ጤናዎ በቤትዎ

Description
በ ያላችሁበት ሆናችሁ ስለጤናዎ የባለሞያ ምክር የሚያኙበት ምርጥ ቻነል፡፡
ጥያቄም ካልዎት እናስተናግዳለን፡፡
ለጥያቄዎ፡- @Tenawo_Bot
Advertising
We recommend to visit

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ

ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot

⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017

Last updated 12 hours ago

ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል

የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና

ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu

ስልክ ቁጥር +251911857852

Last updated 1 month, 2 weeks ago

👉 ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነዉ። ይህ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።

ለማንኛዉም አስተያየት
@wizhasher
@wiz_hasher

Group 👉 @Man_United_ethio_fans_Group

{ስልክ ቁጥር}
0919337648

Last updated 1 day, 16 hours ago

4 года, 1 месяц назад

ጥያቄ ?
ከ አዲስ አበባ

ስለ ደም ግፊት ማወቅ ፈልጌ ነበር , መዳኒቱ ቢቆም ችግር አለው?

በአጭሩ ለመመለስ ያለሀኪም ትዛዝ በፍፁም መዳኒት ማቋረጥ የለብንም ።

ደም ግፊት በሁለት መልኩ ይከፈላል አንደኛው ብዙ ጊዜ በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የምናየው ፕራይመሪ ሀይፐርቴንሽን የምንለው ሲሆን ሁለተኛው ከ ኩላሊት ህመም ጋር, የኩላሊት የደም ቱቦ መጥበብ ጋር ወይም ሌሎች ግፊትን የሚጨምሩ ተጓዳኝ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ የደም ግፊት ሲሆን ይሄንን ሰከንዳሪ ሀይፐሮቴንሽን እንለዋለን። ይህም ወጣቶች ላይ ጎልማሶች ላይ እንዲሁም ህፃናት ላይ ሊከሠት ይችላል።

የደም ግፊት በህክምናው በጣም የተጠና እናብዙ የህክምና መዳኒቶች ያሉት ሲሆን በተጨማሪም አመጋገብን በማስተካከል እንቅስቃሴ በማድረግ የሠውነት ክብደት በመቀነስ መዳኒት በመውሠድ እና ክትትል በማድረግ መቆጣጠር እና ያለ ጤና ዕክል ህይወትን መምራት ይቻላል።

ነገር ግን ይህ ጥንቃቄ ካልተደረገ ግፊት ከመጠን በላይ በመጨመር የ ጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስ ወይም ስትሮክ ሊያስከትል ይችላል ይህም የሚፈጠረው ያለምንም የቀደመ ምልክት ወይም የህመም ስሜት በደቂቃዎች ሊሆን ይችላል ለዚም ሳይለንት ኪለር ይሉታል የደም ግፊትን ።

ግፊትን እንደመቆጣጠር የደም መፍሠስን ማከም ቀላል አደለም ። በሀገራችንም አብዛኞቹ የዚህ ህክምና ሴት አፕ አልተሟሉም ። ቢኖር እንኳን ወደ ቀደመ ጤንነት ለመመለስ አስቸጋሪ ነው።

ስለዚ በቀላል መንገድ ግፊትን መቆጣጠር አማራጭ የሌለው ሲሆን የደም ግፊት ኖሮ አንዴ ደግሞ ኖርማል ቢሆን እንኳን ያለ ሀኪም ትዛዝ እና ክትትል መዳኒት ማቆም ተገቢ አደለም።

እናመሠግናለን።

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@tenawobebeto ጆይን ያድርጉ

4 года, 1 месяц назад

ጥያቄ?
ስለ ማህፀን ዕጢ ብትግሩን...
ከ አዲስ አበባ

በተለምዶ የማህፀን ዕጢ የሚባለው በህክምናው Myoma ሚባለው ሲሆን በተለይ እድሚያቸው ከ45 ዓመት በታች በሆኑ ሴቶች ላይ ሊኖር የሚችል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ከ ወር አበባ መብዛት እና ከተወሠነ የማህፀን ህመም በስተቀር የከፋ የህመም ስሜት አይኖረውም

ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በማህፀን ዕጢ የተነሳ የሚያጋጥሙ ችግሮች አሉ

**1. መውለድ አለመቻል ወይም ደግሞ ማዕፀን ፅንስ ከያዘ በኋላ ያለጊዜው መጨናገፍ : ይህ የሚሆነው የማህፀን ዕጢው ለፅንስ መጀመሪያ ቦታ የሆነው የማህፀን የውስጥ ግድግዳ ላይ የሚገኝ ከሆነ እና መጠኑ ትልቅ ሆኖ ፅንሱ እንዳያድግ የማህፀንን ውስጣዊ ክፍል የሚያጣብብ ከሆነ ይህ ችግር ሊያጋጥም ይችላል ስለዚህ ዕጢው ያለበትን ቦታ በ አልትራሳውንድ ምርመራ ማረጋገጥ እና ክትትል ማድረግ ተገቢ ነው ።

  1. ሌላኛው ደግሞ ይህ ዕጢ በ ርግዝና ወቅት እና አንዳንድ መዳኒቶች ሲወሠዱ መጠኑ ይጨምራል በውስጡ የመቁሠል ባህሪም ይኖረዋል በዚ ጊዜ ቀለል ያለ የነበረው ህመም ከፍተኛ ሊሆን ይችላል በዚን ጊዜ ሀኪም በማማከር ተገቢውን የህመም ማስታገሻ መውሠድ እዲሁም ከመጠን በላይ ደም መፍሠስ ከነበረ የደም መጠንም መላብራቶሪ መሳሪያ መመርመር ያስፈልጋል ።

  2. ሌላው በጣም የተለመደ ባይሆንም አንዳንዴ እነዚ ካንሰር ያልሆኑ የማፀን እጢዎች ወይም ማዮማ ምንላቸው ወደካንሰርነት ሊቀየሩ ሚችሉበት አጋጣሚም አለ ነገር ግን ይህ የተለመደ አደለም ሆኖም ማንኛውም ሰው የ ዕጢውን መጠን በየጊዜው ቼክ ቢደረግ መልካም ነው ቢያንስ በ አመት አንድ ጊዜ.

ከላይ የተወሠኑ ጉዳቶችን እና የበሽታውን ሁኔታ በአጭሩ ለማስቀመጥ ሞክርያለው ። በአጠቃላይ ብዙ የከፋ በሽታ ባይሆንም ለጥንቃቄ ክትትል ማድረግ በጥቂት አጋጣሚዎች የሚኖሩትን የዚን በሽታ በጊዜ ለማወቅና ህክምና ለማድረግ ወሳኝ ነው ።

እናመሠግናለን።
ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ
@tenawobebeto
ጆይን ያድርጉ**

ጥያቄዎትን @tenawo_bot ይላኩልን

4 года, 8 месяцев назад

ህፃናትና ኮሮና
----------------
በ america CDC ጥናት መሰረት ከተጠቂዎች 2% ብቻ ከ18 ኣመት በታች ሲሆኑ ከነዚህም 0.3% ብቻ ከ 1 ኣመት በታች ሲሆኑ ፣በጠና ታመው ICU የገቡ ደግሞ 2% ናቸው !!

በ america acadamy of pediatrics ጥናት መሰረትም ከ 2,000 ህፃናት90% ምልክት ያላሳዩ፣ትንሾ ሞልክት(ሙቀት፣የጎሮሮ ህመም..)ያሳዩ ሲሆን 6%ብቻ ከፍተኛ ምልክት፣ 0.4% ICU ያስፈለጋቸው ናቸዉ!!

ህፃናት ለምን በጣም እንደማይጠቁ በግልፅ ባይታወቅም ፣እንዲሁም በጥናት ያለ ቢሆንም በ ምሁራን የተቀመጡ መላምቶች!!
------------------------------
-የህፃናት innate imunity በተሎየሚመልስ(rapid response) ያለው ሲሆን የኣዋቂዎች ግን ጊዜ ወስዶ እና ኣስታውሶ (longer and adaptive)ስለሚመልስ!!
-የህፃናት መጀመርያ ወሮች imunity cells ብዙ ቢሆኑም ያልዳበሩ ናቸው(immature ) ፣በጊዜ ሂደት ለብዙ የ ከባቢ ኣየር pathogens(ቫይረስ፣ባክተርያ..) ስለሚጋለጡ በጊዜ ሂደት እየዳበሩ ይመጣሉ!!
- ህፃናት ብዙ የ ቫይረስ እና ባክተርያ ክትባት(vaccine) ስለሚሰጡ
-የ ህፃናት መተንፈሻ ኣካላት ከ ኣዋቂዎች የተሻለ በ ኢንፌክሽን ለብዙ ጊዜ ያልተጋለጡ ስለሆነ(healtheir respiratory system)
-ለ ከባቢ ኣየር ብክለት(pollution)፣ሲጋራ ስለማይጋለጡ

- እንደ ኣዋቂዎች imunity ለሚያዳክሙ የቆዩ በሽታዎች(chronic disease) ስለማይጋለጡ!!
-የኣዋቂዎች immune cells ኣንዳንዴ ከ በቂ በላይ ስለሚቆጣ(hyper active) የራሱን cell ሊያጠፋ ይችላል(antibody dependent enhancement)
-ኣንዳንዶች ህፃናት ACE2 የተባለ በ ሳምባ፣ኣንጀት የሚገኙ ቫይረስን የሚያጣብቁ ፕሮቲኖች መጠን ያነሱና መልካቸው የቀየረ (modified)ስለሆነ ሲሉ፣ኣንዳንዶች ደግሞ ይሄ ፕሮቲን imunity የሚያጎለብት ስለሆነ ከ ቫይረሱ የሚከላከላል እና በ እድሜ የሚቀንስ ነው ይላሉ!!
-ኣዋቂዎች በ chicken pox (ኩፍኝ) ከ 25 ጊዜ በላይ እንደሚገድል ፣ኢንፉሊዌንዛ ,MERS,SARS የተባሉ የ ኮሮና ኣይነቶችም የባሰ ጉዳት ያስከተሉት ኣዋቂዎች ላይ ነበር!!

ይህ እንዳለ ሁኖ ግን በቅርቡ በ ኢራንና ኬንያ የ 6 ኣመት፣በ ለንደን የ13 ኣመት፣በቤልጄም የ12 ኣመት፣በ ጆርጅያ የ 11ኣመት ህፃናት ሞተዋል ስለዚ መጠንቀቅ ኣለብን

ነገር ግን ህፃናት ምልክት ባያሳዩም ፣በጣም ስለሚንቀሳቀሱ፣ብዙ እቃዎች ስለሚነኩ ተሎተሎ ስለማይታጠቡ ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ

@tenawobebeto

4 года, 9 месяцев назад

ጥንቃቄ ???

ማንኛውም የንግድ ቤት እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች የእጅ መታጠቢያ ውሃ እና ሳሙና ደጅ ላይ ማድረግ አለባቸው ። እጅን ታጥቦ ወደ መኖሪያ ቤት መግባት ተገቢ ነው

ኮንዶሚኒየም እና አፓርትመንት ላይም ምድር ላይ ደረጃውን ከመውጣታችን በፊት መታጠቢያ ማዘጋጀት ይኖርብናል ።

እቤት ውስጥ መሆን / ወይም ወደውጭ ምንወጣበትን እና ውጭ ምንቆይበትን ሰዓት መቀነስ አለብን

ሁልጊዜ ርቀታችንን እንጠብቅ

ጓንት መልበስ እና ማስክ መጠቀም አሁን ላይ አያስፈልግም የጤና ባለሞያ ወይም የህመም ስሜት ካለው ሰው በስተቀር ።

ጓንትና ማስክ እየተጠቀምን ከሆነ በየ 6 ሰዓቱ አዲስ መቀየር አለብን ካልሆነ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።

የእጅ ሳኒታይዘር መጠቀም ጥሩ ነው 65 -75% አልኮል ያለው ተመራጭ ነው ከዛም ከበለጠ በቀላሉ ከእጅ ላይ ስለሚተን ቫይረሱን ለመግደል በቂ ጊዜ አይኖረውም : ከዛ በታች ከሆነ ደግሞ ቫይረሱን Denature ለማድረግ ጥንካሬ አይኖረውም ። ሳኒታይዘር እየተጠቀምን ቢሆንም ፊታችንን በእጃችን መንካት የለብንም ።

እያንዳንዱ ግለሰብ ሰላም የሚሆነው ወዳጁ ሰላም ሲሆን ነው ፣ ራስን መጠበቅ ሌላውን መጠበቅ ነው።

ፈጣሪ ይጠብቀን ለወዳጅዎ ያካፍሉ ።

Ask @tenawo_bot
@tenawobebeto

4 года, 9 месяцев назад

ጣልያን ውስጥ በ24 ሰዓት ተጨማሪ 743 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 6,820 ደርሷል።

በሀገሪቱ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥርም 69,176 የደረሱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 5,249 ኬዝ በ24 ሰዓት ነው የተመዘገበው።

ጥንቃቄ ከኛ አይቅር ፣ ብቻውን ጤነኛ የሚሆን የለም ራስን መጠበቅ ሌላውን መጠበቅ ነው ።
የተሳሳተ ግንዛቤ ያለውን በመምከር እና በማስተማር ህብረተሠባችንን እንጠብቅ ።

@tenawobebeto

4 года, 9 месяцев назад

ስለ hanta virus በሶሻል ሚዲያ የሚውራው ምንድነው?

Chinese medical experts investigate hantavirus death

Experts in southwest China's Yunnan Province have started a medical investigation into a possible hantavirus outbreak in a local county after a man who tested positive died Monday; the man was traveling by bus on his way back to east China's Shandong Province for work.

Tian and two others with fever symptoms were then taken to a local hospital. Four hours later, Tian died after testing positive for hantavirus. The other two were tested negative for the virus and cleared of the novel coronavirus infection as well. The rest of people on the bus are under medical observation.

The disease is not airborne and can only spread to people if they come in contact with rodent urine, feces, or saliva and less frequently by a bite from an infected host.

The virus can't be passed on from person to person, and is classified in China as causing Class B infectious diseases. Early symptoms include fatigue, fever, and muscle aches, along with headaches, dizziness, chills and abdominal problems. If left untreated, it can lead to coughing and shortness of breath and can be fatal.

Zuo said vaccination is the most effective way to prevent hemorrhagic fever, as the vaccine has been available in the country for nearly 20 years. He added that it's important to keep good hygiene and keep living environments clean, eliminate rodent habitats, and strengthen personal protection to prevent skin damage.

hanta virus ከዚህ በፊት የነበረ እና ክትባት ያለው ከሠው ወደሠው በትንፋሽ የማይተላለፍ በሽታ ነው እንጂ አዲስ ወረርሽኝ አይደለም

@tenawobebeto

4 года, 9 месяцев назад

በመጪዎቹ ቀናት ይህ ኖቬል ኮሮና ቫይረስ እንዴት እና የትኞቹን የሠውነታችንን ክፍሎች እንደሚጎዳ እና እስካሁን ጥናት ላይ ያሉትን የህክምና አማራጮች

ሌላ ተጓዳኝ በሽታዎች ያልዋቸው እና በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ላይ በተለየ ለምን የከፋ እንደሆነ

አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ መሣሪያ ደካማ ጎን እና ጠንካራ ጎኖች ምንድናቸው ስህተትስ ሊፈጠር ይችላል ???

ማስክ መልበስ ያስፈልገናል ? ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ ምንድነው

ለአስተያየት እና ጥያቄ @tenawo_bot

ሌወዳጅዎ ሼር ያድርጉ ? @tenawobebeto

4 года, 9 месяцев назад

ሁላችንም ራሳችንን እንጠብቅ ራስን መጠበቅ ሌላውን መጠበቅ ነው ።

ማንኛውም በጤና ጉዳይ ጥያቄ ካልዎት እቤትዎ ሆነው ይፃፉልን የባለሞያ ምክር ያገኛሉ

ለጥያቄዎ @tenawo_bot ይፃፉልን

@tenawobebeto ይቀላቀሉን

4 года, 9 месяцев назад

መረጃ COVID 19

?መንግስት ለምን እቤትዎ እንዲሆኑ በተደጋጋሚና ይመክሮታል?

Covid 19 የተባለውን በሽታ ሚያመጣው ቫይረስ ለተወሠኑ ሠአታት አልፎም ሁለት ሶስት ቀን ብቻ ነው ሂወት ካለው ነገር ውጪ መኖር የሚችለው ስለዚ በአጋጣሚ በቫይረሱ የተበከለ ቦታ ወይም መገልገያ እቃ ካለ እዛው ቫይረሱ ሂወት ያለው ነገር በማጣት እንዲከሽፍ ለማድረግ

ሁለተኛ ደሞ በሁለት ሣምንት ውስጥ ሁሉም በሽታው የያዛቸው ሰዎች ምልክት ስለሚያሳዪ ያሉንን ኬዞች በሙሉ ለማወቅ ስለሚረዳ

ሶስተኛ በሽታው እደያዛቸው ሳይታወቅ ወደ ሌላ ሰው የሚተላለፉ ኬዞችን ለማስቀረት እና በቀላሉ አብረው የነበሩትን ሰዎችን ለይቶ ለመከታተል ስለሚያስችል

@tenawobebeto

5 лет, 11 месяцев назад

በውስጥ መስመራችን በርካታ ጥያቄዎች እያስተናገድን ነው ። ለትምህርት እና ግንዛቤ ይሆናል ያልናቸውን ፖስት እያረግ ን አብረን እንቆያለን ። አብራችሁን ስላላችሁ እናመሠግናለን
ለወዳጅዎ ሼር በማድረግ ቻናሉን ተደራሽ ያድርጉት

@tenawobebeto

We recommend to visit

ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!

➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአፍሪካ መረጃዎችን በሙሉ
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ

ለማስታወቂያ ስራ @Promotion_4_3_3_Bot

⓸-⓷-⓷ስፖርት በኢትዮጵያ| 2017

Last updated 12 hours ago

ሙሌ ስፖርት ስፖርታዊ መረጃዎችን ከእሁድ እስከ እሁድ ያገኙበታል

የሃገር ቤት መረጃ
የአውሮፓ ሊግ መረጃ
ቀጥታ ስርጭት
የዝውውር ዜና

ለማስታወቂያ ስራ @Mulesporta
@Teme_Ayu

ስልክ ቁጥር +251911857852

Last updated 1 month, 2 weeks ago

👉 ስሜት፣ እምነት፣ ወኔ፣ ፍቅር፣ አልሸነፍ ባይነት የሚንፀባረቅበት የታላቁ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነዉ። ይህ ቻናል ስለ ውዱ ክለባችን ማንችስተር ዩናይትድ 24 ሰዐት መረጃዎችን በፍጥነት ወደ እናንተ ያደርሳል።

ለማንኛዉም አስተያየት
@wizhasher
@wiz_hasher

Group 👉 @Man_United_ethio_fans_Group

{ስልክ ቁጥር}
0919337648

Last updated 1 day, 16 hours ago