አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ

Description
🔔🔔🔔 አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ🔔🔔🔔
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሥርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች ፣ወቅታዊ መረጃ፣ሥርዓተ ማኅሌት ፣ዝማሬ፣የቅዱሳንን ታሪክ የምታገኙበት ቻናል ነው።

ለማንኛውም አስተያየት @SDS12317212729

@Dn_amu_ki_17
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

#ተጋደሉ_ጻድቃን_በእንቲኣሁ

የወልደ እግዚአብሔርን ሕማምና እንግልት ስቅለቱን በማሰብ በርካታ ቅዱሳን አባቶች በሕይወት ዘመናቸው የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሕማም ስቃዩን በማሰብ ባደረጉት ታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ በረከትና ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳንን ተቀብለዋል ፡፡

ዛሬም ዘወትር ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን እያሰቡ በታላቅ ትሕርምትና መንፈሳዊ ተጋድሎ የሚኖሩ ቅዱሳን አሉ ቅዱሳኑ የወልድን ሕማሙን የሚያስቡት በዓመት በዚህ በዐብይ ፆም ቀን ብቻ ሳይሆን በየሰዓቱ በየዕለቱ በየሳምንቱና በየወሩ ነው

ለምሳሌ በየሳምንቱ ዐርብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ነገረ ሕማሙን በማሰብ ታላቅ ተጋድሎ ይፈጽሙ ከነበሩ ቅዱሳን በገድላቸው የተጻፈውን ለአብነት ብንመለከት ፡- ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንዱ ናቸው ።

ሕማማተ መስቀልን በማሰብ ዐርብ ዐርብ ቀን ይህ መራራ ነው ይህ ጣፋጭ ነው ሳይሉ የምድረ በዳ ቅጠል ለቅመው ቅዳሜና እሑድ ይመገቡ ነበር የጾሙ ወራት እስኪፈጸም ድረስም ፈጽሞ ውኃ አይጠጡም ነበር በሌላም ጊዜ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በየሳምንቱ ሦስት ሦስት ቀን ያከፍሉ ነበር...፡፡

#ተክለ_ሃይማኖት_ሆይ በዕለተ : ዓርብ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ የተገረፈውን ፡ ግርፋት ፡ በማሰብ ፡ ጽኑዕ ፡ ግርፋትን ፡ ለተገረፈ ፡ ጀርባኽ ሰላም ፡ እላለው ።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!

አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube

Sador Sisay on Youtube

Sador Sisay on Instagram

Sador Sisay on Facebook

Sador Sisay on Tiktok

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

Facebook

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ | Addis Ababa

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ, Addis Ababa, Ethiopia. 6,842 likes · 137 talking about this. Religion ishues

[#ተጋደሉ\_ጻድቃን\_በእንቲኣሁ](?q=%23%E1%89%B0%E1%8C%8B%E1%8B%B0%E1%88%89_%E1%8C%BB%E1%8B%B5%E1%89%83%E1%8A%95_%E1%89%A0%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%89%B2%E1%8A%A3%E1%88%81)
1 month, 2 weeks ago
1 month, 2 weeks ago

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
#የቀጠለ

ወሀሎ ህየ አሐዱ ብእሲ ዘሠላሳ ወሰመንቱ ክረምት እምዘደወየ ወኪያሁ ርእዮ እግዚእ ኢየሱስ ይሰብክ ውስተ ዓራቱ አእመረ ከመ ጎንደየ ውስተ ደዌሁ ውይቤሎ ትፈቅድኑ ትሕየው።
ከዚያም ከታመመ ሠላሰ ስምንት ዓመት የሆነው አንድ ሰው ነበር ጌታ ኢየሱስም ያን ሰው ከአልጋው ተኝቶ አየና በደዌ ታሥሮ ብዙ ዘመን እንደቆየ አውቆ ልትድን ትወዳለህን? አለው። ዮሐ፡5፥5

