeks ago

?Quotes

“Life is generally meaningless beyond the choice we have to assign how meaningful it can be. I don’t fear death because I know this and therefore am able to live with peace of mind.”
@Quote_U
...

Last updated 3 years, 8 months ago