Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ግን እግዜር እንዴት ነህ?*
ሰማይ ቤት ሰላም ነው?. . . .
👉by.p.belete ✍️ ያ ታዛዡ ባሪያህ ኖህ እንደምንድነው?
መርከብ አሰራሩን ‘ማያሳየን ምነው?
መውጫና መግቢያውን
አንተው እንዳየኸው
ባቡር ተስፋ አድርጎ
ሀይቅ በሀይቅ ነው
ስለዚህ ባሪያህን ቀጭን ትዕዛዝ ስጠው. . . .
ባቡሩ እስኪመጣ
ክረምቱ እስኪወጣ
ሙያ ያስተምረን
ወይ መርከብ ያውሰን. . . . . . . . . .
ዙፋንህ እንዴት ነው? ያ ‘ማይናወጠው?. . . . . . . .
ሳኦልስ ደህና ነው?
ጦሩ በጁ አለ? ዛሬም ወርዋሪ ነው?
እሱን ያህል ንጉስ
እሱን የሚያህል ሰው
ዝም ብሎ ማለፉ
ምንም “ትውፊት” ሳይተው
ራዕይ ሳይኖረው. . . .
በከንቱ መሞቱን
ሲያስበው ሲያስበው
እንዲያው ምን ተሰማው?
ገባዖናውያን ያሉትን ሲሰማ
ትንሽ አለቀሰ? ትንሽ ልቡ ደማ?
“የማይሆን አይሆንም
የሚሆን አይቀርም
ያንተ ልብ መድማት
ምንም አይለውጥም
ይልቅ ይህን ትውልድ
በኔ ይብቃ በለው
ስህተት አይደገም
በልና አስተምረው”
ብሎሃል በልልኝ
ይሄ መልዕክትህ ችግር ከገደፈ
ታሪክ ታሪክህን ሳይደግም ካለፈ
ስርየት ሆኖልሃል. . . . .ይቅር ተብለሃል
ብለህ ንገርልኝ. . . . .
እግዚአብሄር ሃያል . . . . እንደምን ከርመሃል?
እኛ ባንተ ምህረት – ዛሬ ላይ ደርሰናል
የደረሰብንም ያደረሰብንም
የደረሰልንም የደረሰንንም
አንተው ታውቀዋለህ
ስሞታ ላሰማ ቃል አላባክንም
ሰማይ ቤት- ደጃፍህ
እንደምን ከራርሟል?
ደጉ አጎታችን
ሎጥ እንዴት ሰንብቷል?
ሚስቱስ እንደምን ነች?
ዛሬም አንዱ ቦታ የጨው ሀውልት ነች?
በዚህ ውድ ኑሮ
እንኳንም ያልኖረች
ዛሬ እዚህ ብትገኝ
ሃውልት እንደሆነች
ይሄኔ ብዙ ቤት
ብዙ ወጥ ሆናለች!
ዛሬ ግብረ ሰዶም
መብት እንደተባለ
ሲሰማ ይህን ጉድ
እኮ ሎጥ ምን አለ?
ይህን ጉድ እያየ
ህዝቡ በመገረም
ወደ ላይ አንጋጦ
ቢያይም እሳት የለም
ቢጠብቅ አፍጥጦ
ከቶም ዲን አይዘንብም. . . . .
እንደውም አንዲት ሴት ምን አለች መሰለህ
“እግዜር ይህን ትውልድ
ሳይቀጣ ካለፈው
የሰዶምን ህዝቦች
ይቅርታ ሊጠይቅ አስቧል ማለት ነው”
እና. . . . . .
ያለችው እውነት ነው?
እኔ ምን አውቃለሁ. . . . . .
ሊመጣ ነው ሲሉኝ . . . አብሬ የምጨነቅ
አይ ቀርቷልም ሲሉኝ . . . በደስታ የምቦርቅ
የምፈልገውን ከቶ ያላወቅኩኝ
ማስተዋል የሚባል
ከቶ ያልፈጠረብኝ
እኔ ምን አውቃለሁ?
እግዜር አምላካችን . . . አንተ እንደምን አለህ?
“ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ” ብለው በመወድስ
ጧት ማታ ‘ሚያመልኩህ መላዕክቶችህስ?
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ለዘላለም ንገስ!
ዲቦራ እንዴት ነች?
እዛም ትፈርዳለች?
ዛሬም ቅን ነው ፍርዷ?
ፍትህ ነው መንገዷ?
ለሷም ሰላምታዬን
ባክህ አቅርብልኝ
ለሷ አይነቱ ሰው ቦታ እንደሌለን
አብረህ ንገርልኝ
ሙያሽን ቀይረሽ
ገበሬ ሁኝ በላት
ፍሬው ሳይቀጠፍ
ምናልባት ብትበዪ
የማደግ ተስፋ ያለው
ብርትኳን ትከዪ
ብለህ ንገርልኝ. . .
ጌታ ሆይ ለክብርህ አንተ እንደምንድነህ?
በታላቁ እጅህ
በጣቶችህ የፃፍከው
አስርቱን ትዕዛዛት
ቃልህን የያዘው
ያንን ታላቅ ታቦት. . . . .
እስኪ ልጠይቅህ . . .ከወዴት ሰወርከው?
አንተ’ኮ አዋቂ ነህ
እንኳንም ደበቅከው
እንኳንም ሰወርከው
ከግለሰብ ጋራ
ጠልተው ውድድሩን
ከትዕዛዛቱ ውስጥ
አትስረቅ ‘ሚለውን
ሊቀንሱ የሚሹ
መንግስታት በዝተዋል
እንኳንም ደበቅከው
ከመሻሻል ተርፏል።
እንደምነህ አዶናይ? ግዛትህ እንዴት ነው?
ሰማይ ቤት ሰላም ነው?
ዘኬዎስ አጭሩ
ዘኬዎስ ልባሙ ከቶ እንደምንድነው?
ጉምሩክ ነው ስራው? አሁንም ይቀርጣል?
ወይስ ሌላ ስራ አግኝቶ ቀይሯል?
ዛሬም እንደድሮው
ዛፍ ይንጠላጠላል?
ወይስ በሰማይ ቤት
ቁመቱ ጨምሯል?
እሱ ምን አለበት. . .
በሰላሙ ጊዜ
በቀላሉ አምልጧል
የአቅሙን አድርጐ
ባንተ አይን ታይቷል
ጌታ ሆይ. . . .
ያሁን ዘመን አጭር ሃሞቱ መፍሰሱን
ህሊናን ለማርዘም
ወይንም ለማስፋት ያለመፈለጉን
አንድ ባንድ አስረዳው
ዳሩ ምን ዋጋ አለው!
የምን ግንድ አግኝቶ
ምንሰ ላይ ይወጣል?
ሙቀቱ በዝቶበት
ዛፉ ሁሉ ጠፍቷል!
ኧረ እግዜር እባክህ በስልጣን በክብርህ
ሁሉን በተቤዠው በአንድያ ልጅህ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!
እንዴት ነህ ኤሎሄ? ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
መግደላዊት ማርያም ጤናዋ እንደምን ነው?
ይኸውልህ እግዜር. . . .
ባነሳው ብጥለው
በፍፁም ያለገባኝ
ለማርያም የሚሆን
አንድ ጥያቄ አለኝ . . .
“ያኔ ባንቺ ጊዜ . . .
እዚያ ባንቺ አገር
“big brother” ‘ሚባል
ተወዳድረሽ ነበር?”
ብለህ ጠይቅልኝ . . .
ዛሬ ቢሆን ኖሮ . . .
ብለህ ንገርልኝ
“እንኳን ተወዳድረሽ . . . እንኳን እርቃን ታይተሽ
አይደለም አይንሽን
በጨው ተለቃልቀሽ
አይደለም ካክደሽ
አይደለም ተሳልቀሽ . . .
ወጋሪሽ ብዙ ነው
ይቅርታ ጠይቀሽ!
በሞላ ወርዋሪ በረከሰ ድንጋይ
ቢሻው በትዊተር ቢሻው በፌስቡክ ላይ . . . .
እ. . . . . ሺ! ጌታችን ሆይ. . . . .
ግን አንተ ደህና ነህ?
ሁሉም ነገር ሰላም?
ይሁዳስ ደህና ነው?
ይነግዳል ዛሬም?
“ከሰላሳ ብሩ ያኔ ያልከፈልከው
አራት ብር ከአምሳ VAT አለብህ” በለው
ስለንግድ ፈቃድ ከቶ እንዳይጨንቀው
ታዋቂ ነውና ማንም ሰው አይነካው
ዝም ብሎ መጥቶ ይነግድ ንገረው።
መጠየቅ አይቸከኝ . . .
አንተም በቃ አትለኝ . .
በል እንግዲህ እግዜር . . . ልሰነባበትህ
አንተን ሁሉን ቻዩን
ሰላም ሁን ማለቱ
ጉንጭ አልፋ እንዳይሆን
እንዳይቀር በከንቱ
ደግሜ ሌላ ቀን
እንዴት ነህ እንድልህ
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
ብዬ እንድጠይቅህ
እኔን ሰላም አርገኝ
ለኔ ጤና ስጠኝ
መጠየቅ አይቸከኝ . . . . .
አንተም በቃ አትለኝ ።
👉by p.belete ababu ✍️*
ሻሸመኔ
ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
[የእርሶ ስም በየት ፊደል ይጀምራል?
A፡ጉረኛ?
B፡ተጎጂ?
C፡ለፍላፊ?
D፡ዝምተኛ?
E፡ቆንጆ?
F፡አፍቃሪ?
G፡ጠቢብ?
H፡ደረቅ?
I፡ልዩ?
J፡ብልጥ?
K፡ታጋሽ?
L፡ተጫዋች?
M፡የዋህ☺️
N፡ጣፋጭ?
O፡አይናፋር?
P፡ተፈላጊ?
Q፡ተሳዳቢ?
R፡ውብ ?
S፡ስሜታዊ?
T፡አስተዋይ?
U፡ጠበኛ?
V፡ነገርኛ?
W፡ቆጣቢ?
x፡ታማኝ?
y፡አለው ሚል?
Z፡ሰገጤ?
እኔ M~☺️ ነኝ](https://t.me/awdekalat_2112)
እልልታ
ጭብጨባ
ከአውደ ምህረቱ ተነስቶ ይነፍሳል፤
የሰማእቷ ታ'ምር እንደ ጉድ ይወሳል።
"ሰምታኛለች እናቴ..."
"ታውቃለች አርሴማ..."
ክብሯን የሚመጥን
ይገባል ስለት - ጧፍ፣ ጥላ፣ ብር፣ ሻማ።
ሰው ይጸልያል
ሰው ይለምናል ክፍተቱን አይቶ፣
እኔ ከንቱ ግን
የጎደለኝን አላውቅም ከቶ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፣
ደጅሽን ስረግጥ እታደሳለሁ።
እዪኣት ያቺን ሴት
ከአትሮንሱ ጀርባ የምትዘምረው
ስምሽን ደጋግማ የምታነሳው፤
እኔ እስከማውቃት
ፊደል የሚያንቃት
ኩልትፍ አንደበት - ነው የነበራት።
ምን ጸልያ ነው አፏ የተፈታ?
ምን ብላሽ ይሆን
ቃል አቅሙን አጥቶ ለእሷ የተረታ?
የእኔማ ምላስ አግድም ለፋፊ
ለ'ንቶ ፈንቶ እንጂ ለጸሎት ታጣፊ።
እይው ያንን ሰው
ኑሮ የደቆሰው
የደስታን እንባ ሞልቶ ሚያፈሰው፤
እኔ እስከማውቀው
ሞት 'ሚናፍቀው
ማጣት በዝቶበት ገዳይ ሚፈልግ
ተስፋን ተነጥቆ
አለመኖርን የሚያነበንብ።
ምን ሰጥተሽው ነው ፊቱ የፈካ?
ምን አግኝቶ ነው
የደስታው መጠን ጣሪያ የነካ?
እኔ ሳቅ አላውቅ እንባም አይገደኝ
መኖርም መሞት ትርጉም አይሰጠኝ፤
ብቻ እመጣለሁ
ብቻ አይሻለሁ፤
ደጅሽን ስረግጥ ነፍስ እገዛለሁ።
#ኤልዳን
tiktok - ldan291
ልቧን እንዳትሰበረው ?
እሷ አንተን ብላ
ስትጠጋህ አምና፣
ፅሀይ እንጅ መሆን
አትሁን ደመና፣
ሰው እኮ አላጣችም
ነው እንጂ አንተን ወዳህ
ሳታስብ ተግባብታህ
በድንገት ተላምዳህ፣
ልቧ አንተን ቢልም
ፍቅርህን ተርቦ፣
የወደፊት ደስታን
አስቦና አንግቦ፣
ጥሩ አርገህ አፍቅራት
ልብህን ንገረው ፣
አልወድሽም እያልክ
ልቧን አትስበረው፣
ሰመተሀል ጀግናው. @Yonasss19
????????????????????????????
ጥሞና ግሮሰሪ
ተከሳሽ እገሌ፣ በቀደመው ወር ጥር
አራት ሳት' ገደማ፣ ላምስት' ሲቆጥር
ከላዩ ደርቦ የቻይና፣ ሌዘር ኮት
ተሸፋፍኖ ከሰው፣ ጥሶ ከመለኮት
እየተገላበጠ ተራምዶ በእንክብል
ጥቁር ተከናንቦ አርጎ የፊት ጭምብል
(የማይታይ መስሎት!)
ግራጫ ቀለም፣ አርጎ የክት ሱሪ
ደርድሮ ሲጠጣ፣ ገነት ግሮሰሪ
ባይን አማኝ ምስክር
በባዶ ክርክር
ከዛሬ ጀምሮ፣ ከመቅደስ ተባሯል
ለጥሞና ጊዜ፣ ለስድስት ወር ታስሯል።
(ተከሳሽ መልስ አለህ?)
:
እርግጥ ነው
አልክድም ክሳቹን፣ ቅዳሜ አመሻሽ ለውስኪ ስገባ
የኔ ጥያቄ ግን፣
ታማኙ ምዕመን ፣ ያይን ምስክሩ ምን ሊሰራ ገባ?
:
:
(ከስድስት ወር በኋላ)
:
:
የመሰከረበት ያ ታማኝ አገልጋይ
ጥሞና ተብሎ ከታሰረው ታጋይ
የነደደ እሳት፣ በስካር ቆስቁሰው
ከሸንጎ ቆመዋል፣ ክፉኛ ተቧቅሰው
ሸንጎ ተጀምሮ ክሱ ሲዘረዘር
*
ለካ!
ለጥሞና ጊዜ፣ የታሰረው ወጣት
ገነት ግሮሰሪን፣ ለልማት ስላጣት
ሆዱና አድማሱን፣ እስከ ጥግ አስፍቷል
በጥሞና ጊዜው፣ ግሮሰሪ ከፍቷል።
(ጥሞና ግሮሰሪ)
አይን አማኙም ከዚሁ፣ ሰባት ጠጥቶ
ሳይከፍል በጉራ፣ ጥሶ ሄዷል ወጥቶ።
ይልቅ በቢሉ ውስጥ እንዲህ ፅፎለታል
ጠላትህ እዳህን፣ ጠቅልሎ ከፍሎታል።
¶
¶
በጥሞና ጊዜ
ከምዕመን ለማሸሽ፣ ልክ አግባብ ቢኖርምኀ
በግ ከበግ ጋር እንጂ፣ ተኩላ ጋር አይኖርም።
ለስድስት ወር ባለም'፣ የከረመች ነፍስ
ወደ ውጭ እንጂ፣ ወደቤቱ አትነፍስ።
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago