የፍቅር ግጥሞች ♥️

Description
✍️ለምን ወደድኩህ/ሽ?
እንጃ።?‍♀️‍ ♀
✍️ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ?
እንጃ?‍♀️
✍️እንዴት ማረከኝ/ሺኝ?
እንጃ?‍♀️

♥️ይህ ነው ለእኔ የፍቅር አለም? ማለት፤

➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት?
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 week, 6 days ago

7 months, 1 week ago

ላንተ ከተፃፈው 1ኛው
........
**✍
.
.
.የፃፍኩልክ ላንተ ....
ቢሆንም ባይሆንም ....
ፍቅርን መጠርጠር ....
መቼም አያቅትም ....
መፈቀርክን ማመን ...
ቢከብድም ቢቀልም...
መውደድን ማሰብ...
ለክፉ አይጥልም ....
ሁሌ እንደማስብክ...
ብታውቅም ባታውቅም.....
ላንተ ያለኝን ነገር .....
መጠርጠር አይጎዳም ....
እኔን ለመቀበል ....
ብቶድም ብትጠላም....
ከኔጋር መሆንን
እግዜሩ አይፈቅደውም**.........

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 1 week ago

#ግማሽ **ጨረቃ

ከጨረቃ በታች.....
ወጥነት የሳተ ብጥስጣሽ ደመና
አርጅቶ እንዳፈጀ አሮጌ ጎዳና
የሻገተ ነገር ጊዜው ያለፈበት
ያለማማር ወጉ ውበት ያልሻረበት.....
ከሱ ማዶ አጀብ
እዛ እና እዚህ ኮከብ
ማየት ሲያደካክም ያንቺን ነገር ማሰብ።

የሌለሽን አንቺ በፍለጋ ሂሳብ
ከሩቅ እንደ መሳብ
ማውጣት፣ ማውረድ ለጉድ
ከጊዜ መካለብ፣ በሰኞ እና በእሁድ።

ላልበጠስ ውጥር ፣
ላይለይልኝ ነገር ብዳከር ለዘመን
አይቀየር፣ አይሻር ብደበቅ ከማመን
ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ በተመን።

የተሳነው መሙላት፣ ያልሆነለት መጉደል
ጎኑን የደፈረው የጨለማ ገደል
መራቅ ያላጠፋው መቅረብ የመሰለ
ልዳብሰው ስሻ እንደመሄድ ያለ
የቀረበኝ ስለው የራቀኝ ከዘመን
ግማሽ ጨረቃ ነው ትዝታሽ ሲተመን**።

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 2 weeks ago

*?አታላይ ነች?*

"አታላይ ነች እያልክ "ታማኛለህ አሉኝ
ይሄው ባንተ ምክንያት አታላይ ተባልኩኝ።☹️
ባልኖርኩበት አለም ባልሰራሁት ሀጢያት
ባልሄድኩበት መንገድ ባልዳሰስኩበት ጣት?
ባላሰቡኩት ሀሳብ ባላረኩት ጥፋት ?
አታላይ አስባልከኝ እንዲያው አስኮነንከኝ
ቆይ ግን ?? ምን አጠፋሁኝ?
እንዲህ የሚያስኮንን አታላይ የሚያስብል
ውሸትን አንግቦ እውነትን ሚገድል
እንዲያው አባይ ቃላትን ቀጣፊ
እውነትን ሳይሆን ውሸትን ደጋፊ
?አታላይ የሚያስብል ቆይ ምን አጠፋሁ?
ዋሸው ከዳው ወይስ አማሁ?
እኔ እስከማቀው ምንም አላጠፋው
ዝም ብለህ አትማኝ እዳው ላንተ ነው!?

ግን ነኝ እን?ዴ??**

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 2 weeks ago
6 ቀን ብቻ ቀረው ***?*** ስንት …

6 ቀን ብቻ ቀረው ? ስንት ደረሳቹ ?

ያልጀመራቹ መጀመርያ ሊንክ ይሀው 2500 ነፆ ይሰጣቹሀል?

https://t.me/tapswap_mirror_bot?start=r_5685218492

7 months, 2 weeks ago

=====================
ትለኛለህ ደሞ
?*?*?.....

በልኩ ተሰርቶ፤
በፍቅር ተቃኝቶ፤
ዛሬውን አጽድቆ ትናንቱን አጥፍቶ፤
ሃዘኑን ሽሮ ሳቆቹን ተክቶ፤
የትዝታ ቁስሉን ህመሙን ረስቶ፤
ካ'ንቺው ተዋህዶ ካ'ንቺው ተቆራኝቶ።
ክንዴን ተንደርሰሽ ዘላለሜን ብኖር፤
ደስታው ለኔ ነበር......

ዳግም ቀና ብዬ የልቤን ስብራት በፍቅርሽ አክሜ፤
የመውደድን ጎጆ ከአንቺው አዋቅሬ ቢሰራ አለሜ፤
ከፍቅርሽ አዝመራ ባጭድ ታድሜ።
ደስታው ለኔ ነበር.......
ክንዴን አንተርሼሽ ዘላለሜን ብኖር፤
ሆኖም ምን ያረጋል ነበር ቢደረደር፤
ምኞት ሆኖ ባይቀር......

ትናንት ያሳለፍኩት የፍቅር መንገድ፤
ዛሬን እያጠረ አስጠፋኝ መራመድ።
ውስጤ ደካከመው እንደምን ልበርታ፤
በምን አቅሜ ልቁም ካ"ዲስ ሕይወት ተርታ..............
::
::
::
ትለኛለህ ይቅር.......
የኔ ልብ በፍቅር ዝሎና ተዳክሞ፤
እንዲህም አቁስለህኝ ወድሃለሁ ደሞ።

ቁስል ያርግህ አቦ!!!**

======================
♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 3 weeks ago

*ፍቃዱ ግርማ

አንቺዬዋ ወዴ ........
ልጅ መውለድ አሁን ነው
ለምን ........?
ሲባል ሰምቻለሁ .........
ፍቅርና ገንፎ ትኩስ ትኩሱን ነው
እድሜም ቆሞ አይጠብቅ
በደቂቃ ሰዓት ወደ ሞት መንፈፏቀቅ
ስለሆነ ቅሉ .......
በዋዛ ፈዛዛ እድሜን ከምንፈጀው
እውነት እልሻለሁ .......
መውለድማ አሁነው
እናም .......
በቅጡ አዳምጪኝ
የምልሺን ስሚኝ
እድል አንዲቷ ነች ካለፈች አትገኝ
ስለዚህ እንውለድ ...
ልጄም ቅር አይበለው
በስርጌ ቀን ይገኝ ።*

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 3 weeks ago

*የጠፋችው_ኮከብ

በድቅድቁ ባመሻሹ
አንቺን ብዬ ከበራፉ
አንጋጥጬ ወደ ሰማይ
ቁጭ ብዬ ከድንጋይ ላይ
ልጠይቅሽ አንድ ነገር
ልነግርሽም ደሞ ሚስጥር
እንደወዳጅ ላጫውትሽ
እንደዘመድ ልመካብሽ
ስርዝ ድልዝ በበዛበት
ጭምድምድምድም ባለበት
በኮሰሰ በረከሰ በከሰለ በጠቆረ
በተከዳው በተገፋው
በተጠላው ትንሽ ልቤ
ለጨለመው ለነተበው
ለከሰመው ጥቁር ልቤ
ስታሳዪኝ ብርሀንሽን
ስትለግሺኝ ፈገግታሽን
አዛኝ ልቤ ባንቺ ፀና
ኮከቤ ነሽ ፅድቀ መና
ማረፊያዬ ከብዙ ሀሳብ ከልቦና

ሰው አመሉ ብዙ፤ኮከቤ ታውቂያለሽ
አንዱ ሲመሽብኝ አንቺ ትነጊያለሽ
ሌላው ሲጠቁርብኝ ደሞ ትበሪያለሽ
ከአንዱ ስጣላ ካንቺ እታረቃለው
ካንቺ ከታረኩኝ ደሞ ሰው አጣለው
ኮከቤ ነይልኝ ያጣሁትን ልጣ
ቦታሽን ንገሪኝ ካልሆነ እኔ ልምጣ

ትዝ ይልሻል
አንድ ማታ ስገጥምልሽ
ቅኔ ፈሊጥ ስቀኝልሽ
ላጠፋው ሰው ማራከሻ የተበዳይ ስቃይ መርሻ ለበዳዩ የእውነት መንገድ ለተቀባይ አዋቂነት ለሸምጋዩ መሸምገያ ለደቂቃን ነገን ማያ ይቅርታ ነው ከስህተትመከለያ
ብዬሽ ነበር ካስታወሽው
ታዲያ ቃሌን የት ከተትሽው
ቃሌስ ይሁነ እኔ አይጠፋኝ
ያንቺ ዱካ ምነው ጠፋኝ

ሰማይ ካለው ከክዋክብት
ከአእላፋት የምለያት
ማረፊያዬ ብዬ ምላት
ምን አርጌ ተሸሸገች
ምን በድያት ኮበለለች

ከየት ደብር ከየት ሀገር
ከየት ቀዬ ከማን መንደር
ደሞ ከማን ልትደመር
ለቄሱ ነው ለለማኙ
ለሌባው ነው ለዘፋኙ
ለገበሬው ለእረኛ
ለጠበቃ ወይስ ዳኛ
ለንጉስ ነው የቸርቻሪ
ለመቤት ነው ለኮማሪ
እሺ ለማን ልታበሪ

ብርሀንሽን ምን ነጠቀሽ?
የኔ ሀዘን አጠቆረሽ?
ያንቺን ብርሀን ልቤ ሞልተሽ
የኔ ሀዘን አጨለመሽ?
በይ ንገሪኝ አልከፋ
እያወቅሽው እንደምኖር
ባንቺ ተስፋ

ያንቺን አለም አላቀውም
የኔ አለም ለጠየቁ፤መልስ የለውም
አንቺን ጠይቃለው ወዴት ነሽ እላለው
ብቻ የትም ሁኚ እጠብቅሻለው
ብርሀንሽ ናፍቆኛል ላይሽ እጓጓለው
ፈገግታዬ ጠፍቶ ምሽት ዘግሜያለው
እባክሽ ተመለሽ
ኮከቤ ናፍቀሺኝ ሲነጋ ልሞት ነው*

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 3 weeks ago

*?ጥራኝ ሞ?
ጀምበሩዋ ጠልቃለች፣ አንተ ከሄድክ ወዲ?
ጨረቃም ጠፍታለች፣ ፅልመት ነው ከእንግዲ
ከዋክብት ረግፈዋል ፣ሄደዋል ካንተጋ
ብቸኛ ?ሆኛለሁ፣ ቀን መሽቶ እስኪ ነጋ
መሬቱም ደርቋል፣ ዘር ማብቀሉን ትቶ
ሁሉ ነገር ረክሶ፣ ሠው መሆን ተረስቶ
አበቦች ደርቀዋል፣ ንቦችም ጠፍተዋል?
አንተ ከሄድክ ወዲ ፣ጊዜውም እረዝምዋል
ያኔ እንዳላጠረ፣ ደቂቃ ሠዓቱ
ሴኮንዱም እረዝምዋል፣ ወሩ አመታቱ
አንተ ከሄድክ ወዲ ?
ንፋሱም አይነፍስም፣ ልብን አይመልስም
ሰው ጨክንዋል ፣ለሰው አይመለስም
አንተ ከሄድክ ወዲ?
ኑሮም አስጠልትዋል፣ ሠው መሆን ረክስዋል
ፍቅር ሚባል ነገር ፣እንዲያው ተረስቶል❤️
አበባውም ረግፏል ?ቁጥቋጦ ተክቷል
ብቸኝነት እንጂ ፣አለም ሚባል ነገር፣
ስሙ ብቻ ቀርቷል
ጥራኝ ልምጣ ፣ምድር ሰልችቶኛል።?

ሞትትትትት??????????????‍♀**

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 3 weeks ago
ደህና ሁኝ

ደህና ሁኝ

የኔ ቀላል ነበር ቢከፍሉት ገብስ ዕዳ
ያንቺ ግራ አጋባ ዘመድ እና ባዳ
ልክ ነው እንዳንል ልክ አልሆን አለና

ዘንድሮም ልንል ነው "ፍቅር ቀረች አምና"
እንግዲህ ልቻለው ቻይው ግድ የለሽም
የነገን ማን ያውቃል ላይነጋ እኮ አይመሽም
እኔም ነበረብኝ ጠዋት ማታ ለቅሶ
አልቆ ተወኝ እንጂ እምባ ፈሶ ፈሶ
ደህና ሁኝ አልልሽ ደህና ላትሆኝ ሳውቀው
የሆነውንና ሆኖ ሚሆነውን እሱ ነው
ያሚያውቀው
         ....በይ..... ደህና ሁኝ"

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

7 months, 3 weeks ago

እንዴት እንደ መጣሁ ፤ እንዳትጠይቂኝ
ለምን ? ስለምትናፍቂኝ
አውቀዋለሁኛ!

አንድ የበደለሽ ሰው ፤ ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ ... ፌዝ ነው የሚመስልሽ
ግን ናፍቀሽኛል....

አዎ በድያለሁ በግፍ
ደግሞም ...
ናፍቀሽኛል በእጥፍ

ማርያምን የምሬን ነው ፤ በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እሥቃለሁ፤ ግን ያለቅሳል ሣቄ

ብራመድ በሀገሩ፤ ብከንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ ዐያለሁ፤ ቆለፍኩት ያልኩት በር

ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት ?

በሌሊትሽ መጣሁ
ዓለሜን ስላጣሁ

ከትላንት የባሰ፤ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን ዐየሁት፤ እጥፍ መውደድ ሲስብ

አንቺዬዋ ውዴ .....
የበደለ ሁሉ ፤ አይናፍቅም እንዴ?

ማቀፍ እንኳ ባልችል፤ ምሕረት ባላምንም
አትሣቂብኝ እንጂ !
ግጥሙን እያነበብኩ ፤ ናፈቅሽኝ አሁንም

ፀሐይዋን ከተትኳት....
አይንሽን ለማየት፤ ከቤቴ እያወጣሁ
የበደለ ዓይኔን ....
እንዳታዪኝ ብዬ ፤ በጨለማ መጣሁ

ደረስኩኝ ከደጅሽ፤ መፍራቴ በነነ
እሠይ አገኘሁሽ፤ ናፍቆቴ ሰው ሆነ

እከንፋለሁ ይኸው ፤ ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን !
ሳጠፋ ጊዜ ነው ፤ ጭራሽ የናፈቅሺኝ

አጥፍቻለሁ አዎ ! መውደዴን ቀብሬ
አትሣቂብኝ እንጂ ....
ልክ ስበድልሽ፤ ጨመረብኝ ፍቅሬ ።
:
:
ናፈቅሽኝ !!

♡ ㅤ    ❍ㅤ      ⎙         ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ  ?ℎ???
????????
?  @poem_timest
? @poem_timest
????????
?.................................?

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 week, 6 days ago