Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
የሰው ልጆችን የመጥፊያ የምጽዓት ሰዓትን ለመጠቆም በተምሳሌትነት የተቀመጠው ሰዓት አንድ ሰከንድ የጨመረ ሲሆን፣ በዚህም የዓለም መጥፊያ ጊዜ ከመቼው በበለጠ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነው ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
"በኔ ስልጣን ዘመን ወደ ማርስ እንሄዳለን የአሜሪካንን ባንዲራም እንተክላለን ብለዋል ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድትራፕ" ኤለን መሰክም ደስታቸውን ሲገልፁ ታይተዋል።
ለበለጠ መረጃ 👇👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
ጥቂት ስለ መሬት መንቀጥቀጥ እና የሕንጻ መዋቅር ዲዛይን
#Ethiopia | የመሬት መንቀጥቀጥ ከመሬት የውስጠኛው ክፍል በድንገት በሚለቀቅ 'ኢነርጂ' ምክንያት የላይኛው የመሬት ክፍል ላይ በሞገዶች (seismic waves) አማካኝነት የሚተላለፍ ንዝረት ወይም መንቀጥቀጥ ነው።
ለመሬት መንቀጥቀጥ በተጋለጡ አካባቢዎች ያሉ ሕንፃዎች የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እና ነዋሪዎችን ለመጠበቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ኃይሎችን እንዲቋቋሙ ሆነው የተነደፉ መሆን አለባቸው። ይህ የመሬት መንቀጥቀጥን የሚቋቋም ንድፍ earthquake-resistant design (ERD). በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም ለመስራት ልዩ የምህንድስና ትምህርት እና ልምዶችን ይፈልጋል።
በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት መሬቱ በምን ያህል ፍጥነት እንደሚንቀጠቀጥ የሚለካበት በ PGA(Peak Ground Acceleration) መንገድ ነው። ይህ ለዲዛይን ዋናው መሰረት ነው ፤ እርሱም ከፍተኛውን የመንቀጥቀጥ ፍጥነት ከመሬት የስበት ኃይል (9.81 m/s²) ጋር አዛምዶ ያሳየናል። ከፍ ያለ PGA ማለት ጠንካራ መንቀጥቀጥ እና የበለጠ ጉዳት ሊያስከስት የሚችል ማለት ነው።
PGA ከ0.1%g ያነሰ ከሆነ ላናስተውለው እንችላለን ፤ ከ 0.1-1% g ከሆነ ምንም ጉዳት ሳያስከትል በትንሽ እናስተውለዋለን ፤ ከ1-3% g ቀላልና አነስተኛ ፤ ከ3-10% መካከለኛና ትንሽ ጉዳት ፤ ከ10-30% በጣም ጠንካራ የመዋቅራዊ ስንጥቆች (Very strong, structural cracks )፤ከ30-50% ከባድና ከፍተኛ ጉዳት፤ ከ50-100% ኃይለኛና የሕንፃዎች መፈራረስ ፤ ከ100% g በላይ ከሆነ ደግሞ እጅግ በጣም ከባድና አጠቃላይ ጥፋትን ያስከትላል።
የኢትዮጵያ የሕንፃ ኮድ ኢትዮጵያ ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ የሆነ አካባቢ እንዳላት በግልጽ ያስቀምጣል።
ለመሬት መንቀጥቀጡ እንዳላቸው ተጋላጭነት ቦታዎቹን አዲሱ የ2015ቱ ኮድ( EBCS EN: 2015) Zone 0, Zone 1, Zone 2, Zone 3, Zone 4 እና Zone 5 በማለት በ6 ምድቦች አስቀምጧቸዋል። በነገራችን ላይ ይህ ኮድ በጣም የተሻለ ቢሆንም እንኳን በባለሙያዎች ዘንድ በቂ ግንዛቤና ይሁንታን ሳያገኝ እና በበቂ ሁኔታ ተግባራዊ ሳይሆን አዲሱ ኮድ እንደተባለ ይኸው አስር አመት ሞላው ፤ በኮዱ አጠቃቀም ዙርያ በሥራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችንና ያሁኑን ክስተት ከግምት ወስጥ በማስገባት በፍጥነት መከለስ (ክለሳው መጠናቀቅ) ይኖርበታል።