ጌታችን የዚህን ሰው ችግር ብቻ ሳይሆን ብዙ ዘመን እንደዚህ እንደነበረ ያወቀው ማንም ሳይነግረው ነበር በሽታውን ከነመንሥኤው አስቀድሞ ያውቃልና ወደዚህ የብዙ ዓመታት በሽተኛ መጣና ‹ልትድን ትወዳለህን?› አለው ጌታችን የሚፈልገው ይህንን ሰው መፈወስ እንጂ የራሱን ማንነት ማሳየት ስላልነበረ ‹ላድንህ ትወዳለህን?› አላለውም በዚያ ላይ ይህ ሰው የጌታን ማንነት አያውቅም ጌታችን ‹ስታምኑብኝ ብቻ ነው የምፈውሳችሁ›የሚል አምላክ አይደለም ለሁሉ ፀሐይን የሚያወጣ ለሁሉ ዝናምን የሚያዘንም አምላክ ይህንን ሰውም ለመፈወስ እስኪያምነውም አልጠበቀም።

ይህ በሽተኛ‹ልትድን ትወዳለህን?› ሲባል የሠጠው መልስ እጅግ የሚያስገርም ነው እንደሚታወቀው በሽታ አመል ያጠፋል በሽታው በቆየ ቁጥር ደግሞ መራር ያደርጋል ሰዎች በበሽታ ሲፈተኑ በሰው በፈጣሪም ላይ ብዙ የምሬት ንግግር ሊናገሩ ይችላሉ ጌታችን ‹ልትድን ትወዳለህን?›ብሎ ሲጠይቀው ‹ታዲያ መዳን ባልፈልግ ጠበል ቦታ ምን አስቀመጠኝ? እያየኸኝ አይደል… › ወዘተ ብሎ ብዙ ያለፈ ንግግር ሊናገር ይችል ነበር፡፡ ይህ ሰው ግን ምንም የምሬት እና የቁጣ ቃል አልተናገረም ጌታችንም ሲያናግረው በጨዋ ሰው ደንብ ‹ጌታ ሆይ..›ብሎ ነው የመለሰለት፡፡ በዚህ ሁኔታው ትሑት ሊባል ይችላል፡፡

ነገር ግን የመለሰው የተጠየቀውን አይደለም ጥያቄው ‹ልትድን ትወዳለህን?› የሚል ከሆነ መልሱ ‹አዎ መዳን እወዳለሁ› አለዚያም ‹አይ አልፈልግም› ብቻ መሆን ነበረበት እሱ ግን ‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል ብሎ መለሰለት› እንግዲህ የጌታችንን ማንነት ባይረዳውም ጌታችን በወቅቱ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበርና ‹ምናልባት ወደ መጠመቂያው ሊጨምረኝ አስቦ ይሆናል ያም ባይሆን ግን ከተከተሉት ሰዎች አንዱን አደራ ሊልልኝ ይሆናል› ብሎ አስቦ ነበር ‹ሰው የለኝም› ብሎ የሠላሳ ስምንት ዓመታት ብሶቱን ተናገረ ‹ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል› ብሎ እያየ የቀደሙትን ሰዎች አስታወሰ፡፡

ጌታችን ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ› አለው፡፡ ባላሰበው ባልጠበቀው መንገድ ፈወሰው ይህ ሰው ሠላሳ ስምንት ዓመት ሙሉ ሲጠባበቃት የነበረችውን የቤተ ሳይዳ ጠበል ሳያገኝ በመልአኩ መውረድ ሳይሆን በመላእክት ፈጣሪ ቃል ተፈወሰ፡፡ ገባሬ መላእክት ክርስቶስ ራሱ መጥቶ አዳነው ይህ ሰው እግዚአብሔር በዚህች ጠበል ካልሆነ በቀር በሌላ በምንም መንገድ ያድናል ብሎ አስቦም አልሞም አያውቅም ነበር ለመዳን የሚያስፈልገው ምንድን ነው ተብሎ ቢጠየቅ የሚመልሰው ‹ወደ ውኃው የሚጨምር ሰው እና የቤተ ሳይዳ ውኃ› ብሎ ነበር ጌታችን መጻጉዕ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ተስፋ ያደረጋትን ጠበል ወይም ደግሞ ወደ ጠበሉ የሚጨምሩትን ሰዎች ሳይጠቀም ፈወሰው እግዚአብሔር ያለ ጠበልም እንደሚያድን ማመን ካልቻልን እምነታችን ሙሉ አይደለም ይህ ሰው ወደ ውኃው ገብቶ ቢድን ኖሮ‹ጌታዬ አዳነኝ› ከማለት ይልቅ ‹‹መዳን ይነሰኝ? ሠላሳ ስምንት ዓመት እኮ ነው የጠበቅኩት…›› እያለ ልፋቱን ያወራርድ ነበር እንጂ ፈጣሪውን አያመሰግንም ነበር፡፡

ጌታችን ጠበል ቦታ ያገኘውን ያለ ጠበል ፈወሰው ሲባል መቼም ጠበል መጠመቅ የማይወዱ ወይም በጠበል የማያምኑ ሰዎች ደስ ሊላቸው ይችላል ‹‹እኛስ ምን አልን ጌታ እኮ ይህን በሽተኛ ጠበል ቦታ አግኝቶ እንኳን የፈወሰው ያለ ጠበል ነው›› ብለው ባቀበልናቸው በትር ሊመቱን ይፈልጉ ይሆናል ሆኖም እዚሁ ዮሐንስ ወንጌል በዘጠነኛው ምዕራፍ ላይ ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ጠበል በሌለበት ሥፍራ አግኝቶት እኛ እመት (እምነት) የምንለውን አፈር በምራቁ ለውሶ ከቀባው በኋላ ‹ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ› ብሎ ልኮታል፡፡ ጠበል ምንም የማያስፈልግ ቢሆን ኖሮ ዓይነ ስውሩን ሰው ወደ ወንዝ ወርደህ ተጠመቅ ብሎ አይልከውም ነበር፡፡ ዛሬ ለታመሙ ሰዎች ጠበል ሒዱ ብለን ስንመክር ክርስትና ያልገባን ክርስቶስን የማናውቅ የሚመስለው ይኖራል አሁን ባየነው ታሪክ ውስጥ ግን ለበሽተኛው ‹ጠበል ሄደህ ተጠመቅ› ብሎ የመከረው ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ መፈወስ የሚቻለው ክርስቶስ ጠበል ተጠመቅ ብሎ ከተናገረ የታመመን መፈወስ የማንችለው እኛ ኃጢአተኞቹ ከንፈር ከመምጠጥ ይልቅ ሄደህ ተጠመቅ ብንል ምን አጥፍተናል? ጌታችን ሲያደርግ ያየነውን ነው እኔን ምሰሉ ብሎ የለ እንዴ? ዮሐ፡ 9፥7

በእነዚህ ሁለት ታሪኮች ግን ጌታችን ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግ ያለ ጠበል ሲሻው በምክንያት ሲሻው ያለ ምክንያት ሲፈልግ በጠበል ሲፈልግ በህክምና ሲፈልግ በቃሉ ሲፈልግ በዝምታ ሲፈልግ በቅዱሳን መላእክቱ ሲፈልግ ያለ ቅዱሳን መላእክቱ ማዳን እንደሚቻለው እንረዳለን፡፡

ጌታችን ለመጻጉዕ ‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ› ብሎ ሲነግረው ወዲያውኑ ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሔደ፡፡ እዚህ ላይ አባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳደረገው የበሽተኛውን እምነት እናደንቃለን ራሱን መሸከም የማይችለው ይህ በሽተኛ ተነሣና አልጋህን ተሸከም ሲባል አልሳቀም ‹እንዴት አድርጌ ነው ደግሞ አልጋ የምሸከመው› ብሎ አልጠየቀም በፍጹም እምነት ተነሣና ተሸክሞ ሔደ የሠላሳ ስምንት ዓመት ጓደኛውን ሰው ሳይኖረው አብራው የኖረችውን የተሸከመችውን ባለ ውለታው የሆነችዋን አልጋ ተሸከማት አለው – ተሸክሞ ሔደ፡፡

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ

https://youtube.com/@zechristos?si=zUG3tBXDKFNQT5i5

https://youtube.com/@sadorsisay294?si=c13-BuI8aZPW8chG

@sisaysador. https://www.instagram.com/invites/contact/?i=kbmstf6oagyq&utm_content=dww6ru2

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063663641982&mibextid=ZbWKwL

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ  አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

3 months, 2 weeks ago

#አንተ_ሰው_እስኪ_ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #ትምህርት_በእንተ_ሐውልታት መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ

https://www.youtube.com/@SADORSISAY

@sisaysador. https://www.instagram.com/invites/contact/?i=kbmstf6oagyq&utm_content=dww6ru2

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063663641982&mibextid=ZbWKwL

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ  አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

Facebook

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ | Addis Ababa

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ, Addis Ababa, Ethiopia. 6,828 likes · 4 talking about this. Religion ishues

[#አንተ\_ሰው\_እስኪ\_ንገረኝ](?q=%23%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%89%B0_%E1%88%B0%E1%8B%8D_%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8A%AA_%E1%8A%95%E1%8C%88%E1%88%A8%E1%8A%9D)!
3 months, 2 weeks ago
አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
3 months, 2 weeks ago

🌹🌹🌹🌹#ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕት🌹🌹🌹🌹

"ወሀሎ አሐዱ አሐዱ ብእሲ ዘስሙ ፒሉፓዴር ዘበትርጓሜሁ መርቆሬዎስ ብሂል ነገረ ገድሉ መዓርዒር እጹብ በግብር ለተናግሮ በቤክርስቲያን።

እንኳን ለታላቁ ሰማእት ቅዱስ መርቆሬዎስ ዓመታዊ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ
ቅዱስ መርቆሬዎስ ሀገሩ ሮም ነው አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈጸመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል። የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ “ፕሉፖዴር” ነው፤ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው በጥበብ በፈሪሓ እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ተሾመ ንጉሡ ዳኬዎስ ይባላል መምለኬ ጣዖት ነበር በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አጽናንቶት ዘመቱ መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሀዲው ንጉሥ ዳክዮስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለአማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን “አንሰ ኢይክህዶ ለአግዚአብሔር አምላኪየ /እኔ ጌታዬን አልክድም/ ላቆምከው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ። በመጨረሻም ኅዳር ፳፭ ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል፤ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን። ዘኁ፡ 22፥28

“ሰላም ለመርቆሬዎስ ሰማዕት ንጹሕ ድንግል ፈጻሜ ቃለ ወንጌል”፡፡(የወንጌልን ቃል የፈጸመ ለኾነ ለንጹሕ ድንግል ሰማዕት መርቆሬዎስ ሰላምታ ይገባል)

ግሩም ሮማዊ በመንፈስ ቅዱስ የታተምክ
እንደ ምድረ በዳ አበባ የምስጋናህ መዐዛ የጣፈጠ መርቆሬዎስ በበዓልህ ዛሬ ትባርከን ዘንድ ና በመካከላችንም ቁም

ኦ በኅሊናህ ቂም በቀል የሌለብህ
መዓዛህ እንደ ጣፋጭ ሽቱ የሆነ
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ (ከሃዲዎች) እንደ ደመና የበተኑህ
የተጋድሎ ምስክርነትን የፈጸምህ
ኦ መርቆሬዎስ ዘሮሜ (አርኬ)

የታላቁን ሰማዕት የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን የሰማዕቱን ገድል እኛም በሕይወታችን በመድገም የጽድቅን አክሊል እንድንቀዳጅ አምላከ ቅዱስ መርቆሬዎስ ይርዳን።

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ

https://www.youtube.com/@SADORSISAY

@sisaysador. https://www.instagram.com/invites/contact/?i=kbmstf6oagyq&utm_content=dww6ru2

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063663641982&mibextid=ZbWKwL

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ  አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

Facebook

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ | Addis Ababa

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ, Addis Ababa, Ethiopia. 6,828 likes · 4 talking about this. Religion ishues

***🌹******🌹******🌹******🌹***[#ቅዱስ\_መርቆሬዎስ\_ሰማዕት](?q=%23%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5_%E1%88%98%E1%88%AD%E1%89%86%E1%88%AC%E1%8B%8E%E1%88%B5_%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%B5)***🌹******🌹******🌹******🌹***
3 months, 3 weeks ago

🌹🌹🌹🌹ቅዱስ አቤላክ (ባኮስ)🌹🌹🌹🌹

በ34 ዓ.ም ጥምቀትን ያመጣልን ለሀገራችንም ሆነ ለአፍሪካ የመጀመሪያ ሐዋርያችን የሆነው ቅዱስ አቤላክ (ባኮስ) በዚህች ዕለት በሰሜን ተራራዎች ላይ ቅዱስ ያሬድ በተሰወረበት ቦታ ተሰወረ፡፡ እርሱም በጌታችን የተመረጡ የከበሩ ሐዋርያት እንኳን ወንጌልን በዓለም ለመስበክ ገና ከኢየሩሳሌም ባልወጡበት ወቅት ወደ አፍሪካ መጥቶ ወንጌልን የሰበከ ነው፡፡ የመጀመሪያው የአፍሪካ ሐዋርያ ቅዱስ አቤላክ (ባኮስ)፡- ይኽም ጃንደረባ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ንግሥት የሆነችው የህንደኬ የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊና አዛዥ የነበረ ነው፡፡ ከአባቱ እብነ መላክ ከእናቱ ስሂነ ሕይወት ታኅሣሥ 29 ቀን ተወለደ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ለበዓለ ፋሲካ በቤተ መቅደስ ይሰግዱ እንደነበረው ሁሉ ይኽም ጃንደረባ ከ4 ሺህ ማይልስ በላይ ተጉዞ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ በመለስ ላይ ነበረ፡፡ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ በተለይም ስለ ጌታችን መከራ መስቀል በዝርዝር የሚናገረውን ክፍል 53ኛውን ምዕራፍ ያነብ ነበር ነገር ግን ጃንደረባው ስለማን እንደሚናገር አልገባውም ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር በአካባቢው ወንጌልን ይሰብክ የነበረውን ሐዋርያውን ቅዱስ ፊሊጶስን ላከለት፡፡ እርሱም ጃንደረባው ያነበው የነበረውን መጽሐፍ ተረጎመለት፣ የከበረች ወንጌልን ሰበከለት፣ በመጨረሻም አጠመቀው፡፡ ሐዋርያው ባጠመቀውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በጃንደረባው ላይ ወረደ፡፡ ሐዋ 8፡26-40፡፡ ይህን ለእኛ ለኢትዮጵያውን እጅግ የሚያኮራን ታሪካችን ነው፡፡ ዛሬ በእጃችን ላይ በሚገኘው መጽሐፍ ውስጥ ባይኖርም በቆዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዞች ላይ ግን ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ጃንደረባውን ባጠመቀውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያው ጃንደረባ ላይ እንደወረደ ተጽፏል፡፡ (ዝኒ ከማሁ ገጽ 87፣ v.39.cord.alexand. in bible reg. angl-alique plures codd.mss)

ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ጃንደረባውን ያጠመቀበት ወንዝ ‹‹ቤተ ሳሮን›› በተባለችውና እስከዛሬም ድረስ ከኢየሩሳሌም 20 ማይልስ ርቀት በምትገኘው መንደር በኬብሮን መካከል ባለው ኮረብታ ሥር የሚመነጭ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጸሐፊ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ጀሮም ጃንደረባውን ‹‹የኢትዮጵያውያን ሐዋርያ›› በማለት ይጠራዋል፡፡ በሰፊው ለኢትዮጵያውያን ወንጌልን የሰበከ እርሱ ነውና፡፡ ጌታችን የመረጣቸው የከበሩ ሐዋርያት እንኳን ወንጌልን በዓለም ለመስበክ ገና ከኢየሩሳሌም ባልወጡበት ወቅት በ34 ዓ.ም ነው ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ በክርስቶስ አምና ወንጌልን የተቀበለችው፡፡ በምድሪቱም ላይ ወንጌል መነገር የጀመረው ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ 

ሐዋርያው ባኮስ (አቤላክ) ከኢየሩሳሌም ወንጌልን ተምሮና ተጠምቆ ወደ አክሱም እንደተመለሰ በመጀመሪያ ያጠመቀው ንግሥቲቷን ሕንደኬን ነው፡፡ ከእርሷም በኋላ መኳንንቱና መሳፍንቱ ሁሉ አምነው በባኮስ እጅ ተጠመቁ፡፡ ይኸውም በ34 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ባኮስ እስከ ኑብያ ድረስ ሄዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡ በዚህም ጊዜ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በባኮስ እየተሰጠ የነበረውን የወንጌል ብርሃን የበለጠ እንዲበራ አድርጓል፡፡ ከጃንደረባውም ጋር ሆነው በብዙ ቦታዎች አብረው ወንጌልን ሰብከው አምልኮተ ጣዖትን አጥፍተዋል፡፡

ከዚህም በኋላ ባኮስ ወደ የመን በመሄድ በዚያም ክርስትናን በማስተማር ብዙዎችን አሳምኖ ካጠመቀ በኋላ ወደ ፐርሺያ ከዚያም ወደ ሕንድ በመሄድ ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሟል፡፡ በመጨረሻም ጥንት ታፕሮባና (taprobana) ዛሬ ሲሎን በምትባለው ደሴት ወንጌልን በማስተማር ላይ እያለ በሰማዕትነት እንዳረፈ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ (lives of the most eminent fathers of the church, page 87) በሌላም በኩል ሐዋርያው ባኮስ (አቤላክ) ከመጠመቁ በፊት 35 ዓመት ከተጠመቀ በኋላ ደግሞ 41 ዓመት ኖሮ በኢየሩሳሌምም 3 ዓመት ተቀምጦ ወንጌልን ዞሮ ካስተማረ በኋላ በመጨረሻ በ79 ዓመቱ  ጥር 18 ቀን በሰሜን ተራራዎች ላይ ቅዱስ ያሬድ በተሰወረበት ቦታ እንደተሰወረ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ጽፈዋል፡፡

የቅዱስ አቤላክ (ባኮስ) ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!

#ከዜና_ገድለ_ቅዱሳን_የተወሰደ

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ

https://www.youtube.com/@SADORSISAY

@sisaysador. https://www.instagram.com/invites/contact/?i=kbmstf6oagyq&utm_content=dww6ru2

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063663641982&mibextid=ZbWKwL

#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ  አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏

Facebook

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ | Addis Ababa

መምህር ሳዶር ዘ ቅዱስ ፋኑኤል ሐመረ ኖኅ, Addis Ababa, Ethiopia. 6,828 likes · 4 talking about this. Religion ishues

***🌹******🌹******🌹******🌹***ቅዱስ አቤላክ (ባኮስ)***🌹******🌹******🌹******🌹***
3 months, 3 weeks ago
አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
3 months, 3 weeks ago

👉👉በዚህ ምስል ላይ ሁለት አሐት አቢያተ ክርስቲያናት ይታዩኛል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ናቸው

የአርመን ቤተክርስቲያን ስርዐት ይህ ነው ከብፁዕ አባታችን አቡነ ድሜጥሮስ ጋር አብረው የቆሙት የአርመን ሊቀጳጳስ ናቸው ቆብ የሚያደርጉት በአገልግሎት ሰዓት ብቻ ነው ከአገልግሎት በኋላ ቆባቸውን ቁጭ አድርገው ጸጉራቸውን አበጥረው ነው የሚሄዱት

የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን ስርዓት ደግሞ ተመልከታት እናንተዬ ስሟ ብቻ ይበቃል እኮ

👉 ስንድዋ እመቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርዓትዋን ተመልከቱ

አንድ መነኩሴ ከመነኮሰ በኋላ ሞቀኝ አደፈብኝ አለቀብኝ ጎረበጠኝ ምናምን የሚባል ምክንያት የለም ሌሊትም ቀንም አስኬማው ከአባቶች እራስ አይወርድም ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ

ሙሉ ስርዓት የወሰደችው ቀራንዮ ነው በመድኃኔዓለም ራስ ላይ አይሁድ የሾህ አክሊል ጎንጉነው ጭንቅላቱን እስኪበሳሳው ድረስ ሲደፉበት እሾሁ ወጋኝ አመመኝ ደከመኝ አሳርፉኝ አውልቁልኝ አላለም የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ምሳሌውን የወሰደችው ከዚህ ነው

ደስ ሲልህ ምታወልቀው ደስ ሲልህ ምትለብሰው ከሆነ ምኑን ምሳሌ ሆነው

ስርዓትማ ነበርን ታዲያ ስርዓት ብቻውን ምን ያደርጋል
ያለ ፍቅር ስርዓት ብቻውን ምን ትርጉም አለው እንኳን ስርዓት ምግባር የሌለው ሃይማኖት ምን ይሰራል

👉 እውነቱን ለመናገር በክፋት በቅናት በምቀኝነት ዲያብሎስ በእድሜ ካልሆነ አይበልጠንም መጽሐፍም አንትሙሰ ተአክዩ እምሰይጣን እናንተ ከሰይጣን ትከፋላችሁ ይላል

እኛን የጎዳን ወደኋላ ያስቀረን በቀላችን ክፋታችን ነው

አቡነ ሺኖዳ የግብጹ ፓትርያርክ የነሐሴን ጾም ጸሎት ሰብሐተ ነግህ ሰዓታት ቅዳሴ አይተው እመቤታችን በዚህ ሳምንት ስንት ቀን ተገለጸች ብለው ጠየቁ እረ ምንም የለም ይላቸዋል እሳቸውም በጣም አዝነው በጣም ክፉዎች ናችሁ አሉ ይባላል

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ልጆች ያደረገን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏🙏

5 months, 3 weeks ago
***🌹******🌹***[#የሰናፍጭ\_ቅንጣት\_ምሳሌነት](?q=%23%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%8A%93%E1%8D%8D%E1%8C%AD_%E1%89%85%E1%8A%95%E1%8C%A3%E1%89%B5_%E1%88%9D%E1%88%B3%E1%88%8C%E1%8A%90%E1%89%B5) ***🌹******🌹***

🌹🌹#የሰናፍጭ_ቅንጣት_ምሳሌነት 🌹🌹

የሰናፍጭ ዘር ስትዘራ መጠኗ ከዘር ሁሉ ያንሳል፤ በአደገች ጊዜ ግን ከአታክልቶች ትበልጣለች፤ የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች፡፡ ምሳሌነቷም ለመንግሥተ ሰማያት መሆኑ ተገልጧል፡፡ እዚህ ላይ መንግሥተ ሰማያት የተባለች ወንጌል ናት፡፡ ምክንያቱም በሕገ ወንጌል ጸንቶ የኖረ መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳልና፡፡
በዚህም መሠረት ሰናፍጭ ለወንጌል ምሳሌ የሆነችበት ምክንያት ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ፍጽምት ናት፣ ነቅ የለባትም፤ ወንጌልም ነቅዓ ኑፋቄ የሌለባት ፍጽምት ናት፡፡
➛ ሰናፍጭ ላይዋ ቀይ ውስጧ ነጭ ነው፤ ወንጌልም በላይ ደማችሁን አፍስሱ ትላለች በውስጥ ግን ሕገ ተስፋ ናት፡፡ ይህም ተስፋ መንግሥተ ሰማያት ነው፡፡
➛ ሰናፍጭ ጣዕሟ ምሬቷን ያስረሳል፤ ወንጌልም ተስፋዋ መከራን ያስረሳል፡፡
➛ ሰናፍጭ ቁስለ ሥጋን ታደርቃለች፣ ወንጌልም ቁስለ ነፍስ ታደርቃለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ደም ትበትናለች፤ ወንጌልም አጋንንትን፣ መናፍቃንን ትበትናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከምትደቆስበት ተሐዋስያን አይቀርቡም፤ ወንጌልም በእውነት ከምትነገርበት አጋንንት መናፍቃን አይቀርቡም፡፡
➛ ሰናፍጭ ስትደቆስም ስትበላም ታስለቅሳለች፤ ወንጌልም ሲማሯትም፣ ሲያስትምሯትም ታሳዝናለች፡፡
➛ ሰናፍጭ ከበታቿ ያሉትን አታክልት ታመነምናለች፤ ወንጌልም የመናፍቃንን ጉባኤ ታጠፋለች፡፡
➛ ሰናፍጭ አንድ ጊዜ የዘሯት እንደሆነ ባመት ባመት ዝሩኝ አትልም፤ ተያይዞ ስትበቅል ትኖራለች፡፡ ወንጌልም አንድ ጊዜ ተዘርታ ማለትም በመቶ ሃያው ቤተሰብ ተጀምራ እስከ ምጽአት ድረስ ስትነገር ትኖራለች፡፡
➛ ሰናፍጭ የሰማይ ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ እንድትሆን፣ ወንጌልም ሕዝብም አሕዛብም ተሰብስበው መጥተው እስኪያምኑባት ድረስ ደግ ሕግ ትሆናለች፡፡

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago