Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 6 days ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 week, 2 days ago
በዝምታ ልብን ከሚበላ ሀዘን አላህ ይጠብቃችሁ! አሚን በሉ 🙌
በዝምታ ልብን ከሚበላ ሀዘን አላህ ይጠብቃችሁ!
አሚን በሉ 🙌
አደራ👍
bonus
……… ሀቢል ስለ እናቱ ሲያወራ ክፍት አለኝ። ስቶልድክ የሞተች እናትህስ ልለው አቃጣኝ… እኔ ያደግኩበት ትዝ አለኝ… አልሀምዱሊላህ አላህ የርሀማት እድለኛ ነው። ወንድሜ ቢያንስ በሰላም አድጓል… የቀን ተቀን እሳቴን አልቀመሰውም… ምን ላድርግ አልንገረው? ግን ጊዜ የሌለኝ… ያክል ነው ሚሰማኝ… መቼ ይለኛል ውስጤ… አህመድስ የሆነ ነገር ቢያደርግብኝ… ግራ ተጋባው…
……ምን ተብሎ ይወራል እንዴት ይነገራል? ከአንድ ሁለት ሶስት ዱብዳ! ባለቤቴ ሰብር ይጨምርልክ…
" እና ምን አሰቡ… ወ/ሮ አስ…"
" ምን ላስብ አቶ ሀቢሌ… "
" እራት የለም… 🥺…?"
"ውይ… አፈር ልብላ… ና አቦ ልስራልክ ወይስ ፍሪጁ ውስጥም አለ… "
"ትኩስ አስዬ አብሬሽ እሰራለሁ …"
" ስችልበታ ወሬ… "
"ሮም እኮ ነው የኖርኩት የኔ ዶሮ… ከፒዛ ላዛኛ… ከፓስታ እስከ ኢትዮ ሽሮ… 😌 "
"😁 … በቃ ቁርስ ላዛኛ የኔ ወረኛ😆"
"አንቺ ቆይ 😘😘 … በይ እናፍጥነው ጨጓራዬ አንጀቴን መብላት ሳይጀምር… "
………………
××× ××× ×××× ×××
………"አሰላሙ አለይኩም… "
"ወአለይኩም ሰላም ልጄ…! አህመዴ… መቼ መጣህ … "
"በልጅህ ሰርግ ቢዚ ሆነህ ትዝም አልልህ…"
"ወይ አህመዴ… ጓደኛህ አይደል ምነው ብትመጣስ… "
"ተሳስተሃል… ወንድሜ😏"
"ወይ አንተ እና ያቢጤህ አሽሙር አይሰለቻቹ… "
" እና ኡሚስ ?"
"ግባ ውስጥ ናት።…"
…………" አሰላሙ አለይኪ ኡሚዬ …"
"ወ… ወአለይኩም ሰላም ልጄ መጣክልኝ?"
…"አዎ ግፍሽ በስተርጅና ያዘሽ አሉኝ… "
"ተው ልጄ ካላንተ ማን አለኝ… እንዲ አትሁንብኝ… እሞትብካለው…"
"መጥፎ ሰው ይቆያል ባክሽ እናትዋ አላህ ያቆይልኝ። አለችኝም ክብር ነው…"
"ዓየሽ ልጅሽ መጣልሽ ረሂማ… "
"ምነው አቢ በእንጀራ ልጇ ሰርግ ነው እንዴ የታመመችው… ኡሚዬ እኔም ቂም ይዤብሻለው… በዛች ነገር … እ… ምንላድርገው እናቴ ነሽ የኔ እናት… "
"ስለ ሀቢል ሰርግ ከየት ሰማህ… "
" ኑሬ በረስተም ምነው ማወቅ አነበረብኝም… የልጅነት ህልሜን ለልጅህ ስድር!"
" ምን?! ማለት ምን ማለት ፈልገህ ነው?"
" አስ የኔዋ አበባ… ለልጅህ ሀቢል ጠየቅህ… !!"
"ልጄ አላወቅኩም በእውነት አላወቅኩም… "
" አንተ ምንም አታድርግ… የመጣሁት ሁሉንም ላስተካክል ነው!!!!! ሰላም ዋሉ…"
"ልጄ … አህመድ…… በቃ የጡሬ ክፍያ ቃቢል ሀቢልን ሊገድለው ነው😭"
……
……… አሁን ስራ ስለያዙ ለኢሻ ሰላት ተነሳው… "አላሁ አክበር… "……
😰😰😰 ስልኬ ጠራ… የቱ ጋር ነበር ያስቀመጥኩት… በጣም ይጮሀል…
" የማን ስልክ ነው ውዷ… "
አስ: ምላሴ ተሳሰረ "እ… እ…"
ረስተም: አንድ ኮቴ ወደእኔ ሲቀርብ ሰማው… ሶላት አቋርጬ አልዘጋው😰… ቧንቧው ጋር ነው… አላህ😟
ሁለተኛ ኮቴ ሶስት… አራት…
#ክፍል-13 ይቀጥላል
``{ሺይፍ👑ረስተም}´´
#ክፍል-12
……… ልክ በሩን ስትከፍትልኝ… በሚያስደነግጥ ድምፅ ጮሃ…እራሷን ስታ ወደቀች። የእውነት ደነገጥኩ… ስልኩ "አስ… ሃያቴ… ሄለው… " ሀቢል በደቂቃዎች ውስጥ እንደሚደርስ አልተጠራጠርኩም። ምንላድርግ… "አስማ… አስማ… አስማ በአላህ ንቂ… አስ… " እንደምንም አይኖቿን ገለጠች። ሙሉ ሰውነቷ ይንቀጠቀጣል… ጂን ያየች ነው ምትመስለው… ፍጥጥ ብላ አየቺኝ… ፍርሀቷ አሳዘነኝ… እቅፍ አደረግኳት… በጣም እንደጨነቃት ያስታውቃል…
"አስ ተረጋጊ አውፍ በዪኝ😓… "
"አ… አ… አ… ን…"
…በአ ጀምራ በአ ጨረሰችው… ኡፍ ምንድነው ያደረግኩት… ይሀውልሽ … ሁሉንም በደንብ ነገርኳት… ለሷ ስለተፈጠረብኝ ስላደረብኝ ጉድ ሲቀር… በፍራቻ ውስጥ ሆና አደመጠቺኝ… …
…… በሩ ድንገት በሀይል ተደበበ… ብድግ ብዬ ሄጄ ከፈትኩ… ሀቢሌ ነበር…
"ሀያቴ… " በድንጋጤ አገላበጠኝ…
"ደ…ደህና ነኝ… "
"ምን ተፈጥሮ ነው… ቆይ…?" ቤቱን 360°ዞረው…"
"ዘውጂ… ሁሉም ሰላም ነው… በሩ ጋር አይጥ አይቼ እኮ ነው…"
"ምን?… አይጥ…? እዚ😳… "
"እ… እ አው…"
"🤔🤔 እና ደህና ነሽ?"
"አው ሁቢ… ደህና ነኝ… 🫂… ደግሞ በጀት ነው እንዴ የመጣከው😁…"
"አስ ትቀልጂያለሽ… እንዴ ድንጋጤዬን ብታይ… 😟 ኡፍ… 🫂 የሆንሽ አይጥ ነገር "
"በጣም እጅግ በጣም … ti amo እሺ ዘውጂ…"
"ጣሊያናዊቷ ባለቤቴ… 😅"
…… ፈራሁ😥 ቤቱ ውስጥ የደብቅኩትን ጉድ እንዳያየው ፈራሁ … ሀቢሌ በዚ ሰአት ስለዚ ነገር ካወቀ ይረበሻል።አመታት የለፋበት ስራም ማለቂያው ቀርቧል… በዚ ሁኔታ ቢያውቅ የአህመድ እናት ሰጋሁላት… አጎቴ አደምም ጥሩ አልሰሩም… የዚ ጉድ አባል ሆንኩ…ኡፍ… አሁን የገባኝ ነገር ባለፈው ጮሆብኝ የሄደው ይሄ ሰው መሆኑ ነው… የሽቶውስ ቀን ማንን ነው ያቀፍኩት🥺…ኢላሂ ግራ ገባኝ እኮ በግድ መጠንከር በግድ… የባለቤቴን መንቲያ ወንድም እንዴት ነው ከዛ ክፍል ማስወጣው… ሀቢሌ ቤት ሊውል ወስኗል… የመግሪብ ሰላት አዛን ወጣ…
…አላሁ አክበር አላሁ አክበር🗣
…ክፍሉ በልብሶች የተሞላ… አንድ የእጅ መታጠቢያ ቧንቧ ያለበት… በስርዓቱ የተደረደሩ ፎጣዎች… ጠበብ ያለ ክፍል ነው። አስማ በስንት ግሳፄ አሳምኜያታለው… ስለ አህመድ አልቀበል ብላኝ ነበር… ብዙ ማሃላ ቃሎች ምስክሬ ሆኑ አልሃምዱሊላህ አመነችኝ… ከባዱ ነገር ከዚህ ቤት እንዴት ነው ምወጣው… የበሩ ጠርዝ ባለመስታወት ስለሆነ ወደሳሎኑ ይመራል… ሰላቴ ልቤ ክው አለች😳 ሰላቴን… ባንቧውን ተጠቅሜ እንደምንም ውዱእ አድርጌ እዚያው ሰገድኩ… ወንድሜና ሚስቱም ሳሎን ሲያሰግዳት ሰማው… እራሴን እስክጠራጠር ፍፁም የኔ ድምፅ አለው… ሱብሀነላህ…
………ትንሽ ስናወራ አመሸን። ሀሳቤ እዚያች ክፍል ቀረ… ጭንቀቴን ቢያቀልልኝ ለዘውጂ እንዲቀራልኝ ጠየቅኩት… ኪታብ ፊቱ አቅርቤ አይን አይኑን አየሁት… ግንባሬን ስሞ ኪታቡን ተቀበለኝ።
"بسم الله الرحمن الرحيم ………"
…ልብ ቅልጥ የሚያደርገው አቀራሩ ዱንያን አስረሳኝ። ልቤ ወደ ጌታዋ ተጠጋች…
……ወንድሜን ከቅርብ ማየቱ ውስጤን በሀሴት ሞላው ፊት ለፊቴ ምስሌ፣አካሌ፣ ድምፄ … የምስኪኗ እናቴ ልጅ ሀቢሌ…🥹 ማሻአላህ … ቢጤዬ ወንድሜ … ወጥቼ ላቅፈው… ናፍቆቴን ልወጣ ተመኘው… ሀቢሌ ባየህ ባየህ አለኝ ውስጤ… ወንድሜ እዚህ ነኝ ልለው አቃጣኝ……
…… ልቡን በእዝነቱ አርጥቦለት… ውብ አይኖቹ ውሃ አፈሰሱ… የኔ ስለሆነ ኮራው… ጌታዬ ምንያክል ቢወደኝ ሀቢልን ሰጠኝ? ምን ያክል ብወደድ🥹… አይኖቹን እያየው ዱብ ዱብ አሉ የአይኔ እንባዎች… አልሃምዱሊላህ ሳሊህ ባል ሚስቱን ሳሊህ ያደርጋል… እየቀራ አልቅሶ ያስለቅሳል… ወዶ ይወደዳል… አፍቅሮ ይፈቀራል… በልብ ሀገር ያለምንም ተጋሪ ለብቻ ዘውድ ይጭናል… የኔ ሀቢል ማለት እሱ ነው😍ደግሜ ደግሜ ደጋግሜ በፍቅሩ የተሸነፍኩት ጀግና!… ማሻ አላህ!!!
…… መልካም ሁሉ ለንጹሁ ወንድሜ… ኸይር ሁሉ ላንተ የእናቴ ልጅ ስስቴ ብቸኛ ዘመዴ… እንባ የሚወርደኝ አይነት ሰው አነበርኩም… በቀድር ኢማኔ ሙልት ያለ ካለው ይሆናል… ካላለው ለኸይር ነው… ከሀቢል ቅርብ ሆኜ ሱረቱል-ሁድ ሲቀራ ነፍሴ ራደች… እንባዎቼ ተንጠባጠቡ… ተቅዋ ይጋባል… ኢማንም ይተላለፋል… ጀሊሉ ለምን ይሁን እንዲህ ሚሳሱለት ያደረገው… ምን ቢወደኝ የሀቢል ወንድም አደረገኝ… አልሀምዱሊላህ…
"ሰደቀላሁል አዚም!"……
"ሰደቀላህ… "
"እና አስዬ ኢሻ ገባ እኮ… አ?'
"አው ሁቢ አዛን እያለ ነው…"
"ነያ በቃ… "
……… ኢሻዬን ከሁቢ ጋር ሰገድኩ። ድንገት ከልብስ ቤቱ የሳል ድምፅ ሰማን……😳 ልቤን እስክተፋት ሰላት ቆሜ አሳልኩ… ኡኹ… ኡኹ… 🙄😮💨…
…ሰላታችን በሰላም ተጠናቆ ዱኣ አደረግን… ከዚያው ወደ ወሬ ከልዩው ጓደኛዬ🥰…
"ሀቢሌ እስኪ ስለ እናትህ ንገረኝ… "
"እንዴ ውዷ እንዴት ዛሬ ጠየቅሺኝ… ኡሚ እኮ ከ3 አመት በፊት ሞተች😔…"
"ሳቢር ነህ ዘውጂ… አላህ ይዘንላት…"
"ታውቂያለሽ አስ… ልዩ ነበረች። የኔዋ እናት ወደር አይገኝላትም ነበር። የኔ እናት …" አይኖቹ እንባ ዳግም አቀረሩ… "ኡሚዬ ግማሽ ጣሊያናዊት ነበረች… ልትነግረኝ ምትፈልጋቸው ብዙ ነገሮችን ይዛ ተቀበረች… አስዬ… ኡሚ እኮ ብቸኛ ወንድ ልጄ የጌታዬ ስጦታ… እዝነቱ ነበር ምትለኝ… ቡሽን ስትወልድ ታመመች። አቢም ከስንት አንዴ ነው ብቅ ብሎ የሚጠይቃት… ወይ ቅርቡ ስሆን ይሻል ይሁን ብላ ኢትዮጵያ መጣን… ጭራሽ ለንደን ሄደ… የኔ እናት ገንዘብ እንጂ ምንም ድጋፍ ሳታገኝ ነው ያሳደገችኝ… በጣም ሳናዳት ምን አንተን ጣለብኝ ትለኛለች… መጥፎ ሆኜባት አውቃለሁ አሁን ትናገረኝና ቆይታ ይቅር እንድላት ትለምነኛለች… እሷ ላይ ሳይሆን እኔ ላይ ሀቅ ቢበዛባት ይመስላታል መሰለኝ… እህ … ኡሚዬ… ለቡሽ ምንም ከመግዛቷ በፊት እኔን ታስቀድማለች… ቡሽ ቅናታም ናት። 😊 እህቴ ቀውጢዋ አላህ ይጠብቅልኝ… የኡሚ አደራዬ ናት… "
……ጭንቅ አለኝ አሁን ይህች እናት ናት እናትህ አይደለችም የሚባለው…?
"አብሽር አላህ ይዘንላት… ሀቢቢ …"
"አሚን🤲😘… "
ቦነስ ይቀጥል 👍
#ክፍል-11
**
……የሰው ልጅ ፍፁም ደካማ ነው። ፍፁም በትንሽ ነገር የሚረታ ሰነፍ… አው ልክ ነው በጣ… ም ልክ ነው… እራስን ባልጠበቁት፣ እንሆናለን እናልፍበት ባላሉት መንገድ ማግኘት እጅጉን ያስገርማል። በወንድሜ ሚስት ተረታው… ባልጠበቅኩት አጋጣሚ ከአቅሜ በላይ ሆነች። ልረሳት ተሳነኝ። አቃተኝ… አቅሌ በልክ አልሰራ አለኝ… ጠፋው ብን ብዬ ጠፋው። እዚያው ለንደን ውስጥ ማንም የማያገኘኝ ቦታ ሂጄ ተሰወርኩ… ምን የሚሉት ውርደት፣ ምን አይነት መውረድ ዓስማ ሃሃሃ… ውስጤ በራሴ እንዲ ይስቃል። ግርም ይለኛል ትክዝ ያደርገኛል… እነዚያ አሳዛኝ አይኖች ናፈቁኝ… ለአንድ ሙሉ አመት ከሁሉም ማውቃቸው ሰዎች ራቅኩ። እራሴም ከሚነግረኝ ውርደት ሸሸው… ግን አቃታኝ ከአንድ አመት በኋላ ተመልሼ ወደዚያ በር መንገድ ጀመርኩ…
………"የኔ ልዑል… "
"ወዬ ንግስቷ… "
"ዛሬ ቁርስ የለም…?"
"ወይ ጉድ ጉድ እኮ ነው…"
"እህ … ምነው?"
"ሴት ቁጭ ብላ ባል ይሰራል … "
"😃 ነጮችም እንዲህ ታስባላችሁ እንዴ🤭"
"አንቺ ዶሮ😆… እኔ እኮ ሀበሻ ነኝ"
"ዶሮ🥹… እኔን ዶ… ሮ ኡሚ ጋር ደውልልኝ"
"ወይኔ ጉዴ🫢… አስ አውቄ ነው እኮ"
"እኔ ዶሮ🐓**🥺"
"እነዚህ አይኖችሽ ናቸው እኮ ብርክክ ያደረጉኝ… ነይልኝ እስኪ…🫂"
"አውራ ዶሮ😝"
"😁*😁😅😆"
………… "ወአለይኩም ሰላም አህመድ…"
" እንዴት ነህ? ረስተም… "
"አልሀምዱሊላህ… አሳስቦህ ነው😏"
"እንዴ ረስተም ወንድሜ እኮ ነህ! አመት ሙሉ ስትጠፋ እንዴት አላስብ? እ…?"
"ወሬ አታብዛ… እንግዲ ላጣራ ነው በል…! አልነገርኩትም አታስብ… ቢሆንማ…"
"ይቅር ረስተም በቃ አይሆንም!"
……ውስጤ ብግን አለ😡
"ይሆናል! መሆኑ አይቀርም… የጊዜ ጉዳይ ነው።" ብዬ ጠረቀምኩበት…
………"ውዷ መሄዴ ነው…"
"እሺ ዘውጂ… ቆይ አንዴ…"
"ምን?"
"ደስ ሚል ነው…"
"ማሻ አላህ ድንቅ መአዛ… ሽቶ ምርጫሽ እኮ ያኮራኛል ሀያቴ… "
"አውቃለው😌"
"ጉረኛ😘😘…"
"bye"
"bye…"
…………አንዲት ካፌ ገብቼ ቡና መጠጣት ጀመርኩ። ውስጤ ጭንቅ አለው። ለምንድነው ምሄደው… አሳዛኝ አይኖቿን ለማየት ወይስ… ሁሉንም ነገር ለወንድሜ ለመናገር? ለየቱ ልሂድ ዝም ብሎ እግሬ ተነሳ ገሰገሰ…
………ኳ… ኳ… ኳ
"የኔ አውራ ዶሮ…🫂 ምንድነው ደግሞ ልብስክ?"
ዝም አልኳት ዝም አይኖቿን ዝም ብዬ አየኋቸው… አካሌ አልታዘዝ… አንደበቴ አልፈታ አለ…
"ደግሞ ፂሞችክ በጣም እያደጉ ነው እንዴት አላስተዋልኩትም ትንሽ ቅርፅ ማስያዝ ብቻ"
…ባለፈው ያንባረቀው አንደበቴ ዛሬ እጅ ሰጠ ዝም!
"እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው… አትገባም…"
"አይ እቸኩላለው… "
…የናፈቀኝ አንድ እና አንድ አይኖቿ ብቻ ናቸው። ዛሬም ላናዳትና እነዚያን አሳዛኝ አስተያየት ልወፈቅ… ወይኔ ረስተም አፈር ሁን አቦ!……
"እና ናፍቄዎት መሆኑ ነው…?"
…ድንግጥ አልኩኝ… ምን ልበላት አዎ ወይንስ አይ
…" አ… አ አው…"
"🫂🫂🫂😘😘"
…… ልቤ እንደጉድ ትመታለች። "በ… በቃ ልሂድ "
"ቶሎ ና ደግሞ ደሞ ምንድነው እኔ መርጬልክ ምትለብሰውን አትቀያይራ…"
"እሺ…"
…እግሮቼ በፍጥነት መገስገሱን ተያያዙት… ጭንቅ አለኝ… ካንድ ሁለቴ ዞሬ አየኋት… አይኖቿን ቁልጭልጭ እያረገች… "bye …" አለቺኝ … ቤት ሄድኩኝ ውዱእ አድርጌ ሁለት ረከአ ሰገድኩ… "ኢላሂ ፈራሁ😥 ነፍስያዬ በያዛት ክጃሎት ተሳቀቅኩ… ደካማ ባሪያህ አይኖቼ በከለከልከው አረፉ! በእዝነትህ ኢላሂ በእዝነትህ ከሸይጣን ጋላቢዬ ነፃ አውጣኝ። ልቤ እኮ ለወንድሜ ሚስት መታ😰… ያሀዩ ያቀዩሙ ቢራህመቲከ አስተጊስ አስሊህ ሊ ሸእኒ ኩለሁ ወላተኪልኒ ኢላ ነፍሲ ጠርፈተ አይን😥🤲"
××××× ×××× *
"ሄለው አባ… "
"ሄለው… አህመዴ… አሰላሙ አለይኩም"
"ወአለይከ ሰላም… አቢ ረስተምን አውርቼው ነበር ደህና ነው… እናም… እ… ምንም አልተፈጠረም "
"አልሀምዱሊላህ… ኡፍ…"
"መናገሩ ግን የሚቀር አይመስለኝም ምን እንደመለሰው ነው ያልገባኝ🤔***"
"ዋናው አለመናገሩ ነው ልጄ…"
"እሺ በቃ አቢ ኡሚ እንዴ ናት…"
"ልጄ ጡር እኮ አይለቅም…"
"ምነው ደህና አይደለችም እንዴ?"
"ያቃዣታል… ሁሌም ቢሆን ሩቂያ እያለች ነው የምትነቃው… እንደው እኔ እራሱ እንደ ጠዋት ዚክር የሷን ስም ሳልሰማ እነቃለው ብለህ… "
"በቃ መጥቼ እዘይራታለሁ አቢ… ሰላም ሁኑ"
"ሰላም ሁን ልጄ አሰላሙ አለይኩም…"
"ወአለይኩም ሰላም አቢ ቻው"…
……… አስማን ወንድሜ የነጠቀኝ የረሂማ ልጅ እኔ ነኝ። አዎ ረስተም ልክ ነው… ጭካኔ በእናቴ ደም በኩል የተላለፈብኝ ይመስል… ውስጤ ቆራጥ ነው። ትግስቴ ለምክንያት ነው። አመት ሁለት አመት 3…4… ቢያልፍም እንኳን ዛሬም በልጅነት ፍቅሬ ተስፋ መቁረጥ አልችልም። አስማ የኔ ነበረች። በእርግጥም የኔ ትሆናለች! ሀቢልም ለክህደቱ የእጁን ያገኛል በቅርቡ!
……… አልሀምዱሊላህ ከባለቤቴ ጋር ለንደን ውስጥ 1አመት ከ1 ከወር ሆነን🤲 ሀቢሌ አንዳንዴ ግራ ግብት ያደርገኛል። ሁለት ጊዜ ከወጣበት በጊዜ ሲመለስ ልብሱን ይቀይራል። እንደውም ዛሬ የቀባሁት ሽቶ ጭራሽ ጠረኑ የለም🤔… ልጠይቀው አስቤ ግን ቢቀርስ ብዬ ተውኩት… አቅፌ ሰላም ስለው የማያውቀኝ ሰው ይሆናል… ከዚያ ደግሞ ሄዶ ተመልሶ ሲመጣ ቅይርይር ይላል… ሙሉ ፍንድቅ የሚያደርገኝ ምርጡ ዘውጄ ይሆንልኛል… "ቅድም ልብስክ… ሽቶክም አነበረም እኮ…" ሀቢሌ ግን እኔን ከማመን ይልቅ… ስለእኔ የተጨነቀ ፊት ያሳየኛል። እያበድኩ ነው እንዴ… 😥… ወይስ ምን ሆኜ ነው… የቀኑ እና ይሄ ሀቢሌ ምን ለያቸው… ምን ሆኜ ነውስ ልብሱ ተቀይሮ ሚታየኝ…
"የኔዋ… "
"ወዬ…"
"ዛሬ ይዤልሽ የመጣሁትን … ብታይ"
"ምን😃… "
"🧁🧁"
"የኔ ባትሆን ነበር ሚቆጨኝ😘… ደግሞ እንዴት አምሮኝ ነበር በአላህ😍🫂"
"እስኪ ቅመሺው😋…"
* ……… ከዱኣዬ በኋላ ቅልል አለኝ። ትንሽ ተረጋጋው… ስለአስማ ያለ እረፍት ሲያስብ የነበረው አይምሮዬ ወደጌታው ኮበለለ… ረሳኋት! በጠዋቱ ሀቢል ጋር ሄጄ ሁሉንም ነገር ልነግረው ወስኛለው… ከሚገጥሙኝ መሰናክሎች ሁሉ በአላህ እጠበቃለሁ🤲 ነፍሴን ባንተ ፍራቻ ሙላት ያረብ ረስተምን ከነፍሲያውና ከጠላቷም ተንኮል ጠብቀው🤲** ሀስቢየላሁ ወኒእመል ውኪል!
"እሺ ሁቢ እሰራለሁ ደግሞ ብቅ በል😍"
"ከመች ወዲ… በቃ ሀቢብቲ 😘 ቻው"
"bye…"
…… ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ የሚጣፍጥ ምግቦችን ሳበስል… ዘሉዬ ጋር ደውዬ ስለ አዲሱ ቤቷ ስናወራ ጊዜው ይበራል… ድንገት ስልኬ ጠራ … yes! ሁወ ሁቢ🥰
"አሰላሙ አለይክ… ሀቢቢ"
"ወአለይኪ ሰላም… የኔ ፍንድቅድቅ…😘"
………………………… ……………… …………"😁………………… ……………"…………"…… እስኪ ቆይ ሁቢ በር እየተንኳኳ ነው።" "እህ ማን ነው ሚያንኳኳው ውዷ ከእንግሊዞችም ጓደኛ አገኙ😁… " "እንኳን ከእንግሊዝ ጣሊያናዊ ባል አለኝ አይደል?😌"
" በይ ክፈቺው ወረኛ… "
"መጣው… "
…………አይኖቼ ፈጠጡ😳 ሰውነቴ ራደ ተንቀጠቀጥኩ… "ሄለው ሃያቴ… ሄለው…"
"ዋ………… ይ"!!!!
ክፍል-12 ይቀጥላል……
.
ማንም በሌለበት ጨለማ ቦታ ውስጥ ዱዐ ማድረግ 🥰
@abudi_seid
«እንደ ጨረቃ ውብ ሁነሽ ለምን
ትሸፋፈኛለሽ?!» ሲሏት «ልክ እንደ
ፀሐይ አይኖች ሁሉ የሚጋረድላት
መሆን ስለምፈልግ ነው» አለች!!
@abudi_seid ❤️🔥...✍
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
...........``{ሺይፍ👑 ረስተም}´........
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
✍ሀሪስ
#ክፍል-10
…………የኔ እናት ከሀገር ቤት ወደከተማ በድህነት ምክንያት ተሰደደች። ከተማም መጥታ ብዙ ዳከረች… በመጨረሻም አንድ ባለሀብት የሆነ ሰው ለትዳር ጠየቃት። ከሀብቱም በላይ በፍቅሩ ስለተረታች… አገባችው። ግን የህይወት ውጣውረድ ያልተፋታት እናቴ ለአመታት ልጅ መውለድ አቃታት። በዚ የተበሳጨው ባል ሁለተኛ ሚስት ያገባል። ረሂማ ፍፁም እርኩስ ሴት! የአህመድ እናት! እሷን አገባ። እሷም በአመት ውስጥ ወንድ ልጅ አሳቀፈችው። ጥሎ ማይጥለው ኻሊቅ ለዚህችም ሴት በወራት ልዩነት ልጅ ወፈቃት… ይች ሴት ደስታዋ ወደር አጣ ወደ ባሏ በረረች። ቀድማ ያገኘችው ግን ሚስትየውን ነበር። ልቧ ተሰበረ… ሞራሏ ደቀቀ… የምስራቿን ውጣ ተመለሰች።… እርጉዝ መሆኗን ከቆየ በኋላ ታወቀ… ረሂማም በቅናት ሲህሯን ጠመጠመችባት። ይህች ሴት አበደች። ልጅ በሆዷ ይዛ አቅሏን ሳተች።ዓደምም ሁሉንም ነገር አወቀ። ግን ምንም እንዳላደረገች ሚስቱን ችላ አላት። ምስኪኗ ሴትም መንታ ልጆችን ተገላግላ ከህይወት ድካም አረፈች። ሞተች! ይህ ጨቃኝ ባል መንትዮቹን ልጆች ወስዶ አንዱን ጣሊያን በሶስተኛ ሚስት አንዱን ኢንጊሊዝ ሞግዚት ቀጥሮ በአመት አመት እየጎበኘ አሳደገ። ከሶስተኛ ሚስቱም ሴት ልጅ ወለደ… ያቺ ምስኪን ሴት ግን ደመ ከልብ ሆነች። … ሩቂያ! አንዱ ልጇ ለንደን ውስጥ ከአረመኔ አባቱ ጋር ሁለተኛ ልጇ ከአዲስ ቤተሰብ ተቀላቀለ። እናትም ዓገኘ። ያልወለደችው! እኔም ወ/ሮ ረሂማ(የእንጀራ እናቴ) በተመላለሰች ቁጥር ቀስ በቀስ እውነታውን እያወቅኩ መጣው። ጣልያን የራቀውን ወንድሜ መጠየቅ ጀመርኩ… ግን እኔና ሀቢል ከተገናኘን ብዙዎቹ ነገሮች ይፋ ይወጣሉ… ሀቢል ብዙ ነገር መጠየቅ እንደሚጀምር ግልፅ ነው።
ትፈርዱብኛላችሁ አባቴን አባት ባልለው?! ትፈርዱብኛላችሁ የእናቴ ገዳይ ልጅ ወንድሜ ባይመስለኝ…?! ትፈርዱብኛላችሁ… ልገድላቸው ቢያምረኝ?! … ፍርድ አለ በኔ የአህመድ እንዲህ መሆን ሁሉም ነገር መውጣት ያለበት ጊዜ መሆኑን ጠቁሞኛል… ከምስኪኗ እናቴ የቀረኝን አንድ ወንድም ጫፍ እንዲነካ አልፈቅድም! አሁን ሁሉንም ነገር ያውቃል ድብብቆሹ ያበቃል!ዛሬ!!! … ሀቢል ያረፈበትን አይቻለሁ ። ዛሬ አወራዋለው ዛሬ ስለ እናታችን!!
………"ሁቢ ደስ ምትል ሃገር ናት😍😍"
"ገና ምን አይተሽ ብዙ ቦታዎችን ነው ማሳይሽ… "
"እውነት… ስወድክ እኮ"
"እ… አልሰማውም😁 ምን አልሺኝ"
"ወረኛ … "
"እ… ይሄ ነው እንግዲ ቤታችን አስ"
"ዋው ማሻአላህ ቆንጆ ነው…"
"ወደድሽው…"
"በ…ጣም"
"በቃ አረፍ በይ የኔ ቆንጆ አንዲት ቦታ ደርሼ እመጣለሁ እ…?"
"እህ… እሺ በቃ ቶሎ ተመለስ"
"አሁን አሁን😘😘 bye"
"bye"
"ሄለው… "
"አሰላሙ አለይክ ረስተም…"
"ወአለይከ ሰላም… አንተን ደሞ ላከ…"
"ረስተም በቃ የተዳፈነ ነገር አትቆስቁስ… ተው"
"ምነው? ፈሩ እንዴ ሀቢል እንደኔ ትግስት የለውም? ለእናትህ ሰጋህ እንዴ… ?"
"ረስተም እኔ ምልህን ስማ አቁም… የሀቢልንም ህይወት አትበጥብጠው…"
" አህመድ ሀቢልን ታጠፋዋለህ! አንተ እኮ የረሂማ ልጅ ነህ!"
"ረስተም…!!"
"አህመድ!! ልንገርክ ሙት እናቴ ፊቴ ብትቆም አትመልሰኝም!"
………ኳ ኳ ኳ…
"እንዴ ዘውጂ ከመቼው መጣክ🫂"
"አይ ቆይ … እኔ…"
"እህ ምንድንነው ደግሞ ልብስክ እዚያው ቀይረክ ነው… ና ግባ ለምን ቆምክ… "
"እኔ … ማለቴ… እኔ ማለት…"
" ኡፍ ሀቢሌ… 😘"
"አቁሚ!!…"
"ምን ሆንክ😧"
"እኔ እኮ አስማ እኔ ማለት… "
"አስማ!!? እኔን አስማ! ሀቢሌ በሙሉ ስሜ ጠራከኝ🥺"
………ምላት ጠፋኝ አሳዛኝ አይኖች። ምስኪን ፊት ላፍታ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለብኝ። ኡሚ እሷን ይሁን ምትመስለው… የኔ ምስኪን እናት እንዲ አሳዛኝ ነበረች ? አንደበቴ ተሳሰረ ምን ልበላት… ከየት ልጀምር?
"ሁቢ… ምን አጥፍቼ ነው🥺"
……ድንገተኛ ድንጋጤ ወረረኝ ። ደጋግሜ ቀና እያልኩ አየኋት። ባይኖቿ ውስጥ ሩቅ መንገድ ታየኝ… በጣም ፈራኋት… የማላውቀው መደንዘዝ ማላውቀው መደናበር …
"ዘውጂ…"
… ለስላሳ እጆቿን ጉንጬ ላይ አሳረፈች።
"አቁሚ😠…"
…ጮኬባት በፍጥነት እየተራመድኩ ወጣው። ያልገባኝ ፍርሃት ወረረኝ… ከጀርባ ደጋግማ ትጣራለች።
"ሀቢሌ… ዘውጂ" ሳግ ባነቀው ድምጽ። ውስጤ ርብሽ አለ: በረርኩ ጥፍት ከቦታው ስውር……
……ኳኳኳ…
በፍጥነት ሄጄ ከፈትኩት…
"ሀቢሌ…"
"ወዬ ንግስቴ…"
…ፈራሁት አሁንም እንደቅድሙ ቢያመናጭቀኝስ…
"ምን ሆነክ ነው? እኔ እኮ አምኜክ ነው እዚህ ድረስ የመጣሁት🥹 አምኜክ እኮ ነው ሀቢሌ 😭😭"
"እንዴ አስ ምን ተፈጥሮ ነው? ምን አደረግኩኝ…? 🫂"
"ልቀቀኝ… በጭንቅላቴ ነው የምትጫወተው…?! እኔ እብድ ነኝ እንዴ?!"
"እረ ሀያቲ በአላህ… ግራ ገባኝ እኮ…😟"
… ወደ መኝታ ክፍሉ ገብቼ ቀርቅሬ ስቅስቅ ማለት ጀመርኩ…
"ወይኔ አስ ጨነቀኝ እኮ በአላህ ምን ሆንሽብኝ…? ምናጠፋው ሃያቴ… ?"……
……መኪና ውስጥ ገብቼ በፍጥነት ነዳሁት። ልብ ምቴ ጨምሯል… ማላውቀው ጭንቀት ያዘኝ… አስማ ከአይምሮዬ አልወጣ አለች። ቅፍፍ ዝግንን አለኝ… እራሴን ባገኘሁበት መደናበር ናቅኩት… ሁሉም ነገር ከምናቤ ተነነ… ጭንቀት ወረረኝ…… ረስተም ምንሆነህ ነው እራሴን ደጋግሜ ጠየቅኩት… ❓❓❓
{አላሁመ ላኢላሀ ዒላ አንት ሱብሀነክ፣
ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዟሊሚን😥}
#ክፍል-11 ይቀጥላል ……እረ ተዉ ተዉ like አይቆጥርም እኮ
typing😮💨 ያለ like ሲሆን ደግሞ🙆♀😵💫😵💫ተጫኑት👇
ሰላም ለእነዛ ...🕊**
መናገር ፈልገው ለስሜታቸው መግለጫ ቃል አጥተው ዝምታን ለመረጡ ሁሉ 🥰**
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 6 days ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 1 week, 2 days ago