ኦርቶዶክሳዊነት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Description
እዚህ Channel ላይ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት ፣መዝሙር ፣ኬነጥበቦች እና መፅሕፍት ይለቀቁበታል
"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"


ቅዱስ ኤፍሬም
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

6 дней, 2 часа назад
6 дней, 8 часов назад

†                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[            ክፍል  አርባ አምስት           ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ 🕊   የቅዱስ መቃርዮስ ዕረፍት  🕊 ]

🕊      

ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ ..... !       

❝ ይህ ቅዱስ እንደ ልማዱ በመሬት ላይ ወድቆ ከደዌው ጽናት የተነሣ መነሣት የማይችል ሆነ ፤ ሰውነቱም እንደ እሳት የሚያቃጥል ሆነ፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በታዩት በስምንተኛው ሌሊት ፣ ይኸውም በመጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከእርሱ የነበረ ኪሩባዊ ከቅዱሳን አባቶች ማኅበር ጋር ሆኖ ወደ እርሱ መጥቶ ፦ “እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን እየጠበቁህ ነውና ወደ እኛ ና” አለው፡፡ ያን ጊዜ ኣባታችን ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ በማለት ጮኸ ፦ “አቤቱ ነፍሴ የምትወድህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ ነፍሴን ወደ አንተ ተቀበል፡፡" ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ፡፡

እንደ ወትሮው ይመክራቸውና የሚያጸናቸውን መንፈሳዊ ነገር ይነግራቸው ስለ ነበር ሕማሙ ቢያደክመውም ብዙዎችም ዕረፍቱ ያን ጊዜ መሆኑን አላወቁም ነበርና ወደ እርሱ አልመጡም ነበር፡፡ በተራራው በአራቱ ገዳማት ውስጥ የነበሩት መነኰሳት ሁሉ በሰሙ ጊዜ እያለቀሱና ልባቸው አዝኖ ሁሉም ተሰበሰቡ፡፡ ሁሉም ከእርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ አውቀዋልና ፣ እግዚአብሔርን መፍራትንና መልካም ምግባርን ከእርሱ ከሕይወቱ በተግባር ተምረዋልና ፣ የሰይጣናትን ኃይል ይቃወሙና በሰልፍ የጸኑ ቀዋምያን እንዲሆኑ የተጋድሎን ፈሊጥ አስተምሯቸዋልና ፣ በማይነዋወጽ ጽኑ መሠረት ላይ አንጾዋቸዋልና፡፡

ሌሎችም ሁሉ ማረፉን በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ስለ መለየቱ በታላቅ ኃዘን ሆነው ከየበአታቸው እየወጡ መጡ:: መነኰሳትም መጥተው የከበረ ሰውነቱን አወጡት፡፡ ከዚያ በኋላ አባ እንጦንዮስንና የቅዱሳንን አንድነት ማኅበር ፣ ሰማያውያን የሆኑ የመላእክትንም ሠራዊት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን እስከሚሰጥ ድረስ ያዩ ነበር፡፡

የቅዱስ መቃርስ ነፍስ ከሥጋው በተለየች ጊዜ ከፀሐይ ብርሃን ሰባት እጅ እያበራች ፍጹም ብርህት ሆና ከሰማይ የወረደው ኪሩባዊ በእጁ እንደ ተቀበላትና ከኪሩባዊውም ጋር ማንም ማን ክብራቸውንና ግርማቸውን ሊተረጉመው በማይችል በብዙ ሰማያውያን ኃይላት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ እንዳዩ ፣ ሰይጣናትንም ደቀ መዝሙሩ አባ በብኑዳ የናቅዮስ ኤጲስ ቆጶስ ፣ አባ ሰራጵዮን እና በዚያ የነበሩ ብዙ ቅዱሳን አረጋውያን እንደ ሰሟቸው ምስክር ሆኑ፡፡

ሰይጣናት ነፍሱን እንዲህ ሆና ባዩዋት ጊዜ እየተከተሉ ፦ “መቃርዮስ ሆይ ፣ ከእጃችን ዳንክ እመለጥክም” እያሉ ይጮኹ ጀመር፡፡ እርሱም ፦ “ገና አላመለጥኩም” አላቸው፡፡ አየር ላይ በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት አሁንም እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ሄድክ እኮ” አሉት፡፡ እርሱም ፦ “የለም ገና ነኝ” አላቸው፡፡ አንድ እግሩ ወደ ውስጠኛው በር በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ገባህ” አሉት ፤ እርሱም ፦ “ገና ነኝ” አላቸው፡፡ በደረሰ ጊዜ እና ሁለት እግሩን ወደ ውስጥ ባስገባ ጊዜ ፈጽመው እያለቀሱ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ደረስክ እኮ” እያሉ አብዝተው ጮኹ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ ሲል አሰምቶ ተናገረ ፦

“የአምላኬና የመድኃኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ተቀብያለሁ ፣ እኔም ከእጃችሁና ሥፍር ቁጥር ከሌለው ወጥመዳችሁ ያዳነኝን ፣ በምሕረቱ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ የጠበቀኝን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰግነዋለሁ::” ያን ጊዜ ኪሩባዊው ከእነርሱ ሰወረው ፣  ከዚያም በፍጹም ልቡ ወደ ወደደው ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅደረ ስብሐት ገባ፡፡

ይህ በእውነት ቅዱስ የሆነ አባትም ከመልካም ነገር ሁሉ ወደ ተመላች ሰማያዊ ማደሪያ ሄደ፡፡ በበአታት ሁሉ እየዞሩ የቅዱሱን ዕረፍት በነገሯቸው ጊዜ የሁላቸው አጽናኝና መካሪ ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ምግብን የሚመግባቸው መጋቢያቸው የነበረው አባታቸው ከእነርሱ ዘንድ በመታጣቱ ሁሉም አረጋውያን እያዘኑና እያለቀሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጡ፡፡ እያለቀሱ ከቅዱሱ ሥጋ ይባረኩ ዘንድና ይስሙት ዘንድ ዙሪያውን ቆሙ:: የሥጋ በሽታ የነበረባቸው ሁሉ እግዚአብሔር ያን ጊዜ ፈውስን ሰጣቸውና ዳኑ:: ስለ እርሱም ብዙ ጸሎትን አደረሱ ፣ ቅዳሴ ቀድሰውም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበሉ፡፡ ሥጋውንም በቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ባነጸው በአት ውስጥ ቀበሩት ፤ ከእርሱ ስለ መለየታቸው በታላቅ ሐዘን ሆነው ወደየ በአታቸው ተመለሱ፡፡ የዕረፍቱ ቀንም መጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ነው:: ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

6 дней, 16 часов назад
3 месяца назад

?ከፀሎት አይነቶች ውስጥ የሚካተተው የቱ ነው?

3 месяца назад

ሌሎች የእንቁጣጣሽ እና የመስቀል መዝሙሮችን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forward በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን

??አበባዮሽ??

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(፪)?
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን?
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ዘመን መጣ ብለን
??
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ባልንጀሮቼ - - - ለምለም
ግቡ በተራ - - - ለምለም?
በእግዚአብሔር መቅደስ - - - ለምለም
በዚያች ተራራ - - - ለምለም
እንድታደንቁ - - - ለምለም
የአምላክን ሥራ - - - ለምለም
ህይወት ያገኛል - - - ለምለም
እርሱን የጠራ - - - ለምለም

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)?

አበባዮሽ - - - ለምለም (፪)
ክረምት አለፈ - - -ለምለም
ጨለማው ጠፋ- - - ለምለም
የመስቀሉ ቃል - - -ለምለም
ሆነልን ደስታ - - -ለምለም
እናገልግለው - - - ለምለም
ቤቱ ገብተን - - - ለምለም
ትንሽ ትልቁ - - - ለምለም
ተሰልፈን - - - ለምለም?

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)?

አበባዮሽ - - -ለምለም(፪)
ያንን ኩነኔ - - - ለምለም
ዘመነ ፍዳ - - - ለምለም
የሞቱ በራፍ - - - ለምለም
ያ ምድረበዳ - - - ለምለም
ልክ አንደ ክረምት - - - ለምለም
ሄደ ተገፎ - - - ለምለም
ፀሐይ ወጣልን - - - ለምለም
ጨለማው አልፎ - - - ለምለም?

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)?

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው መስከረም - - - ለምለም
ይኸው ፀሐይ - - - ለምለም
ንጉሡ ወርዶ - - - ለምለም
ከላይ ሰማይ - - -ለምለም?
አውደ ዓመት ሆነ - - - ለምለም
ደስታ ሰላም - - - ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ - - - ለምለም
በአርያም? - - - ለምለም

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)?

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው አበባ - - - ለምለም
ለምለም ቄጤማ? - - - ለምለም
አዲሱ ዘመን - - - ለምለም
አምጥቷልና - - - ለምለም
በሩን ክፈቱ - - - ለምለም
መኳንንቶቹ - - - ለምለም
የክብር ንጉሥ - - - ለምለም
ይግባ ቤታችሁ - - - ለምለም

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪) ?

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ቤታችሁ ይሙላ - - - ለምለም
ሰላም ደስታ - - - ለምለም?
ሰጥቷችሁ እርሱ - - - ለምለም
የሁሉ ጌታ - - - ለምለም
ከዘመን ዘመን - - - ለምለም
ያሸጋግራችሁ - - - ለምለም?
የሽበትን ዘር - - - ለምለም
ይሸልማችሁ - - - ለምለም

?አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ?

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ?

አብዬ ኧኸ አባብዬ
ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ?
ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት
አደረሰዎት ብዬ?
?
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው?
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው?

መዝሙር
?በዘማሪያን?
ወርቅነሽ ተፈራና ፅጌሬዳ ጥላሁን

<< በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል >>
መዝ ፷፭፥፲፩?

3 месяца назад
3 месяца, 1 неделя назад
3 месяца, 1 неделя назад

?

† እንኳን ለቅዱሳን ፯ቱ ደቂቅ እና ለአቡነ ሰላማ ካልዕ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †

[ † ? ቅዱሳን ፯ ቱ ደቂቅ ? † ]

† እነዚህ ፯ ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: ፯ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ፪ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::

በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::

ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ ለጣዖትም ያልሰገደ ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ እጅ እግሩ ለእስር ደረቱ ለጦር አንገቱ ለሰይፍ ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::

የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ ፯ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::

ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ወጣ::

ከመውጣቱ በፊት ግን ፯ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::

ዓለምን ንቀው ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር [በጐች አሉት] ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::

አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ፯ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::

ያ የበጐች ባለቤት [ወታደር] ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::

ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ፫፻፸፪ ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::

በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን ፬፻ ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::

በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::

ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: [ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው]

በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም ሊቀ ዻዻሱም [አባ ቴዎድሮስ ይባላል] ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው ፯ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: ፯ቱም ለ፯ ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::

ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: ፯ቱ ቅዱሳን ግን በ፯ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ በ፯ የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::

[ † ? አቡነ ሰላማ ካልዕ  ? † ]

እኒህ ታላቅ ደግ ሰው የነበሩት በሃገራችን ኢትዮዽያ ከ፲፻፫፻፵ እስከ ፲፻፫፻፹ ዓ/ም ነው:: በትውልድ ግብጻዊ ቢሆኑም ለኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ውለታን ውለዋል:: በዘመኑ ዻዻስ ሁነው ቢመጡም እንደ ሌሎቹ ዻዻሳት በቤተ መንግስት አካባቢ ሥራ ፈትተው መቀመጥን አልፈለጉም::

ወዲያው እንደ መጡ የግዕዝ ልሳንን ልቅም አድርገው ተማሩ:: ቀጥለው ኢትዮዽያውያን ሊቃውንትን ሰብስበው ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተረጉሙ ገቡ:: አሥራው መጻሕፍትን [፹፩ ዱን] ጨምሮ ብዙ መሠረታዊ መጻሕፍትን መተርጐም ችለዋል::

ይህም ሥራ አድካሚ በመሆኑ ከ፴ ዓመታት በላይ ጊዜን ወስዷል:: ከተረጐሟቸው መጻሕፍትም :-

◉  ስንክሳር
◉  ግብረ-ሕማማት
◉  ላሃ-ማርያም
◉  ፊልክስዩስ [መጽሐፈ መነኮሳት]
◉  መጽሐፈ-ግንዘት
◉  ድርሳን ዘቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ. . . ይጠቀሳሉ::

አቡነ ሰላማ በስብከተ ወንጌል አገልግሎታቸውና በገዳማዊ ሕይወታቸው ይታወቁ ነበር:: በተጨማሪም በየቦታው እየዞሩ ይናዝዙ ያጠምቁም ነበር:: በወቅቱ ልክ እንደ ስማቸው ሰላም እንዲሰፍን ይተጉ ነበር:: መሣፍንቱን ነገሥታቱን እያስታረቁ ለቤተ ክርስቲያን በአንድነት እንዲቆሙ አድርገዋል::

ጻድቁ አቡነ ፊልዾስን ጨምሮ ቅዱሳንን ገንዘውም ቀብረዋል:: በቀደመ ስማቸው አባ-ፊቅጦር የሚባሉት ካልዕ [፪ኛው] ሰላማ በ፩ ሺህ ፫፻፹ ዓ/ም ከ፵ ዓመታት ትጋት በሁዋላ ዐርፈዋል:: ሲጠሩም :-
◉  መተርጉም [መጻሕፍትን የተረጐሙ]
◉  ብርሃነ አዜብ [የኢትዮዽያ ብርሃን]
◉  መጋቤ ሃይማኖት ተብለው ነው::

† አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን እንዳጸናቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

[ † ነሐሴ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ተዝካረ ፍልሠታ ለማርያም ድንግል [፭ኛ ቀን]
፪. ቅዱሳን ፯ቱ ደቂቅ
፫. አቡነ ሰላማ ካልዕ [መተርጉም]
፬. ቅድስት ሔዛዊ

[ †  ወርኀዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፪. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፫. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፬. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፭. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
፮. ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት

† "በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን::" † [፪ቆሮ.፲፫፥፲፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

†              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
?                   ?                    ?

3 месяца, 1 неделя назад
3 месяца, 2 недели назад

ደብረ ታቦር የተባለው ጌታ ክብሩን የገለጠበት ስፍራ ደብረ ታቦር ስለሆነ በዚሁ በዓሉ ስያሜውን አግኝቷል፡፡
ቡሔ ይባላል ፡- ቡሄ ብርሃን ማለት ነው በደብረ ታቦር ቧ ብሎዐ የተገለጠውን የጌታችንን የፊቱን ብርሃን ጸዳል፤ የልብሱንም እንደ ነጭ በረዶ ጸዓዳ መሆን ያስረዳል፡፡
• አንድም፡- ቡሔ ማለት መላጣ (ገላጣ) ማለት ነው፡፡
ይኸውም በበዓሉ ዋዜማ ልጆች ‹‹ ቡሔ በሉ፤ ቡሔ መጣ ፣ ያ መላጣ፣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ›› ይላሉ እዚህ ላይ ቡሄ ያለው ዳቦውን ነው፡፡
• አንድም፡- ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንደሚባል ወቅቱ በሃገራችን የጸዓተ ክረምት ዋዜማ ስለሆነ የክረምቱ አፈናው ተወግዶ /ተጋምሶ/ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት ፤ በዶፉና በጎርፉ ተሸፍና የነበረች መሬት የምትገለጥበት በመሆኑ ነው፡፡
• አንድም፡- ቡሔ (ቡሔእየ) ተብሎ ይተረጎማል ይኸውም የደብረታቦር እለት እርሾ ሳይገባበት ተቦክቶ የሚጋገረውን
ኅብስት ያሳያል፡፡

→ ችቦ የመብራቱ ፣ የሙልሙል ዳቦ የመጋገሩና የጅራፍ ማጮኽ ምክንያት፡-
• የጌታችን ክብሩ በተገለጠበት ጊዜ ብርሃኑ የሌሊቱን ጨለማ ገፍቶት እስከ አርሞንዔም ደርሶ ነበርና በዚያ አካባቢ የነበሩ እረኞች በኹኔታው ተገርመው ቀንም መስሎአቸው ሌሊቱም ተዘንግቷቸው በዚያው ቆይተው ነበርና ቤተሰዎቻቸው ምን አግኝቷቸው ይሆን በማለት መብራት አብርተው (ችቦ ይዘው)፣ የሚመገቡትን ይዘው ወገኖቻቸውን ፍለጋ ወጥተዋል እረኞችም ያሉበትን ቦታ ለቤተሰዎቻቸው ጅራፍን በማጮኸ አመልክተዋቸዋልና ይህን ለማሰብ ነው፡፡
• ዋናው ምስጢሩ ግን፡- የችቦው ብርሃን የጌታ ክብር መገለጡን፣ የጅራፋ ጩኸት ሐዋርያትን ያስደነገጣቸው የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ሲሆን፣ ኅብስቱ ጌታችን በመስቀል ላይ መሥዋዕት የመሆኑ (የሥጋ ወደሙ) ምሳሌ ነው፡፡
• ማስታወሻ፡- ከላይ እናዳየነው ጅራፋ መጮኹ የአብ የምስክርነቱ ቃል ምሳሌ ነው ይኸውም በታቦር ተራራ ላይ እንደሆነም ተገልጧል ስለዚህ ዛሬም ምሳሌነቱን ለማጉላት ጅራፍ የማጮኹን ሥርዓት በተራራ ማድረግ የተሻለ ነው፡፡
መልካም በዓል ይሁንላችሁ።

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago