Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

AL-RISAALA JAMA'AA

Description
ጌታችን ሆይ!_

አንተን ከሚፈሩት
አንተን ከሚገዙት
አንተን ከማያምፁት
ጥንቁቅ ባሮችህ አድርገን
በእዝነትህም ጀነትን ወፍቀን🤲!

𝐉𝐨𝐢𝐧 ➪ https://t.me/alrisala02
𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 ➪ https://t.me/alrisala02
Advertising
We recommend to visit

Jeet ek Nasha hai aur is Nashe ki Factory ka mai ek lauta Baadshah hoon !

My Telegram Channel Link
https://t.me/+S9lLIcfDkRrhG-VZ

For Any Query Contact
My Username - @RehanBaadshah

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Youtube Irraattis nu Argattu

https://www.youtube.com/c/KaachuuEntertainment

Yaada qabdan kamiifuu bot kana fayyadamaa
@Walaloo_bot

Last updated 1 month, 3 weeks ago

𝗝𝗶𝗿𝗲𝗲𝗻𝘆𝗮 𝗺𝗶𝗹𝗸𝗮𝗮'𝗮𝗮 𝗷𝗶𝗿𝗮𝗮𝗰𝗵𝘂𝘂𝗳 𝗸𝗮𝗸𝗮'𝘂𝘂𝗺𝘀𝗮 𝗬𝗔𝗔𝗗𝗔𝗔 𝗳𝗶 𝗗𝗔𝗡𝗗𝗘𝗘𝗧𝗧𝗜𝗜 𝗱𝗵𝗼𝗸𝗮𝘁𝗮𝗮 𝗼𝗳𝗶𝗶𝘁𝘁𝗶 𝗳𝗮𝘆𝘆𝗮𝗱𝗮𝗺𝘂𝘂𝗳 𝗾𝗼𝗽𝗵𝗶𝗶 𝘁𝗮'𝘂𝘂 𝗯𝗮𝗿𝗯𝗮𝗮𝗰𝗵𝗶𝘀𝗮!
💥 @Oromoo_Inspire_YaadaafBot 💥

Last updated 3 weeks, 2 days ago

3 weeks, 3 days ago

ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️#سنن_يوم_الجمعة

➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ 
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ

t.me/alrisala02

3 weeks, 4 days ago

ከቁርኣን መራቅ ምን ማለት ነው?
~

{وَقَالَ الرَّسُولُ يَا رَبِّ إِنَّ قَوْمِي اتَّخَذُوا هَٰذَا الْقُرْآنَ مَهْجُورًا} [الفرقان : 30]

"መልዕክተኛውም ጌታየ ሆይ ሕዝቦቸ ይህንን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት አለ" አል–ፉርቃን 30

ቁርአንን መራቅ ከሚገለፅባቸው መካከል፤
1/ በቁርአን ከማመን መራቅ
2/ በቁርአን አምኖ ግን እምነትን አለመተግበር
3/ በቁርአን አለመዳኘት
4/ ከማስተንተን እና ከማወቅ መራቅ
5/ ከልብ በሽታዎች በቁርአን አለመታከም

እነዚህ ነገሮች በሙሉ ቁርአንን ከመራቅ (ሀጅር) ይመደባሉ! ደረጃው ቢለያይም ሁሉም ከቁርአን መራቅና ማፈንገጥ ናቸው ። ከቁርአን የራቀ  አላህ የተጨናነቀ ኑሮን እንደሚሰጠውና በዕለተ ትንሣኤ እውር አድርጎ እንደሚቀሰቅሰው ገልፆልናል!!

አላህ ይጠብቀን!!

https://t.me/alrisala02

4 weeks ago

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ لَهُمۡ جَنَّٰتُ ٱلنَّعِيمِ(8)

"እነዚያ ያመኑና መልካሞችንም የሠሩ ለእነርሱ የጸጋ ገነቶች አሏቸው!!"

Surah Luqman; 8

t.me/alrisala02

2 months, 3 weeks ago

*😣*:ማንኛዉም መከራ በዉስጡ መልካም ነገር ይዟል። ወይ ብርታት ይሠጥሃል ፣ ወይ ልምድ ያወርስሃል ፣ ወይ ዱዓ ያስለምድሃል ፣ ወይ ዕውቀት ይገልጥልሃል። ሸይጧን ግን ይህን ሁሉ የመከራን በጎ ክፍል ይደብቅና ጨለማዉን ጎን ያሳይሃል። በጨለማ ተደብቀው የሚመጡ ብርሃን የየያዙ መከራዎች አሉ። አላህ የእዝነት ብርሃኑን ያሳየን።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗 @alrisala02 💌**

2 months, 4 weeks ago

መጣልን ረመዳን🌙🌙🌙💫

ተናፋቂዋ ወር የአመታት ወር ንጉስ፣
ወራትን አክላ በፍቅር ምታነግስ፣
እቺው መጣችልን ከራህመቱ ልታነግስ፣
"' "

ተራዊው ተሀጅዱ የወራቶች ንፍቅታ፣
የመተሳስብ እዝነት እርህራሄ ሲበረታ፣
የቁርዐን ሀሴት የውዴታ ልኬት፣
ድባቡ መጣልን ይዞ የመድመቂያ ቀናት፣
ይሄው ደረሰልን ጊዜያትን ጠብቆ፣
ምስጋና ይገባው ለአላህ ብቻ ልቆ፣
"" ""

በ ሀያት ዩሱፍ

2 months, 4 weeks ago

*🪴「 እንትከል 」🌱
▭▬▭▬▭▬▭▬▭
*:እስልምና እንዲህ ሰፍቶ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ላይ  ከመድረሱ በፊት የመጀመሪያዎቹ አማኞች ዉድ ዋጋ ከፍለውበታል። ዲናቸው ነፃነት አግኝቶ ፣ አድጎና አብቦ ፣ ማየት ይፈልጉ ነበር - ግና አልታደሉም።

🪴:ቆራጧ ሱመያ ፣ ብርቱው ያሲር ፣ ዉቡ ሙስዐብ እስልምና በሁለት እግሩ ቀና ብለው ሲሄድ ለመመልከት አልበቁም - ሞት ቀደማቸው።

🪴:ሐምዛ ኢብኑ ዐብዱልሙጦሊብ ፣ ዐብደላህ ኢብኑ ጀሕሽ ፣ ሰዕድ ኢብኑ ረቢዕ ፣ ዐምር ኢብኑ አልጀሙሕ ፣ ሰዕድ ኢብኑ ሙዓዝ ... በሐያታቸው የእስልምናን ከፍታ ማየት ይፈልጉ ነበር - አልደረሱበትም።

🪴:ከፊሎች አማኞች በመካ በደረሰባቸው ስቃይ ሲሞቱ ፣ ሌሎች በስደትና በጦርነት ተንገላተው አለፉ። አንድም ቀን የዱንያን ጥፍጥና ሳይቀምሱ ፣ አንድም ቀን ጠግበው ሳይበሉ ... ምድርን ተሰናበቱ። ትልቅ መስዋዕትነት ከከፈሉት መካከል ብዙዎቹ ፦

🌿:የኻሊድን የድል ዉሎዎች አይተው አልፈነደቁም ࿐

🌿:የዑመርን ሰፋፊ የበላይነቶች ተመልክተው አልረኩም ࿐

🌿:የዑመር ዐብዱልዐዚዝን ዘመን ጥጋብ አላዩም ࿐

🌿:ሰዕድ ቃድሲያ ላይ ተክቢር ሲል ࿐

🌿:ሪብዒይ ፋርስ ላይ ሩስቱምን ጥሎ ሲንጎማለል ࿐

🌿:ሃሩን አርረሺድ ዝናብ ሆይ የትም ዝነቢ ከግዛቴ ዉጭ አትዘንቢም ብሎ ሲመፃደቅ ࿐

🌿:አቡ አዩብ አልአንሷሪ ቆጵሮስን ሲሻገር ࿐

🌿:ዐምር ኢብኑ አልዓስ የፈርዖንን ምድር ሲያስገብር ࿐

🌿:አቡ ዑበይዳ የሻምን አገር ሲቆጣጠር ࿐

🌿:ሙሐመድ አልፋቲሕ ኮንስታንቲኖፕልን ሲያንኮታኩት ࿐

🌿:ጣሪቅ ስፔን ምድር ሲዘልቅ ࿐

🌤:ወሬውን ያደረሣቸው የለም። ለማየትም ለመስማትም አልበቁም።እነርሱ የሰሙት ነገር ቢኖር "ይህ ዲን ፀሐይ የደረሠችበት የምድር ክፍል ሁሉ ይደርሳል።" የሚለውን ነብያዊ ቃልኪዳን #ብቻ ነበር።

✑ :እነርሱ ሰሙ ፣ እኛ አየን።
✑ :እነርሱ መንገዱን ጀመሩ ፤ እኛ ቀጠልን።
✑ :እነርሱ የዲንን ችግኝ ተከሉ ፤ እኛ ቀጠፍን።

🌻:አሁንም የኛ ድርሻ መሆን ያለበት ዉጤቱን አየን አላየን #መትከል ነው ፣ ፍሬውን ቀጠፍን አልቀጠፍን በመልካም ነገር ወደፊት መቀጠል ነው። ሰብሉ ደረሰ አልደረሰ በጎ ነገር መበተን ነው።

📜:#ቀደምቶች ስለዘሩ እኛ በላን። እኛ የዘራነውን ደግሞ ከኛ በኋላ የሚመጣው ትውልድ ይበላዋል።
ስለሆነም ከሰውም ፣ ከእህልም ፣ ከንግግርም ፣ ከተክልም መልካምን ነገር ሁሉ እንተክላለን ፣ ተንከባክበንም እናሳድጋለን።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 🌻
┊  ✿ 🍃
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩• @alrisala02┣━━━╗ 🌻 ╔━━━━━⎙**

3 months ago

*🪴「 በርግጥ ዳኑ . . . 」📖
▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬
📌:እነማን ናቸው #የዳኑት*? አላህ ﷻ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ይገልፃቸዋል ࿐

🔸:قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ

🔹:ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡

🔸:الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ

🔹:እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡

🔸:وَالَّذِينَ هُمْ عَنِ اللَّغْوِ مُعْرِضُونَ

🔹:እነዚያም እነርሱ ከውድቅ ንግግር ራቂዎች፡፡

🔸:وَالَّذِينَ هُمْ لِلزَّكَاةِ فَاعِلُونَ

🔹:እነዚያም እነርሱ ዘካን ሰጭዎች፡፡

🔸:وَالَّذِينَ هُمْ لِفُرُوجِهِمْ حَافِظُونَ

🔹:እነዚያም እነርሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት (አገኙ)፡፡

📕 [ አል - ሙዕሚኑን 1- 5 ] 📕

━━━━━ • ஜ • 📝 • ஜ • ━━━━━

¹:በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች ༻

²:ከውድቅ ንግግር ራቂዎች ༻

³:ዘካን ሰጭዎች ༻

⁴:ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች የሆኑት ༻ በርግጥ #ዳኑ ይለናል አላህ (ሱብሃነሁ ወተዐላ)።
┊  ┊  ┊  ┊
┊  ┊  ┊  ✿
┊  ┊  ❀ 📝
┊  ✿ 📌
                               
╠═══ •『 ﷽ 』• ═══╣
┣𝐆𝐫𝐨𝐮𝐩• @alrisala02┣━━━╗ 📝 ╔━━━━⎙
┣**

3 months ago

¸.📮¸.💌**.¸

:የዱንያን ጭንቀት አትሸከም ዱንያ ያአላህ ነች ৲

:ስለሪዝቅህም አይጭነቅህ ሪዝቅም ከአላህ ነው ৲

:ወደፊት የሚያጋጥምህን ችግር አታስብ በአላህ እጅነው ያለው ৲

:ስለ አንድ ሀሳብ ብቻ ተጨነቅ አላህን እንዴት ማስደሰት እንደምትችል : አላህን ካስደሰትክ ተደስቶብህ ያስደስትሀል መብቃቂያ ሆኖህ የደስታን ሀብት ይሰጥሀል ৲

:ልብህ በደማበት የሂወት ችግር ተስፋ አቱቅረጥ ৲

:ወደ አላህ ተጣራ ወደ ኸይር ቀይርልኝ ብለህ ৲

:ሀዘን በስግደት ይጠፋል ৲

:ደስታ በዱአ ይመጣል ৲

╭┈─────── ೄ🌻ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤ᢀ @alrisala02 💌**

3 months, 1 week ago

**:ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው። መሥራት ባትችሉ አመላክቱ ፣ መፃፍ ባትችሉ ሌሎች የፃፉትን አጋሩ።

↬ዱንያ ላይ የምንቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። ምድር ላይ እንደሁለተኛ ዕድሜ ሆኖ የሚያገለግለን ዛሬ እዚህ የምንጽፈው ነገር ነው። ከሶላታችን ፣ ከፆማችን ምንም ምንዳ ላይኖረን ይችላል። መልካም ነገሮችን ማጋራት ወደ አኺራችን ከምናስቀድማቸው ጠቃሚ ስንቆች መካከል አንዱ ነው። ብልህ እንሁን። አላህ ያፅናን።

► ዓለማዊ ጥቅም አለው ብዬ አልወተዉታችሁም፣ በስነልቦናም ሆነ በዲኑ ጉዳይ ሊጠቀምበት የሚችል ሰው ሊኖር ይችላልና ይህን ቻናል አጋሩት።

╭┈─────── ೄ🌹ྀ࿐ ˊˎ-

╰┈➤🌗 @alrisala02 💌**

We recommend to visit

Jeet ek Nasha hai aur is Nashe ki Factory ka mai ek lauta Baadshah hoon !

My Telegram Channel Link
https://t.me/+S9lLIcfDkRrhG-VZ

For Any Query Contact
My Username - @RehanBaadshah

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Youtube Irraattis nu Argattu

https://www.youtube.com/c/KaachuuEntertainment

Yaada qabdan kamiifuu bot kana fayyadamaa
@Walaloo_bot

Last updated 1 month, 3 weeks ago

𝗝𝗶𝗿𝗲𝗲𝗻𝘆𝗮 𝗺𝗶𝗹𝗸𝗮𝗮'𝗮𝗮 𝗷𝗶𝗿𝗮𝗮𝗰𝗵𝘂𝘂𝗳 𝗸𝗮𝗸𝗮'𝘂𝘂𝗺𝘀𝗮 𝗬𝗔𝗔𝗗𝗔𝗔 𝗳𝗶 𝗗𝗔𝗡𝗗𝗘𝗘𝗧𝗧𝗜𝗜 𝗱𝗵𝗼𝗸𝗮𝘁𝗮𝗮 𝗼𝗳𝗶𝗶𝘁𝘁𝗶 𝗳𝗮𝘆𝘆𝗮𝗱𝗮𝗺𝘂𝘂𝗳 𝗾𝗼𝗽𝗵𝗶𝗶 𝘁𝗮'𝘂𝘂 𝗯𝗮𝗿𝗯𝗮𝗮𝗰𝗵𝗶𝘀𝗮!
💥 @Oromoo_Inspire_YaadaafBot 💥

Last updated 3 weeks, 2 days ago