በአዲስ አበባ ያሉ ሕንጻዎች አሁን ባለው የሕንጻ ኮድ (EBCS EN-1998-1:2015)መስፈርት መሰረት ለ 0.1g (ማለትም 10% g) PGA የተሠሩ እና ሊሠሩ የሚገባቸው ናቸው። የቀድሞው ኮድ እንኳን (EBCS 8 1995) በአዲስ አበባ ለሚሰሩ ሕንጻዎች ከ 5% g እስከ 7% g PGA ታሳቢ ተደርገው እንዲሰሩ ያዛል ። በዚህም መሰረት እስካሁን ባለው ሁኔታ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት ጥንካሬ (ማለትም 1% g) በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉት በበቂ ባለሙያ እና ኮዱን ተከትለው የተሠሩ ሕንጻዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀት በጣም ትንሽ ነው። ነገር ግን፣ ከመሬት መንቀጥቀጡ በተወሰኑ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለው አካባቢ፣ 10% g የመሬት መንቀጥቀጥ በሚገመትበት ቦታ ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።
ይህ ማለት ግን ስጋቱ የለም ማለት አይደለም ፤ የመሬት መንቀጥቀጡ እየጨመረበት ያለበት ሁኔታ እና ከዚህ ቀደም በ1961 ካራቆሬ ላይ በሬክተር ስኬል 6.5 ተከስቶ የሰዎች ሕይወት እንዳለፈ ሲታሰብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሰፈልግ እንረዳለን ።
ሊደረጉ የሚገባ ጥንቃቄዎች
ተደጋጋሚ እና ጥልቅ የባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የቀጥታ ውይይትና ገለጻ ችግሩ እስኪቀረፍ ድረስ በቋሚነት በሁሉም የመንግስት እና የግል መገናኛ ተቋማት ያስፈልጋል ። ጉዳዩ በመግለጫ ብቻ የሚታለፍ አይደለም ።
አደጋ ቢከሰት ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች ቀድሞ ማስተማር እና ማዘጋጀት
ያረጁ ሕንፃዎች - በዲዛይን ጊዜ የሚታሰበው የሕንጻዎቹ የአገልግሎት ዘመን ያበቃ (ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው)ያረጁ ሕንፃዎች በብዙ ምክንያት ለዚህ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። በዘመን ብዛት በCreep effect እና fatigue ምክንያት የኮንክሪት ስትራክቸር ጥንካሬ ይቀንሳል። በንጉሡ ጊዜ ተሠርተው አሁንም አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሕዝብ መገልገያ ሕንጻዎች ማለትም ትምህርት ቤት ፤ የህክምን ተቋማትና ሌሎችም ። እነዚህ የማጠናከርያ ሥራ (Retrofitting) ይፈልጋሉ ።
በድንጋይ ግንብ (Masonry) ብቻ እና መሰል የአርማታ ብረት የሌላቸው ግንባታዎች።
ተገቢውን የአፈር ጥናት፣ ዲዛይን እና ክትትል ሳይደረግላቸው የተገነቡ ግንባታዎች ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው።
በሚገባው ባለሙያ ዲዛይን ያልተደረጉ እና ያልተገነቡ ግንባታዎች ለዚህ ተጋላጭ ናቸው። ከተገነቡ በኋላ በተለይ ግርግዳቸውና ሌሎች የሕንጻ አካላት ፍርሰው ባዶ ሲሆኑ በወለሎቹ መካከል የጥንካሬ ልዩነት ሲከሰት (Soft stories) በሰላም ለዘመናት የኖሩትን ሕንጻ ለአደጋ እንዳርጋቸዋለን።
የሕንጻ ኮድ ክለሳውን ማፋጠን
መልካሙን ነገር ያሰማን
ጠፈርተኞች ጠፈር ላይ ሲተኙ እራሳቸውን በቀበቶ ልክ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ያያይዛሉ ይሄም የሆነበት ምክንያት ጠፈር ላይ ግራቪቲ ወደ ዜሮ የተጠጋ ሰለሆነ ዝንብለው ቢተኙ በቀላሉ ሰለሚንሳፈፉ ወይም የተረጋጋ እንቅልፍ መተኛት ሰለሚቸገሩ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ???????
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13
ቴሌግራም ከጀመራቹ ምን ያክል ቀን ሆናቹ
ዛሬ PAWS የተሰኘውን airdrop ከፈት ሳደርግ ቴሌግራም መጠቀም ከጀመርኩ 1656 ቀን አንደሆነ ነገረኝ በነገራችን ላይ ቴሌግራም ከተጀመረ 12 አመቱ ነው።
?እስኪ እናንተስ ቴሌግራም መጠቀም ከጀመራቹ ስንት ቀን ሆናቹ።
ከታች ያለውን link ተጭናቹ ተመልከቱ ከዛም comment ላይ screen shot አድርጋቹ ላኩልን react እንሰጥበታለን?
?
"በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት አሁን ረገብ ብሎ ወደ ታች መውረድ ጀምሯል"
በኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ በአዋሽ ፈንታሌ አካባቢ በመሬት ውስጥ የተፈጠረው የቅልጥ አለት እንቅስቃሴ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እና በሩቅ ቦታዎች ደግሞ የመሬት ንዝረት እንዲፈጠር ማድረጉ ይታወሳል።
የመሬት መንቀጥቀጡ አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የመሬት ንዝረት አስከትሎም ነበር።
በኢትዮጵያ በስምጥ ሸለቆ ውስጥ ለ22 ቀናት ወደ መሬት ለመውጣት ተፈጥሯዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ቅልጥ አለት የመወጠር ሁኔታ አሁን ረገብ ብሏል፤ አሁን ባለን መረጃ ቅልጥ አለቱ ወደታች እየወረደ ነው ብለዋል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሌዊ (ዶ/ር) በተለይ ለኢቢሲ ሳይበር።
በዚህም ምክንያት ባለፉት 2 ቀናት የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ዝቅተኛ መሆኑን ነው ያስታወቁት።
ቀደም ሲል የነበረው ስጋት ባለፉት ቀናት ቀንሷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ነገር ግን በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምንገኝ እንደመሆናችን ስጋቱ ተመልሶ ሊመጣ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ስለ መሬት መንቀጥቀጡ በማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው ያሉት ዶ/ር ኤሊያስ፤ ሚዲያው ሀሰተኛ መረጃ ከማሰራጨት ይልቅ በጥናት የተረጋገጠ እና ትክክለኛ መረጃ ብቻ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ስምጥ ሸለቆ እና አካባቢው በተፈጥሮ ለመሬት መንቀጥቀጥ ተጋላጭ መሆኑ የማይቀየር ተፈጥሯዊ እውነታ ነው፤ እንደ ሀገር፣ እንደ ህዝብ የራሳችንን ጥንቃቄና ዝግጀት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
ማንኛውም የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋን በተመለከተ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂዮ ፊዝክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በመገናኛ ብዙኃን ተደራሽ እንደሚያደርግ በመጠቆም ህብረተሰቡም ይህንኑ እንዲከታተል አሳስበዋል።
በላሉ ኢታላ
ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል?????
ለ8 ቀናት አቅደው ወደጠፈር የሄዱ ጠፈርተኞች ለሥምንት ወራት ሊቆዩ እንደሚችሉ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ8 ቀናት ወደጠፈር የሄዱት ጠፈርተኞች እስከፈረንጆቹ 2025 ሊቆዩ እንደሚችሉ ተሰምቷል፡፡
ከሁለት ወራት በፊት አሜሪካውያን ጠፈርተኞች ወደዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ የሙከራ ተልዕኮ ሲላኩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደምድር ይመለሳሉ ተብሎ ነበር፡፡
ሆኖም ግን ነገሮች በተያዘላቸው እቅድ መሄድ ሣይችሉ ቀርተዋል፡፡
በዚህም እስካሁን ባሪ “ቡች” ዊልሞር እና ሱኒታ ዊሊያምስ ጠፈር ላይ እንደሚገኙ የተገለጸ ሲሆን፥ አሁንም በዚያው እንደሚቆዩ ነው የተገለጸው፡፡
የ61 ዓመቱ ዊልሞር እና የ58 ዓመቷ ዊሊያምስ የቦይንግ ስታርላይነር የጠፈር መንኮራኩር ሰዎችን ይዞ በመደበኛነት ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት እንዴት እንደሚሰራ ለማየት የተነደፈ ሙከራ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
ሆኖም ያልተጠበቀ የቴክኒክ ችግር መፈጠሩም ነው የተገለጸው፡፡
ስለዚህ ወደ ጠፈር ጣቢያው በሰላም ቢደርሱም በስታርላይነር ወደ ምድር ለመመለስ ደህንነቱ የተጠበቀ ካልሆነ አማራጭ የመጓጓዣ ዘዴ ያስፈልጋቸዋል።
የናሳ ባለስልጣናት እስካሁን በዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ገልጸው፥ ሆኖም ግን ሌሎች አማራጮች እንዳሉን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን እቅድ አዘጋጅተናል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
እየታሰበበት ያለው አንዱ አማራጭም ሁለቱን ጠፈርተኞች በመስከረም ወር ሊደረግ ከታቀደው ተልዕኮ ወደ ምድር እንዲመለሱ ማድረግ ሲሆን፥ ይህም በፈረንጆቹ 2025 የካቲት ወር ላይ መሆኑ ነው፡፡
ይህም የጠፈር ተመራማሪዎችን ከታቀደው የሥምንት ቀን ቆይታ ወደ ሥምንት ወራት የሚያራዝም እንደሆነም ነው የዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ ያስታወቀው፡፡
በዚህም ተጨማሪ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ናሳ ለሁለቱ የጠፈር ተመራማሪዎች አልባሳትን ጨምሮ ምግቦችን እና ቁሳቁሶችን ለማድረስ ስፔስ ኤክስ ሮኬት ተጠቅሟል ተብሏል።
የናሳ ባለስልጣናት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪደረግ ድረስ አንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ሊወስድ እንደሚችል ተናግረዋል።
ባለፈው ወር በአጭር ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጠፈርተኞቹ ወደምድር እንደሚመለሱ እርግጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን አስታውሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡
subscribe?????
https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago