Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

በ2007 የተቀሩ የሱና ቂርአቶች

Description
የሱና ቂርአቶችና ዳዕዎዎች ማስቀመጫ ቻናል ነው ።

አስተያየት ካለዎት @JEMALEndro
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month, 2 weeks ago

ኢስላም ያለ አንድ ሰይፍ አውሮፓን እያጥለቀለቀ ነው
~
ኢስላም በአሁኑ ሰዓት በምእራቡ አለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ ነው። ብሪታንያን እንደ ምሳሌ እንመልከት። መረጃዎቼን የወሰድኩት የኢስላም በሃገሪቱ በከፍተኛ ፍጥነት መስፋፋት እንቅልፍ የነሳው ፀሐፊ “ለንደን 500 ቤ/ክርስቲያናትን ዘግታ 423 አዳዲስ መስጂዶችን ከፈተች” በሚል ርእስ ከፃፈው አርቲክል ሲሆን በዚህ ድረ ገፅ ታገኙታላችሁ። http://yournewswire.com/london-churches-mosques/
ኢስላም ብሪታንያን እየዋጣት ነው ይላል የፅሁፉ ጭብጥ። ይህንን ለማሳየትም የተለያዩ መረጃዎችን ዘርዝሯል። ሀሳቡ ሲሰበሰብ የሚከተለውን ይመስላል:-
በሂያት ዩናይትድ ቤ/ክ በግብፃውያን ኮሚዩኒቲ ተገዝቶ መስጂድ ሆኗል። ቅዱስ ጴጥሮስ ቤ/ክ “መዲና መስጂድ” ተብሎ ተቀይሯል። ብሪክ ሌን መስጂድ ቀድሞ የሜተዲስት ቤ/ክ ነበር።
ህንፃው ያለ ምክንያት አልተቀየረም። ህዝቡም እየተቀየረ ሆኖ እንጂ። አዎ የሰለምቴዎች ቁጥር በእጥፍ አድጓል። ፀሐፊው ዴይሊ ሜይልን አጣቅሶ እንደፃፈው በለንደን እምብርት ውስጥ በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ቤ/ክ እና መስጂድ ይገኛሉ። ይሄ ምንም አይደንቅም። የሚደንቀው 1,230 ሰዎችን ለማስተናገድ የተዘጋጀው ቅዱስ ጊዮርጊስ በተሰኘው ቤ/ክ ውስጥ ሳምንታዊ ባእልን ለማክበር የተገኘው ክርስቲያ 12 ሰዎች ብቻ መሆናቸው ነው። በሳንታ ማሪያ ደግሞ 20 ብቻ። በአንፃሩ በአቅራቢያው የሚገኘው የብሩን ስትሬት ኢስቴት መስጂድ የገጠመው ችግር ከዚህ የተለየ ነው፣ ለሰጋጆች የሚበቃ ቦታ በማነሱ መጨናነቅ! መስጂዱ 100 ሰዎችን ብቻ የሚያስተናግድ ጠባብ ክፍል ያለው በመሆኑ ለጁሙዐ የሚታደመው ምእመን ጎዳና ላይ ሊፈስ ግድ ሲለው ይታያል። ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ ክርስትና በእንግሊዝ ወደ ታሪካዊ ቅርስነት እየተቀየ ሲሄድ ኢስላም ግን የሃገሪቱ የወደፊት ሃይማኖት ይሆናል።
ይህን ግምት የሚያጠናክሩ ተጨባጭ እውነታዎች አሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከሃገሪቱ ሙስሊም ማህበረሰብ ውስጥ ግማሽ (50%) አካባቢው ከ25 አመት እድሜ በታች መሆኑ ሲሆን ከክርስቲያኑ ህዝብ ደግሞ ሩቡ (25%) ከ65 አመት እድሜ በላይ ያሉ አዛውንቶች መሆናቸው ነው። ይህም ከ20 አመታት በኋላ ወደ ቤ/ክ ከሚሄዱ ክርስቲያኖች የሚልቁ ንቁ ሙስሊሞች ይኖራሉ ማለት ነው፤ የናሺናል ሴኪዩላር ሶሳይቲ ዳይሬክቴር የሆነው ከይዝ ፖርቺየስ እንደገለፀው።
በሌላ በኩል የሃገሪቱ ክርስቲያን በየጊዜው ለክርስትናው ጀርባውን እየሰጠ በመሆኑ የተነሳ የቤ/ክርስቲያናቱ ቁጥር በፍጥነት እያሽቆለቀለ ነው። ከ2001 ጀምሮ ለንደን ውስጥ ብቻ 500 ቤ/ክርስቲያናት ወደግል መኖሪያነት ተቀይረዋል። በተመሳሳይ ጊዜ በሃገሪቱ የሚገኙ መስጂዶች ቁጥር ሲታይ ግን በከፍተኛ ፍጥነት እያሻቀበ ነው ያለው።
ከ2012 እስከ 2014 ባሉት አመታት ራሳቸውን የአንግሊካን ክርስትና ተከታዮች እንደሆኑ ሲገለፁ የነበሩ እንግሊዛውያን ቁጥር ከ21% ወደ 17% በማሽቆልቀል በሶስት አመታት ውስጥ ብቻ ቤ/ክርስቲያኗ የ1.7 ሚሊዮን ተከታይ ኪሳራ ደርሶባታል። የሙስሊሙ ቁጥር ግን በአንድ ሚሊዮን አካባቢ እድገት አሳይቷል። ይሄ 5% ከማይሞላው ከሃገሪቱ የሙስሊሙ ቁጥር አንፃር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ እድገት ነው። (ይስተዋል! በጁላይ 2015 በተካሄደው የህዝብ ቆጠራ መሰረት የእንግሊዝ ህዝብ ብዛት 64 ሚሊዮን ሲሆን የሙስሊሙ ቁጥር ከዚህ ውስጥ 4.4% ነው።) ሆኖም ግን ግምቶች እንደሚያስቀምጡት በ2020 የጀማዐ (ህብረት) ሶላት ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ቁጥር ቢያንስ ወደ 683ሺ ያሻቅባል ተብሎ ይጠበቃል። በአንፃሩ ሳምንታዊው በዓል ላይ የሚገኙት ክርስቲያኖች ቁጥር ወደ 679ሺ ይወርዳል ተብሎ ይገመታል።
ወደ ቤ/ክ የሚመላለሰው ህዝብ ቁጥር ወደ መስጂድ ከሚመላለሰው ሙስሊም ህዝብ ጋር ሲነፃፀር በአንድ ትውልድ ዘመን ውስጥ ብቻ ሶስት እጥፍ ያነሰ ይሆናል።
በ2015 በተደረገ ትንተና በሃገሪቱ የብዙ ሰዎች ስያሜ በመሆን ልቆ የተገኘው “ሙሐመድ” የሚለው ስም ነው። ታላላቅ የሃገሪቱ ከተሞች ከፍተኛ የሙስሊም ቁጥር አላቸው። ማንቸስተር 15.8%፣ በርሚንግሀም 21.8%፣ ብራድፎርድ 24.7%። በክርስቲያን ቤተሰብ ከሚወለደው ይልቅ በሙስሊም ቤተሰብ የሚወለደው ህፃን ቁጥርም የላቀ ነው። በብራድፎርድና በሌስተር ከከተማዎቹ ህፃናት ግማሾቹ ሙስሊሞች ናቸው። ከተወሰኑ አመታት በኋላ የከተማዎቹ ነዋሪዎችን የህዝብ ብዛት ስብጥር ይገምቱ እንግዲህ።
በሌላ በኩል ለንደን ውስጥ ብቻ ኦፊሻሊ የሚታወቁ 100 የሸሪዐ ፍርድ ቤቶች አሉ። የሃገሪቱ ህግ አንዳንድ የሸሪዐ ህጎችን እንዲያካትት በሃገሪቱ ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች ሳይቀሩ እየጠየቁ ነው ያሉት። የብሪታኒያ ዩኒቨርሲቲዎችም ኢስላማዊ ህግ እያስተማሩ ነው። (የኛዎቹ ያሉትንም እየዘጉ እንደሆነ ልብ ይሏል።)
በሳዑዲ ዐረቢያ የብሪታኒያ አምባሳደር የሆነው ሲሞን ኮሊስ ኢስላምን ተቀብሎ ወደ መካ በመሄድ ሐጅ አድርጓል። ጠላቶቹ የፈለገ ቢያሴሩ መጪው ዘመን የኢስላም ነው። በሃገራቸው ያለው አንፃራዊ ነፃነት ለኢስላም መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሆነ የገባቸው ምእራባውያን በነፃ መድረኩ “ፍልሚያ” ኢስላም ልቆ እየወጣ እንደሆነ ቢረዱ ጊዜ በሙስሊሞች ላይ የነፃነት ምህዳሩን ማጥበብ፣ ሃይማኖቱን ጭራቅ አድርጎ የመሳል (islamophobia) ሰፋፊ ዘመቻዎችን መደገፍ፣ እንደ ዳዒሽ (isis) ያሉ ጠርዘኞችን በስውር መደገፍ፣ ኢስላማዊ ሃገራትን ማፈራረስና ሙስሊሞችን በገዛ ቀያቸው መጨፍጨፍ እንዲሁም ፀረ ኢስላም ፖሊሲ የሚያራምዱ አምባገነን ሃይላትን በፀረ ሽብር ዘመቻ ስም ያልተገደበ ድጋፍ ማድረግ አማራጭ ፖሊሲያቸው ሆኖ በገሃድ እየታየ ነው። “ልፋ ያለው በህልሙ ዳውላ ይሸከማል” እንዲሉ መስሏቸው እንጂ የኢስላም ግስጋሴን ምድራዊ ሃይል አይገታውም። ምክንያቱም ከላይ የተገባ መለኮታዊ ቃል አለና።
{ یُرِیدُونَ لِیُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ }
“የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ። አላህም ከሃዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው።” [አሶፍ፡ 8]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 03/2010)

1 month, 2 weeks ago

[{ የሸሪያ ዕውቀት አስፈላጊነት }]

🎙  በኡስታዝ አህመድ ሙሀመድ አርባ ምንጭ /ገራዶ
➽ በሙሐደራው ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል
➪  ሸሪያዊ ዕውቀትን መፈለግ  ያለው ደረጃ
➱ ዕቀትን ለመፈለግ በዋነኝነት ምንድነው የሚያስፈልገን?
➱ የዕውቀት ዓይነቶች
ፈርዱል ዓይን
ፈርዱል ኪፋያ
ሱና

➩ የሸሪያን ዕውቀት መፈለግ ብይኑ ምንድነው?
➩ ዕውቀትን ከማን ነው የምንወስደው

🕌በወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
ጁመዓ 4/08/2016
ከመጝሪብ እስከ ኢሻ የተደረገ ዳዕዋ

የጁመዓ ኹጥባውንና ከጁመዓ በሗላ የተደረገውን ዳዕዋ ኢንሻ አላህ እንለቃለን ...
https://t.me/tewuhidWereilu/5270

2 months ago

**የትብብር ጥሪ በተከበረው ረመዿን ወር
وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ
በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡ሱረቱል ማዒዳ: 2

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

ውድና የተከበራችሁ የሱና ወንድምና እህቶች

ይሄን ከላይ ያለውን ቪድዮና ድምፅ ሰምታችሁ ለማገዝ የፈለጋችሁ!

የአመታዊ የኡስታዞች ደመወዝ

የትላልቆቹ የአዋቂዎች ኡስታዝ 10,000 ×12 = 120,000 ብር /አንድ መቶ ሃያ ሽህ ብር
የልጆች አቅሪ 3000×12 = 36,000 (ሰላሳ ስድስት ሽህ ብር)
የልጆች መድረሳ ቤት ኪራይ 500 ×12 =6000 ብር እያደር ሊጨመር ይችላል ለቂርአት ስለሆነና አቅም እንደሌለን ስለሚያውቁ ነው የቀነሱልን አሁን

የባንክ አካውንት የተከፈተው
1 ሸህ ሃሰን ሙሀመድ
2 ሙሃመድ ሃምዛ
3 ጀማል እንድሮ

1000469868587
ወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት
87813274
የወረኢሉ ከተማ ዘምዘም መስጅድ የአቢሲኒያ ባንክ አካውንት**

ሁላችሁም የቻላችሁትን 5, 10 ሳትሉ ተባበሩን ለማለት ያክል ነው

በኸይር ነገር መተባበር ድናችን ያዘዘው መሰረታዊ ነሀር ነው በመልካም ነገር እንረባረብ

ለበለጠ መረጃ
ጀማል እንድሮ 0933519871
ኡመር አሳልፍ 0938369567
ሸህ ሃሰን ሙሃመድ 0914063769
ወሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ!

በቴሌግራም
@JemalEndroAbuMeryem
@Zulbijaden

https://t.me/YeZemzemMesjidJemea/20249

3 months, 2 weeks ago

ሙሓደራ ክፍል 189

አዲስ ሙሓደራ ክፍል 01

ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ

የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇

““የ አብዱል ሀሚድ አልለተሚይ እና  ሁሰይን ሙሀመድ ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed

6 months, 2 weeks ago
6 months, 2 weeks ago
6 months, 2 weeks ago
6 months, 2 weeks ago

👇👇 ሸርሁሱና የኢማሙልበርበሀሪ👇👇
በኡስታዝ ነስረድን ሙሀመድ ሃፊዘሁላህ መትን ብቻ!

6 months, 2 weeks ago

*ይህ በኡስታዝ ነስረዲን ሙሐመድ
የተቀሩ ኪታቦች ዝርዝር ነው። በተቀመጡት ሊንኮች መሰረት የኪታቦቹን ድምፅ ማግኘት ይችላሉ።
t.me/ustaznesredin1443 *1⃣ኢርሻድ👉 t.me/ustaznesredin1443/11 2⃣ቡሉግ 👉 t.me/ustaznesredin1443/104 3⃣ከሽፉሹቡሃት 👉 t.me/ustaznesredin1443/156 4⃣ሚን ዑሱሊ አቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀማዓ (ፈውዛን)👉 t.me/ustaznesredin1443/164 5⃣ኪታቡ ተውሒድ ፈውዛን👉 t.me/ustaznesredin1443/199 6⃣ዑሱሉል ዒማን የሸይኽ ሙሐመድ ኢብን አብድልወሃብ 👉 t.me/ustaznesredin1443/226 7⃣ሸርሁስ'ሱና በርበሃሪ 👉 t.me/ustaznesredin1443/241 8⃣አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ👉 t.me/ustaznesredin1443/255 9⃣አል ወጂዝ የሸይክ አብዱላህ አብዱልሀሚድ 👉 t.me/ustaznesredin1443/322 🔟ሉምዓቱል ዒዕቲቃድ *👉t.me/ustaznesredin1443/427* 1⃣1⃣ሪያዱ ሷሊሂን👉 t.me/ustaznesredin1443/447 1⃣2⃣መንዙመቱ ሃዒያህ ኢብኑ አቢ ዳዉድ👉 t.me/ustaznesredin1443/559 1⃣3⃣ኹዝ አቂደተክ👉 t.me/ustaznesredin1443/2597 1⃣4⃣ተንቢሁ ዘዊል አፍሃም👉 t.me/ustaznesredin1443/2626 1⃣5⃣ሹሩጡ ሶላት ሸይኽ መሀመድ ኢብኑ አብዲል ወሃብ👉 t.me/ustaznesredin1443/2774 ጥንቅር፦
©ኹበይብ መስጂድ**

Telegram

የኡስታዝ ነስረዲን ሙሀመድ ትምህርቶች(Official)

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሙስሊም ወንድም እና እህቶች ወደ ግሩፑ እንኳን በደህና መጣችሁ። √ ይህ ግሩፕ የተከፈተበት አላማ በተለያዩ ጊዜዎች በወንድም ነስረዲን ሙሀመድ(ደብረብርሀን ዩኒቨርሲቲ) አማካኝነት ይሰጡ የነበሩ እና በ አሁኑ ሰአት እየተሰጡ ያሉ ትምህርቶችን ለማስተላለፍ ታስቦ ነው።

*****✨***ይህ በኡስታዝ ነስረዲን ሙሐመድ
6 months, 3 weeks ago

*🟦ዳዕዋ & ኮርስ
📣 ዜና ለሀዋሳ ከተማ ሰለፍዮች*

እነሆ ዛሬ ማለት ቅዳሜ እና እሁድ ቀን ሙሉ ታላቅ የኮርስ እና የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል

በእለቱም የሚገኙ እንግዶች

🎙[የተከበሩ ሼይኽ ሙሳ አልቀጧኒ

🎙ውዱ ኡስታዛችን አብዱረሕማን አቡ ሒዛም](http://t.me/abuUseyminabdurehman)

እና ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ በእለቱም እርሶም ቤተሰቦም ይታደሙ ላልሰሙ ያሰሙ

ኮርሱ የሚሰጠው በአረብ ሰፈር መስጅድ ሲሆን በሌሎች መስጅዶች የዳዕዋ ፕሮግራም ይኖራል::

ቦታ = ዓረብ ሰፈር መስጅደ ረህማ

👉ኮርስ:
👉በሁሉም መስጅድ ዳዕዋ:
👉ጥያቄና መልስ የመሠሳሰሉት ፕሮግራሞች ይኖራሉ

በዚሁ አጋጣሚ ወንድም #ሸምሱ_ጉልታ  የሚገኝ ከሆነ ለውይይት እንድቀርብ ሀሳብ ቀርቧል ። ሀቅን የፈለገ ይታደሞ በአደባባይ እንድመጣ ጥሪ ቀርቧል ከተገኘ አላህ ብሎት ከተሳካ ።

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 months ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month, 1 week ago